የኬርያ ኢብራሂም በሀሰት መስክሪ ተብዬ ነው – ጌታቸው ሽፈራው

የማይመስል ነገር!

kerya
kerya
1) ትህነግ የራሱን ብቻ ሳይሆን የሌላውን ዘርፎ ለጦርነት ሲያውለው የኬርያ ኢብራሂምን መኪና ሾፌሯ ወደ አዲስ አበባ ይዞት መጣ። ወዲያውኑ ዜና ተሰራለት። “ታማኝ ሾፌር የመንግስት ንብረት እንዳይባክን አደረገ።” ተባለ። ነው እንዴ? ታማኙ እንኳን ሾፌሩ አይመስልም። ቀጥሎ፣ ከዛም ቀጥሎ፣ ከዛም ሲቀጥል የሆነው የሚያሳየው ይሄን ነው።
2) አዛውንቶቹ የትህነግ አመራሮችና አባላት ጫካ ሲገቡ ኬሪያ ኢብራሂም መቀሌ ቤቷ ውስጥ ቁጭ ብላ ተያዘች። እነ ስብሃት ነጋ እንኳን ጫካ ሲገቡ እሷ ቁጭ ብላ የተያዘችው ለምን ይሆን? ከአሜሪካ ተንከልክላ የመጣችው የሀየሎም ሚስት፣ ሌሎቹ ከኬርያ በእድሜ የሚገፉ ሴቶች ጫካ ለጫካ ሲንከራተቱ ኬርያ ቁጭ ብላ የተያዘችው ረስተዋት ሄደው ነው?
3) ኬርያ ወደ አዲስ አበባ ከመጣች በኋላ አንድ ሰሞን /ለአንድ ወር ያህል/ ፍርድ ቤት አልቀረበችም። የፍርድ ቤትን ጉዳይ የሚወስን የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበረች ሴትዮን ፍርድ ቤት ሳትቀርብ አንድ ወርና ከዛ በላይ ማቆየት ጫና ስለማይፈጥር አይመስለኝም። መንግስት የጨከነባት ለማስመሰል ይሆናል። ሕግ እንዳላከበረላት፣ እንደበደላት ለማሳየት ይመስላል። እንደማትሰራት ለማሳየት ይመስላል።
4) ባለፈው ከእስር እንደተፈታች “ለኦፕሬሽን የሚጠቅም መረጃ ሰጥታኛለች” ተብሎ ተነገረ። ዛሬ አልመሰክርም አለች ቢል ያሳምናል ወይ? ጫካ ያሉትን የሚያስደመስስ መረጃ ሰጠች ከተባለ በእስር ላይ ያሉት በእስር እንዲቆዩ ለማድረግ መረጃ አልሰጥም ትላለች?
5) እነ ስብሃት ነጋ ላይ ለመፍረድ የሰው ምስክር አያስፈልግም። የትህነግ አመራሮች ናቸው። መቀሌ ሆነው የትህነግን አቋም ይዘው የተናገሩበት፣ የዛሩበት መረጃ ሞልቷል። የተያዙት እጅ ከፍንጅ ነው። ጫካ ከተዋጊው ኃይል ጋር ሆነው ሰራዊቱ ተዋግቶ ነው የያዛቸው። ለእነዚህ ሰዎች የሰው ምስክር ይህን ያህል አስፈላጊ አይደለም። የሰው ምስክር ካስፈለገ ደግሞ የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት በቂ ናቸው። ተዋግተው ነው የያዟቸው። በሰራዊቱ ላይ ጥቃት ፈፅመው፣ ጦርነት ከፍተው ጫካ ገብተው ተያዙ የሚለው ነው ዋናው ወንጀል። ዋናው መረጃ የሚሆነው ከትህነግ ጋር የተያያዘው ነው። በድርጅት ስም የፈፀሙት ነው። እንደ ድርጅት ነው ያጠቁት። ስብሃት ነጋ ሲያዝ ዋናው የትህነግ ሰው ብለው በሚዲያ አልተናገሩም? ዋነኛው ትህነግ ብለው ዘጋቢ ፊልም አልሰሩበትም? በሰነድ፣ እንደ ድርጅት ያለውን ሚና ነውኮ። በዚህ ረገድ የሰው ምስክር ካስፈለገ ከኬርያ ያልተናነሰ የብልፅግና ሰዎችስ በአደባባይ አይመሰክሩትም? አብይ አህመድ፣ ደመቀ መኮንን፣ አብርሃም በላይ…… አይመሰክሩም?
6) መጀመርያ እንደተወራው ኬርያ ለኦፕሬሽን ጠቃሚ መረጃ ሰጥታለች። አሁን ደግሞ ትህነግ አሸባሪ ተብሏል። ሰጠችው የተባለው መረጃ አሁን አይጠቅምም። አሁን ሌላ የሚጠቅም ነገር አለ። አሸባሪዎች እስር ቤትን እንደ አንድ ትልቅ ማዕከል ይጠቀሙበታል። ያልታወቀበት መልዕክት መለዋወጫ ነው። እስር ቤት አይጠረጠርም። አንዳንዴ አዲስ አበባ ሆነው ዝም የሚባሉ ሰዎችም አንዳንድ ነገር ስለሚጠቅሙ ይሆናል። የእስር ቤቱ ደግሞ የበለጠ ነው። አልመሰክርም ብሏል የተባለ ሰው ይታመናል። ሰው አምኖት መረጃ ያካፍለዋል። እሱም ለሚመለከተው ያካፍላል።
7) ኬርያ የታሰረችው ገና ትህነግ ከእነ ብዙ ኃይሉ እያለ ነው። የተፈታችው ከእነ ብዙ ኀይሉ እያለ ነው። አሁን ብዙ ደክሞ ጭራሹን አሸባሪ ተብሏል። ያኔ የመደራደር እድል እያለው፣ አዲስ አበባ ያሉት ጠያቂዎቿ “መቀሌን ሊቆጣጠር ነው” እያሏት እመሰክራለሁ ብላ የወጣች ሴትዮ ዛሬ መቀሌ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተዋቅሮ፣ ትህነግ በአሸባሪነት ተፈርጆ “አልመሰክርም” ብላ እንደገና ትገባለች?
8/ ኬርያ “አልመሰክርም” ብላ መንግስት መልሶ ማሰር ቢፈልግ፣ እሷን በሚያጀግን መልኩ “አልመሰክርም ብላ ነው” ብሎ ዜና ይሰራል? ጭራሽ “በሀሰት መስክሪ ተብዬ ነው ብላለች” ብሎ ራሱን ይከሳል? ከፈታት በኋላ ከትህነግ ጋር ግንኙነት አላት ብሎ በሌላ ጉዳይ ሰበብ መፈለግ አቅቶት ነው? እሷ የራሷን መልስ ልትሰጥ ትችል ነበር። መንግስት ግን ፊት ለፊት “አልመሰክርም ብላ መልሸ አሰርኳት” ብሎ በራሱ ሚዲያ ዜና ያራባል?
ያኔም የነበረው፣ አሁንም የምናየው የዜና ጋጋታ ምን ለማሳመን ነው?

1 Comment

  1. one day they appoint them to highest positions without abilities. The other day they use and throw them into the bins. This is the habit of dictators who hate more educated and experienced citizens because of their inferiority complex. They appoint cadres, kill the country and die with it.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.