የውጭ ሃገራትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሃገራዊ አንድነትን ማስጠበቅ ያስፈልጋል – ሲኖዶሱ

193398066 4081306075293434 1299934782905421868 n
ፎቶ፡-ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን አገልግሎትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤ አጠናቀቀ።

ከቤተክርስቲያን ሰላም እስከ ሃገር ደህንነት፣ ከቀያቸው ስለተፈናቀሉና ለስደት ስለተዳረጉ፣ በተለያዩ ቦታዎች ስለሚታዩ አለመግባባቶች እና ሌሎች ማህበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይም ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የጠፋ የሰው ህይወትና ንብረት በየአህጉረ ስብከቱ ተጣርቶ እንዲቀርብ ወስኗል።
የአምልኮ ስፍራ፣ ስም እና ተጠብቆ የቆየ የቤተክርስቲያኗ ክብር እንዲሁም በካህናትና ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለ ሞትና ስደት ከየአህጉረ ስብከቱ እንዲጣራና መንግስትም አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ አሳስቧል።
የአምልኮ ስፍራዎች በተለይም በዩኔስኮ የተመዘገቡ ስፍራዎችን ልዩ ጥበቃና ትኩረት በመስጠትም ከእነማንነታቸው ተጠብቀው እንዲቆዩ መንግስት የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ዳር ድንበሯንና አንድነቷን አስጠብቃ የኖረች ሃገር መሆኗን የጠቀሰው ቅዱስ ሲኖዶሱ፥ አሁን የሚታየው የውጭ ሃገራት በሃገሪቱ ህልውና ላይ እያደረጉት ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሃገራዊ አንድነቱን ከምንጊዜውም በላይ ማስጠበቅ ያስፈልጋልም ነው ያለው።
የህዳሴ ግድብ ከድህነት ለመውጣት አንድ እርምጃ ወደፊት መሆኑን የጠቀሰው ጉባኤው የአንድነት ማሳያ የሆነውን ይህንኑ ግድብ ፍጻሜውን በማፋጠን ከጨለማ ለመውጣት መላው ኢትዮጵያውያን እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርቧል።
በአረንጓዴ አሻራ በኩልም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልምላሜን ስታስፋፋ መኖሯን በማስታወስ መንግስት ባዘጋጀው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመሳተፍ መላው ዜጋ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ነው ጥሪውን ያቀረበው፡፡
በሌላ በኩል ህብረተሰቡ ራሱን ከኮቪድ19 ወረርሽኝ በመጠበቅና በተለይም ባለመግባባት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በተለመደው የኢትዮጵያዊነት መተሳሰብ እንዲደርስላቸውም ጥሪ ያአቅርቦ ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫም ጨዋነት የሚመሰከርበት ምርጫ እንዲሆን የሰላም ጥሪውን አስተላልፏል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከሰኔ 14 ቀን ጀምሮ እስከ ሃምሌ 4 ቀን 2013 አ.ም. ድረስ በመላው ሃገሪቱና በውጭ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ውሳኔ በማሳለፍ አጠናቋል።
በማህሌት ተክለብርሃን
ኤፍ ቢ ሲ

3 Comments

  1. በሚመጥናቸሁ የሃላፊነት ደረጃ ላወጣችሁት መግለጫ ከእግራችሁ ሥር ዝቅ ብዬ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
    በምርጫ ብቻ!

  2. ኤርትራውያን አማራዎችን በመዳፋቸው ከተዋቸዋል። ጉረኛ ጎንደሬ አማራ ነኝ ብሎ በአፉ እየጎረረ ኤርትራውያንን ተቆጣጥረውታል። በረከት ስምኦን እስር ቤት ስለገባ አማራ ከኤርትራውያን የቁጥጥር መረብ ወጣ የሚባለው ውሸት ነው። አማራ የሚያደንቀው ጉራውን እውነት ነው ጉራ ብቻ አይደለም የሚሉት እንደ ኤርትራውያን ያሉ አፈ ቀላጤዎችን እስካገኘ ድረስ ተያይዞ ገደል እየገባ ነው። በተለይ የህወህት ዘመንን ያላዩ የደርግ ርዝራዦች ጎንደሬ አማራዎች አስካሪ ኤርትራውያን ከበዋቸዋል። በያሉበት ጎንደሬዎች ጎበዝ አማራዎች እያለ የሚያዳንቃቸው እስካገኙ ድረስ ኢትዮጵያን በአፍ ብቻ የሚጠርዋት ሆነዋል።

  3. ለማንጁስ እንዲያው ምን ነካህ ጃል በሲኖዶሱ ጉባኤ የተላልፈው መልክት ሌላ ከየትኛው ስንኝ ላይ ነው ስለ ኤርትራ ፤ ስለጎንደሬ ጉራ ፤ስለ በረከት ስሞን አና አማራ ጉረኞች የሚያወራው? ምነው ይህንን ያህል በአማራው ላይ ጥላቻው ከእግር እስከ ራስህ የመነጀሰህ? አይ የሚገርም ነው የአማረኛ ፊደል መጻህፍ እንጂ የምትበላበትን ሣህን ቆሻሻ እና ንጽሁን የመለየት ቀውሰሃል እና ታከም። ካልሆነም በየመንገዱ እየዞርክ መንጂስ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.