ኢትዮጵያ ታላቅ ልጇን አጣች! ታላቁ ምሁር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ በ89 አመታቸው አረፉ

ኢትዮጵያ ታላቅ ልጇን አጣች!

getachew
ታላቁ ምሁር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ በ89 አመታቸው አረፉ

ኢትዮጵያ ዛሬ ቅርሷ፤ የጥንታቂ ቋንቋዋ ሊቅ፤ የጽሑፎቿ ሰብሳቢ፣ ጥልቅ ተመራማሪና የእውቀቶቿ ተርጓሚ፤ በሴሜቲክ ጥናት ዘርፍም በዓለም ላይ ወደር የማይገኝለት ጠቢቧን፤ በርካታ መጽሐፍትንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የታሪክ፣ የቋንቋና የሥነ ጽሑፍ ምርምሮችን ያሳተመ የስነ ጽሑፍና የታሪክ ተመራማሪ፤ የአገር ተቆርቋሪ፣ የፍትሕ፣ የነፃነትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነውን ታላቁን ልጇን ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን አጥታለች።

ፕሮፈሰር ጌታቸው ኃይሌ በሕይዎት ዘመኔ ካገኘኋቸው፣ እድሜ ዘመናቸውን ካካበቱት እውቀታቸው ትንሽም ቢሆን የተማርሁባቸው፣ ሥርዓት በተላበሰ ሥነ ዘዴ የሞገትኋቸውና የተጣራ የታሪክ ማስረጃ ሲቀርብላቸውም [አንዱን ይህን በመጫን ይመለከቷል

] ለዘመናት ደክመው የጻፉትን መጽሐፍ ሳይቀር ለማረም ዝግጁ እንደሆኑ ካየኋቸው ታላላላቅ የአገራችን ምሑራን መካክል በአንደኛ ደረጃ የማስቀምጣቸው ታላቅ ሰው ነበሩ። እኔና ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በተለያየ ካካሄድናቸውና ተቀድተው ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ከፈቀዷቸው ውይይቶቻችን መካከል የተሰወኑትን ወደፊት እዚህ ለመለጠፍ እሞክራለሁ።

ከፕሮፈሰር ጌታቸው ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ያወራሁት መታመማቸው ሰምቼ ለመጠየቅ ከወራት በፊት በደወልሁበት ወቅት ነበር። በዚህ ከወራት በፊት በነበረን የስልክ ውይይት [ከታች ተያይዟል] ብዙም ጤና እንደሌላቸው፣ መተንፈስ እንደተቸገሩና አንድ ቀን የእስትንፋሳቸው መጨረሻ እንደሚሆን በሚያሳዝን ድምጽት ነግረውኝ ነበር። በዚህ አባባላቸው ምንም ልቤ ቢሰበርም ላበረታቸው ስለፈለግሁ ገና ከሳቸው ብዙ እንደምንጠብቅና እንደሚሻላቸው ተስፋዬን ገልጨላቸው ነበር።

ከዚህ ውይይታችን በኋላ ላገኛቸውና ስለ ጤናቸው ደግሜ ልጠይቃቸው በተደጋጋሚ ወደ እጅ ስልካቸው ብደውልም ስልካቸው አይነሳም። ይህ ከፕሮፌሰር ጌታቸው ጋር የነበረኝ የስልክ ቆይታ የመጨረሻው ይሆናል ብዬ አላሰብሁም ነበር። ሆኖም ግን በሰው ላይ ሞትን የሚያህል እዳ አለና የኔታ የነገሩኝንና ያሰቡትን ሁሉ ለመፈጸም ሳይችሉ አንድ ቀን የእስትንፋሴ መጨረሻ ይሆናል ያሉት ቀን ደረሰ። እጅግ ያሳዝናል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ስለሰጡን ሁሉ እናመሰግንዎታለን! በሰላም ይረፉ! እግዚአብሔር ነፍስዎን በአጸደ ገነት ያኑራት። ለቤተሰባቸው በሙሉ ጽናትንና ብርታትን ፈጣሪ ይሰጣቸው ዘንድ ከልብ እመኛለሁ።

አቻምየለህ ታምሩ

image

image (1)
image (1)

8 Comments

 1. የእግዚአብሔር ፍርድ ይግባኝ አይባል። ኢትዮጵያ ሌላ ብርቅየ ልጇን አጣች። አይ ዘንድሮ።

 2. የፕሮፌሰርን ነፍስ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ።
  እንደው ስሜቴን ለማጋራት ያህል፣ በውነት የዚህ አይነት የመርዶ ዜናዎች እጅግ ልቤን ያሳዝኑታል። ኢትዮጳያን ብለው፣ ከሷም ርቀው፣ “በእውቀቴ ህገሬንና ወገኔን ሳላገለግልበት” እያሉ እየተብሰለሰሉ፣ “ለህገሬ አፈር አብቃኝ” እያሉ እየጸለዩ አመታትን ገፍተው ኢትዮጲያ በሌለችበት ይቺን አለም መሰናበት ማቆሚያው መቼ ይሆን? ፈጣሪ እባክህ ታረቀን!

 3. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
  እናመሰግንዎታለን! በሰላም ይረፉ! እግዚአብሔር ነፍስዎን በአጸደ ገነት ያኑራት። ለቤተሰባቸው በሙሉ ጽናትንና ብርታትን ፈጣሪ ይሰጣቸው ዘንድ ከልብ እመኛለሁ።
  RIP his soul

 4. ያሳዝናል ሚዛን አስጠባቂ መካሪ ትውልድ አስቀጣይ ጀግና አባት አጣን እንግዲህ ምን ይባላል ነብስ ይማር ማን ይተካቸው ይሆን አምላክ ይሁነን።

 5. ኢትዮጵያ ታላቅ ልጇን አጣች! Ethiopia is dead and she lost her children what a funny title is that ? mehaim yetsafew article

  egna amaroch benante mikniyat de sudan alekin

 6. ሞት ለማንም አይቀሬ ነው። የፕ/ሩ እልፈት ያሳዝናል። ያው ሃገሪቱ ያሏትን አንጡራ ልጆች በወረፋ በሞትና በሌላም መንገድ እየገበረች ነው። ምን ይባላል። ዝም ነው። ይህን እንጂ ከሞቱ አይቀር በዘርና በቋንቋ ሳይሰለፉ ለአንዲት ሃገርና ህዝብ ፍሬ አፍርቶ ማለፍ መታደል ነው። የፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ሞት የደስታም የሃዝንም ጭምር ነው። ደስታ እድሜ ጠገብ ሆነውና ለሃገራቸው በሚችሉት ሁሉ አስተዋጾ በማድረጋቸው ሲሆን ሃዘኑ ደግሞ እውነተኛ ሰው በተወደደበት ዓለም ላይ ኡስን የመሰለ ጀግና ማጣታችን የልብ ጉዳት ነው። ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ በሥራና በኑሮው ለእውነት የመሰከረ ከብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች አንድ ነው። ያው ሰው በፍሬው አይደል የሚታወቀው። ልጆቹ፤ የልጅ ልጆቹ ሁሉ ለሃገርና ለወገናቸው ያላቸው ቅናትና ጽናት ይደነቃል። አይዞአችሁ። እጅግ ለማደንቀው ለፕ/ር ጌታቸው የተጻፈ አጭር ግጥም።

  ምነው አዘናችሁ ፊታችሁ ጠቆረ? ምን አግኝቷችሁ ነው ልቧችሁ ያዘነ
  ያሳዘነንማ የጌታቸው ሞት ነው ሽዋ ላይ ተወልዶ ሸንኮራ ያደገው
  በዓለም ተንከራቶ ሃገርን ያስጠራው አለፈ እንደ ዋዛ ሰው እንደሚሆነው
  አይደለም አትበሉ ሄዷል ላናገኘው እኔ እርግጠኛ ነኝ አልሞተም እንደ ሰው
  ሥራና ድርጊቱ ለሃገር ያቆመው እሱ ነው ታሪኩ ህያው የሚይደርገው።

 7. አባታችንን አጥተናል አቻምየለህ ጧፉን ተረክበህ ለተከታይ ታስተላልፋለህ ብለን እናምናለን የሚመጥናቸው እንኳን ይገኛል ብለን አናምንም። አምበሳው መሄዱን አይተው ያዙኝ ልቀቁኝ ማለታቸው አይቀርም

  • ውድ ሰመረ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸውን አሳነስኻቸውሳ! አቻምየለህ ገና ምኑን ለይቶ ነው? ዘፈኑ አንዲት ነች፤ በአንድም በሌላም አማራ ከሁሉ ይበልጣል ነው! ሲያጋንን ፕሮፌሰር ጌታቸው “በሴሜቲክ ጥናት ዘርፍም በዓለም ላይ ወደር የማይገኝለት ጠቢብ” ብሏቸዋል። “ለዘመናት ደክመው የጻፉትን መጽሐፍ ሳይቀር ለማረም ዝግጁ እንደሆኑ ካየኋቸው ታላላላቅ የአገራችን ምሑራን መካክል በአንደኛ ደረጃ የማስቀምጣቸው ታላቅ ሰው ነበሩ” ይለናል፤ አቻም ስለ ምርምር አኳኋን ብዙ የገባው አይመስልም፤ ምርምር በወቅቱ በተገኘው መረጃ ነው የሚካሄድ፤ ሌላ የተሻለ መረጃ ሲገኝ መቀበል ግድ ነው፤ ፕሮፌሰር ጌታቸው ከ፷ ዓመት በፊት ምርምራቸውን ሲጀምሩ ዛሬ የምንገለገልባቸው የቴክኖሎጂ እሴቶች አልነበሩም፣ ወዘተ ፩/ አየኋቸው የሚለን ታላላቅ ምሑራን እነማን ናቸው? አይነግረንም፤ ፪/ ራሱን ሲያተልቅ “ከፕሮፈሰር ጌታቸው ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ያወራሁት” ይለናል፤ ስንቴ ነው ከእርሳቸው ጋር ያወራው? ማንስ በስልክ ደውሎ ያወራቸው የለ? አንተም ሰመረ፣ ራስህን ለመካብ ወዳጅህን አትካብ፤

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.