“ጎንደር ተበላሸ!” ማለትስ አሁን ነው (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

gonder

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ([email protected])

አንድ ሰው ተወልዶ እስኪሞት የሀዘንና የደስታ ፍርርቆች ውስጥ መኖሩ የማያሻማ ግልጽ አውነት ነው፡፡ ተመጣጥኖው ግን እንደሰውዬው ዕድልና የጥረት መጠን ሊለያይ ይችላል፡፡ ሀዘን የሚበዛበት ይኖራል፤ ደስታው የሚያይልም እንደዚሁ፡፡  ደስታና ዘሀን ደግሞ በገንዘብ መሙላትና ማጠጥ አይወሰኑም፡፡ ለሀዘንም ሆነ ለደስታ የገንዘብ ሚና አንድ ግብኣት እንጂ ብቸኛው ወሳኝ ነገር አይደለም፡፡ በአእምሮ እንጂ በገንዘብ ድህነትህ ብዙም አትከፋ ታዲያ – የእግረ መንገድ ማስታወሻ ነው፡፡ የገንዘብ ድህነትህ ስትሞት ይጠፋል፤ የአእምሮ ድህነትህ ግን ስትሞት ይበልጥ ይገናል፡፡ “ገንዘብ የኃጢኣት ምንጭ ነው” መባሉ ለኔ ቢጤዎች ያለው መጽናኛነት በበጎ ጎኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ያዘለውን እውነት ካለይሉኝታ መቀበሉ ከብዙ ቁሣዊና መንፈሣዊ ውጣ ውረድ ይታደጋል፡፡

በሕይወት ዘመኔ እንደዚች ቅጽበት ያዝንኩበትን አጋጣሚ ብፈልግ አጣሁ – ብዙ ጊዜ አዝኛለሁ፤ ደስ ለመሰኘት ሞክሬያለሁም፡፡ በጎንደር የብል(ጽ)ግና የድጋፍ ሰልፍ ምክንያት መፈጠሬን እስክራገምና ኢትዮጵያዊነትን እስክጸየፍ ክፉኛ አዝኛለሁ፡፡ ኢትዮጵያ እውነትም ሰው አይውጣብሽ ተብላ ተረግማለች፡፡ በእውነቱ በቁማችን ሞተናል፡፡

በአፄ ኃ/ሥላሤ ዘመን ነው፡፡ አዲስ አበባ ይኖሩ የነበሩ አንድ የጎንደር ባላባት የአውሮፕላን ትኬት ለመቁረጥ ከአሽከራቸው ጋር ወደ አንዱ የአየር መንገዱ የትኬት ቢሮ ይሄዳሉ፡፡ እንደደረሱም “ከነአሽከሬ ወደ ጎንደር እምሄድ ነኝና ስንት ነው ክፍያው” ብለው ትኬት ቆራጩን ይጠይቁታል፡፡ ሠራተኛውም “ለአንድ ሰው 75 ብር፤ ለሁለታችሁ 150 ብር ነው ጌታየ” ይላቸዋል፡፡ ሰውዬው ያኔ እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው “ምን አልክ? እሱንም እንደሰው ቆጥረህ እኩል ልታስከፍለኝ ነው? አንት የሰው ልክ የማታውቅ ባለጌ የባለጌ ልጅ?…” በማለት በባላባታዊ የነገር ጅራፍ እስካጥንቱ ገብተው ይገሸልጡታል፡፡ ትኬት ቆራጩ ብልኅ ነበርና “አፌን አዳልጦት ነው ጌታየ! እባክዎ ይቅርታዎትን፡፡ እኔ ተሳስቼ እንጂ ክፍያው ለእርስዎ 100፣ ለአሽከርዎ ደግሞ 50 ብር ነው፤ አይለመደኝም ጌታየ” በማለት ተለሳልሶ ያስረዳቸዋል፡፡ እሳቸውም “አዎ፣ እንዲያ ነው ጨዋ ማለት፡፡ ጌታና አሽከር እኩል አይደለም፤ እኩልም አይከፍልም…” ብለው ቁጣቸውን ወደ አፎቱ ይመልሳሉ፡፡ ነገሩ ሥነ ልቦናዊ ነው፡፡ ሰውዬው እውነቱ ጠፍቷቸው ሳይሆን አሽከራቸው ከእርሳቸው እኩል እንዳልሆነ ይህችን ጠባብ ዕድል ሳይቀር በመጠቀም እንዲረዳቸው ለማድረግ ፈልገው ነው፡፡

የሽማግሌው ነገር በዚያ ብቻ ቢያበቃ ማለፊያ በሆነ፡፡ ጉዞው ሊጀመር ሲል ምናልባት ሲወዛወዙ ሆዳቸው ተረብሾ ያኮረፈ ምግብ ወደላይ ፍልቅ ቢል መቀበያ እንዲሆናቸው በሚል አስተናጋጆቹ ፌስታል ነገር ለተሣፋሪዎች ሁሉ ማደል ይጀምራሉ፡፡ ምክንያቱን አስረድተው ለዚያ ባላባት ሊሰጧቸው ቢሉ “ማን? እኔ? እኮ እኔን ሊያስመልሰኝ?” በማለት በስድብ ወርፈው አስተናጋጆቹን ያባርሯቸዋል፡፡ መኳንንት አያስታውክማ! ሆ! አስተናጋጆቹም ድፍረታቸው፡፡

አውሮፕላኑ ተነስቶ ጥቂት እንደተጓዘ የተፈራው አልቀረም ሽማግሌው ፊታቸው ይለዋወጣል፡፡ ከጥቂት ቅጽበት በኋላም አፋቸውን በመዳፋቸው ግጥም አድርገው በመያዝ ከተቀመጡበት ተነስተው ወደፓይለቱ በር ያመራሉ፡፡ ከዚያም “አቁም በለው! ጎንደር ተበላሸ አቁም በለው! እኔ ነግሬያለሁ…” እያሉ በመጮህ ሕዝቡን በሣቅ ገደሉት ይባላል፡፡ አንድ ሰው አስመለሰውና ጎንደር ሲዋረድ ይታያችሁ፡፡ ለሽንትና ለንፋስ በአንዳንድ ሥፍራዎች ቆም የሚያደርግ የክፍለ ሀገር አውቶቡስ ሳይመስላቸው ይቀራል? ለዚያ አባት “አልሰሜን ግባ በለው” ብላቸው ደስ ባለኝ፡፡

አዎ፣ አቢይ አህመድ ጥቁር ውሻ ይውለድ! መሬት አትቀበለው፡፡ ሁሉም የሰማይ በሮች ይዘጉበት፡፡ ኢትዮጵያን አዋርዷልና የእጁን አይጣ፡፡ የእግዚአብሔር በትር ትረፍበት! ፈጣሪ ፍርዱን በቅርቡ ይስጠው፡፡ ሌላ የምለው የለም፡፡

ብዙ ነገር እያሳጣን ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ ብዙዎችን አሳጣን፡፡ አሁን ደግሞ አንድ ክፍለ ሀገር ቀማን፡፡ ይህ ሰው እግዚአብሔር እስኪፈርድበት ድረስ ስንት ነገር እንደሚያሳጣን መገመት ይቸግራል፡፡ የርሱ መጨረሻ በተቃረበ ቁጥር የምናጣው መብዛቱ ግን እያሳሰበኝና እያስጨነቀኝም ነው፡፡ ወገኖቼ በአንድ አምላክ ጽኑና ጸልዩ! ጊዜው ቀርቧል፡፡

በሰሞነኛ የጎንደር የብልግና ሰልፍ የማይናደድ ጤናማ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሲሆን የማይናደድ የለም፡፡ ያመኑት ፈረስ በደንደስ ሲጥል የማይበሳጭ አይኖርም፡፡ “አማራ እንኳንስ ተለያይቶ አንድ ሆኖም በሆነለት” ለሚሉ ወገኖች ይህ ዓይነቱ የጎጥና የሸጥ ክፍፍል ትልቅ መርዶ ነው፡፡ ለኦህዲድ ሸኔ ደግሞ ፌሽታ፡፡

ለፀጉር ስንጠቃ አንሩጥና እኔ በመሠረቱ በሕዝብ ኅልውና አምኜ አላውቅም፡፡ አንድ ዓይነትና የአእምሮ ብስለትን የሚጠይቅ ነገር ከሕዝብ አይጠበቅም፡፡ ሕዝብ ጎርፍ ነው፡፡ ጎርፍ ደግሞ ቆም ብሎ ማሰብ አይችልም፡፡ በፊቱ ያገኘውን እያገለባበጠ መውሰድ የጎርፍ ዓይነተኛ ባሕርይ ነው፡፡ ኃላፊነትን መሸከም ጠባዩ ስላልሆነ ሕዝብ የሚባለው ነገር ከጽንሰ ሃሳባዊ የማስመሰያ ትንታኔዎችና ገለጻዎች ባለፈ ሚዛን ሊደፋ የሚችል ብዙም የረባ ትርጉም የለውም፡፡ ከዚህ አኳያ “ሕዝብ ይፍረደኝ” የምትለዋ አስቂኝ አባባል ሁሌም እኔንም ታስፈግገኛለች፡፡ ማንን ለማስደሰት እንደምትባልም አላውቅም፡፡ ክፉም ሆነ ደግ የሚያስቡ ጥቂቶች ከፊት ሆነው እንደፈለጉ ሊያሾሩት ይችላሉ – ሕዝብን፡፡ ማንን እንምትደግፍ ሳታውቅና በተሳሳተ ወይ በተንጋደደ መረጃም ግልብጥ ብለህ ወጥተህ ወዳጅህን ልትቃወም ወይም ጠላትህን ልትደግፍ ትችላለህ፡፡ ሕዝብ የሚባል ነገር ስለሌለም ጸጸት የሚባል ነገር ሲያልፍ አይነካውም – ማን ይጠየቃል? ማንስ ነው ጠያቂው? ከዓለም መፈጠር ጀምሮ በተሳሳተ መረጃ ያበደ የሕዝብ መንጋ በሽዎችና በሚሊዮኖች ላይ እጅግ ብዙ ዘግናኝ አደጋዎችን አድርሷል – ዘቅዝቆ እስከመስቀልና ሰውነትን ቆራርጦ በእሳት እስከማቃጠል፡፡ ክርስቶስ የተሰቀለው በዚህ ዓይነት የስቅሎ ስቅሎ የመንጋ ፍርድ ነው፡፡ ያኔ እንዲያ የሆነ አሁን እንዲህ አይሆንም ብለን አንጠብቅም – በጎንደር ግን ሰቀጠጠኝ፤ ክፉኛም አዘንኩ – ከትግል ክብሪት መለኮሻ ሥፍራ የትግል ማኮላሻ በረዶ ይፈጠራል ብሎ ማን ሊገምት ይችላል? ለማንኛውም ይህን ሰልፍ ያስተባበሩና የመሩ፣ ይህን ደግና ጨዋ ሕዝብ ለዚህ ውርደት የዳረጉ ሰዎች ዘር አይውጣላቸው፡፡ በአካባቢው ያላችሁ ጤነኛ ወገኖች ታሪክን መዝግቡ፡፡ ጎንደርን ለዚህ የወረደ ተግባር ያበቁ ሰዎችን ስምና አድራሻ ያዙ፡፡ ለመበቀል አይደለም – ነጋችንንም እንዳያበላሹ ምናልባት ጥቂቶችም ብንሆን ለነገ መድረሳችን አይቀርምና ለጥንቃቄ ያህል ነው፡፡ እንጂ ከእግዚአብሔር ፍርድና ፍርዱም ከሚያላብሰን መለኮታዊ ፀጋ በስተቀር እኛ አንበቀል፡፡ እግዚአብሔር “በቀልን ለኔ ተዋት” ብሏልና ወደርሱ ብቻ እንጩህ፡፡

ዝናሽ ታያቸው ጎንደሬ መሆኗ፣ ብዙዎቹ የተላላኪው ብአዴን አጋሰሶች በጎንደሬነት መታማታቸው፣ ትብታባሙና ርኩስ መንፈስ የተቆራኘው አቢይ ለጠነሰሰው ሸር ስኬት ሲል ወደዚያ አካባቢ መመላለሱና አንዳንድ የአማራ ባለሀብቶችን ማባበሉ፣ ተረኞቹ ኦህዲዶች ጎንደርን ለማታለል ሲባል ለፋሲል ከነማ 25 ሚሊዮን ብር መመጽወታቸው፣ … ለዚህ በእውን ሊታሰብና ሊደረግ ቀርቶ በህልምም ሊታሰብ የማይችል ውርደት ዳርጎን ከሆነ አላውቅም፡፡ “የቀን እንጂ የሰው ጀግና የለውም” ይባላልና የነገ ሰው ብሎን ነገ ሁሉም ተፍረጥርጦ እናየዋለን፡፡

እጅግ የሚገርመው ደግሞ እኔ በጎንደር ውስጥ ሲውለበለብ የማውቀው ባንዲራ የጥንቱን ነበር፡፡ አሁን ያየሁት ግን ባለአምባሻውና የዲያቢሎስ ዓርማ ያለበት የኢሕአዲጉን ነው – የጎንደርን መለወጥ ለማመን ጊዜ ያስፈልገኝ ነበርና ክፉኛ የመደንገጤ ምክንያትም ይሄው ነው – ቀኝ እጄን የተቆረጥኩ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡ ይህን ሕዝብ ከአማራ ወንድሞቹ ለመነጠል የተጎነጎነው ታላቅ ሤራ አሁን ነው ቁልጭ ብሎ የታየኝ፡፡ ይህንንም ስል ሁሉንም የጎንደር ነዋሪ ማጠቃለሌ እንዳልሆነ መግለጽ እወዳለሁ፤ ሁሉም ብልጽግናን ደጋፊ ሆኖ ከተገኘ ግን ከዚህም በላይ ከማለት አልመለስም – ለምሳሌ “ብልጽግናን መደገፍ አማራንና ኢትዮጵያን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ቆርጦ እንደመነሣት በመሆኑ ብልጽግና ፓርቲን የደገፈ፣ ሰላማዊ ሰልፉን ያስተባበረ፣ በአባልነት ወደብልግና ፓርቲ የተደመረና ንጹሓንን ያስደመረ … ሁሉ፡- በመተከል፣ በጉራ ፈርዳ፣ በወለጋ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በባሌ፣ በሶማሌ … የታረዱ አማሮች አጥንት እሾህ ሆኖ ይውጋው” ማለት አይከብደኝም፡፡ ለማንኛውም ሁሉም የሥራውን እንደሚያገኝ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ሰው ነኝና ግን በማየው ነገር ለጊዜው መንጨርጨሬ አልቀረም፡፡ ከነፃነት በፊት ወደዚህ መድረክ ባልመጣ ደስ ይለኛልና የምታስቡልኝ ካላችሁ ጸልዩልኝ፡፡ የኢትዮጵያ ነፃነት ስለመቅረቡ ግን አደራችሁን ቅንጣት አትጠራጠሩ!! ጨለማ የሚበረታው ፈንቅሎት ሊወጣ የሚፈልግ ብርሃን ከኋላው እያስጨነቀው መሆኑን ካላመንን ተሳስተናል፡፡

10 Comments

 1. እንደዝህ ያለ በትክክለኛ ምሬት የተሞላ ግልጽ ጽሁፍ አንብቤ የማውቅ አይመሥለኝም።ግሩም ነው በውነቱ ።ሰው ግን ማሠብ እያቆመ ነው መሠል።እንዴት የራሡንወገኖች ገዳይና አፈናቃይ ደግፎ ሠልፍ ይወጣል? እውነትም ሠውየው አንዳች ነገር አለው ።

 2. ውድ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ፣
  አልገባኝም። “የጎንደር ባላባት” የምትለው ራስህን ነው? ሌላው ሁሉ ካንተ ያነሰ ይመስልህ እንደሆን ብዬ ነው! ቊጣና እርግማንህ በጎንደሩ ባላባት ትውከት ላይ ተቅማጥ የጨመረ መሰለ። በነገራችን ላይ፣ እኔም እንዳንተው የህወሓትን ባለ ሃምባሻ ባንዲራ አልፈልገውም፤ አሁን ህወሓት ሸሽቶ ገደል ገብቷልና ምልክቱ በቅርቡ ተፍቆ የሚጣል ይመስለኛል። ባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ እኮ “ግንቦት ቅብጥርሴ” መባል ካቆመ ወራት አለፉ እኮ! ለማንኛውም የግሌን ፓርቲ ሳቋቊም ለቅስቀሳ ጎንደር ብቅ ከማለቴ አስቀድሞ ፈቃድ እንድጠይቅህ አድራሻህን ላክልኝ።

 3. የጽሁፉ ቃል አገባብ መልካም ቢሆንም ” የኢትዮጵያ ነጻነት ስለመቅረቡ ግን አትጠራጠሩ” ስለተባለው ኢትዮጵያ ከጥንቱ ጀምሮ ነጻነትን የተጎናጸፈች ሀገር፤ በነጻነቷም የጥቁሩ ዓለም መመኪያ እና መኩሪያ፤ ለነጫጭቦች እና እንደአንተ ላለው የነጫጭባ ፍርፋሪ ለቃሚዎች እንደ ቁር እና ሐሩር ሲያፈዳያችው ይኖራል እንጂ ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝብ የነጻነት አርማ እና መለያ ሀገር መሆኗን ተረዳው። በመሆኑም በሁሉም ላይ እርግማንህን አወረድከው ጉዱ ካሣ እንደአንተ እርግማን እንኳን የ44ቱ ታቦት ሊሰማህ ቀርቶ የሳጥናኤል አሽከርም ካለው አይሰማህ።እርግማን ከየትም አያደርስምና ንሥሃ ግባ። ለብልጽግና ድጋፍ የጎንደር ህዝብ ሰልፍ በመውጣቱ በድንጋጤ “የቀኝ እጄ እንደተቆረጠ ተሰማኝ” ላልከው ደግም ግራህንም ድገመው እግርህንም አክለው ምርኳዝ ይታዘዝልሃል እንጂ የድጋፍ ሰልፉ ተፈጽሞአል ከሁለት ሳምንት በኋላም ይደገማል።በዚያን ግዜ ደግሞ ግራ እግርህን ቁረጥ የሁይልቸር ገፊ ይታዘዝልሃል።እንዲሁም በነጻነት እንድትናገር እና እንድትጽፍ ነጻነት ያገኘኸው በዶክተር ጠቅላይ ሚንስቴር አስተዳደር እንጂ በ27አመታት በወያኔ አስተዳደር ቢሆን ኖሮማ በጋለ የወገል ብረት መቀመጫህ ተተኮሰ እስር ቤት እየተንፏቀቅህ ሙጀሌህን ትፈለፍል ነበር።በመሆኑም የሀገር አፍራሾችን ፍርፋሪ መልቀሙን ትተኽ ለራስህ ንሥሃ ገብተህ ለሀገር ለወገን ሰላም እና አንድነት ጸልይ።

 4. ዳጉካ፡
  የጎንደሩ ባላባት ታሪክ እጅግ የሚያዝናና ነው። በውነት በጣም አስቆኛል! ግን ግን ይህንን በዚህ ጊዜ መጻፍ መልክቱ ግልጽ አይደለም። በዚያ ላይ “ጎንደሬ ያልሆነ አማራ ሁሉ ብልጽግናን የማይደግፍ” ወይም በግልባጩ “ጎንደሬ ሁሉ የብልጽግና ደጋፊ ነው” ወደሚል ከፋፋይ መደምደሚያ ሄደህ የአማራን ህዝብ በነጭና ጥቁር ሁለት ቦታ የተሰነጠቅ አስመሰልከው።
  በመንጨርጨር ከራስህ በስትቀር ማንንም አትጎዳም። ሰውየው ምንም አንዳች ነገር የለውም። “አማራን አስገዳይ አብይ ነው” የሚለውን አጉል ትርክት እስካልተውክ ድረስ ልክ ወያኔ “አማራ ጠላቴ” ነው ብላ የገባችበት አይነት የታሪክ ቅርቃር ዉስጥ እንደገባህ ትቀራለህ። የፖለቲካ ትንታኔህ ሁሌም ሸውራራ እንደሆነ አንተም እድሜ ዘመንህን ሁሉ እንደተንጨረጨርክ ትኖራለሕ። ልክ አጸ ሚኒሊክን እንደሚጠሉት ፖለቲከኖች ጥላቻው ወደ ልጆችህ እና የልጅ ልጆችህ ሊተላለፍም ይችላል። ምርጫው ያንተ ነው።
  ይልቃል ጌትነት ቀኑ እየደረሰ ሲመጣ እንዴት እንደሚንጨረጨር አይተሃልሃል? አቢይ ላይ ካለው ጥላቻ እና ንቀት ብዛት በአደባባይ “ወያኔ ጋርም ቢሆን መደራደር አለበት” ብሎን አረፈው። ከዚያ “ምረጡኝ” ዘመቻ። እንደማይመረጥ ሲገባው 6 ሊሎች ፓርቲዎች ሰብስቦ ለG7 መግለጫ ግብአት የሚሆን “ምርጫው ከወዲሁ ተበላሽቷል” ብሎ እየተወራጨ መግለጫ ሰጠ። G7 “noted” ብለው በለዘብታ አለፉት። ታዘብኩሽ ምኔ ነበር ያለው ሰውየው? የሌሎቹ የሚጠበቅ ነው። በለጠ ሞላ ግን ምን ይሁን ብሎ እዚያ መግለጫ ላይ እንደተገኘ ፈጣሪ ይወቅ።
  በምርጫ ብቻ!

  • wondime Alem! amar’gna yemiastem’rih sew feligina betinishu lesebat ametat yahil temar. megibabat kequanqua chilota yijemralina beqidimia quanquawn temar wondmalem. qeriwun dinqurinahin lemaswoged woym lemeqref degmo andand metsahiftin manbeb new. lela mircha yelem. partihin lememesret degmo fetari yirdah. yemagizih neger kale shuk belegn tadia. gin 1.5 milion birun yizeh endatitefa – bezian semon yizo teffa endetebalew ye’and party meri. yegudoch hager!
   leloch tesadabiwochim mejemeria slesidib aynetochina sle’asedadeb ‘tibeb’ siltena wusedu. alebelezia anbabi “enezih sewoch yeblgna party abalat nachew” blo yiferjachihual. yebilitsigna party degmo tkuretu siltanin madeladel enji sle’sidib aynetina asedadeb teknik aychenekim, min gedot! yetim fichiw duketun amchiw new yenesu neger. Atayena akababiwa beOLF shene (most probably by the order of Abiy Ahmed) eyenededech sale yaninim kistet be’and se’at wust masqom eyetechale leqenat zim teblual – yam alama slalew new. Aya dofter Abiy gin teshmonmuno beTV biq yilina ager aman endehone chigign sitekil yasayal woim menafesha simerik. yezih hulu finta ena qeld ajabiwochna gibre belawoch ezih ene lay yichohalu (‘yiqereshalu’ endalil bilgina slemihonibign new) – lemin ewunetun tenagerik bemil new yih hulu chachata. yandit hager lejoch bezih melk meleyayetachin asasabi new. ergit new yihm yalfal. liyunetu seffina asdengach bihonim ketarik endetemarnew yemayalif yetarik yemekero dof ena yemaytegene yetarik sibrat yelem.

  • Kedro, welcome dear. The owner of that ‘tazebkush qite’ story is not a he character; it is a she one. She tried to not fart, but all the effort she made failed and farted in front of her friends. She said that phrase or clause at that time, for farting in public is a culturally disgracing act.
   I have begun to like your way of commenting especially in recent times, by the way. We may become good friends after some more experiences of grooming each other in its modest and decent sense of the word grooming.
   Being harsh doesn’t take us anywhere. I know I am too harsh with respect to the devil in SOMEBODY whom I believe he is dismantling this nation perhaps on purpose or perhaps, which I don’t take it true, unintentionally. I don’t understand why people are myopic of what he does as of his coronation some 3 years back.
   You asked, Kedro, the applicability of the story of that old guy in my piece. The phrase he used should rather work perfectly now than his time. Have you got me now?
   The rest, fine and we shall come inch after inch and meet somewhere in the middle, though it may take us some time and patience as well. Bye. With much respect and love.

 5. ወዳጄ ጤና ጎሎሃል? ዝም ብለህ ትዘባርቃለህ። አማራ ለአማራ ቀድሞም ሆነ አሁን ተደጋግፎ አያውቅም። አዲስ ነገር አይደለም። ለዚህም ነው ዛሬም ትላንትም ወደፊትም የመከራ ቀማሽ የሆነው። የመከራ ዝናቡም ያለማቋረጥ የሚወርድበት። የጎንደሩ ሰልፍ ግን እንዲህ ከራራይሶ በሉ የሚያሰኝ ነገር የለም። ግን ያነተ ኡኡታ ፍሬ ቢስ ነው። ለምን ዶ/ር አብይን (የብልጽግና ፓርቲን) ደግፈው ሰልፍ ወጡ በማለት የባንዲራ ጉዳይ ታስገባና ጸልዪ ትላለህ። በመሰረቱ ጸሎት የሚያስፈልግህ አንተ ነህ። ምርጫ ማለት እኮ ሰው የፈለገውን በራሱ ተነሳስቶም ሆነ ወይም ሌሎች ሲገፉት ተገፍቶ የሚፈጸም ተግባር ነው። አንዴ ጎንደርን ሌላ ጊዜ የኦሮሞ ገለ መሌ በማለት የተማታ ሃሳብህ ምን ለማለት እንደፈለክ እንኳን ግልጽ አላደረክም።
  ሃይማኖትና ፓለቲካ ውሃና ዘይት ናቸው። ለሃገርና ለወገን መቆርቆር ዘርና ቋንቋን ሳይለዪ አንድ ነገር ነው። የእኔ አውራ ጣት ከዚያኛው ይሻላል ማለት ግን ጅልነት ነው። በመሰረቱ በሃበሻው ፓለቲካ ፈጣሪ አይገባበትም። ጭራሽ ስትጠራው ውለህ ብታድር ዝም ጭጭ ነው የሚለው። በሸፍጥ፤ ገድሎ ለመኖር፤ በያዘው ጥለፈው የፓለቲካ አተካራ ውስጥ ፈጣሪን መጥራት ተንጋሎ እንደመትፋት ነው። የሃበሻ ህዝብ በተንኮል የታሰረ ህዝብ ነው። ዘር፤ ጎሳ፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖት ሳይል ይበልጡ በውስልትና ዓለም የኖረና የሚኖር ነው። የጎንደር ህዝብ ከጎጃም፤ ከሃረር፤ ከትግራይ ከሌሎቹ ወገኑ የሚለየው የለም። ከጥቂቶች በስተቀር ትላንትም ዛሬም ከእጅ ወደ አፍ ኑሮን የሚኖር ነው። በዚህም ቀንተው ያው አሁን በውጭም በውስጥም ያሉ ሃይሎች ያባሉናል። ፓለቲካ የሙታኖች እንደሆነ የደርግ ታሪክና የወያኔ የሮም አወዳደቅ ትምህርት ሊሆንህ ይገባል። ዝም ብሎ መቦጫረቅ ነው። ኢትዪጵያዊነት ሱስ ነው ያሉን አቶ ለማ የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች በአሜሪካ ጭንቅላታቸውን በርዘው ገና ሳይጀመር ከመደመሩ ስሌት የተቀነሱ መሆኑን ልብ ላለ የሃበሻው ፓለቲካ የአስረሽ ምቺው ፓለቲካ በመሆኑ ብልህ ሰው ዝም ይላል።
  አሁን በአውሮፓና በአሜሪካ ትግራይ ተበደለ ብለው የሚጮኹት ለትግራይ ህዝብ ገዷቸው ሳይሆን ተላላኪዎቻቸውና ሰርቀው የሚያበሏቸው ወያኔዎች ቀን በመጨለሙ ነው። የሮማው ጳጳስ ለትግራይ ህዝብ አስባለሁ ሲሉን ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር በሥፍራው የነበሩት መርቀውና ይቅናችሁ ብለው ነው የላኳቸው። ጊዜው ጨለማ ነው። ትሻልን ስንሻ ትብስ ትተካለች። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ይሉሃል እንዲህ ነው። የቀንና የማታ ቀማኞች በሚራወጡባት ምድር የድረሱልኝ ጥሪ ስሚ የለም። የኢትዪጵያ ህዝብ ይፍረደኝ ማለትም በዘልማድ እንጂ ፈርዶ አያውቅም። የሞተላት ቀርቶ የገደላት በላ የተባለው እንዲህ ባለው ዓይነት የፓለቲካ ትርምስ ሃገሪቱ እድሜ ልኳን ስትንደፋደፍ ስለኖረች ነው። ገና ብዙ እናያለን። ቀንና ወራጅ ጎርፍ አያመጣው የለ። እንሰንብት። በቃኝ።

 6. በመጀመሪያ አንድ ህዝብ ቢፈልግ ለአብን ወይንም ብልፅግና ወይንም ኢዜማ ወዘተ የፈለገውን ቡድን ደግፎ የመውጣት መብቱን ማክበር ይገባሀል:: ህዝብ ለራሱ የሚበጀውን ያውቃል:: አንተ የጥንቆላ ስራውን ተዝናናበት::ዘመኑ የሳይንስና በእውነት ላይ የተመሰረተ ማስረጃ አሳማኝ ይሆናል:: እኔን የሚገርመኝ ሁሉም እየተነሳ የጠላ ቤት ራፖር እያቀረበ አሰለቸን::

  • ተስፋ አንተም አጀማመረህ መልካም ነው። እንዲህ እንዲህ እያልን በርትተን ከሰራን 110 ሚልዮን ፓርቲ 110 ሚልዮን መሪ 110 ሚልዮን አገር ይኖረናል ለዚህ በርትቶ ማፍረስ ነው ጊዜ ማባከን አያስፈልግም። የጸሎቱ ጉዳይ ተንቋል እስቲ ደግ ጊዜ ያምጣ።።

 7. እውነቱ አንለወጥ በማለታችን ሳናስቸግርህ አልቀረንም ምሬትህን ሳየው ቦታህ ከሊቀ ሊቃውንቱ ጎን ሁኖ ታየኝ እዚህ እየመጣህ ከምትበሳጭ የአለቃ ክንፉን መጽሀፍ ብትደጋግመው ይሻልህ መሰለኝ በዚህ ሂደት መጽሀፋቸውን ተንተርሰህ ብታሸልብ አሟሟትህ ያማረ ይሆናል። እውቀትን ሲቆፍር ጥልቁ ውስጥ የቀረ ተብሎም ይታመንልሀል እስከዛው ለምሁራን ጉባኤ የምትልከውን ድርሳንህን ቀጥልበት። እውቀት ያብዛልን

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.