ምርጫ ቦርድ የባልደራስ አመራሮችን በእጩነት የመመዝገብ ሂደት መጀመሩን አስታወቀ

birtuአቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን በዕጩነት የመመዝገብ ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቦርዱ የፓርቲው አመራሮች ለሚወዳደሩባቸው ቦታዎች፤ ቀደም ሲል አሳትሟቸው የነበራቸውን ወደ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እንዲቃጠሉ ትዕዛዝ ማስተላለፉንም ገልጿል።

ቦርዱ ይህን የገለጸው ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 26 ላስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ አንደኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለችሎቱ እንደተናገሩት፤ የባልደራስ ፓርቲ ቀደም ሲል አስመዝግቧቸው በነበሩ ዕጩዎች ምትክ፤ ለምርጫ እንዲቀርቡለት የሚፈልጋቸውን ግለሰቦች እንዲያሳውቅ፤ በመስሪያ ቤታቸው በኩል ጥያቄ ቀርቦለታል። በዚህም መሰረት ፓርቲው በትላንትናው ዕለት አዲሶቹን ዕጩዎች ማሳወቁን አስረድተዋል።

ይህንን የቦርዱን ሰብሳቢ ገለጻ የባልደራስ ፓርቲ ጠበቃ የሆኑት አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለፍርድ ቤቱ አረጋግጠዋል። ምርጫ ቦርድ የዕጩዎችን ምዝገባ ለመፈጸም እንዲያስችለው፤ ባልደራስ በተተኪነት የሚያቀርባቸውን ዕጩዎች ፎቶግራፎች እንዲያቀርቡ መጠየቁን ጠበቃው ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። በጥያቄው መሰረትም የዕጩዎችን “ፎቶግራፎች ለቦርዱ ሰጥተናል” ያሉት አቶ ሄኖክ፤ ሆኖም “ማረጋገጥ የምንችለው የዕጩዎችን ሰርተፊኬት ስንቀበል ነው” ብለዋል።

“የዕጩዎች ሰርተፊኬት የመስጠት ሂደት ቦርዱ በ30 ደቂቃ ማከናወን የሚችለው ነገር ነው። ነገር ግን ቦርዱ ይህን ማድረግ አልቻለም” ሲሉ የባልደራስ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። የዕጩዎች ሰርተፊኬት የመስጠት ሂደት በምን ያህል ጊዜ ሊያልቅ እንደሚችል በፍርድ ቤቱ የተጠየቁት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ፤ “ነገ ጠዋት ያልቃል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

4 Comments

 1. እንዲህ ነው የህግ የበላይነት ማለት። ምንም ይሁን ምን የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይከበር! ባልደራስ ጉዳዩን በህግ ለማስፈጸም የሄደበት ርቀት የሚደነቅና ትልቅ ማስተማሪያ ነው። እነ መረራ ቤታቸው ቁጭ ከሚሉ ችግር ካለባቸው ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዳያቸውን እንደዚህ በፍርድ ቤት ማስፈጸም ይችሉ እንደነበር ባልደራስ አሳይቷል።
  ብርቴም ለህግ የበላይነት ያለሽ አቋም ከጥንቱም ግልጽ ነው። የፍርድ ቤትን ትእዛዝ ተቀብለሽ ማስፈጸምሽ ደግሞ ለሂደቱ ትልቅ አስተዋጾ ነው። የፍርድ ቤት ዉሳኔዎች ሊመሩም ሊጣፍጡም ይችላሉ። ግን መፈጸም አለባቸው። ዋናው ተስፋ እንዳንቆርጥ ነው፤ የህግ የበላይነት በኢትዮጵያ ምድር ይረጋገጣል!
  በምርጫ ብቻ!

  • ከድር ማን ነኝ አልከኝ? የህግና የመንግስት አወቃቀርን አስመልክቶ ብዙ ወገኖች እንዳንተ የእውቀት ክፍተት ላለበት ዜጋ ለማስተማር ቢጥሩም አንተ ግን ያለኝ ይበዛብኛል በሚል እሳቤ ተቸንከረህ ቀርተሀል። ብርቱካን የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ከማስፈጸም ውጭ ምን ንርጫ ነበራት? ያንተ ምስጋናስ ምን የሚሉት ነው? በስዋና ሶልያና ስራቸውን ባግባቡ ባለመወጣት የደረሰው ክሽፈት የዲሞክራሲ ሀሁ ላልገባቸው ጎልቶ አይታያቸውም።

 2. በአሸባሪነት የተከሰሱት እስክንድር ነጋ እና አጋሮቹ ከተመረጡ እዛው እስር ቤት እያሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ ከንቲባ ፣ የምክር ቤት አባል እና ሌሎችንም ከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ይዘው ከእስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን በእስር በመሆን እየፈፀሙ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣንነት ስራዎቻቸውን በማከናወን ማገልገል መቻላቸው ምን ያህል የፖለቲካ ምህዳሩ ሁሉንም አቀፍ እንደሆነ ያሳያል። እነርሱ ታሳሪዎቹ የባልደራስ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከተሜዎቹ ፡ የተተከለ አበባ ውሀ ያመጠጣት ፣ ግብዣ በመናፈሻ ፓርክ የመደገስ ፣ የዛፍ ችግኝ የመትከል ፣ የውጭ ሀገራት እንግዳ በአውሮፕላን ማረፊያ ዝግጅት የመቀበል እና የመሳሰሉት ወሳኝ አታካች የመንግስት አመራር ስራዎችን የማከናወን ብቃቶች እምብዛም ስለሌላቸው ባላቸው የአመራር ዝንባሌያቸው ከእስር ቤት ሆነው በፖስታ ደብዳቤ እየተላላኩ ሀገር መምራት ይችላሉ። አለበለዛማ ከእስር ቤት ወጥተው ስልጣን ላይ ከወጡ እንደልማዳቸው በመንገድ በአደባባይ እየተንቀሳቀሱ እንደ ጋሽ ታድዮስ ታንቱ : ቤቀለ ገርባ ወይም እንደ ጃዋር መሀመድ በአዲስ አበባ አደባባይ ወጥተው አፀያፊ የሽብር ተግባራቸውን ስለሚቀጥሉ ፡ ይህ መፍትሄ ነው የተባለው ከእስር ቤት ሆነው ሌሎች እነርሱ የሚሾሙዋቸውን ሰዎችንም እስር ቤት እንዲገቡ ና አብረዋቸው ታስረው ሀገራቸውን የሚያገለግሉበት ሁኔታዎችን እያመቻቹ ኢትዮጵያን ከውጭ እና ከውስጥ ችግሮችዋ በማያዳግም አመራር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያን የሚታደጉበት እድል ማግኘታቸው ለዲሞክራሲ ትልቅ ድል ነው።

  ይቅርታን ባህል ያደረገው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት እና የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ያሳዩት አሰራር ለባልድራስ አሸባሪዎች ይቅርታ ስላሰጡዋቸው መላው ሀገር ወዳድ የኢትዮጵያ ህዝብ ለተከበረችው ምሁር ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ እጅግ የላቀ አክብሮት እና ታሪካዊ ምስጋና ልናሳያት ይገባል። እውነትም ይቅርታን ባህላችን ማድረጋችንን የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው ይህ ለእነ እስክንድር ነጋ የተወሰነው ውሳኔ።

 3. Good judgement. Responsibility is not as easy as changing wigs or painting faces. We all knew that people like Eskinder are innocent citizens, making peaceful; struggle for justice.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.