ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ የተባለው ድምጽ እንዴት ተቀናበረ?

ግንቦት 24 ቀን 2013 (ኢዜአ)

194059271 2951293821779744 5673781794107421719 n

“ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ ድምጽ ነው” ተብሎ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ድምጽ እንዴት ተቀናበረ?
ከሰሞኑን የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አቢይ አህመድ የተናገሩት ሃሳብ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ አንድ የተቀነባበረ ድምጽ ተሰራጭቷል።
ኢዜአ ባደረገው ማጣራትም ‘ሾልኮ ወጣ’ የተባለው ድምጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ወቅቶች ከተናገሯቸው ሃሳቦች ተለቅመው በቅንብር የተሰሩ መሆናቸውን ሊያረጋግጥ ችሏል።
የኢዜአ ማረጋገጫ በምስል ማስረጃ ጭምር የተደገፈ ነው።
የመጀመሪያው ሃሳብ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ባካሄደበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በአካል በመገኘት ኢህአዴግ ስላካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማና የሊቀመንበርነት ምርጫ ማብራራታቸው ይታወሳል።
በዚህም የጁንታው ቡድን ‘ምርጫውን አሸንፈናል’ በማለት ደጋፊዎቹን በየመጠጥ ቤቱ ማስጨፈሩን አንስተዋል።
“የመጀመሪያው የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ በኢህአዴግ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለሳምንታት Brain wash ለማድረግ ሰውን መልክ ለማስያዝ ግምገማ ሲባል ሲጀመር ሲበተን ስንሰበሰብ ስንበተን ሚጨበጥ ነገር ሳንይዝ ከቆየን በኋላ ምርጫውን ያደረግንበት ዕለት ሙሉ ቀን በምርጫ criteria ላይ ስንወያይ ውለን እስከ ሌት አጋማሽ ድረስ ያው እንደሰማችሁት እጅግ አጨቃጫቂ ካሁኑ ጦርነት ያልተናነሰ የተደራጀ የጁንታው ስብስብ በቀጥታ መዋጋት የማይችልበትን በጎን ማዋጋት በሚቻልበት መንገድ ሰፊ ስራ ከሰራ በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል አካባቢ ምርጫውን አሸንፈናል ብሎ የጁንታው የውጭ ክንፍ በየመጠጥ ቤቱ መጨፈር ጀመረ። ያ ከመሆኑ በፊት እኛ እማንፈልጋቸው ሰዎች አይመረጡም It is on our dead body በመቃብራችን ላይ ብቻ ነው የሚፈጸመው ብለው በግልጽ ይፎክሩ ነበር”
“ሾልኮ ወጣ” በተባለው ድምጽም ከዚህ ሃሳብ ውስጥ በምርጫ ስለማሸነፍ የተናገሩትን በዚህ መልኩ ተቀናብሮ ተለቅቋል።
“ምንም ጥርጣሬም ሚስጢርም የለውም ምርጫውን አሸንፈናል”
ሌላኛው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚያዚያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የክልሎች የምርጫ ዝግጅትን በሚመለከት ከክልል ርእሳነ መስተዳደሮች ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን ለውጥ የማይፈልጉ የውጭ ሃይሎች ምርጫውን በማጨናገፍ ታዛዥ መንግስት እናቆማለን ብለው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
“ከአንድ አመት በፊት ገደማ ጀምሮ ኢትዮጵያ የጀመረችው አጠቃላይ የብልጽግና ጉዞ እና ያላትም ትልልቅ ራዕዮች የሚቀናቀኑ ሃይሎች በተቻለ መጠን ምርጫውን አጨናግፈን ምርጫው እንዳይሳካ አድርገን ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ አባልተን ከዛ የሽግግር፣ የስብስብ፣ የድርድር የሚባል ማህበር ፈጥረን መንግስት በማድረግ እንደ አንዳንድ የጎረቤት አገሮች ደካማ መንግስት ብቻ ሳይሆን የምናዘውን የሚፈጽም መንግስት እናደርጋለን ብለው ዶክመንት አዘጋጅተው ማሰራጨት ከጀመሩ ውለው አድረዋል”
“ሾልኮ ወጣ” በተባለው ድምጽም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልጽግና ፓርቲ ምርጫውን በማጨናገፍ የሚፎከካከሩ ሃይሎችን ተስፋ ለማስቆረጥ እንዲሰራ መመሪያ እንደሰጡ ተደርጎ በሚከተለው መንገድ ቀርቧል።
“ምርጫውን አጨናግፈን ተፎካካሪ ሃይሎች ተስፋ እንዲቆርጡ የማረግ ትልቅ ሃላፊነት አለብን”
በዚሁ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ስህተቶችን በማረም ምቹ የምርጫ ምህዳር ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
“ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚከሷቸው ክሶች አልፎ አልፎ የሚደመጡትና ምርጫ ቦርድም የሚያነሳቸው እኛ ነን ማየት ያለብን ትናንሽ የሚባል ስህተት ማረም አለብን። ትናንሽ የሚባል ጥፋት እያጠፋን የሚፎካከሩ ሃይሎች ተስፋ እንዲቆርጡ ምርጫ ቦርድ ድጋፍ አላገኘሁም ብሎ እንዲያስብ ማድረግ የለብንም ስህተት ማረም አለብን” ብለዋል።
ከዚህ ሃሳብም የብልጽግና ፓርቲ ምርጫውን በሃይል ለማሸነፍ ስህተቶችን ማረም እንዳለበት ተደርጎ ነው በድምጽ ተቀናብሮ የቀረበው።
“እንደምታውቁት ፖለቲከኛ የሚባለው ሃይል አክቲቪስትን ጨምሮ ስልጣን ለመያዝ ነው የሚሰራው ስለዚህ የእኛ ካድሬዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ትንንሽ የሚባል ስህተት ትንሽ የሚባል ጥፋት በየዕለቱ ገምግመን ማረም መቻል አለብን” የሚለው ድምጽ ሊቀናበር ችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተዘጋጀው “የአዲስ ወግ” የውይይት መድረክ ላይ ምርጫው ይዞት ስለመጣው እድልና ተግዳሮት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
“አሁን ትልቁ ችግር ለምሳሌ ምርጫ አይደረግ የሚሉ ሰዎች ማነው ሀላፊነት ወስዶ ምርጫ አይደረግ የሚለው መንግስት ስልጣኔ እንዲቀጥልልኝ ስለማልመረጥ ምርጫ አያስፈልግም ካለ ያው ድሮ የምታውቁት የሽግግር መንግስት እያልን ለረዥም አመታት የምንቆይበት ሁኔታ ይፈጠራል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ አሁን እህቴ እንዳለችው አውቶሜቲቭ ሲስተም ኖሮ ምርጫ ይደረግ አይደረግ ቮት ማድረግ የሚችልበት ደረጃ አልደረሰም ማነው የሚወስነው ወሳኙ አካል ኮንስኮንሱንም ነው ሀላፊነት ሚወስደው መሆን አለበት በዚህ ምክንያት መሀል ላይ ስንቸገር ምርጫን እንደ አማራጭ እንወስዳለን “
ከዚህ ጥቅል ሃሳብ ውስጥ የሚከተለው ሃሳብ ተወስዶ ህዝብን ለማደናገር ተሞክሯል።
“አሁን ደግሞ ምርጫው አለማድረጉ መልሶ ከነበረው ሁኔታ የዘቀጠ ነገር እንዳይፈጠር ምርጫን እንደ አማራጭ እንወስዳለን” ይላል።
በምርጫው ሁሉም ታዛቢ እንዲገባ መፈቀዱን በመጥቀስ የግርግር ስጋት እንደሌለ የገለጹበት ከሚከተለው ሃሰብ ውስጥ የተወሰዱ ቃላቶች ስለመኖራቸው ማወቅ ተችላል።
“በነገራችን ላይ እኔ በከተማው ውስጥ የድንጋይ ሰልፍ አይነት ነገር ብዙ አልሰጋም በአሁኑ ምርጫ እንደዛ ስጋት የለኝም ምክንያቱም ለሁሉም ታዛቢ ተፈቅዷል ከሞላ ጎደል በምርጫው ብልሽት እንዳይኖር ጥረት ይደደረጋል የሚያስፈራኝ ቅጥረኞች የተገዙ ሰዎች ራሳቸውን ከህዝብ ጋር አመሳስለው አንዳንድ ቦታ መራጭን አስመራጭም በማጥቃት ጥፋት እንዳያስከትሉ ነው”
ሾልኮ ወጣ በተባለው ድምጽ ውስጥ የሚከተለው ሃሳብ ተቀናብሯል።
“በዚህ ምርጫ በኛ በኩል በተወሰ ደረጃ ብልሽት እንዳይኖር ጥረት ይደረጋል
“ብዙ ሀይሎች ገንዘባቸውን ግዜአቸውን አጥፍተው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነገር በማመስ የኢትዮጵያን ቀጣይነት ማስተጓጎልና ያላትን ሀብት መዝረፍው የሚፈልጉ ሀይሎች ከቅርብም ከሩቅም አሉ”
የሀሰት መረጃ “በዚህ ምርጭ ስልጣን ለመያዝ ሚፎካከሩ የፖለቲካ ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚድያዎች ከምትገምቱት በላይ ከሩቅም ከቅርብም አሉ”
“ጎረቤቶቻችን ካልያዝን ፈተና ይገጥመናል የሚል ሀሳብ ነበረ ደሞ አየን በተግባር ዘንድሮ ከእርትራ ጋር ታርቀን ባይሆን ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ያስቸግራል መታረቃችን የግለሰቦች ባለመሆኑ መታረቃችን የህዝቦች መሆኑን ከኤርትራ መንግትስ በላይ የኤርትራ ህዝብ በተግባር አሳይቶናል”
የተሳሳተ መረጃ “ምርጫ ቢደረግ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ያስቸግራል”
“ሾልኮ ወጣ” በተባለው ድምጽም መንግስት ምርጫውን ካለፍላጎቱ ተገዶ እንደገባ በማስመሰል ቀርቧል። በዚህ መልኩ ተቀናብሯል።
“አሁን ትልቁ ችግር ለምሳሌ ምርጫ አይደረግ የሚሉ ሰዎች ማነው ሀላፊነት ወስዶ ምርጫ አይደረግ የሚለው መንግስት ስልጣኔ እንዲቀጥልልኝ ስለማልመረጥ ምርጫ አያስፈልግም ካለ ያው ድሮ የምታውቁት የሽግግር መንግስት እያልን ለረዥም አመታት የምንቆይበት ሁኔታ ይፈጠራል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ አሁን እህቴ እንዳለችው አውቶሜቲቭ ሲስተም ኖሮ ምርጫ ይደረግ አይደረግ ቮት ማድረግ የሚችልበት ደረጃ አልደረሰም ማነው የሚወስነው ወሳኙ አካል ኮንስኮንሱንም ነው ሀላፊነት ሚወስደው መሆን አለበት በዚህ ምክንያት መሀል ላይ ስንቸገር ምርጫን እንደ አማራጭ እንወስዳለን”
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ መድረክ ላይ መንግስት ምርጫው እንዳይስተጓጎል መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
“በነገራችን ላይ እኔ በከተማው ውስጥ የድንጋይ ሰልፍ አይነት ነገር ብዙ አልሰጋም በአሁኑ ምርጫ እንደዛ ስጋት የለኝም ምክንያቱም ለሁሉም ታዛቢ ተፈቅዷል ከሞላ ጎደል በምርጫው ብልሽት እንዳይኖር ጥረት ይደደረጋል የሚያስፈራኝ ቅጥረኞች የተገዙ ሰዎች ራሳቸውን ከህዝብ ጋር አመሳስለው አንዳንድ ቦታ መራጭን አስመራጭም በማጥቃት ጥፋት እንዳያስከትሉ ነው”
ተቀናብሮ በወጣው ድምጽ ግን መንግስት በተወሰነ ደረጃ ብቻ ምርጫው እንዳይስተጓጎል መዘጋጀቱን ‘በተወሰነ ደረጃ’ የሚል ድምጽ ከሌላ ቦታ በማምጣት ተቀናብሮ ቀርቧል።
“በዚህ ምርጫ በኛ በኩል በተወሰ ደረጃ ብልሽት እንዳይኖር ጥረት ይደረጋል”
በዚሁ በአዲስ ወግ የውይይት መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቅርብ ከውጭም ያሉ ቅጥረኞች ኢትዮጵያን ለማተራመስ እየሰሩ ነው ሲሉ ይገልጻሉ።
“ብዙ ሀይሎች ገንዘባቸውን ግዜአቸውን አጥፍተው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነገር በማመስ የኢትዮጵያን ቀጣይነት ማስተጓጎልና ያላትን ሀብት መዝረፍው የሚፈልጉ ሀይሎች ከቅርብም ከሩቅም አሉ”
ይህ ሃሳብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫውን አሸንፈው ስልጣን የመንጠቅ አቅም ያላቸው አስጊ ሃይሎች ከቅርብም እንዳሉ እንደተናገሩ ተደርጎ ተቀናብሯል።
“በዚህ ምርጭ ስልጣን ለመያዝ ሚፎካከሩ የፖለቲካ ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚድያዎች ከምትገምቱት በላይ ከሩቅም ከቅርብም አሉ”
ሌላኛው ሃሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር እርምጃን አስመልክተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር እርቅ ባትፈጥር ኖሮ የህግ ማስከበር እርምጃው ምን መልክ ሊኖረው እንደሚችል አብራርተዋል።
“ጎረቤቶቻችን ካልያዝን ፈተና ይገጥመናል የሚል ሀሳብ ነበረ ደሞ አየን በተግባር ዘንድሮ ከእርትራ ጋር ታርቀን ባይሆን ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ያስቸግራል መታረቃችን የግለሰቦች ባለመሆኑ መታረቃችን የህዝቦች መሆኑን ከኤርትራ መንግትስ በላይ የኤርትራ ህዝብ በተግባር አሳይቶናል”
ይህን ሃሳብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮሮና ባይመጣና ምርጫ ቢካሄድ ኖሮ ምን ሊገጥመን ይችላል እንዳሉ በማስመሰል እንደሚከተለው ተቀናብሮ ቀርቧል።
“ምርጫ ቢደረግ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ያስቸግራል”
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተመሳሳይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሀገር መከላከያ ትጥቅ ለምን ትግራይ ክልል እንደተከማቸ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
“በነገራችን ላይ መከላከያ ስንቁም ትጥቁም፣መካናይዝዱም ለዓመታት እዛ እንዲከማች የተደረገበት ምክንያት ይሄ ለውጥ ባይመጣም በሆነ መንገድ የሀገሪቷ አቅም እዛ ብቻ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ነው።ምንም ጥርጣሬም ምስጢርም የለውም፤ ይሄ ማለት ነው።”
ከዚሁ ሃሳብም ቃላትን በመውሰድና ከምርጫ ጋር በማገናኘት እንደሚከተለው በድምጽ ተቀናብሮ ቀርቧል።
“ነገር ግን ከወዲሁ እርግጠኛ ሆኜ የሚነግራችሁ ምንም ጥርጣሬም ምስጢርም የለውም ፤ምርጫውን አሸንፈናል።”
ሌላኛው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የክልሎች የምርጫ ዝግጅትን በሚለከት ከክልል ርእሳነ መስተዳደሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ” ከውጭ በተውሶ የሚገቡ ሃሳቦች ምን ያህል ኢትዮጵያን ዋጋ እንዳስከፈሏትና ኢትዮጵያዊያንን ደም እንዳፋሰሰ እንደሚከተለው አብራርተዋል።
“ከውጭ የምንበደራቸው ሀሳቦች ናቸው (imported thought) የዛሬ 50፣60 ዓመት ገደማ አሁን ኢትዮጵያን እያመሰ ያለ እሳቤ ከሸቀጦቻችን ጋር ከውጭ የገባ ነው።ከሸቀጦቻችን ጋር በተለመደው መንገድ ከውጭ የገባ ሃሳብ የሆነ ቦታ ዲዛይን ተደርጎ ታስቦበት በትምህርት ስርዓትና በተለያየ የመንግስት ተቋማት ውስጥ እንዲገባ ተደርጎ እዚህ ያለ ሰው በትክክል ሳያሰላስል፣ ሳያስብ እሳቤዎቹን ወስዶ እውቀት አድርጎ በመቀበሉ በህዝባችን መካከል ከፍተኛ የሆነ ፍጅት፣ደም መፋሰስ አስከትሏል።”
ይህን ሃሳብ በመውሰድ ከምርጫ በኋላ መንግስት በሚወስደው እርምጃ ብዙ ደም መፋሰሶች እንደሚኖሩ አስመስሎ ቀርቧል።
“ብዙ እርምጃዎች ይወሰዳል። ለዚህ የተዘጋጀ ግብረሃይል ሥራውን ጀምሯል።ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ ፍጅት፤ ደም መፋሰስ ይፈጠራል።”
በዚሁ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የክልል እርሰና መስተዳድሮች ፈተናዎች ሳይበግሯቸው እንዲሰሩና ካለፉት ፈተናዎች ተምረው ኢትዮጵያን ለማሻገር እንዲተጉ መመሪያ ሰጥተዋል።
“ስጋት እንዳይፈጠርብን የሚፈልገው ብዙ ፈታኝ ቻሌንጆች ከግራ በቀኝ አሉ። በየቀኑ የምንሰማው ክፉ ዜና ነው። በየቀኑ የምንሰማው እሳት ማብረድ ነው። በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን አሁን እየገጠመን ያለው ፈተና ከመጣንበት አንጻር ኢመንት ነው።የመጣንባቸው ፈተናዎች ከባድ ነበሩ።አሸንፈናቸዋል፤እናሸንፋለን፤ሰላም እናመጣለን፤ብልጽግና እናመጣለን፤ ኢትዮጵያን እናስቀጥላለን፤ይሄን የማይፈልጉ ሃይሎች ከዚህ ቀደም እንደሆነው እነሱም ይቀበራሉ።”
“ሾልኮ ወጣ” በተባለው ድምጽም ይህን ሃሳብ የብልጽግ ፓርቲ አመራሮች ፈተና ሳይበግራቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተስፋ እንዲቆርጡ እንዲሰሩ እንደመከሯቸው ተደርጎ ወጥቷል።
“የሚፎካከሩ ሃይሎች ተስፋ እንዲቆርጡ የማድረግ ትልቅ ሃላፊነት አለብን ፤ካለፍንባቸው ፈተናዎች አንጻር ይሄን ማሳካት ብዙም ከባድ አይደለም።”
የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ቢቂላ ይህን የሃሰት መረጃ ያሰራጩ አካላት ዓላማ ህዝብን ማሳሳት፣ ማደናገር፣ የህዝብን አብሮ የመኖርና የመቻቻል እንዲሁም የአንድነት ስሜት ለመጉዳት መሆኑን አስረድተዋል።
በኅዝብ መካከል ያለውን መተማመን ለመሸርሸር እንዲሁም የህዝብና የመንግሥትን መልካም ግንኙነት ላማበላሸት ትኩረት ያደጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተሰራጨው መረጃ ላይ በፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ የተነሱ ጉዳዮች አለመኖራቸውንና የተሰራጨውም መረጃ መሰረተ ቢስ አደናጋሪ የሐሰት መረጃ መሆኑንም ጠቁመዋል።
”ሰሞኑን እንደዚህ አይነት ሃላፊነት በጎደላቸው ሃሰተኛ የመረጃ ምንጮች የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ስብሰባን አስመልክቶ ከስራ አስፈጻሚ ሰብሰባ ሾልኮ የወጣ ነው ቢል ድምጽ በእነዚህ ሃሰተኛ የመረጃ ምንጮችና ሚዲያዎች አየተላለፈ የሚገኘው ድምጽ ፍጹም ሃሰት የሆነ ምንም አይነት መሰረት የሌለው ከእነዛ ድምጾች ውስጥ አንድም ቃል ከዛ ከስራ አስፈጻሚ ስብሰባ የሚገናኝ ቃል የሌለው በተለያዩ ወቅቶች የፓርቲያችን ፕሬዝዳንት ካደረጓቸው ንግግሮች ውስጥ የተወሰዱ ቃላትን ቆርጦ በመቀጣጠልና በመገጣጠም ትርጉም የሚሰጥ አረፍተ ነገር እንዲመስሉ በማድረግ ህዝብን ለማደናገር የተሞከረ እጅግ በጣም እኩይና አደገኛ ሃላፊነት ተግባር ነው”
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት የኢዜአ ን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCSjaw-eGJSkvcXHyTpQyT1Q
የሀገር ውስጥና አለም ዓቀፍ መረጃዎችን በዝርዝር ለማግኘት የዌብሳይታችን ደንበኛ ይሁኑ፡ena.et/
======================================================

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት ሥልጣን ለማስረከብ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን የሚናገሩበት በምሥጢር የተቀዳ ድምጽ ቅጂ ይፋ ሆነ

Amba Digital – አምባ ዲጂታል
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ማጠቃላያ ላይ ተናግረውታል ተብሎ ‹‹ኬሎ›› በተባለ የኦንላይን ሚዲያ በተለቀቀ የድምጽ ቅጂ፤ እስከሚቀጥለው 10 ዓመት ድረስ ማንም ሰው መንግሥት መሆን እንደማይችልና ሥልጣን ለማስረከብም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል፡፡
ምርጫው እንዲራዘም ብልጸግና ፓርቲ ፍላጎት እንደነበረው የገለጹት ጠ/ሚ ዐቢይ የኮሮና ቫይረስ መምጣት ምርጫውን ለማራዘመ ፓርቲያቸውን እንዳስገደደው አስታውሰዋል። በዚሁ የድምጽ መልዕክት «እንደምታውቁት ፖለቲከኛ የሚባለው ኃይል አክቲቪስቱን ጨምሮ ሥልጣን ለመያዝ ነው የሚሠራው» ያሉ ሲሆን፣ የፓርቲያቸው ካድሬዎች በዚህ ሂደት ጥቃቅን ስህተቶችን ማረም መቻል እንዳለባቸውና አንድም ስህተት ቢሆን ብዙ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አስምረውበታል።
ጠ/ሚሩ «በዚህ ምርጫ ስልጣን ለመያዝ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ሰዎች፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች ከሚገመተው በላይ ብዙ ኃይሎች ከቅርቡም ከሩቁም» መኖራቸውን በመናገር ይህ እንደሚያስፈራቸውም ገልጸዋል።
ነገር ግን «እስከሚቀጥለው 10 ዓመት ድረስ ማንም ሰው መንግሥት መሆን አይችልም» በሚል አቋማቸውን በግልጽ አስቀምጠዋል።
«እሞታታለሁ እንጂ ስልጣን አልሰጥም» ሲሉም በድምጹ ላይ ተሰምተዋል። ለዚህም ብዙ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የገለጹት ጠ/ሚሩ «ለዚህ የተዘጋጀው ግብረኃይልም ሥራውን ጀምሯል» ብለው ሲናገሩ ተደምጠዋል። መንግሥታቸው በሚወስደው እርምጃ ሰበብ «ከፍተኛ የሆነ ፍጅት፣ ደም መፋሰስ» ሊፈጠር እንደሚችል ያልሸሸጉት ጠ/ሚ ዐቢይ «ነገር ግን ከወዲሁ እርገጠኛ ሆኔ የምነግራችሁ ጥርጣሬም ምስጢርም የለውም፣ ምርጫውን ከወዲሁ አሸንፈናል፤ በቀላሉ ነው ያሸነፍነው።» ሲሉ ለፓርቲያቸው ሥራ አስፈጻሚ አባላት ተናግረዋል።
በተለቀቀው የሦስት ደቂቃ ድምጽ ማጠቃላያ ላይ ጠ/ሚሩ ስለ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሲናገሩ የተሻለ እቅድ እንዳላቸው ያሳወቁ ሲሆን፣ «በተቻለ መጠን ምርጫውን አጨናግፈን፤ የሚፎካሩ ኃይሎች ተስፋ እንዲቆርጡ የማድረግ ትልቅ ኃላፊነት አለብን» እንዲሁም «ካለፍንባቸው ፈተናዎች አንጻር ይህን ማሳካት ከባድ አይደለም» ሲሉም ተደምጠዋል። ይህ ብቸኛውን መንገድ እንዲሳካና እንዳይበላሽም የፓርቲኣቸው አመራሮች «ድርብ ኃላፊነት ወስደው እንዲያሳኩት ጠይቀዋል።

1 Comment

  1. ኪያ የሚባለውን የኬሎ (ቂሎ) ሚዲያ ባለቤት/ሥራአስኪያጅ ትንስ ልጅ ቢጤ ከአንድ “ባውንሰር” ከሚመስል ጋዜጠኛ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ አድምጣቹሃል? ፟ “ልለቀው ነው” እያለ ሲፎክር ማለት ነው። በትንሽዬ እውቀቱ [I bet he is no more than 10th grader!] እንደ “ጃዋር ጁኒየር” መሆንም ያምረዋል። እና ድንቁርናውን የት ጋ ታገኙታላቺሁ መሰላችሁ? የሆነ ቅንና ሰዓት ጠራና “ስፖንታኒየስሊ እንለቀዋለን” አለ። አይ ተሳስቶ ይሆናል ብዬ ምንም አላኩም ነበር፤ ደገመው! ምን ለማለት ፈልጎ መሰላችሁ፣ “ሳይመልቲኒየስሊ እንለቀዋለን”። አስፈላጊም አልነበረም። በአንድ ጊዜ ካልሆነ እንዴት ለተለያዩ አህጉሮች በተለያየ ሰአት እንደሚለቀቅ ፈጣሪ ይወቅ። ስለፊልም ምረቃ የሰማውን መሰለኝ ወደ ዩቱብ ያመጣው። እንግዲህ እንደዚህ የእለት እንጀራ ማግኛ መንገዱ ተራራ የሆነባቸው ናቸው ዩቱብ ከፍተው ህዝብ ነጻ እናወጣለን እያሉ እስክ እንደዚህ አይነት ዝቅጠት ድረስ የሚወርዱት። ለነገሩ አነ ጃዋር በተመሳሳይ ቅንብር አባይ ጸሃዬ ላይ በተሳካ ሁኔታ ስሙን አጠልሽተው ነበር፤ “የኦሮሞን ህዝብ ልክ እናስገባለን” ብሏል የሚል አይነት ነገር አቀነባብረው ማለት ነው። “የለመደች ጦጣ …….” አሉ እማማ አረጋሽ
    Obviously the fact that the video turned out to be fake has disappointed many and wider than the circles of Kiya and company.
    በምርጫ ብቻ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.