አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ(ም) አነጋጋሪ ሆነ አሉ – አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

andargachew

የዚህች ሀገር ፖለቲካ ከማርጀት አልፎ እየጃጀ መምጣቱን የምንረዳው በየቀኑ ሊባል በሚችል ሁኔታ በጣም አስቂኝና አነጋጋሪ የሆኑ ክስተቶችን በመታዘባችን ነው፡፡ ፖለቲካን ከከተማ እስከጫካ ከልጅነት እስከሽምግልና ሲያራውጠው የነበረው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በዕረፍት ከሚገኝበት ሥፍራ ሆኖ ሰሞኑን በአሜሪካ ላይ በወሰደው አደገኛ ስጉምቲ ማለትም እርምጃ አሜሪካ እየተንቀጠቀጠችና ዲያስፖራውም ሰውዬውን በማግባባት አደገኛ እርምጃውን ቀለል እንዲያደርግ በማባበል ላይ እንደሚገኝ በኢትዮ360 አንድ ዝግጅት ዛሬ ምሽት ሰማሁ፡፡ ጀግና ማለት እንዲህ ነው! አሜሪካን በዓለም ላይ እንደልቧ የምትፈነጨው እንደ አቶ አንዳርግ ያለ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢንተርናሲዮናል ወደር የለሽ ጀግና በመጥፋቱ ነው፡፡ ይህን አንግሎ-ኢትዮጵያዊ ወይም ኢትዮ-እንግሊዛዊ ቼኩቬራና ሆቺሚን በዚህ ወቅት ማግኘት ለግንቦት ሰባትም፣ለኢዜማም፣ለብልጥግናም ….እ … ለአርበኞች ግንቦት ሰባትም፣ ለኦነግም፣ ለኦህዲድ ሸኔም፣ ለብአዴንም ትልቅ የምሥራች ነው – ምሥር ያብላንና፡፡ ግን ግን እውነቱን ለመናገር ካበዱ አይቀር እንዲህ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ገና ከዚህ የባሰ ለጥገና የሚያስቸግር የአእምሮ ብልሽትም ያሳየናል፡፡ “ካላበዱ ወይ ካልነገዱ (የልብ አይገኝም)” መባሉም እኮ ለዚህ ነው፡፡

አሞራና ጭልፊት መጥተው ጫጩቶቹን ሲልፏቸው በአጥር ሥር ተወትፎ ካሳለፈ በኋላ በሚስቱ በእመት እናት ዶሮ ፊት አንድ አውራ ዶሮ እንዲህ ብሎ ፎከረ አሉ – እንደመፎገ(ከ)ር የሚቀል የለምና፡፡

አምጪማ አምጪማ ጦሬን፤ ወንዙን ሳይሻገር እንድዠልጠው ወገቡን! ዘራፍ! ዘራፍ አካኪ ዘራፍ!

እመት እናት ዶሮም መለሰች፡-

አንቱም አንቱም አይዋሹ፤ አሁን ተመልሶ ቢመጣ አጥር ላጥር ሊሸሹ፡፡

የዛሬ ስንት ዓመት ገደማ ደግሞ (በ1978ዓ.ም ይመስለኛል) አሜሪካ ሊቢያን አጥቅታ ጋዳፊ ለጥቂት ከሞት ተረፈ፤ አንዲት ሴት ልጁ ግን በአየር ጥቃቱ ሞተችበት፡፡ ያኔ ታዲያ ኢትዮጵያም ፀረ አሜሪካ ስለነበረች (ወግ አይቀርምና ሲዳሩ ማልቀስ) ሚዲያዎቿ ሁሉ በአሜሪካ ላይ ተቃውሞ አዘነቡ፡፡

በዚያን ወቅት ከሰማሁት ዜና መቼም የማይረሳኝ የሚከተለው ነው፡-

“የአጋርፋ ገበሬዎች ማኅበር የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምን አስጠነቀቀ!”

የሚገርም ማስጠንቀቂያ ነበር፡፡ እርግጠኛ ነኝ – የአሜሪካ ጦር ያኔ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠንቀቅ ተሰልፎ የአጋርፋ ገበሬዎችን ወረራ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ግና እግዜር ሰወራቸውና አሜሪካኖች ተረፉ፡፡

ቀልድ ጥሩ ነው፡፡ ያለ ቀልድ ሕይወት ጎምዛዛ ናት፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ግሥላ ሆኖ አሁን “አንድነቷ ተጠብቆ” ስለሚገኘው ሀገሩ ምን ነበር ያለው?

“እኔ ክንዴን ሳልንተራስ አሜሪካ ኢትዮጵያን አታፈርስም፡፡ ባንዲራቸውን ዐይናቸው እያዬ አቃጥላለሁ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘሁትም ከዚያ በላይ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፡፡” ፐ! ፐ! ፐ! አይ ወኔ!! ወላድ በድባብ ትሂድ፡፡ እንኳን የኔው ሆነ አንዱካ! የኛ ባይሆን እንዴት በቆጨኝ፡፡

በል አንተ ደግሞ “ስልብ አሽከር በጌታው እንትን ይፎክራል” በልና ሳንወድ በግድ አስቀን፡፡

ጥቂት ጥያቄዎች አሉኝ፡፡ አንደኛ ነገር ባንዲራው ምን አጠፋ? ሁለተኛ ነገር ባንዲራን ማቃጠል የሥልጡን ፖለቲካ አካል ነው ወይ? ሦስተኛ ነገር ዋናው አገር አፍራሽ መሀል አራት ኪሎ ተቀምጦ የማይመስል ነገር ውስጥ መግባት የምጣዱን ትቶ የዕንቅቡን እንደማማሰል አይቆጠርምን? አራተኛ የሰው ሀገር ባንዲራ ማቃጠል አማራን በነፃነት ትግል ስም ወደ ኤርትራ በረሃ ወስዶ በአውሬና በአማራ-ጠል ፖለቲከኞች ሤራ እንደማስጨረስ ቀላል ነው ወይ? አምስተኛ በሀገራቸው መኖር ያልቻሉ የዘር ፖለቲካ ሰለባዎችንና የኢኮኖሚ ስደተኞችን በክፉ ቀን ያስጠጋችን ሀገር በዚህ መልክ ወሮታውን መክፈል ነውር ከመሆኑም ባሻገር በህጉ መሠረትና ከህግ ውጪም ለሚደርስ ቅጣትና የበቀል በትር ተጠያቂው ማን ሊሆን ነው?

የምን አትርሱኝ ነው? በቃ፤ ዒላማ ተስቶ ዓላማ ሲጨናገፍ አርፎ መቀመጥም እኮ ያባት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን ሁሉም ነገር ገብቶታል – በጎንደርኛና በኃይሌ ገ/ሥላሤኛ ልንገር፡፡ የዓዞ ዕንባን ከእውነተኛ ዕንባ የመለየት ችሎታውም በእጅጉ አድጓልኝ፡፡ ይህን ጥሬ ሃቅ አንዴክስ አልሰምቶ ከሆነ ችግሩ ከሌላ ሳይሆን ከራሱ ነው፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያ ስም ለትዝብት ከሚዳርግ ንግግርና የማስመሰል ሞቅታ መቆጠብ ይገባል፡፡ እንዳማሩ መሞት በዚህ ዘመን ሲያምር የሚቀር ቢሆንም አንዳንዴ አካባቢያዊና ሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ማጤን በቀላሉ ሊያስወግዱት ከሚቻል ሕዝባዊ ትዝብት ይታደጋልና ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥን መቀነስ ደግ ነው እላለሁ፡፡ እውነታን ማሽሞንሞን ለማንም አይጠቅምም፡፡ አንዳርጋቸውና በብዙ ውጣ ውረዶች አልፎ ኢዜማ ላይ የደረሰው የፖለቲካ ስብስብ ፈተናውን ዘጭ ብሎ ወድቋል፡፡ “ማንነትህን እንድነግርህ ጓደኛህን ንገረኝ” የሚባለው ምሣሌያዊ አባባል ትልቅ መልእክት አለው፡፡ ሽንት ቤት ውስጥ የተቀመጠ ሰው የፈረንሣይ ሽቱ ቢቀባ ወይም የናርዶስ ሽቱ ሰውነቱ ላይ ቢያርከፈክፍ እውነተኛ መዓዛውን ለመለወጥ ይቸገራል፡፡ ከአሁን በኋላ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በማስመሰልና በጠላትህ ጠላቴ ነው የሲብስቴ ፈሊጥ የሚመራ አይሆንም፡፡ ይህን ሁሉ ስል ግን የአንዱን የቀደመ አስተዋፅዖ የማላወድስና የሰሞኑን ተቃውሞ መነሻ ምክንያት የማልቀበል ሆኜ አይደለም፡፡ ሰውዬው ለሀገሩ ብዙ ለፍቷል – በተሳሳተ አቅጣጫ ቢሆንምና ትግሉ በአሰለጦች ቢጠለፍም፡፡ “ኢትዮጵያን አትንኩ” ብሎ መጮህም ያስመሰግናል እንጂ አያስወቅስም – የአጯጯሁን መንገድ አለመለየት ለትዝብት ከመዳረጉ በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወዝና ጣም ከሌለው ትያትራዊ የብልጽግናዎች ቀልድ ወይም ኮሜዲ እንታቀብ – The moral of the story. አሃ፣ ያን ያል ትልቅ ስብዕና ያው ሰው እንደዚህና እስከዚህ መውረድ የለበትማ! “ሳይበላስ ቢቀር” አለ ቴዲ አፍሮ፡፡ “እኔ ቆሜ ዐቢይ ማነው አሜሪካ ኢትዮጵያን አታፈርስም!” ይባላል? ዋናው አፍራሽ ማን ሆነና? ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ፡፡ በልጅነቴ እንግሊዝኛን እያጣመምኩና የአማርኛ ፈሊጦችን በቀጥታ ወደ እንግሊዝኛ እየመለስኩ ጓደኞቼን አዝናና ነበር – አንደኛዋ ፈሊጥ አሁን ትዝ አለችኝ – “tell me sayer!” – ከገባችህ ወንድ ነህ! ሆድህን አሞህ ውሎ አሞህ ይደር እንጂ አልነግርህ፡፡ “ንገሩኝ ባይ”፡፡

 

8 Comments

 1. አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እራሱን እንደየዳያስፖራዎች መሪ አድርጎ ከቆጠረ በጣም ብዙ አመታት ተቆጥረዋል። የግንቦት ሰባት መልማይ ሆኖ ፤ የመን ሄዶ በየአመቱ ከኢትዮጵያ ወደ የመን እየተሰደዱ የሚሄዱትን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያኖችን ባገኘበት አነጋግሮ በወቅቱ የሀገሪቱ መሪ የነበሩትን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን እና ህወሀትን/ኢህአዴግን ከሥልጣን ለማስወገድ የትጥቅ ትግል እያደረገ የነበረውን የግንቦት ሰባትን ጦር የመን ያሉት ኢትዮጵያውያኖች እንዲቀላቀሉ እያነሳሳ ፤ በየመን ያሉትን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሜሪካ ማዕቀብ ወደጣለችባት ኤርትራ ሄደው ግንቦት ሰባት አርበኞችን ኦነግን ተቀላቅለው ጦርነት እንዲለማምዱ ሲመለምል በነበረበት ወቅት በመለስ ዜናዊ እና በአሜሪካ ትዕዛዝ የየመን መንግስት አንዳርጋቸውን አስሮ ለመለስ ዜናዊ እስር ሲያበቁት ዳያስፖራዎች መሪያችን አንዳርጋቸው ስለታሰረብን ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለን በትጥቅ ትግል አንዳርጋቸውን እናስፈታለን ብለው ግንቦት ሰባትን ይቀላቀላሉ ተብሎ ኤርትራ ውስጥ በነበሩት ሰልጣኞች እንደተጠበቀ እና ዳያስፖራዎች ግን እንኳን ዘምተው ሊያድኑት ሰልፍ ወጥተው ለእርሱ ሲጮሁ እንደአልተገኙ አይዘነጋም። በእዚህም የተነሳ አንዳርጋቸው ፅጌ ለብዙ ችግር ተዳርግዋል። ብዙ ሚስጥር ለወያኔም ሽጥዋል። ከተማ ለከተማ በመኪና እየተዘዋወረም ሲጎበኝ አንዳርጋቸው ሌላው እስረኛ ግድግዳ ያስገፉት ነበር ህወሀቶች። አንዳርጋቸው ፅጌ በአዳማ ከተማ ከአባዱላ እና ሙክታር ከድር ጋር እየተዝናና ሶዶሬ ሆቴል አከባቢ የነበሩትን ሰፋፊ የሽንኩርት ልማት ፕሮጀክቶችን ኦሮሙማን ከደገፈ በሙሉ የሽንኩርት ልማት እርሻዎችን ከኢንቬስተሮቹ ቀምተው ለእርሱ እንደሚሰጡት ቃል ሲገቡለት ያልዘከዘከው ሚስጥር አልነበረም። እስከአሁንም ሶዶሬ ሆቴል አከባቢ የሰፋፊ እርሻ ባለቤት የመሆን ተስፋውን ስላልቆረጠ ለኦሮሙማ እያጎበደደ : በአንዳርጋቸው ፅጌ አባባል “ታስሬ በነበረበት ወቅት የካዱኝ ዳያስፖራዎችን በተራዬ እኔም ዳያስፖራዎችን እንደመሰላል ተጠቅምብያቸው ፤ ሚሊየኖች ብሮችን ለኢሳት ለሚዲያ ማደረጃ ከኦሮሙማ መንግስት እየተሰጠኝ ፤ በመቀጥልም የሶደሬ አከባቢን ተቆጣጥሬ ቤተሰቦቼን ለሽንኩርት ጌትነት አበቃቸዋለሁ ” ብሎ ተነስትዋል።

  ኢትዮጵያውያን ፤ ይኸው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ እስር ቤት እያለ ብዙ የመሰሪነት ትምህርት ቀስሞዋል።

 2. Watching this guy totally lost in the very woods of deadly cancerous political game of the so called Prosperity is really sad ! He tragically sold himself to those politicians whos hands are badly stained with the very blood of innocent citizens for a quarter of a century under the supremacy of TPLF . He unfortunately became one of the most notorious opportunists in the past three years. The more he became the good or loyal servant of the two most arrogant and narcissist friends , Abyi of Ethiopia and Isaias of Eritrea, the more he badly damaged the very essence of his own common sense . Now, he totally lost in the woods of a very deadly politics of Oromuma/Prosperity .
  i wonder why and how he does not care about his own family particularly about his children who witnessed how genuinely concerned Ethiopians were with them when he was languishing in the hands of TPLF /EPRDF security people of which the current so called change agents were parts and parcels of it . I wonder what his answer could be if they ( his children) would ask him why he changed himself to a very self-damaging political personality .

  I read and heard some fellow men and women saying that with all the very terrible things he is doing, they still give due credit to what he did before . Yes, he did good things . But it must be clear that he is invalidating his own past credits by doing the most horrible things that are deeply painful to the people who have paid a lot of sacrifices hoping that things could change for the better . He became one of the leading and dangerous political personalities in this very critical moment .
  By the way, I was one of his admirers . I know individuals as human beings can change their behavior any time and for any reason and he is not exceptional in this general context. What this guy keeps doing is really painful to the people of Ethiopia who honestly hoped that he could be a good asset to their struggle for the realization of rue democracy , not to be a very bad agent of bad guys who control the deadly ethno-centric political system in a much more horrifying manner.

 3. አምባቸዉ በግንዛቤህ ምልከታህን አጋርተኸናል እናመሰግናለን አንዳርጋቸዉ ስንል ብርሀኑና ኤፍሬም ማዴቦን ይጨምራል። በዉነቱ ባስበዉ ባስበዉ የነዚህን ሰዎች አስተዋጽኦ መገንዘብ አልቻልኩም ብልጣ ብልጦች ጥቅም ከየት እንደሚገኝ ቀድመዉ መገንዘብ የሚችሉ ተራዉን ህዝብ ምን እንደሚያሰስጨፍረዉ ቀድመዉ የሚገነዘቡና የነሱን ቋንቋ ጠንቅቀዉ መናገር የሚችሉ በሀሳብና ባስተሳሰብ የተጎዱ ሁነዉ ነዉ ያገኘሗቸዉ።

  አምባቸዉ በግንዛቤህ ምልከታህን አጋርተኸናል እናመሰግናለን አንዳርጋቸዉ ስንል ብርሀኑና ኤፍሬም ማዴቦን ይጨምራል። በዉነቱ ባስበዉ ባስበዉ የነዚህን ሰዎች አስተዋጽኦ መገንዘብ አልቻልኩም ብልጣ ብልጦች ጥቅም ከየት እንደሚገኝ ቀድመዉ መገንዘብ የሚችሉ ተራዉን ህዝብ ምን እንደሚያሰስጨፍረዉ ቀድመዉ የሚገነዘቡና የነሱን ቋንቋ ጠንቅቀዉ መናገር የሚችሉ በሀሳብና ባስተሳሰብ የተጎዱ ሁነዉ ነዉ ያገኘሗቸዉ። የኛ ህዝብ ግንዛቤዉ አጠር ያለ ነዉ የሚባለዉ እዉነትነትን አያጣም ትህነግ የኢትዮጵያን መከላከያ በተኛበት ያረደዉ ተረስቶ ዛሬ ዜጋ የሚጮኸዉ አቦይ ስብሀት የተመጣጠነ ምግብ አልገባላቸዉም እያለ ነዉ።
  ጎበዝ ትህነግን ተምበርክኮ ያገለገለዉ በአዲስ አበባነቱ መልክ መልክ አስይዞ ይቅናችሁ ብሎ የተሰናበተ ሰዉ እኮ ነዉ ቋንቋዉ ሁሉ መርዘኛ ለሀገር አንድነት የማይጠቅም አለፍ ሲል ደግሞ እዉነትነት የሌለዉ ነዉ መከረኛዉ አጼ ምንሊክ ቡኒ ከተባለዉ አያቱ 20,000 ከብት ዘረፉ ብሎ መጽሀፍ የጻፈ ሀገር በቀል ተስፋዬ ገ/አብ እኮ ነዉ ሂሳቡ ሲሰላ ቡኒ በነበረበት ዘመን የአጼ ምንሊክ አያት አልተወለዱም ከዚህ በላይ አማራን ጥላቻ አለ? ስለ አንዳርጋቸዉ በድፍረት እኮ አልተነገረም የግምቦት 7 ጄነራል ሁኖ አዲስ አበባ ልንገባ ሳምንት ነዉ የቀረን ሲለን የነበረ ኮሜዲያን እኮ ነዉ።
  ተናግራችሁ አታናግሩን። የብርሀኑ እንኳ እራሱን እራሱ እየጠለፈ ስለሚጥል የሱን ግድፈት ከራሱ ታገኙታላችሁ የሚያሳዝነዉ በየተ በኩል ሾልኮ ገብቶ በትግሬ ሲሰቃዩ የነበሩትን ገልብጦ ከላያቸዉ መቀመጡ ነዉ :: የጠለፋ ስራቸዉን ስለተካኑበት የህ ለነሱ አስቸጋሪ አይደለም የሚቀጥለዉ ኢላማቸዉ ዶ/ር አብይን መገልበጥ ነዉ ካወቀ ይወቅበት። በተረፈ አማራ ክልል የብርሀኑ ፓርቲ የሚመጣበት ምንም ምክንያት ስለሌለዉ የአማራ ወጣት ተዘጋጅቶ መጠበቅ ይኖርበታል የብርሀኑ ፓርቲ እዛ አካባቢ ዝር እንዲል ከተፈቀደለት እነ ህወአትም እንዲወዳደሩ ሊፈቀድ ይገባል ስልጣን ሳይዝ አማራዉ ላይ እልቂት ከለፈፈ ስልጣን ሲይዝ ምን ሊሆን እንደሚችል አማራዉ ሊገነዘብ ይገባዋል።

 4. አምባቸዉ በግንዛቤህ ምልከታህን አጋርተኸናል እናመሰግናለን አንዳርጋቸዉ ስንል ብርሀኑና ኤፍሬም ማዴቦን ይጨምራል። በዉነቱ ባስበዉ ባስበዉ የነዚህን ሰዎች አስተዋጽኦ መገንዘብ አልቻልኩም ብልጣ ብልጦች ጥቅም ከየት እንደሚገኝ ቀድመዉ መገንዘብ የሚችሉ ተራዉን ህዝብ ምን እንደሚያሰስጨፍረዉ ቀድመዉ የሚገነዘቡና የነሱን ቋንቋ ጠንቅቀዉ መናገር የሚችሉ በሀሳብና ባስተሳሰብ የተጎዱ ሁነዉ ነዉ ያገኘሗቸዉ። የኛ ህዝብ ግንዛቤዉ አጠር ያለ ነዉ የሚባለዉ እዉነትነትን አያጣም ትህነግ የኢትዮጵያን መከላከያ በተኛበት ያረደዉ ተረስቶ ዛሬ ዜጋ የሚጮኸዉ አቦይ ስብሀት የተመጣጠነ ምግብ አልገባላቸዉም እያለ ነዉ።
  ጎበዝ ትህነግን ተምበርክኮ ያገለገለዉ በአዲስ አበባነቱ መልክ መልክ አስይዞ ይቅናችሁ ብሎ የተሰናበተ ሰዉ እኮ ነዉ ቋንቋዉ ሁሉ መርዘኛ ለሀገር አንድነት የማይጠቅም አለፍ ሲል ደግሞ እዉነትነት የሌለዉ ነዉ መከረኛዉ አጼ ምንሊክ ቡኒ ከተባለዉ አያቱ 20,000 ከብት ዘረፉ ብሎ መጽሀፍ የጻፈ ሀገር በቀል ተስፋዬ ገ/አብ እኮ ነዉ ሂሳቡ ሲሰላ ቡኒ በነበረበት ዘመን የአጼ ምንሊክ አያት አልተወለዱም ከዚህ በላይ አማራን ጥላቻ አለ? ስለ አንዳርጋቸዉ በድፍረት እኮ አልተነገረም የግምቦት 7 ጄነራል ሁኖ አዲስ አበባ ልንገባ ሳምንት ነዉ የቀረን ሲለን የነበረ ኮሜዲያን እኮ ነዉ።
  ተናግራችሁ አታናግሩን። የብርሀኑ እንኳ እራሱን እራሱ እየጠለፈ ስለሚጥል የሱን ግድፈት ከራሱ ታገኙታላችሁ የሚያሳዝነዉ በየተ በኩል ሾልኮ ገብቶ በትግሬ ሲሰቃዩ የነበሩትን ገልብጦ ከላያቸዉ መቀመጡ ነዉ :: የጠለፋ ስራቸዉን ስለተካኑበት የህ ለነሱ አስቸጋሪ አይደለም የሚቀጥለዉ ኢላማቸዉ ዶ/ር አብይን መገልበጥ ነዉ ካወቀ ይወቅበት። በተረፈ አማራ ክልል የብርሀኑ ፓርቲ የሚመጣበት ምንም ምክንያት ስለሌለዉ የአማራ ወጣት ተዘጋጅቶ መጠበቅ ይኖርበታል የብርሀኑ ፓርቲ እዛ አካባቢ ዝር እንዲል ከተፈቀደለት እነ ህወአትም እንዲወዳደሩ ሊፈቀድ ይገባል ስልጣን ሳይዝ አማራዉ ላይ እልቂት ከለፈፈ ስልጣን ሲይዝ ምን ሊሆን እንደሚችል አማራዉ ሊገነዘብ ይገባዋል።

 5. ዐብይ በምን አማረኛ ቢናገር ልናዳምጥ ጆሮችንን ክፍት እንደምናረግ ራሳችንን እንጠይቅ፡፡አነዳርጋቸው አብይን ቢደግፍ የራሱ ነው አገር አትነካ ማለት የግሉ ነው፡፡አሁን ባለው የፖለቲካ አስተዳደር ማንም ተግባብቶ/ተስማምቶ የመንግስት መዋቅር መምራት አይችልም፡፡ሀገሪቱ ትፍረስ ካልተባለ በስተቀር።ስር የሰደደው የወያኔ የዘር ፖለቲካ በየደጃችን ተኮትኩቶና አድጎ ፍሬም አፍርቶ እሾኩና መርዙ እየወጋንና እየገደለን ባለበት ሁኔታ የሽግግር መንግስትና ሌላ ሌላም አንደማይሆን ማየት አለመቻል አነዴት እንደተሳነን ራሳችንን ቆም ብለን እንጠይቅ፡፡ችግሮች/ስህተቶች ይኖራሉ ሊታረሙ የሚችሉት ግን በአገራችን ጉዳይ/ህልውና ላይ መጀመሪያ አንድ መሆን አንዳለብን ከልብ ስንሰማማ ነው፡፡

 6. ዐብይ በምን አማረኛ ቢናገር ልናዳምጥ ጆሮችንን ክፍት እንደምናረግ ራሳችንን እንጠይቅ፡፡አነዳርጋቸው አብይን ቢደግፍ የራሱ ነው አገር አትነካ ማለት የግሉ ነው፡፡አሁን ባለው የፖለቲካ አስተዳደር ማንም ተግባብቶ/ተስማምቶ የመንግስት መዋቅር መምራት አይችልም፡፡ሀገሪቱ ትፍረስ ካልተባለ በስተቀር።ስር የሰደደው የወያኔ የዘር ፖለቲካ በየደጃችን ተኮትኩቶና አድጎ ፍሬም አፍርቶ እሾኩና መርዙ እየወጋንና እየገደለን ባለበት ሁኔታ የሽግግር መንግስትና ሌላ ሌላም አንደማይሆን ማየት አለመቻል አነዴት እንደተሳነን ራሳችንን ቆም ብለን እንጠይቅ፡፡ችግሮች/ስህተቶች ይኖራሉ ሊታረሙ የሚችሉት ግን በአገራችን ጉዳይ/ህልውና ላይ መጀመሪያ አንድ መሆን አንዳለብን ከልብ ስንሰማማ ነው፡

 7. The contribution of Andaregachew so far is negative. He is opportunist and power monger. As EPRP, he participated in red -white terror killing in the 1970’s. When TPLF assumed power, he was the first from diaspora to work with despite all opposition. When TPLF no longer offer him VIP post except mid level cadre, he runaway. He attempted to use the opportunity in 2005 election thinking CUD will hold power and he will get his share; but that failed and he runaway after few months of imprisonments in Ziway.

  He is ruthless cold character and suspicious nature. He would sell out any group or organisation if he doesn’t see self opportunism in it. TPLF hijacked him from Yemen, partly the Eritreans who read his character gave him away.

  He denied the Amhara people existence to please the new people on power, the Oromumma folks. He sold out his colleagues ( Arebegnoch tagays) and now working with Oromumma proponents. He is no longer Ethiopians ( he is British) so he better be away from Ethiopian poltics, either he has to abandon his British Citizenship otherwise no more game.

  His theatrical speech to safe Abiy regime from the Donors anger is amusing. He is still raw like when he was EPRP killing squad.

 8. Many people do not understand Andargachew Tsige. He lived in London for many decades, but has been uneducated and unemployed. Such people are highly vulnerable. He used to assist the London TPLF office. These kinds of people can easily be bought for money to serve as cadres, changing their words as they fit. He did under Meles. He is doing it now. I feel sorry for people who buy or sell his rubbish ‘books’. Shame. Shame. Shame.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.