አቶ አገኘሁ ተሻገር አምርረዉ ተቆጡ – ሰመረ አለሙ

ሰመረ አለሙ [email protected]

agegnehu

ምናልባት ለማታዉቋቸዉ እኝህ በምስሉ የሚታዩት በኢህአደግ መልካም ፈቃድ አማራን እንዲገዙ ስልጣን የተሰጣቸዉ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር ናቸዉ። ይህን ያህል ካስተዋወቅናቸሁ በሗላ

ባለፈዉ አማራ ክልል ተብሎ ትግሬዎች  በካለሉት ቦታ ምድር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ተካሂዶ ስርአት በጠበቀ መልኩ እህል ሳይቀነጠስ ቅጠል ሳይበጠስ ህዝቡ ከሊህቅ እስከ ደቂቅ መንገዱን ሞልቶ ጭንቀቱን፤ስጋቱን፤ፍርሀቱን ለገዢዎቹ  አሰምቶ በሰላም  ወደመጣበት ተመልሷል። በዚህ ሰልፍ ህዝቡ  የወደፊት ተስፋችን ጨልሟል  ለ30 አመት የቀጠለዉና ማለቂያ ያልተገኘለት የኢትዮጵያና የአማራ ጠላት የፈጠረዉ ብአዴን የሚሉት ንጉሳዊ ስርአት በየጊዜዉ በአማራ ጠላቶች እየተጫነ  የጠላት መጠቀሚያ በመሆን እኛን ከመከላከል ይልቅ አስገድሎናል፤ የራሳችንን አጽመ ርስት ለባእዳንና ለሌሎች አሳልፎ አሰጥቷል፤ ታሪካችንን አንቋሿል፤ አዋርዶናል፤ ሰድቦናል፤በሌላ ክልል ለሚኖሩት ወገኖቻችን ዋስትና መስጠት አልቻለም  በማለት የማሳሰቢያ ደወል አሰምቶ ስርአት በጠበቀ መልኩ ወደመጣበት በሰላም ተመልሷል።

ታዲያ ለዚህ ማስተዋል ለተሞላበት ህዝብ እነ አቶ አገኘሁ ተሻገር  ምስጋና ከማቅረብ ይልቅ  ሰልፈኛዉ አምስትና አስር የማይበልጥ  ይመስል ተነቅሎ ወጥቶ ወግዱልኝ ብሎ የጠየቀዉን አማራ በማይመጥን መልኩ አንዴም በመገሰጽ አንዴም በማስፈራራት አንዴም ቆይ ጠብቁ በማለት ጥርሳቸዉን አግጥጠዉ አይናቸዉን አቅልተዉ ጌቶቻቸዉን ለማስደሰት የጥፋት በትራቸዉን ለመሰንዘር ቀን ቆርጠዉ እርምጃም ጀምረዋል።

የፈሲታ ተቆጢታ እንዲሉ 30 አመት የአማራን ህዝብ ሲያሳርዱ ሲያዋርዱ ትግሬዎች በሰጧቸዉ ቀጭን ትእዛዝ እየተመሩ ከተሰጣቸዉ መመሪያ አልፈዉ አማራዉን የምድር ሲኦል ያደረጉ፤ የአማራዉን ክልል ሸንሺነዉና አስሸንሺነዉ ኦሮሚያና ትግሬ ለሚባለዉ ክልል የሰጡ፤ አማራዉን መድረሻ ያሳጡ ብአዴኖች  ዛሬ ላይ በነሱ ብሶ ተደፈርን ብለዉ ከነታየ ደንዳና ሺመልስ አብዲሳ ጋር በመናበብ አማራዉን መከራ ከማብላት አልፈዉ ሲቆጡ ማየት በእጅጉ ያስገርማል። እንደ እዉነቱ ከሆነ በአማራ ክልል ካርድ ወስዶ የሚመርጠዉ ህዝብ በሰልፉ ካየነዉ የበለጠ ሊሆን አይችልም በእለቱ የተመለክተነዉ አማራም  በዛን ቀን ድምጹን ሰጥቷል። እነ አቶ አገኘሁንና የበድን አባላትም ይህንን እንደ በቂ የምርጫ ዉጤት በመቀበል በስልጣናቸዉ ዘመን በቀጥታም ሆነ በተደባይነት ባደረሱት በደልና ወንጀል አንድም በፈቃደኝነት ወደ እስር ቤት መሄድ፤ አንድም ቪዛ አዘጋጅቶ መዉጫቸዉን እንደመጠበቅ ያን ያህል ድንፋታ በህዝቡ ላያ ማዝነብ ባልተገባ ነበር። እነዚህ ቡድኖች  የሚያስተዳድሩትን ህዝብ ዘወትር በጠላትነት እየፈረጁ ሊኖሩ አይችሉም  ደቀ መዝሙሩ እንደ መምህሩ እንዲሉ እነሱም የሚገዙትን ህዝብ እንደ መለስ ዜናዊ  እንዳዋረዱ ይኖራሉ።

አብዲ ኢሌ ባቅሙ እነ አባዱላ የዘረፉትን መሬት ለሱማሌ ያስመለሰ የሱማሌ ባለዉለታ ነበር አባዱላም ዛሬላይ የዘረፈዉን ገንዘብ እንዲያጥብና በየመንግስት ስልጣን ከዚህ በፊት ያደረገዉ በደል ሳይታይ የተቀመጠዉ እነ ጁዋርን እነ ለማን እነ አብይ መሀመድን ታየ ደንዳን ሺመልስ አብዲሳን የመሳሰሉ ቄሮዎች  ህወአት ጉያ ዉስጥ ሁኖ በመፈልፈሉ ነበር።

የብአዴን ምስለኔዎች ግን ጌቶቻቸዉን ሲያገለግሉ ቆይተዉ የፊተኞቹ ጌቶቻቸዉ ሲሄዱ ለአዲሱ አስረክበዋቸዉ የሄዱ ለአማራዉ መከራ አንጂ መፍትሄ  ያላመጡ ምቾታቸዉን ብቻ የሚወዱ ለህዝብ ክብር ያልታደሉ ምስለኔዎች ለመሆናቸዉ ማስረጃ ፍለጋ መድከም አያስፈልም እነሱም ለአማራዉ ማህበረሰብ ይህን ሰራን ብለዉ የሚናገሩት የላቸዉም። የኦሮሞ ድርጅቶች ኦነግ፤ኦሆዴድ፤ሸኔ…. አብረዉ ሲሰሩ ብአዴን የአማራዉን ድርጅትና ለአማራ የተቆረቆሩ አክቲቪስቶችን እያሳደደ ሙልጭ አድርጎ የበላ ዛሬም ሊረዳቸዉ የሚገባዉን የአብን ድርጅቶችን ለማፈን ሴራ በመጎንጎን የሚገኝ ለአማራዉ መከራ ትግሬዎች ያዋቀሩትና ሊወገድ የሚገባ ድርጅት ነዉ።።

ሺመልስ አብዲሳ ያንን ሁሉ በደል አማራዉ ላይ ከፈጸመ በሗላ  እነ ተሻገር ጠርተዉ  ካባ ሲያለብሱት  በጀመርከዉ ቀጥል አማራዉን ጨፍጭፍ ደግ አደረግክ ማለታቸዉ ነበር ይህ ብአዴን የተባለዉ ሌላዉ ቀርቶ ለማኩረፍ እንኳን አቅሙ የሌለዉ ከመሆኑ ባሻገር በዚህ አሳፋሪ ስራዉም  በታሪክ ሲታወስ ይኖራል። እነ በረከት ሰምኦን፤ ታደስ ጥንቅሹ፤ ተፈራ ዋሉዋ ፤  ሞንጆሪኖ፤ ታምራት ላይኔ የበላይ ጠባቂዎቹ የሆነዉ ብአዴን እንኳን ለመሳደብና  ለመፎከር ቀርቶ  ቀና ብሎ መሄድ ባልቻለ ነበር። ታዲያ  እነ ነዉር ጌጡ  በክልላቸዉ ዉስጥ ሙልጭ አድርገዉ አጣየን ያጠፉት ኦነጎችን ልቀቁ ሲባሉ እንኳንስ ለመደራደር እስከ መሳሪያቸዉ ተርበድብደዉ የለቀቁ መሆናቸዉን መርሳታቸዉ ነዉ። ታየ ደንዳ በጥፊ ቢመታቸዉም ግምገማ ለምነዉ ከመቀመጥ ሌላ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር የላቸዉም።ቁሳዊ ፍላጎታቸዉ እስከተሟላ ክብር ምናቸዉም ባለመሆኑ ዛሬም ጌቶቻቸዉን ለማስደሰት የማይሄዱበት እርቀት የለም።

አባዱላም ሆነ አብይ መሀመድ ሌሎችም የኦሮሞ ባለስልጣኖች  ጃል መሮ የት እንዳለ ያዉቃሉ እጃቸዉን ግን አላነሱበትም ። እነ አገኘሁ ተሻገር ግን አሳምነዉን ጓደኛቸዉን ነብሱን ከማትረፍ ይልቅ  አባሪ ተባባሪ ሁነዉ አስበልተዋል። ዛሬ አሳምነዉ ቢኖር ለአማራዉ መከታ ሁኖ  ብአዴኖችን  ነጻ ከማዉጣት ባሻገር የሰሜኑ ዘመቻ ተጠናቆ ሱዳንም አደብ ገዝታ አይናችን ካይሮና አስዋን ላይ ባነጣጠረ ነበር። አሳምነዉ ምንም ሳይጎድለዉ ለሀገሩና ለወገኑ ሞተ ነገር ግን ሳይዉል ሳያድር ክብሩ ከመቃብር ፈንቅሎ የአማራዉ ነገድ ልብ ዉስጥ ቀረ ተከታታይ ትዉልድም እየተቀባበለ ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ስሙን ያነሳዋል ለእንዲህ አይነት ክብር የታደሉ ጥቂቶች ናቸዉ።

ብአዴኖች ወይ የተማረካችሁ ወይ በህወአት ስልጠና የተሰጣችሁ ወይ ወዶ ገባዎች  ናችሁ  ዲስኩር ስትጀምሩ  ትግል ላይ በነበርንበት ጊዜ እያላችሁ ስትመጻደቁ ምን ያህል በአሳፋሪ ስራችሁ ተመፃዳቂ ከመሆናችሁም በላይ ነገርን  ለማመዛዘንና ለማገናዘብ የአስተሳሰብ ብቃታችሁን ጥያቄ ላይ ይጥላል ። የብልጽግናና የኢዜማ ፖስት ካርድ ተቀደደ ብሎ ማለት ምን ማለት ነዉ? እነዚህ ፖስተሮች  አማራዉ ክልል ካልተቀደዱ የት ይቀደዱ?። ስለ ኢዜማ ምንንትና የአማራዉን ጥላቻ ለመረዳት የብርሀኑ ነጋን ዲስኩር ወደሗላ ተመልሶ ስለ አማራዉ የተናገረዉን መመልከት ነዉ። የኢዜማ የጀርባ ሰዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በየጊዜዉ የሚናገረዉንና የሚጽፈዉንም ማየት ኢዜማ አማራ ላይ ያለዉን ጥላቻ ለመገንዘብ ከበቂ በላይ መረጃዎች ናቸዉ።ብርሀኑ ነጋ ባለዉለታዉ የሆነዉ ኦሮሚያ ክልል እንጅ አማራዉ ክልል ምን ይስራል?

አቶ አገኘሁና ካቢኔዎ በኦሮምያ ክልል ተመሳሳይ ሰልፍ ተደርጎ ነበር በሰልፉ ላይ እነ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተዘቅዝቀዉ ሲሰቀሉ ኦርቶዶክስና ኢትዮጵያ ክብር የሰጠቻቸዉ መሪዎች ሲብጠለጠሉ ፖስተሮች ሲቀደዱ ነበር ሺመልስ አብዲሳም ሆነ ታየ ደንዳ በርቱ እንጂ ተግሳጽ አላሳረፉባችሁም የናንተዉ ቁጣና ተግሳጽ ምን የሚሉት ነዉ የናንተ ጠላት የአማራዉ ጠላቶች ሳይሆኑ ህዝብ ሊደግፈዉ ይችላል ብላችሁ የምትፈሩት አብን ነዉ።

ይህ ህዝብ ብአዴንን/ብልጽግናን የሚመርጥበትን አንድ ምክንያት የሚያቀርብ የብአዴን ባለስልጣን ይገኛል? ወልቃይትና ጠገዴ ራያን ለህወአት ቀሪዉን ለኦሮሚያ አስረከባችሁ የሱዳንን አዋሳኝ የአማራን ግዛቶች በጌቶቻችሁ ትእዛዝ  ዉሰዱልኝ ብላችሁ መማጸናችሁ ወይስ አማራዉ መሪ አጥቶ ትግሬዎችን አስተዳድሩን ብላችሁ መጠየቃችሁ ነዉ እንዲህ ልባችሁን በእብሪት የሸፈነዉ?  አቶ ተሻገር የምትመሩትን ህዝብ ለሀጫም ብላችሁ ሰድባችሁ እስከዛሬ በዛ ቦታ መቀመጣችሁ የተከለለዉ ክልል ትግራይ ወይ ኦሮሞ ሊሆን ይችላል እንጅ የአማራ ክልል ነዉ ብለን አንገምትም። አስቲ ለቁሳዊ ኑሮ ከመኖር ትንሺ ጊዜያችሁንም ለታሪኩ አስተርፉለት።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

4 Comments

  1. if any of you want go America and visa is cancelled, try to go to asmara . Eza hulum ale .ayzon

    leba hula America atenakra tiketilalech bilitsigna yiwedmal 3 amet 6 were buwela yitefal gonder fasil yiwedimal sudan tigebalech etiopia tifersalech

    Al Mariam, Yosef Yitna, Tolossa Ibsa , Mekononnen kebede , zehbesha henok be hig yiteyekulin

    • አይ ሽንቁጤ ሰውን በሳቅ ፈጀኸው አራጆች አጎቶችህ ለፍርድ ሳይቀርቡ እነ ሄኖክና አልማርያም ሌባና ነብሰ ገዳይ ትግሬ ለፍርድ ይቅረቡ ብለው በመጠየቃቸው ታብዳለህ? ሲሆን በፈቃደኝነት ምስክር መሆን በተገባህ ነበር ብዙ ወንጀል ላይ በመሳተፍህ።

  2. Well, it is an open secret that this guy was and is nothing but the very disgraceful and idiotic cadre of the very deadly political circle of TPLF and now ODP or Oromuma which has made the situation much more horrifying ! What is extremely outrageous is the way the so called opposition groups and of course so called intellectuals behave or act toward this very deadly political cancer . It is deeply painful to watch these people decrying and crying but not doing any significant political work ! It is so terrible to watch them just talking the talk not walking the walk !
    Believe or not, Agegnehu , Demeke , Gedu and do on will never have any sense of doing the right political work because they have already spoilt themselves in incurable manner !

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.