ለክብርት ወ/ሪት ብርቱካን ሜዴቅሳ (የመትከል ድጋፍ ኮሚቴ በብሪታንያ)

metekel2021@gmail.com
ሰኔ 2 ቀን 2013 ዓም

birtukan

ለክብርት ወ/ሪት ብርቱካን ሜዴቅሳ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዳይሬክተር

የጉዳዩ፦ በመተከል ዘርንና ማንነትን መሰረት አድርጎ በአገው/አማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም እንዲቻል፤ አሳታፊና ታማኒነት ያለው ምርጫ እንዲደረግ ምርጫ ቦርዱን ስለመጠየቅ፦

እኛ በታላቋ ብሪታንያ የምንኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፤ በመተከል ዘርንና ማንነትን

መሰረት አድርጎ በንፁሀን ዐማራዎችና አገዎች ላይ እየደረሰ ያለው እልቂት ያሳሰበን፤ የማሕበራችን ዋና አላማ፤ በመተከልና በሌሎችም የአገራችን ዳርቻዎች ሁሉ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዜግነት ማግኘት የሚገባቸው መብት ሳይሸራረፍ እንዲተገ በር፣ የሰው ልጅ መብት በሰውነቱ ታውቆ እንዲከበር የሚታገል መሆኑን እየገለጽን፤ ለየትኛውም የአገራችን ብሔረሰብ በአ ድሎነት የቆመ አለምሆኑን ለቦርዱ ፍጹም በሆነ ቃል ልናረጋግጥ እንዎዳለን። ስለሆነም ምርጫ ቦርድ አቤቱታችን ቀና በሆ

ነ መንገድ ተመልክቶትና የአገራችን ህገ መንግስትና ስለ ሰው ልጆች መብት መከበር በብዙ አንቀጾች የተደገፈውን ኢትዮጵያ የስማማችበትን የአለማቀፍ ህግ ለማስከበር ሲልም ጭምር የአቀረብነውን ማመልከቻ በአውንታዊነት ተቀብሎት ሁሉም የመተከል ኗሪዎች እኩል የፖለቲካ ወክልና አግኝተው የንጹሀን ወገኖቻችን ሰቆቃ እንደ ሚያከትም ተስፋችን ከፍተኛ ነው።

ምርጫ ቦርድ በተቋምነቱም ፕሮፌሽናል በሆኑ፣ የኢትዮጵያ የቊርጥ

ቀን ልጆች በመመራቱ በዚህ አጋጣሚ የተሰማንደስታ ልንገልጽ እንወዳለን። ከዚህም ባሻገር በጉምዝ ብሔረሰቦች ስም ከአ

ሸባሪዎች ጋር ተባባሪ በሆኑ ወንጀለኞችና በፖለቲካ ነጋዴዎች ምክንያት ማህበራችን በተጠቀሱት ብሔረሰቦች ላይ ጥላቻ እደሌለው፤ ይልቁንም ለወደፊቱ ለጉምዝ ብሔረሰቦች ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ እድገት ማህበራችን የበኩሉን አስተዋጾ ማድረግ የሞራል ግዴታው እንደሆነ ይገነዘባል።

እንደሚታውቀው ቤንሻንጉል ክልል የሚባል የአስተዳደር መዋቅር ወያኔ ከመመስረቱ በፊት መተከል የጎጃም ጠቅላይ

ግዛት/ከፍለሐገር አንደኛው አውራጃ ነበረ። እንደ ኃያሉ የንጉሰነገስታችን፣ የአፄ ቴወድሮስ የትውልድ አውራጃ፣ እንደ ቋራ ቁጥራቸው በጣም ያነሰ በሱዳንና በኢትዮጵያ ግዛት ያለ ቪዛ እየተሸጋገሩ የሚኖሩ የጉምዝ ብሔረሰቦች ሲኖሩበት፤ ነገር ግን የአማራ/አገው ብሔረሰቦች ከሌሎች ኗሪዎች ጋር ሲወዳደር ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት እንደነበረው ሊታወቅ ይገባል። ለዘመናት የዐማራ፣ የአገው፣ የሺናሻና የኦሮሞ ብሔረሰቦች በንግድና በቋሚ የግብርና ስራ በመሰማራት ይኖራሉ። የተጣለባቸውን ግብር በመክፈልና ለሚፈለገው የአገር ልማት የዜግነታቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። በ1888

ዓ ም በተደርገው የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት መተከል የሚኖሩ የዐማራና የአገው ተወላጆች የጎጃም ንጉስ ከነበሩት ከንጉስ ተክለሀይማኖት ጦር ጋር ዘምተው ለኢትዮጵያ ነጻነት የህይወት መሳዋትነት በመክፈል አድዋ ድረስ በግራቸው ተጉዘው ተዋግተዋል። እንደገናም 1928 ዓ ም ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ዘመን በመተከል የሚኖሩ

የዐማራና የአገው ብሔረሰብ ኗሪዎች በወቅቱ የጎጃም ጠቅላይ ግዛት አገረገዥ ከነበሩት ከራስ እምሩ ሐይለሥላሤ ጦር ጋር ተቀላቅለው በሽሬ ግምባር በተደርገው ጦርነት ከመዝመታቸውም በላይ፤በአምስቱ ዓመት የአርበኝነት ዘመን በመተከል ይኖሩ የነበሩ የአማራና የአገው ብሔረሰቦች ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን ታሪክ የሚዘክረው ነው። በመሆኑም አፄ ኃይለሥላሤ ከስደት ወዳገራቸው ሲመለሱ የገቡት በመተከል በኩል ነው። በዚያን ወቅት ለጎጃም አርበኞችና ለንጉሱ ጦር በመተከል ይኖሩ የነበሩ አማሮችና አገዎች፤ መንገድ በመምራትና ከእለት ምግብ እስከ ስንቅ በማዘጋጀት ከፍተኛ እርዳታ ያደርጉ እንደነበር የሚታወቅ ነው። በመተከል ልዩ ስሙ በላያ የተባለውም አካባቢ የኢትዩጵያውያን አርበኞች የጦር ሰፈር እንደነበር የሚታወቅ ነው። አጼ ሐይለሥላሤም “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” በሚለው

መጻሕፋቸው በመተከል የአማራ/አገው ኗሪዎች ስለአደረጉላቸው መስተንግዶና አርበኝነት አመስግነው ጽፈዋል። ከላይ ከተጠቀሱት በሔረሰቦች ለየት ያለ የኑሮ ባሕል ያላቸው የመተከል ኗሪዎች የበርታ፣ የጉምዝ፣ የማኦና የኮሞ ብሔረሰቦች በተለምዶ የጉምዝ ብሔረሰቦች እያልን የምንጠራቸው ናቸው። እነኝህ ብሄረሰቦች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ

ብዙዎቹ ከብት በማርባትና በአደን ስለሚኖሩ፤ከላይእንደተጠቀሰው ድንበር ተሻግረው በጎረቤት አገሮችም ይኖራሉ።

በነገስታቱና በደርግ ዘመን በዚህ በመተከል የሚኖሩ ብሄረሰቦች በመተባበርና በመደጋገፍ በጎጃሜነት የሚኖሩ

ነበሩ። በተለይም በደርግ ዘመን በመተከል የሚኖሩ ብሄረሰቦች የነበራቸው ቅርርብ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ የጎጃም

የባህል ኪነጥበብ የሚንፀባረቀው ከነዚህ ብሔረሰቦች በተገኙ ከያንያንና ሙዚቀኞችም ጭምር ነበር። ከላይ

እንደተጠቀሰው ዐማራ/አገው ህዝብ ብዛት ዛሬ ባለቤት ናቸው ከሚባሉት ብሔረሠቦች በእጅጉ ብልጫ እንዳለው

ቢታወቅም፣ ዐማራ አገውና ኦሮሞ ብሔረሰቦች የዜግነታቸው መብት ተገፎ የፖለቲካ ውክልና

እንዳይኖራቸው ታግደዋል። በዚህም ምክንያት በክልሉና በፌደራል መንግስቱ ዉስጥ ወገን የሌላቸው አማራዎችና

አገዎች በባርነት ከመኖራቸውም በላይ ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ስለተገደዱ አምራች የነበሩ ገበሬዎች በሌላ አካባቢዎች

ሂደው በዘማዊነትና ባልባሌ ስራ ተሰማርተው ኑሮአቸውን በችግር በመግፋት ላይ ይገኛሉ። በመተከል የተፈፀሙ

ወንጀሎች በአለም ላይ ባሉ ጭካኔዎች ሁሉ በከፋ ፤ በ21ኛው ከፍለ ዘመን ብቻም ሳይሆን በሰው ልጅ ታሪክ ተሰርተዋል

ያልተባሉ ናቸው። በዚህ አስቃቂ ድርጊት ወንጀለኞችንና ይህን አሰቃቂ ወንጀል የማስቆም ሀላፊነት ያለባቸው የፌደራልና

የክልል ባለስልጣናት ብቻም ሳይሆኑ፤ ይህን የአረመኔዎች ወንጀል ሰምቶ በዝምታ የአለፈውን የኢትዮጵያን ህዝብ

ጭምር፤ በአለማቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ የሚያስጠይቀውና

የሚያስወቅሰው ነው። ይህ ሁሉ ወንጀል የሚፈፀመው አገራችን ኢትዮጵያ 1945 ዓ ም የተባብሩት መንግስታት ሲቋቋም

መስራች አባል የሆነችበትንና ተስማምታ የፈረመችበትን ሕግ በመጣስ ነው። በተለይም እንደ አ-አ ታህሳስ 10 1948 ዓ

ም ፖሪስ ላይ በተደረገው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ፤ 30 መስረታዊ የሰው ልጆችን መብት እንዲከበሩ የሚያስገድዽ ሕጎች (30 Basic Human Rights List | Universal Declaration of Human

Rights) በጸደቁበት፤ ወቅት ኢትዮጵያም በስብሰባው ተገኝታ በስምምነቱ ግንባር ቀደም ከነበሩት አገሮች አንዷ ሁና

ፈርማለች። ይሁን እንጅ በወያኔና በብልጽግና ዘምነ መንግስት በመተከልና በአንዳንድ ክልሎች የሰው ልጅ መብት እንዲከበር የሚጠይቁ ዓለም ዓቅፍና የሰለጠኑ ሕጎች የሚተገበሩ ሳይሆኑ፤ በደቡብ አፍሪካ ነጮች በጥቁሮች ላይ የበላይነታቸውን ያረጋግጡበት የነበረውን የአፖርታይድ ስርአት ዛሬ በአገራችንም ያለሀፍረት እየተሰራበት ይገኛል።

ክብርት ሆይ ፤ የምርጫ ቦርድ የአገር መሪዎችን አስመራጭ ተቋም በመሆኑ፤ የአንድን አገር የወደፊት እድል አስመልክቶ ወሳኝ ሚና ያለው ነው። በመሆኑም በዚህ ዓመት የሚደረገው የአገራችን መሪዎች ምርጫ ፤ በርስዎ የሚመራው የምርጫ ቦርድ ለአገራችን የወደፊት እድል ወሳኝ ሚና ከሚጫወቱት ተቋማት ሁሉ በግምባር ቀደምነት የሚታይ በመሆኑ፤ታሪካዊ

ሀላፊነት ተጥሎበታል። ጭምብል ለብሶ ተቋማዊ በሆነ አደረጃጀት፤ በጉምዝ ታጣቂዎችና በኦነግ ሸኔ ስም በአገራችን እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት ግድያ፣ ዘረፋ፣ አስገዾ መድፈርና የኃብትውድመት፤ ምክንያቱ ከመነሻው ከዚህ በፊት የነበረው የምርጫ ቦርድ ሕግን ያልተከተለ፣ ሀላፊነት የጎደለውና አድርባይነትን የተላበሰ ምርጫ እንዲደረግ በመፍቀዱ፤ የዜጎች የመምረጥ የመመረጥ መብትና የፖለቲካ ውክልና እንዳይኖራቸው በመደረጉ ያስከተለው ውጤት ነው። ከዚህም በመነሳት የአለፈው ወደ ጥፋት የመራን የምርጫ ቦርድ አሰራር ታርሞ፤ አገራችን ከገባችበት ችግር ማውጣት እንዲቻል በርሰዎ የሚመራው የምርጫ ቦርድ:

1/ መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት ባልተከበሩበት የምርጫ ወረዳዎች፤ ነጻና ፍሕታዊ ምርጫ ማካሄድ ስለማይቻል፤ በመተከል ከቦታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ያሉ የአማራና ያአገው ብሔረሰቦች መብታቸው ተጠብቆ ወደነበሩበት ቦታ እስኪመለሱ ድረስ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ምርጫው እንዲራዘም በትህትና እንጠይቃለን። ምክንያቱም ሁኔታዎች ተሟልተው ምርጫው በሚደረግበት ወቅትም፤ ሁሉም የመተከል ኗሪዎች ዘርን፣ ቀለምን እምነትንና ሌሎችንም የልዩነት መስፈርቶች ምክንያት ሳይቅርብባቸው፤ የመምረጥ መመረጥ እንዲሁም የፖለቲካ ተውካያቸውን የመምረጥ መብታቸው ተጠብቆ፤ አገራችን በተባበሩት መንግስታት በፈረመችው ውል መስረት እንዲፈፀም እንጠይቃለን።

Universal Declaration of Human Rights (UDHR) by United Nations, signed in Paris on 10 December 1948. 21. ” Right to democracy Everyone has the right to take part in the government of his country, directly or through freely chosen representatives. Everyone

has the right of equal access to public service in his country.” ለሎችም ከተራ ቁጥር 1 እስከ 30 ያሉትም የሚጠቀሱ ናቸው

2/ በተረጋጉና የምርጫ መስፈርቱን ያሟላሉ በሚባሉ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች ዜጎች በእኩልነትና ወከባ ሳይደርስባቸው መብታቸው ተጠብቆ ምርጫው እንዲካሄድ፤ በተለይም በኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ

ሕገመንግስት፤ በአንቀጽ 25፣32፣ 38 እንዲሁም ለሎችም ሕጎች መሰረት በማድረግ ምርጫው ዲሞክራሲያዊና አሳታፊ እንዲሆን በታረዱ፤ በቀስትና በጦር ተጨቅጭቀው በተገደሉ ሙታን ስም በአክብሮት እንጠይቃለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

የመተከል የድጋፍ ኮሚቴ በብሪታንያ

4 Comments

  1. Birtukan mideksa anbessa yenetsanet tagay ayehuna ya abey teshkerkari wenber(rimorike) ashkabach

    Planting trees and killing people” Prosperity party motto

  2. “ጂብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” የሚባለው ተረት
    የተጻፈው ታሪክ እንደተጠበቀ ሆኖ የምርጫ አካባቢ እና ጊዜን የሜውስነው የምርጫ ቦርድ እንጂ የምርጫ ቦርድ ዴሪክተር አለመሆኑ ግንዛቤ ይሰጠው። እንዲሁም ለምርጫው ተወዳዳሪ ክፍሎች እና በኢትዮጵያ የሚኖረው ህዝብ ጋር እንጂ በዲያስፓራው እለመሆኑን ግንዛቤ ይሰጠው። በዲያስፓራው ትዕዛዝና ምክር ቢሆን ኖሮማ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ጠቅላይ ሚኒስቲር አብይ እኔን ማማከር ነበረበት እንዳሉት ሆነ ማለት ነው ።በመሆኑም በብርታኒያ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ ሂዶ ተመዝግቦ መመረጥ ነው። ለመሆኑ በየትኛው ዓለም ነው የሀገሩን መሪ ሰላም ባለበት የመረጠ ሰላም በሌለበት በይደር የመረጠ? የአሜሪካ ፕሪዚዳንት ሲመረጥም ሆነ ምርጫው ከተካሄድ በኋላ የውስጥ ከፍተኛ ሁከት ነበር እኮ እንዲያውም በአመጽ በኋይት ሀውሱ ለይ መገዳደል ተፈጽሞአል።ታዲያ ምርጫው ሁለት ሳምንት እንኳን የማይሞላ ጊዜ ሲቀረው በጽሁፉ ተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው አሁን ማቅረብ አሳፋሪ እና አስነዋሪ አይደለምን? ይህንን የጽፍኩት እኔም በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በኋላም ክፍለ ሀገር በመተከል አውራጃ ኦሜድላ ከተማ ተወልጀ ያደግሁ በመሆኔ የተፈጸመው የወገኖች መፈናቀል ከልቤ እየተቆረቆርኩ ይህ ምርጫ ደግሞ ወሳኝ በመሆኑ መፍትሔም ያመጣል ተብሎ ስለታመነበት “የመተከል ድጋፍ ኮሚቴ በብሪታንያ” አጀንዳችሁ ፍሬ ከርስኪ “ጂብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” ነው ።

  3. “ጂብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” የሚባለው ተረት እንደአንተ አይነት ገልቱን ነዉ የሚገልፀው። አስተሳሰብህ የባለግዜ ወይንም የተረኝነት ሥሜት ሰለተናወጠህ እንጂ በዘላን ነፍሰ ገዳዬች ወንድም ወይንም እህት ታርዶ ገደል ቢወረወርብህ ወይንም ከሞት የተረፉ በግዜያዊ መጠለያ ተንጠልለው ባለበት የህዝብ ተወካይ መምረት ይችላሉ ብለህ ስትነግረን ህሌና ቢስ መሆን ብቻ ሳይሆን ከነፍሰ ገዳዬች ለይተን አናይህም። ወደድክም አልወደድክም አማራዉ እንዳይመልስ ከመቼዉም በላይ በህብረት ስለተነሳሳ የወገኖች ደም ፈሶ ስለማይቀር የጨርቃ ምርጫ ሆነም አልሆነም ወገናችን ነፍሰ ገዳዬችን ወደመጡበት ገደል ከተን በሰላም የምንኖርበት ሩቅ አይደለም።

  4. “ጂብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” የሚባለው ተረት እንደአንተ አይነት ገልቱን ነዉ የሚገልፀው። አስተሳሰብህ የባለግዜ ወይንም የተረኝነት ሥሜት ሰለተናወጠህ እንጂ በዘላን ነፍሰ ገዳዬች ወንድም ወይንም እህት ታርዶ ገደል ቢወረወርብህ ወይንም ከሞት የተረፉ በግዜያዊ መጠለያ ተንጠልለው ባለበት የህዝብ ተወካይ መምረጥ ይችላሉ ብለህ ስትነግረን ህሌና ቢስ መሆን ብቻ ሳይሆን ከነፍሰ ገዳዬች ለይተን አናይህም። ወደድክም አልወደድክም አማራዉ እንዳይመልስ ከመቼዉም በላይ በህብረት ስለተነሳሳ የወገኖች ደም ፈሶ ስለማይቀር የጨርቃ ምርጫ ሆነም አልሆነም የወገኖቻችን ነፍሰ ገዳዬችን ወደ መጡበት ገደል ከተን በሰላም የምንኖርበት ቀን ሩቅ አይደለም። ኦመዲላ እንገናኝ፨

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.