አገር ሠሪ፣ አገር አልባ ሕዝብ! ዐማራው በትግሬ ወያኔ/ኦነግ አገር የለሽ ተደርጓል! – በተክሌ የሻው መኮንን

constitutionዐማራ እግሩን ለጠጠር፣ ደረቱን ለጦር ሰጥቶ ኢትዮጵያን እንደ አገር ከሠሯት ነገድና ጎሣዎች መካከል አንዱና ግንባር ቀደሙ መሆኑን የአገሪቱ የረጅም የመንግሥትነትና አገራዊነት ታሪክ ያስረዳል። ዐማራው ቋንቋን ከፊደል፣ ሃይማኖትን ከሥርዓት፣ ሕግን ከባህል፣ አጣጥሞና አዋሕዶ ለኢትዮጵያውያን የወል መጠቀሚያነት ያበረከተ ሕዝብ ነው። ጀግናና ኩሩም ነው። የዛሬውን አያድርገውና፣ መብቱ ሲነካበት የማይወድ፣ ለማንነቱና ለነፃነቱ ቀናዒ ሕዝብ የነበረ ነው። እነዚህ መገለጫዎቹ መሆናቸውን የድሆኖ፣ የእንትጮ፣ የሣር ውኃ፣ የመተማ፣ የዐድዋ፣ የአምባላጌ፣ የወልወል፣ የቆራሄ፣ የመቀሌ፣ የማይጨው ወዘተ ጦር ሜዳዎችና የተገኙት ድሎች ሕያው ምስክሮች ናቸው።

ይሁንና ዛሬ የትናንት አገር ሠሪው አገር አልባ እንዲሆን ተደርጓል። በተገኘበት ማንም ያሻውንና የፈለገውን ግፍ የሚፈጽምበት እና የግፍ ዓይነቶች መለማመጃ ሆኗል። ከ1972 ዓም ጀምሮ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ሁመራ፣ ራያ እና ቆቦ፣ወረዳና አውራጃዎች ነዋሪ ዐማራዎች ፣እንዲሁም ከ1983 ዓም ጀምሮ ሐረርጌ፣ ወለጋ፣ኢሉባቡር፣ ከፋ፣ ጎጃም(መተከል) ወዘተ ክፍለ-ሀገሮች ነዋሪ በሆኑ ዐማሮች ላይ፣ የተፈጸመውና እየተፈጸመ ያለው ጅምላ ግድያ፣ እሥራት፣ ግርፋት፣ ማፈናቀል፣ ማዋከብ፣ ዘር ማጥፋትና ዘር ማጽዳት መሠረት ያደረጉት፣ “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት” ከተባለው የወይኔ/ኦነግ የጥፋት ሰነድ ነው። ይህ ደግሞ የተዘጋጄው የዐማራ ጥላቻን ገንብቶ ባደገው መለስ ዜናዊና እርሱ በመራው የኦነግ ቡድን ነው። አስፈጻሚዎቹም የትግሬ-ወያኔ በልኩ ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ ሊያስቡ ይችላሉ ብለው በመጨነቅ የጌቶቻቸውን ዕኩይ ዓላማዎች በከፋ እና በባሰ መልኩ ለማስፈጸም ባምሳላቸው ኮትኩተው ባሳደጓቸው ባንዳዎች ነው።

አገርሠራ አገር አልባ –


 

2 Comments

 1. ለመሆኑ አማራዎች ሐረርጌ፣ ወለጋ፣ኢሉባቡር፣ ከፋ፣ ጎጃም(መተከል) ወዘተ ክፍለ-ሀገሮች ምን ለመስራት ሄዱ? ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋ የአማራ ሃገር መጥተው የሰፈሩ ኦሮሞዎች፣ ሶማሌዎች፣ ወላይታዎች ወዘተ አሉ ወይ?? አሁንም የቅኝ አገዛዝ እየተመኛችሁ ነው?? ካልሆነ ከነባር ህዝቦቹ ጋር ተስማምቶ መኖር ያቃታችሁበት ምክንያት ምንድር ነው?? አሁንም እየገደላችሁ ታለቅሳላችሁ! ኢትዮጵያን ታፈርሳላችሁ እንጂ የድሮ የበላይነታችሁ ጭራሽ ተመልሶ አይመጣም!

  • አባ ጫላ
   1. ማንም መሬት የጠፈጠፈ “ነባር” የሚባል ህዝብ የለም፡፡ ለምሳሌ ኦሮሞ ዛሬ የሰፈረባቸውን ቦታዎች የያዛቸው ከግራኝ አህመድ አገር የማስፋፋት ውጊያ በኋላ ነው፡፡
   2. “አማራዎች ሐረርጌ፣ ወለጋ፣ኢሉባቡር፣ ከፋ፣ ጎጃም(መተከል) ወዘተ ክፍለ-ሀገሮች ምን ለመስራት ሄዱ?” ያልከውን በተመለከተ ባጭሩ “ሀገራቸው ስለሆነ” የሚል ነው መልሱ፡፡ ይሄ በየትም ሀገር ያለ ነው፡፡ ኒውዮርክ፣ ለንደን፣… የሚኖሩት እዚያ የተወለዱ ብቻ አደለም፡፡ ምናልባት አንተ ውጭ ሀገር እየኖርክ ከሆነ ለምን አሜሪካ/አውሮፓ ሄድክ?
   3. “ከነባር ህዝቦቹ ጋር ተስማምቶ መኖር ያቃታችሁ ምክንያት ምንድር ነው?” ያልከውን በተመለከተ በኃ/ስላሴ፣ በደርግ፣ ዘመን ለምን ጠብ አልነበረም? የሚል ጥያቄ አቀርብልሃለሁ፡፡ ሁለተኛ፡- አብሮ መኖር ያቃተው አማራው ሳይሆን አንተ “ነባር” ያልከው ህዝብ ነው ከ“መጤዎቹ” ጋር መኖር ያቃተው፡፡ ምክንያቱም “ነባር” የተባለው ህዝብ ሰነፍ ነው፡፡ ካለው አኗኗር ራሱን መለወት አልቻለም፡፡ “መጤ” የተባለው ህዝብ ጠንክሮ ሰርቶ ራሱን ለወጠ፡፡ ሀብት አካበተ፣ ከበረ፣ መኪና ገዛ፣ ፎቅ ሰራ፣… እንዲህ ያለው ሁኔታ “ነባሩን” በቅናት እርር ድብን አለ፡፡ እሱም ሰርቶ እንደመለወጥ የሌሎችን ላብ ለመቀማት ተራወጠ፣ እናም ውጣልኝ ምናምን እያለ ጠብ ጫረ… ይሄ ነው እውነቱ፣

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.