የዐፄ ቴዎድሮስ አማራጭ ዶ/ር መኮንን ብሩ።

abiy 4ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ቤንሻጉል ክልል ተጉዘዉ የሕዳሴ ግድቡን እየተመለከቱ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡና መጪዉንም የኢትዮጵያ ብልፅግና እና ርዐይ በርቀት ለማመላከት ሲጥሩ በተመሳሳይ ሰዓት ደርዘን የሚሞሉ የአሜሪካን ነጭ ሴኔተሮች ዋሽንግተን ዲሲ ተቀምጠዉ በትግራይ እየተፈፀመ ይገኛል ያሉትን የጦርና የዘር ማጥፋት ወንጀል በመወያየት በኢትዮጵያ ላይ ሊወስዱ የሚችሉትን ማዕቀብ ይወያዩ ነበር። የሁለት ከተሞች ወግ አልያም የሁለት ሀገሮች ሕልም አልያም የአልገዛምና ትገዛለህ እሰጣግባ መገለጫ መሆኑ ነበር።

ነፍሳቸዉን ይማርና ታላቁ የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪና ፀሐፊ ተክለ ጳድቅ መኩሪያ ‘የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ’ ሲሉ በሰየሙት መፅሐፋቸዉ የሚከተለዉን ቃል በቃል አስፍረዋል “የእንግሊዝ መንግስት ወደ ዐፄ ቴዎድሮስ ለሚልከዉ የጦር ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል ሮቤርት ከርኔሌስ ናፒየር የሚባለዉን ሾመ። ….በዚህ ጊዜ በንጉሱ በዐፄ ቴዎድሮስ ላይ ከሸፈቱት ከትግሬ ሹማምንቶች ከነደጃች በዝብዝ ካሳ ከላስታዉ ከነዋግ ሥዩም ጎበዜ መላላክ ዠምረዉ የትግሬና የላስታ ሕዝብም የእንግሊዝ ወታደር መምጣት ደስ ብሎት መንገድ እየመራ በማንኛዉም ነገር ይረዳቸዉ ዠመር።” (ገፅ ፴፮)
ታሪክ አልፎ አልፎ እራሱን ይደግማልና ዛሬ ኢትዮጵያ በተመሳሳይ የታሪክ አጋጣሚ ዉስጥ ያለች ይመስላል። የእንግሊዝ ጦር ነጋሪት እየጎሰመና ጦሩን እየሰበቀ ወደ ንጉሱ ድንበር መቅደላ ድረስ ብዙ ሺህ ሰራዊት ይዛ እየገሰገሰች ባትታይም የዘመኑ ነጋሪትና ጦር ግን ከዋሽንግተን እስከ ለንደን፣ ከካርቱም እስከ ካይሮ፣ ከእስራኤል እስከ አየርላንድ ወደ ታሪካዊቱ ሀገር ኢትዮጵያ እየተሸረበና እየተሰበቀ ይገኛል። የዛሬዎቹ ካሳ በዝብዞችም ኢትዮጵያን ለሰላሳ ዓመታት በዝብዘዉ አጥንቷን ካስቀሩ በኃላ ዋሽንግተንና ለንደንን መንገድ እየመሩ የጠቅላዩ ድንበር ድረስ ለመዉሰድ እየተቁነጠነጡ ይገኛሉ።

ዐፄ ቴዎድሮስ ያኔ በመቅደላ ተራራ ለእምዬ ኢትዮጵያ የመጨረሻዉን መስዋዕትነት ከመክፈላቸዉ በፊት የከዷቸዉን መሰሪዎች እጅ ቆርጠዋል፣ ከወራሪዎች ጋር ያሴሩትን ጉድጓድ ዉስጥ ወርዉረዋል፣ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የመጡትን በሙሉ ተራግመዉም ጥይት እንደ ዉሃ ጠጥተዋል። ዛሬም የአብይ መንግስት ያለዉ አማራጭ ይህ ብቻ ነዉ።

በዉጪ ሀገርም ሆነ በሀገር ዉስጥ ተቀምጠዉ በኢትዮጵያ ላይ የሚያሴሩትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት መጀመር አለበት። ሀገር ከዲሞክራሲ በላይ በመሆኗ የሚከፈለዉን ሁሉ ለመክፈል መወሰን ይገባዋል። የኮሶ ነጋዴ ልጅ ብሎ ያቅራራዉን አዝማሪ ኮሶ አጠጥቶ በቅዘን እንደገደለዉ ዲሲና መሰል ከተሞች ተቀምጠዉ እንደ ካሳ በዝብዝ ለጠላት መንገድ የሚያመቻቹትን በቶሎ ፈር ማስያዝ ያስፈልጋል።

የአማራ ልዩ ኃይል የትግራይ ሴቶችን ደፍሯል ሲል ያላየዉን የሚቀባጥረዉ የርዕዮት ሚዲያ ትናንት የወልቃይትና ጠገዴ ሴት ትግሬ ካላገባሽ መሃን እናደርግሻለን ተብላ ስትጎሳቆልና ወንድ ልጆቿ ሲገደሉና ሲሰደዱ ቃላት ወጥቶት የማያዉቀዉ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ዛሬ አማራን ሲወነጅል ለሚሰማ ዉንጀላዉ ኢትዮጵያን መሆኑ ግልፅ ነዉ።
አማራ ለሰላሳ ዓመታት ሞትና ጉስቁልና የተፈረደበት፤ የአባቶቹንም መሬት ተነጥቆ የተሰደደበት ዘመን የእኛዉ ዘመን ሆኖ ሳለ ሴት ደፋሪና ወራሪ በሚል ሰንካላ ዉንጀላ ታሪካዊ ማንነቱ ይጎድፍ ዘንድ ሲደረግ ጠቅላዩን ስለጠላን ብቻ ካሳ በዝብዝን ለመሆን መምረጥ በታሪክ ያስጠይቃል።ከወያኔ ዘመን በፊት በጌምድር የሚባለዉን የአማራ ሀገር የአማራ ልዩ ኃይል ለምን ሰፈረበት ብሎ የሚያቅራራን የዋሽንግተን ኑዛዜ ርዕዮትና 360 ሚዲያዎች ሲያንቆለጳጵሱት ለሚሰማ የአማራን ሕዝብ መደናገር በቀላሉ ይረዳል። አብይንም ይሁን ኦሮሙማን ከኢትዮጵያ ጋር እኩል አድርጎ በሀገር ላይ ሲሸበር መተባበር እንግሊዞችን ወደ መቅደላ ከመሩት እነ ካሳ በዝብዝ ጋር አንድ ያደርጋልና እናስብበት።
በመጨረሻም እዉነት ዐፄ ቴዎድሮስ ቢኖር ሰራዊቱን ከበጌምድር በአሜሪካ ትዕዛዝ ያስወጣል ብለዉ ያስባሉ? … ይህንን ዉሳኔ የሚያንቆለጳጵሱትን ሰዎች ምላስ አይቆርጥም? … መልሱን ለእራስዎ!

እኛ ግን ያለን አማራጭ የዐፄ ቴዎድሮስን አማራጭ መከተል እና ታሪክ መስራት ብቻ ነዉ። …. ያዉም ለነቀዘ ስንዴ!!

ኢትትዮጵያ ትቅደም
ዶ/ር መኮንን ብሩ።

 

6 Comments

 1. ዶክተር እናመሰግናለን የክተት ጥሪ ነው ለጊዜው ልዩነታችንን አቻችለን በአንድነት መቆም ያስፈልጋል ለጊዜው የማይመጥኑ ሹሞችም አርፈው ቢቀመጡ መልካም ነው ቴዎድሮስ ጸጋዬ ላልከው ከስብሀት ነጋ የባሰ ሸለምጥማጥ ጁንታ ነው ኢትዮጵያዊ መስሎን ከብዙ ሰው ጋር ተቀያይመን ነበር ስዩም መስፍን ከሞተ በሁዋላ አቅሉን ነስቶታል አንድ የህግ ተማሪ እንደዛ አይነት አስነዋሪ ቃል በየፕሮግራሙ ሲተፋ ማየት ያሳዝናል። አንዳንድ ኢትዮጵያንም እየጠራ የስድቡ ተሳታፊ ሲያደርጋቸውም ማየት ሌላው ስቅጣጭ ነገር ነው።

 2. በዝብዝ ካሳ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳኖች አልሰጥም ብሎ አንገቱን ተቀልቶ የአገራችንን ነጻነት ያስጠበቀ ቆራጥ መሪ ነበር። አብይ ግን ያንን መሬት አስረከበልህ። የተማርክ ትመስል ደግሞ ራስህን ዶ/ር ብለህ ትፈርማለህ። ሀፍረተቢስ! ዝቃጭ እንዳንተ አይነቶቹ ናቸዉ ኢትዮጵያን የሚያዋርዱት!

 3. It is sad to see “learned” people making emotional statement than rational one. Dr Mekonnen Biru wrote an emotional statement which he will regret when he reads it with calm and rational state of mind.

  Although We adore the Atse Tewdros for his great contribution to reunite Ethiopia from Zemene Mesafinet ( Era of princes), he made big mistake for keeping European prisoners in Mekdela Amba. Had he released them, Britain wouldn’t send General Napier and it’s army.

  Tewdros II fall out with all including the church and at last he committed suicide. The atrocities in his final year was comparable to mad person on power.

  When we learn and teach history, it should be not only the good part but also the bad part. Tewdros did great in attempting reuniting Ethiopia but he did bad in keeping it united by mistakes of falling out with all including unnecessary imprisonment of the Europeans.

  Dr Mekonnen Biru advising Colonel Abiy (PhD) to do the same is wrong. Abiy started his rule with good inspiring speech but his deed is the opposite. Abiy believed he is to reign as king ( he doesn’t deny this). Instead of peace, national reconciliation and dialogue, forgiveness, transitional government with all stake holders, he preferred to rule as mighty king as Napoleon. To advise Abiy to continue this madness is a mistake and unexpected from “learned” person.

  • ኢትዮጵያ እንደ ሰባራ ጥጃ ታማለች ፥፥ ምርጫው ለአሥር አመት ይራዘም፥፥ከዚያ በኋላ የተሻለ ነፃ ምርጫ ይደረጋል፥አቢይ ያኔ በፍላጎቱ ይለቃል፥፥እናቱ ሦስት አመት ትነግሣለህ ብላው ነበር፥ወደ ሰሜን የዘመትክ እንደሆን ለአሥር አመት ትገዛለህ ለዛ ነው ሰው የሚጨፈጭፈው የጠንቋይ ልጅን ጠንቋዮች ይከተሉታል፥አብረው ያልቃሉ፥፥
   መፍቻ፥ጠንቋዮች=የአማራ ልሙጣን(ልሂቃን)
   የፋሲል ግንብ ይፈርሳል ጎንደር ትጋያለች አሥመራ ትፈራርሳለች ኤርትራውያን እርሻ እንደገባች ውሻ ይሆናሉ(ወደ ደንቢያ ይጠረዛሉ)ኤርትራ ዳግማዊቷ ባቢሎን በቅርቡ ይጠብቁ)

 4. if any of you want go America and visa is cancelled, try to go to asmara . Eza hulum ale .ayzon

  leba hula America atenakra tiketilalech bilitsigna yiwedmal 3 amet 6 were buwela yitefal gonder fasil yiwedimal sudan tigebalech etiopia tifersalech

  Al Mariam, Dr Mekonnen Biru Yosef Yitna, Tolossa Ibsa , Mekononnen kebede , zehbesha henok be hig yiteyekulin

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.