ኢዜማና አዲስ አበባ ፤ ትላንትና እና ዛሬ – ፊልጶስ

addis ababa zehabesha……….. ጨልሟል፣ ጨላልሟል
አዎ የእኛ ግዜ ጨልሟል፣ ጨላልሟል
ዓይነ-ስውር እንኳን ውጭ ማየት ፍርቷል።……….

ኢዜማ ሰሞኑን በአዲስ አበባ “የፊኒንፊኒ ፍርድ ቤት “ መቋቋሙን እና ስራ መጀመሩን በመቃወም  ”ህጋዊነት የለውም” በማለት ፍርድ ቤት እንዲያብራራለት ጠይቋል። የኦሮሚያ ፓሊስ ኮሚሽን፣ ትምህርት ቢሮ፣ ወዘተ እኮ ከተቋቋመ ዓመታት እስቆጥሯል። ኢዜማ ዛሬ ነው እንዴ የሰማው? “አለዘገየሽም ወይ?” አለ ዘፋኙ። ምርጫ ሲደርስ ከአዲስ አበባ ህዝብ ድምጽ ለማግኘት  ነው ወይስ ከብልጽግና ጋር የነበረው ወዳጅነት ተቀዛቀዘ? “ታሪክ ራሱን ይደግማል “ይባላል፤ የመኢሶን ታሪክ ሊደገም ይሆን?

የትላንቱ እንቅፋት ዛሬ ይመታናል
የትላንቱ አሽከላ ዛሬም ይጠልፈናል
ላለመማር – መማር እኛ ተምረናል።

ምነው ኢዜማ ህገ-ወጥ ከንቲባ ሲሾም  ያኔ ህጋዊነት እንደሌለው አልታየውም? ያኔ በህገ-ወጥ “በምክትል ማዕራግ”’ በሚል ተለጣፊ ስም የተሾሙትን  እነታከለ ኡማን ”አትናገሩብን! አሻጋሪዎቻችን ናቸው፡ እፋችሁን ዝጉ’’ ተብለን ነበር።  የአዲስ አባባን  በኦነጋዊ ኦዴፓ መዋጥን የተቃወሙትን እና አሁንም በእስር ላይ የሚገኙትን እነ ባልደራስን ”ሕገ-ወጥ ናቸው” ተብለን አልነበር እንዴ? እንዴት ነው ነገሩ ? ወይስ የአዲስ አበባ ህዝብ ”የማስታወስ ችሎታውን አጥቷል መሰላችሁን? ለነገሩ ከነተረቱም ‘’የወጋ ይረሳል፤ የተውጋ እንጅ..”

አሁን ደርሳችሁ የአዲስ አባባ ተቆርቋሪ ለመምስለ የሄዳችሁበት መንገድ ”ወይ አገሪ!” ያሰኛል። እንኳን እናንተ ማንም እንደሚረዳው አዲስ አበባ የኢትዮጵያና የኦሮሚያ ዋና ከተማ ልትሆን አትችልም። የኦሮሚያ ዋና ከተማነቷን ከተቀበልን  በከተማይቱ የማዘዝ መብት የኦሮሚያ ጉዳይ ነው፤ አራት ነጥብ። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነች ብለን ከተቀበልን ኦሮሚያ ምንም መብት የለውም። ከናዝሪት ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ የተደረገው እኮ ህዝብን ለመበቀል ተብሎ መሆኑ የትላንት ትዝታ ነው።  ግን በሁለት ቢላ ለመብላት ሲባል በህዝብና በአገር ላይ እንዲህ አይነት አሳዛኝ ስራ ይሰራል። ስለ ህግ አራዊቱ እንኳን እናውራ ካልን የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናዝሪት ፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ነው። አዲስ እበባም ተጠሪነቷ ለፌደራል መንግስቱ ብቻ ነው።  ትላንትም ሆነ ዛሬ  በአገራችንም ላይ ሆነ በአዲስ አበባ ላይ የሚካሄደ  ይህ ዓይን ያወጣ ህገ-ወጥነትና ዘርኝነት እኮ የዛሬውን አያደርገና  የእናንተ ”የዳዊት መዝሙር” ነበር፤ ነበር ባይሰበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ንፁሃንን ወህኒ እሚዶል ዳኛ በሽተኞቹን ተሚገል ሀኪምም የከፋ ነው! - በላይነህ አባተ

ኢዜማዎች በእውነቱ ትላንት በእና’ተ ብዙ ተስፋ ያደረጉትን አንገት ማስደፋታችሁና ከብልጽግና ጉያ ውስጥ ተውሽቃችሁ በግዜው ማደርግ ያለባችሁን ባለማድረጋችሁና መሆን ያለባችሁን ባለመሆናችሁ አሁን አገራችን ላለችበት ውድቀትና የአዲስ አበባም በኦነጋዊያን ብልጽግና መሰልቀጥ የአንበሳውን ድርሻ ትወስዳላችሁ።  አሁን በአለቀ ሰዓትና ”የፎጌ ምርጫ ” ሲባል አብራችሁ ማጨብጨብጨባችሁ ሳያንስ   ለአዲስ አበባና ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥብቅና እንደቆማቻሁ ለማስመሰል  የምታደርጉትን መጋጋጥ ትታችሁ “የህዝብ ድምጽ” እንዳይከፋፈልባችሁ

ከብልጽግና ጋር “ብትዋሃዱ“ እንደምትጠቀሙ ከውዲሁ እንምከራችሁ። ካላያ ግን በቁስላችን ላይ እንጨት እየጨመራችሁ መናገር የማንፈልገውን ነገር አታናግሩን።

በመጀመሪያ የወያኔን ህገ-መንግስት ይዘን ስለ “ህጋዊነት ‘’ ማውራታችን ትላንት ”ለስር-ነቀል ለውጥ ነው የምንታገለው፤ የወያኔ ህገ-አራዊት እያለ በኢትዮጵያ ምድር ዲሞክራሲና ሰላም ሊመጣ አይችልም።” ብላችሁ የስንቱን አገር ወዳድ ዜጋ ህይወት አስቀጥፋችሁና በእስር ቤት አካለ ስንኩል አድርጋችሁ እናንተ ግን  በጓዳ በር ኦነጋዊዮን ብልጽግና ተቀላቀላችሁ። ይህም አልበቃችሁም  ለአገርና ለወገን በሃቀኛነት የሚታገሉትን አሁንም ከብልጽግና ጎን ተለጥፋችሁ ራሳችሁን ለኢትዮጵያዊነት ጠበቃ የቆማችሁ በማስመሰል ህዝብን ያለ  ጠ’ካራ ተቃውሚና  ፓርቲ አስቀርታችሁ የብልጽግና መፈንጫና የእናንተ ማላገጫ እንዲሁም  ዛሬ ላለንበት አደረሳችሁን። ሌላው ቀርቶ  የጎንዮሽ ፍትጊያሽሁን ለግዜውም ቢሆን ትታችሁ፤ አገርን ህዝብ  ከማንም የሚበልጥ ብቻ ሳይሆን አሁን ህልውነዋ በውስጥና በውጭ  ሰይፍ እየተገዘገዘች ላለች ለኢትዮጵያችን ቅድሚያ ብትሰጡ ለህሊናችሁም  ሆነ ለነገው ትውልድ የምትነግሩት የኖራችኋል።

ጨልሟል፣ ጨላልሟል
አዎ የእኛ ግዜ ጨልሟል፣ ጨላልሟል
ዓይነ-ስውር እንኳን ውጭ ማየት ፍርቷል።

ህዝቤ ግን በተስፋ ይነጋገራሉ
ነገም ሌላ ቀን ነው እየተባባሉ።

አዎ! …..ነገም ሌላ ቀን ነው::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች

——-//—–ፊልጶስ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ ሰላም የሚያመጣ የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ያስፈልጋል- (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ)

ግንቦት 2013

e-mail: philiposmw@gmail.com

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.