ኢዜማን የምደግፍበት 7 ምክንያቶች – ሺፈራዉ አበበ

Habesha | zehabesha.info

 1. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ)፣ ከፖለቲካ በፊት አገርን እንደሚያስቀድም መረዳቴ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባብኛዉ የተቃዉሞ ፖለቲካ ነዉ። ፕ/ር መስፍን፣ ማፍረስ እንጂ መገንባት ላይ እምብዛም ነን እንዳሉት ነዉ። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርአት በህዝብ ተቃዉሞ ሲፈርስና ጉልበተኞች ለእነሱ እንደሚመቻቸዉ አድርገዉ ሲገነቡት፣ የቆየ ነዉ። ዛሬ ላይ ግን አገራችን ሌላ የማፍረስ-መገንባት ልምምድ ለማስተናገድ የምትችልበት ቁመና ላይ አትገኝም። በ27 ዓመታት የህወሃት አገዛዝ ወቅት አገሪቱ የተሸመነችበት ታሪካዊ፣ ባህላዊና፣ ቤተሳባዊ ድር ሲበጣጠስ ቆይቶ አንድነቷ በሰለሰሉ ክሮች እንደነገሩ ተያይዞ ያለበት ሁኔታ ላይ ነዉ ያለችዉ። ይህን ልብ ያሉ አገር በታኝ ሃይሎች ባለፉት ሶስት አመታት አጋጣሚዉን ለመጠቀም  ተረባርበዋል። የተከተሉት ስትራቴጂ ዘር-ተኮር ጥቃትን በመፈጸምና በማስፈጸም በተለይ በሁለቱ ትልልቅ ማህበረሰቦች መካከል ግጭት በማስነሳት አገራዊ ቀዉስ መፍጠር ነዉ። የዚህ ስትራቴጂ ዋና አካል፣ በዘር ተኮር ጥቃቶች ምክንያት የሚፈጠሩ ብሶቶችና ቁጣዎች በፌዴራል መንግስቱ ላይ እንዲያነጣጥሩ በማድረግ የአገሪቱን ማእከላዊ አመራር ማሽመድመድና አገሪቱን ለዉጭ ጥቃት ማጋለጥ ነዉ። የዚህ ስትራቴጂ ዋና ባለቤቶች በይፋ፣ በስም የሚታወቁ ቢሆንም፣ ባለማወቅ፣ በእልህና የቁጭት ስሜት ወይም ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲሉ በተግባር የእነሱን ስትራቴጂ የሚፈጽሙ በአፍ ግን ስለአገር አንድነት እንጨነቃለን የሚሉ ብዙ ናቸዉ።

ዛሬ አገራችን በምታልፍበት የፖለቲካ ቀዉስ ወቅት፣ ወገን ለይቶ ፍጥጫን ማጋጋል፣ የፌዴራል መንግስትን በኃፊነቱ ደረጃ ከመጠየቅ አልፎ እንደ ጠላት ማዬት፣ ጊዜያዊና ወገንተኛ የሆነ ሙገሳንና ተቀባይነትን ሊያስገኝ ይችል ይሆናል እንጂ አገርን አያረጋጋም፣ አንድነቷንም አያረጋግጥም። በቀዉስ ወቅት የሚያስፈልገዉ፣ ከስሜታዊነት እና ከፖለቲካ ጥቅመኛነት (opportunism) የዘለለ አቋምና አካሂያድ ነዉ። ከዚህ አንጻር፣ ባለፉት ሶስት አመታት ኢዜማ ለአገር በታኝ ሃይሎች እድል ላለመስጠት ሲል፣ የስም አጥፊዎችን አሉባልታ በመቋቋም ያሳየዉ ስክነትና ታጋሽነት የተሞላበት አመራር የድርጅቱን ጥንካሬ የሚያሳይ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። የተወሰነ ጊዜያዊ የፖለቲካ ዋጋ ሊያስከፍለዉ ቢችልም እንኳ፣ ውሎ አድሮ ትክክለኛዉ የአገር ወዳድነት አቋም የኢዜማ እንደሆነ ታሪክ ያረጋግጠዋል ብዬ አምናለሁ።

 1. ኢዜማ አገር አቀፍ የሆነ ፓርቲ መሆኑ

ኢዜማ ለሁሉም የአገሪቱ ክፍሎችና ማህበረሰቦች  እኩል ዋጋ የሚሰጥ፣ ይህንንም ከንድፈ ሃሳብ በዘለለ በተግባር ሊታይ በሚችል ሁኔታ ያረጋገጠ ፓርቲ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ከተመሰረተ ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አስቸጋሪ የሆነ የደህንነትና የዘር-ተኮር ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ 80 ፐርሰንት በሚጠጉ የአገሪቱ ወረዳዎች፣ የፓርቲ መዋቅር ለመዘርጋት መቻሉ እጅግ የሚያስደንቅ ከመሆን ባለፈ፣ ፓርቲው ለሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ያለዉን አክብሮትና እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ ውክልና እንዲኖራቸዉ ለማድረግ ያለዉን ቁርጠኝነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነዉ ብዬ አምናለሁ። ሰሞኑን የፓርቲዉ መሪ ከዋና መንገድ በርቀት የሚገኙ የደቡብ ወረዳዎችን ጨምሮ ያደረጋቸዉ ጉብኝቶችና ያስተላለፋቸዉን መልእክቶች ልብ ላለ ሰዉ፣ ኢዜማ ከምርጫ ቅስቀሳና ዉጤት ባሻገር የሚትኖር አገርን ለማያያዝና አንድነቷን ለማረጋገጥ  ያለዉን ቁርጠኝነት ይረዳል፣ ያደንቃልም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ – አእምሮዉ በአሉባልታና በጥላቻ የታጨቀ ሰዉ ካልሆነ በስተቀር።

ከብልጽግና ፓርቲ ዉጭ ያሉት በስም ሃገራዊ ፓርቲዎች አገራዊ የመሆን ፍላጎቱ ቢኖራቸዉም እንኳ፣ አብዛኛዎቹ የቤት ስራዉን ለመስራት አቅምም ተነሳሽነትም የጎደላቸው፣ እንቅስቃሴያቸዉን በሚዲያና፣ በአዲስ አበባ የወሰኑ፣ መሪዎቻቸዉ የፓርላማ ወንበር የማግኘት እድላቸውን ከመሞከር ባለፈ ፓርቲዎቻቸዉ አገራዊ ውክልና እንዲኖራቸው የማድረግ  ተስፋን የዘጉ ሆነዉ እናያቸዋለን። የብልጽግ ፓርቲ ያለፈዉን የኢህአዲግ መዋቅር በመዉረሱ የተነሳ በሁሉም የአገሪቱ ወረዳዎች የተዘረጋ መዋቅር ቢኖረዉ አይደንቅም።

 1. ኢዜማ እዉነተኛው የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ፓርቲ መሆኑ

የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ቋንቋ፣ ባህል፣ ወጎችና ሌሎች እሴቶች በሙላት መከበር እንዳለባቸዉ፣ ሁሉም ምልኡና እኩል እንደሆኑ፣ የኢትዮጵያውያን የጋራ መገለጫዎችና መኩሪያዎችም እንደሆኑ ኢዜማ ያምናል። እዉነተኛ አገራዊ ፓርቲ በመሆኑ፣ ከዚህ አይነት እምነትና አመለካከት ዝንፍ ሊል አይችልም ብዬ አምናለሁ። ይሁንና ኢዜማ የፖለቲካ ትርጉም ሆነ የፖለቲካ መሰረቱ ዜግነትና ዜግነት ብቻ መሆን እንዳለበት ከታሪክ፣ ከአመክዮና ከአለፉት 30 ዓመታት የአገራችን ልምድ በመነሳት ሲያስረዳና ሲያስተምር የቆዬ ፓርቲ ነዉ። ኢዜማ ከገዢዉ የብልጽግና ፓርቲ በተጻራሪ፣ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ያለው ህገ-መንግስትም ሆነ ዘር-ተኮር የፖለቲካ ስርአት፣ ዜጎች በእኩልነት ሊሳተፉ የሚችሉበት እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርአት ሊያመጣ አይችልም ብሎ ስለሚያምን ህገ-መንግስቱ እንዲቀየርና፣ የፌዴራል ስርአቱ አስተዳደራዊ ክልሎች አወሳሰን ቋንቋን ጨምሮ በሌሎች በርካታ መስፈርቶች ላይ እንዲመሰረት የሚታገል ድርጅት ነዉ።

በዜግነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ፍልስና የሚያራምዱ ሌሎች ፓርቲዎች መኖራቸዉ ይታወቃል። ይሁንና ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸዉ አትኩሮትም ሆነ የምርጫ ዉክልና ኢላማቸዉ (presumed constituency)፣ ልክ እንደብሄር ድርጅቶች ሁሉ፣ ከአንድ ብሄር ማህበረሰብ አይዘልም። አንድ ድርጅት 100% የፖለቲካ እንቅስቃሴዉን ባንድ ማህበረሰብ ዙሪያ ከልሎ የዜግነት ፖለቲካ አራምዳለሁ ማለት አይችልም። ከዚህ አንፃር፣ ከቃልና ከፍላጎት ባለፈ በተግባር የሚታይ የዜግነት ፖለቲካ የሚያራምድ ፓርቲ ኢዜማ ብቻ ነዉ ብዬ አምናለሁ።

 1. የኢዜማ ዲሞክራሲዊነት በተግባር የታየ መሆኑ

ለዚህም አንዱ ማስረጃ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ፓርቲዉ የተመሰረተበትና የፓርቲዉ አመራር የተሰየመበት፣ በአሁኑም ወቅት ለተለያዩ ምክር ቤቶች ምርጫ የሚወዳደሩ አባሎቹ የተመረጡበት ሂደት ነዉ። ብዙ ሌሎች ፓርቲዎች በዉስጣቸዉ ያልተለማመዱትን የዲሞክራሲ ስርአት በአገር ደረጃ እናመጣለን እያሉ፣ ደግፉን ምረጡን ይላሉ። ጥቂቶቹ ከእነአካቴዉ እንደ ኢዜማ አይነቱ ፓርቲ የሚጠራዉን ህዝባዊ ስብሰባ በወሮበሎች እንዲስተጓጉጎል እየሰሩ፣ ያለምንም ይሉኝታ፣  በድፍረት፣ የምንታገለዉ ለዲሞክራሲ ነዉ ይላሉ። በተለይ በዘር የተደራጁ ፓርቲዎች፣ ሁሉም፣ ዲሞክራሲን እንደጦር ነዉ የሚፈሩት። ምክንያቱም በዘር የተደራጀ ፓርቲ በተፈጥሮዉ የአግላይ ፖለቲካ ዉልድ ስለሆነ ነዉ።

ኢዜማ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ስልጡን ፓርቲም ነዉ። ለአሉባልታ፣ ለወሬና ለሃሜት ቦታ የማይሰጥ፣ ከስድድብና ከጉንጭ አልፋ አታካራ ራሱን ያራቀና ማህበረሰቡን በማንቃት ምቹ ሃገር ለመፍጠር የሚተጋ፣ የሚያምንበትን በወሬ ሳይሆን በስራ የሚያስመሰክር፣  አመራሩም ሆነ አባላቱ በበጎ ስነምግባር የታነጹ፣ የኢትዮጵያን የፓርቲ ፖለቲካ ባህል መሰረታዊ በሆነ መንገድ ለመቀየር ቆርጠዉ የተነሱ ሆነዉ አግኝቻቸዋለሁ።

 1. ኢዜማ የፖለቲካ ስራ ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረዉ የሚሰራ ፓርቲ መሆኑ

ለአንድ አገር የተረጋጋ የፖለቲካ ስርአት ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ በጊዜያት ዉስጥ ጸንተዉ የሚኖሩ የፓርቲ ተቋሞች መኖር ነዉ። እንደዚህ አይነት ፓርቲዎች በአራት ወይም በአምስት አመት ከሚደረግ የምርጫ ሂደት የሚሻገሩ፣ ዘላቂ የሆኑ አላማዎችና ፕሮግራሞች ስለሚኖራቸዉ፣ ይህን ማስተናገድ የሚችል የፖለቲካ ባህል እንዲፈጠር የሚጫወቱት ትልቅ ሚና በሌላ በምንም ሊተካ የማይችል ነዉ። ከዚህ አንጻር፣ ኢዜማ ለፓርቲ አደረጃጀት የተከተለዉ መንገድና ቁርጠኝነት፣ ፓርቲዉ በጊዜያዊ የፖለቲካ ትኩሳትና ብርድ ሳይፍረከረክ፣ ከመቶና ሁለት መቶ አመታት በኋላም ጸንቶ እንዲኖር ታስቦበት መሆኑ የሁላችንንም አድናቆት ሊያሰጠዉ የሚገባ ነዉ።

ሌሎች ፓርቲዎች የኢዜማን ምሳሌ በመዉሰድ ከጊዜያዊ መቆራቆስና የምርጫ ፉክክር ባሻገር ጸንቶ የሚቀጥል፣ የተረጋጋ፣ ስልጡን ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ የፖለቲካ ባህል በአገራችን እንዲፈጠር ከራሳቸዉ ቁመና ጀምሮ ቢሰሩ መልካም ነዉ። ያን ቢያደርጉ፣ የፖለቲካ ሜዳዉ ዛሬ እንደምናየዉ 40 እና 50 ፓርቲዎች  የሚርመሰመሱበት መሆኑ ቀርቶ ቢበዛ ከ5-10 የሚሆኑ ጠንካራ ፓርቲዎች የሚፈጠሩበትና፣ ፖለቲካዉ ከመረጋጋት አልፎ ስልጡንና ከበሬታ ያለዉ ይሆናል ብዬ አምናለሁ።

 1. ኢዜማ የኢትዮጵያ ህዝብ እድል ቢሰጠዉ፣ ነገ መንግስት የመመስረት ሙሉ አቅም ያለዉ ፓርቲ መሆኑ

ኢዜማ በሰዉ ኃይል፣ በሰከነ የፖለቲካ ፕሮግራምና በዝርዝር ፖሊሲዎች የተሟላ ዝግጅት ያደረገ ፓርቲ ነዉ። ኢዜማ፣ ድርጅታዊ መዋቅሩን በአገሪቱ ውስጥ ከፈጠረ በኋላ፣ የአገሪቱን ችግሮች ነቅሶ በመተንተን፣ ለችግሮቹ መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ ያላቸዉን ከአርባ በላይ የሆኑ ፖሊሲዎችን፣ በዉስጥ አባላቱና ከፓርቲዉ ዉጭ ባሉ ምሁራንና ባለሙያዎች አስገምግሞ ያቀረበ ብቸኛ ድርጅት ነዉ። ኢዜማ የፖሊሲ ዝግጅት ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ በየመስኩ የሰለጠኑና ለአመታት የሰሩ ባለሙያዎችን በአባልነት ያካተተ ፓርቲ ነዉ። የዚህ ዝግጅት ዉጤት በፓርቲዎች መካከል በመደረግ ላይ ባሉት የምርጫ ክርክሮች ላይ የኢዜማ ተወካዮች ባሳዩት ከተፎካካሪዎቻቸዉ የላቀ ብቃት የተንጸባረቀ ሆኗል።

አንዳንዶች የአገር ህልዉና አደጋ ላይ ሆኖ ዝርዝር ፖሊሲ ማዉጣት ቅንጦት ነዉ ይላሉ። ይህ ከስንፍና የመነጨ፣ ምናልባትም የብቃት ጉድለትን ለመሸፈን የሚሰጥ አስተያየት ነዉ። የአገርን ህልዉና በዘለቄታነት ማረጋገጥ የሚያስችል ብቸኛ መፍትሄ የለም። የአንዲት ሃገር የህልዉና አደጋ፣ የብዙ ዉስብስብ ችግሮች ድምር ዉጤት ነዉ። የእነዚህን ችግሮች መሰረትና ቁርኝት ሳይረዱና ዝርዝር የፖሊሲ አቅጣጫ ሳያስቀምጡ፣ አገርን ከህልዉና አደጋ ማዳን አይቻልም።

 1. ኢዜማ በመሪዎች የታደለ መሆኑ

ኢዜማ በስብእናቸዉ፣ በአገር ወዳድነታቸዉ፣ በአስተሳሰብ ብስለታቸዉ፣ በሃላፊነት ቁመናቸዉና በጽናታቸዉ የታወቁ መሪዎች ያሉት ድርጅት ነዉ። እነዚህ መሪዎች በግል ህይወታቸዉም ሆነ በፖለቲካ ጉዟቸዉ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ወይም ሌላ ጥቅም የማያጎበድዱ፣ አገር ፍጹም ነፃና ዲሞክራሲያዊ እስክትሆን የሚያስፈልገዉን ዋጋ ለመክፈል የቆረጡ መሆናቸዉን ደጋግመዉ ያስመሰከሩ፣  እስካሁን በሰሯቸዉ ታሪኮች ባይኩራሩም ደረታቸዉ ነፍተዉ መሄድ የሚችሉ መሪዎች ናቸዉ ብዬ አምናለሁ። የኢዜማ ድርጅታዊ ቁመናም ሆነ የአባላቱ ስልጡንነት፣ የሞራልና የዲስፕሊን ገጽታ የመሪዎቹ ስብእና፣ የእምነት ጽናትና ቁርጠኝነት መገለጫ ነዉ ብዬ አስባለሁ።

ማጠቃለያ፦

ኢዜማን መደገፍ/መምረጥ የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም፣ የዜጎቿን ያልተሸራረፈ መብትና፣ የብሄር ብሄረሰቦቿን ፍጹም እኩልነት መምረጥ ነዉ! የኢትዮጵያ መጻኢ እጣ ፋንታ ብሩህ እንዲሆን መምረጥ ነዉ!!!

…….

ከላይ የቀረቡት ምልከታዎች የግሌ ናቸዉ።

10 Comments

 1. እንደዚህ ነው መሰልጠን፣ በግልጽ ወጥቶ ሌላውን ሳያጥላሉ፤ ጥላቻን ሳይዘሩ፤ የራስን ሃሳብ መግለጽ። ይመችህ አቦ!
  በምርጫ ብቻ!

 2. ሄኖክ ነውር አይደለም የፓርቲን የምረጡኝ ቅስቀሳ እዚህ መለጠፍ። ብርሀኑ ነጋ/አንዳርጋቸው ጽጌ/ኤፍሬም ማዴቦን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቅጥ አምባሩን ያጠፉ ወሮበሎች ምረጡ ትለናለህ?

 3. Well, It is up to you or your right to trust your buddies even to the extent of worshiping . But the very problem with your extremely shallow if not infantile way of political understanding about your “good buddies “ does not make a real sense of democratic process and achievement . Yes, there may be some who have personal nicety . But we are actually talking about what they are and what they do as far as the very issue of making a truly democratic Ethiopia a reality is concerned. Do you really believe that a leader of a party Who wholeheartedly argue that he hundred percent trust those politicians whose hands are stained with the very blood of innocent citizens for three decades is a genuine and a great political leader??? Do you really believe those politicians who unfortunately have become the very underdogs of the palace politics of the so called Prosperity by badly waging their very ugly political tails are great political leaders ? In short, all the points you tried to enumerate have nothing to do with the very hard reality on the ground . You look like like badly fooled or indoctrinated , unfortunately !!! This is what I wanted to say for now. I am very willing to come back with a much more critical views of mine . I have to tell you that I was one of genuinely concerned compatriots who have been sympathizing and closely following the former G7 , now EZEMA politicians . This is to say that my critical views toward those politicians is not a matter of easygoing approach but a matter of telling the truth and only the truth !!!

  • What are you talking about, Tegenaw? Where did you get this crazy idea that Ezema leaders trust those whose hands are stained with the blood of innocent people? Do you know who you are talking about? Do you ever do some homework to find the honest truth rather than swallow the ‘alubalta’ of those who make a living by fabricating lies? If you are telling the truth, where is the evidence? What you heard from social media is hardly an evidence. Think for yourself. Don’t parrot what others with an agenda say. Sorry I didn’t understand what you are trying to say with the underdog point.

 4. Why don’t you just tell us to go and kill our selves instead of asking us to vote for these scoundrels called EZEMA?For your info these charlatan politicians like Birhanu Nega, Andargchew Tsige and so on of ginbot 7 and now Ezema are enemy of Ethiopia. As far as Ethiopian people are concerned they should be persona non grata if you know what I mean. By the way didn’t Birhanu call 50 million Amaras “mete Sefis ” in their own land and you want them to vote for him? You have the nerve to ask buddy.

  • You didn’t argue with any of the 7 points raised because you can’t, because they are true. BTW, Berhanu didn’t call Amharas ‘mete’ or ‘sefari’, he was using the terms used by those who attacked Amharas to make a point. The point being the only way you can stop Amharas from being seen and attacked as ‘mete’ and ‘sefari’ is by claiming Ethiopia for all Ethiopians. This may be hard to grasp for those who get their daily ‘alubalta ‘ from Ethio330. The fact is you cannot find a bone in Berhanu or Andargachew that hates Amharas. None.

   • Mattheos
    I don’t have to argue any point about Birhanu and co. I know them by heart. I have been following their work for a long time, if you think I was born yesterday you are mistaken. I know them when they busted kinjit working for Meles Zenawi, I know them when sabotaging Arbegnoch ginbar, I know them when they deal with liberation fronts while excluding Amaras, I know them when they excluded Amaras from leadership by writing a language that says “only a person with two language skills can be in ginbot 7 leadership”. And most of all I know them when they preach there is no such nation called Amara. So, do I say more. Wait for the coming books. But again you may be one of their groupie, good luck defending Ezema, they are paid spies they are not even Ethiopians per se. You are trying to defend the undefendable bunch, some people learn slow, so you may go and watch esat to get dumber and more dumber by the day.

 5. የኢዜማ የዜግነት ፖለቲካ ከወረቀት የማያልፍ መሆኑን ራሱ በተግባር አሳይቷል።ከመንግስት መተባበር የቻለ ፓርቲ ከተቃዋሚዎች ለመተባበር ለምን ተቸገረ ? ኢዜማ ሲፋቅ ለምን እህዴድን መሰለ? የመንግስትነ ለሆዝብ የማይጠቅም ስራ መተቸት መንግስት ማፍረስ ነው? ህዝብ ላይ እሳት ሲነድ ሰላም ነው ብሎ መስበክ መንግስት እንዳይወድቅ ነው? ሲተች የሚወድቅ መንግስት ይውደቅ።

 6. ሽፈራው አበበ ኢዜማን ምረጡ የምትለው እውነትህን ከሆነ አዲሱ አምላክ አዱኛ ፈይሳ ይዩልህ ሌላ ምን ይባላል ሁሉም ቀልድ ሁኗል መቼም

 7. EZEMA ARBEGNOCH GIM7 , PROSPERITY PARTY AND OLF ARE ALL TRAITORS BANDAS , PUPPETS OF ISAIAS AFEWORKI, THEY ARE ALL WORKING TO BURRY ETHIOPIA BY LETTING ERITREA COLONIZE ETHIOPIA.

  EZEMA GURAGES ARE SLAVES WHO ARE TRYING TO TURN THEMSELVES INTO HOUSE SLAVES/SLAVE CABOS FOR THE FIRST TIME IN THEIR HISTORY, IN ANYWAY POSSIBLE.

  OROMOS WANT TO BE THE GADGETS OWNERS THE TRACTOR TOYS OWNERS SO THEY ARE EASILY MANIPULATED BY THE ERITREAN PROSPERITY PROPAGANDA.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.