“መጤ እና ዜግነት”  ምን እና ምን  ናቸዉ !! – ማላጂ

Birhanuከሰሞኑ  ከ“ኢዜማ ” ከአንድ ጉምቱ የፖለቲካ መሪ  ዜጎችን መጻተኛ በሚል በአገራቸዉ እና ዕትብታቸዉ በተቀበረበት ቦታ /ቅየ  “መተከል አዉራጃ ” መጤ ናቸዉ የሚል  አስተያየት ሰጥተዋል የሚል ወሬ  ስንሰማ ፈራን ፤ ተሳቀቅን ፤ተጠራጠርን ፡፡

ርግጥ ነዉ  ይህ የ1960ዎች  የብሄር ጭቆና የትግል ስልት ነጸብራቅ እና ቅሪት አካል እንጅ አሁን ከሚያራምዱት የዜግነት ፖለቲካ ጋር የሚሄድ መሆን አለመሆኑን ልብ ስለማለታቸዉ እንጠራጠራለን ፡፡ ታስቦበት ከሆነም  ስንወጣ ስንገባ ከብሄር  ወደ ዜጋ ተኮር ርዕዮተዓለም የሚያሻግር ኢዜማ ወደ  ማዜም ከሆነ ማዜም እና ወርቅ ዋንጫ ማስጨበጥ ከምርጫ ቅስቀሳ አስከ ምርጫ ዋዜማ ወግ መሆኑን እና በተለያየ ቅኝት ማዜም ለረጅም ዓመታት የተለመደ መሆኑን ከእኛ በላይ አዛሚዎች ያዉቁታል  ፡፡

ከዚህም በላይ  ህገ መንግሰቱ እንዲሻሻል የሚሉንም እንዳለ ሳንረሳ መጤ እንዲሉ ያስቻላቸዉ ይህ  ህገ መንግስት የቀደደዉ ቦይ መሆኑን ሲያዉቁ  የሚሻሻለዉ የሚሉት የትኛዉን ህገ መንግስት እንደሆነ አሁንም በመጻተኛ እና ነባር ዜግነት ላይ ሊኖር የሚችለዉን የልዩነት መስመር  አጥርቶ አለመለየት ጉዳዩን እንቆቅልሽ የሚያደርግ ነዉ ፡፡

የዜግነት የህዝብ አስተዳደር እና የግዛት ወሰን ህብረ ብሄራዊ ኢትዮጵያዊነት እንጅ በጎጥ እና በቋንቋ  ነባሩን ስደተኛ ዕንግዳዉን ባለቤት ማድረግ የቤት ቀጋ የዉጭ አልጋ  ከመሆን በላይ ዜጎችን የዜግነት መብት በጠራራ ፀሃይ የሚቀማ ፣ ሰባዊ እና ተፈጥሯዊ ማንነትን የሚያሳጣ የህገ መንግስት ይዘት እናሻሽላለን ለምትሉን በአንድ አገር ህዝብ ለዚያዉም ለነባር ዜጎች የመኖር ዋስትና የሚነፍግ አስተሳሰብ በስደተኛ/ መጤ መሰየም እና መጀቦን  እንዴት የሀሳብ አንድነት ሳይኖር ተግባር ሊታሰብ የሚችልበት አማራጭ ሩቅ አለመሆኑን እንዴት እንተማመን ፡፡

እኮ እንዴት ሆኖ ይሆን የዜግነት ርዕዮተ ዓለም ፣ የህገ መንግስት( ብሄር ተኮር ) የግዛት አስተዳደር መሰረት  እንዲሁም በነባር እና መጤ( ብሄር/ቋንቋዊዝም) አስተሳሰብን እና ተግባርን አንግቦ ወደ ዜግነት(ኢትዮጵያዊነት) ኢትዮጵያንዚም እንጓዝ የምትሉን ፡፡

አገር እና መንገድ የጋራ ነዉ  ዕንግዳ እና ባዕዳ ብሎ በአገር ጉዳይ ላይ  ነባሩን መጤ ሲባል የብሄራዊ አንድነት / ዜግነት  አብሮነት እና ጉዞ ማን ከፊት ይሁን ዞትር ህዝብ ከፊት መሪ እንደ ከብት ዕረኛ ከኋላ ምን ይሉት የአስተዳደር ዘይቤ ነዉ ፡፡

መሰሳት ሠባዊነት እና ተፈጥሯዊ  ጠባይ እና ክስተት ቢሆንም  ለዓመታት በአገር አንድነት እና በህዝቦች አብሮ መኖር ችግር ዉስጥ የከተተ የፖለቲካ አካሄድ እና ብዙ ኢትዮጵያዉያንን በኢትዮጵያዊነታቸዉ ብቻ በህይዎት የመኖር ፣ ሰርቶ የማግኘት ምብታቸዉን የነፈገ እና የብዙዎችን ህይዎት ዕርደ ከልብ በማድረግ ዕልፍ አዕላፍ ህይወትን የነጠቀ እና ያሳደደ መሆኑን መርሳት ሰባዊነት ላለዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚቻለዉ አይሆንም ፤ይህም  ከትናንት አስከ ዛሬ የሚታይ ትዝታ እና ዕዉነታ  ስለሆነ ነዉ ፡፡

በዚህ አጋጣሚ የነገ መሪ እንሆን ሰዎች ዛሬ በህዝብ እና አገር ጉዳይ የመሀል ተመልካች እየሆኑ እና ህዝብን እና አገርን ሊያስከፋ በሚችል አገላለጥ ይቅርታን ለመድፈር እና ህዝባቸዉን በይቅርታ እንዲታለፉ ለመጠየቅ እንደ ቋጥኝ  ለሚከብዳቸዉ ነገም ለሚያደርጉት ሁሉ በእነርሱ ልክ ትክክል ስለሚሆን ይህ ዛሬ በአገራችን ያለዉን መከራ እና ፍዳ እንደምን ሊያቆሙት እንደሚችሉ ለምናስብ ድካማችንን  የጨለማ ሩጫ ሆኖ ይገኛል  ፡፡

ስለዚህ የምንወዳችሁ እና የምናከብራችሁ ኢትዮጵያዉያን ቢያንስ የማትኖሩትን ብትነግሩንም የምትሉትን ሊሆን የሚችለዉን በአንደበት እንኳን  “ወርቅ ማስጨበጥ ” ካለፉት ተሞክሮዎች  ዉሰዱ እንጅ  እንዲሁ አራባ እና ቆቦ  የማይዛመድ አገላለጥ ለኢትዮጵያ እና ህዝቧ አይመጥንም  እንዲያዉ  በደፈናዉ “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ….”   በሉት ፡፡

የዜግነት አስተሳሰብ በአንድ ሉዓላዊት አገረ ኢትዮጵያ  ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዕኩል ሠባዊ ፣ ማህበራዊ ፣የአገር ባለቤትነት እንዲኖረዉ እንጅ  ኅዝብን በራሱ አገር ፤ምድር መጻተኛ /መጤ ማለት የብሄርተኝነት (ethnicity ) ከ ዘመናዊ የጭሰኝነት እና የጉለተኝነት አስተሳሰብ ዉጤት ነዉ ፡፡ እናም ደግሞ እንለምናችኋለን፤ እንማጠናችኋለን ቢያንስ በመከራ ፣ በድህነት ፣ በተለያ ተግዳሮት ያለፈን እና ያለን ህዝብ በሞት እና በተለያየ መስዋዕት ይችን አገር  ያስረከበንን ህዝብ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ አግላይ እና በዳይ አይስማሜ ነገሮችን እየደረትን በቁስል ላይ መርዝ እንደማይገባዉ እያሰብን ቢሆን መልካም ነዉ እና እየተስተዋለ ቢሆን ዕድለኞች በሆን ነበር  ፡፡

ከዚህ ዉጭ ማዜም እና የብሄራዊ መብት ተቆርቋሪ ( የዜግነት ጉዳይ) በይዘትና በተግባር አንድ ስለማይሆኑ የመጤ ( አካባቢያዊ ብሄርተኝነት / ቐንቋይዝም) እና ዜግነት ( ብሄራዊ አንድነት / ኢትዮጵያዊነት) ምን እና ምን እንደሆኑ በመሰረተ ሀሳብ መግባባት ለብሄራዊ አንድነት እና ህብረተሳባዊ ኢትዮጵያዊነት  ለሚደረግ  ጉዞ በግማሽ የሚያፋጥን እና ድካም የሚቀወንስ  ይሆናል ፡፡

ማላጂ

አንድነት  ኃይል ነዉ  !!!

 

6 Comments

 1. “መጤ” ዘመዶቼ

  Nice and respectful comment by Malaji. Thank you.
  አንድን ሰው የሆነን ስህተት አውቆ ይሄንን አደረገ ብሎ ከመውቀስ ባለማወቅ ነው ያደረገው ብሎ ለማስተማር ከስህተቱ እንዲመለስ ለመሞከር መጀመር ይሻላል። ምንም ያህል አንድ ሰው እውቀቱ ባንድ ጉዳይ የተሟላ ቢሆንም በሌላው ጉዳይ ደግሞ ትልቅ ክፍተት ይኖረዋል።
  ዶ/ር ብርሃኑ ነጋም ሕይወታቸውን በሙሉ በፖለቲካ ትግል ውስጥ ያሳለፉ፣ ሕይወታቸውንም ለአደጋ አጋልጠው በሚያምኑበት ነገር የታገሉ፣ እስርና እንግልት፣ ስደትና በረሃ መውረድን ያካተተ የተጋድሎ ሕይወት በአንድ በኩል በሊላ በኩል ደግሞ በትምህርት ራሳቸውን ያነጹና ሌሎችንም ለማነጽ እስከ ፕሮፌሰርነት ደርሰው በዮኒቨርሲቲ ያስተማሩ እንደመሆናቸው ይህንን እውቅና ነፍጎ እሳቸውን ደርሶ መዘርጠጡ ተገቢነት አይኖረውም። ስለዚህ ምንም የፈጸሙት ስህተት እጅግ አደገኛና በአማራና በአገው ሕዝብ ላይ የተክፈተበትን ጄኖሳይድ የሚያባብስ ቢሆን ከተጋድሏቸው አኳያ ንግግራቸው አውቆ ለማጥፋት ሳይሆን እስኪ ባለማወቅ የተደረገ ስህተት ነው ብለን እንየው። ምክንያቱም የ “ያ ትውልድ” አንጋፋ አባል እንደመሆናቸው ትውልዱ ከሠራቸው አንጋፋ ስህተቶች ነጻ አይሆኑምና “ያ ትውልድ” በኢትዮጵያ ታሪክ አረዳድ ላይ በሕዝቡ መሠረታዊ ችግሮችና በመፍትሔያቸው ላይ የነበረውን አመለካከት መፈተሽና ከዚያ አኳያ መገንዘብ የግድ ይላል።
  እነ መለስ ዜናዊን ጨምሮ በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የትውልዱ አባላት ባባዶ እግሯ የምትሄደው እናታቸው አሳዝናቸው፣ በእሾህ እንዳትሰቃይና ከሌላው ሰው እኩል እንድትራመድ ከውጭ ሀገር ያስመጧቸውን ከሷ እግር መጠን ጋር ያልተዛመዱና የተለያዩ የግራና የቀኝ እግር ጫማዎች ሊያጠልቁላት ሲሞክሩ የኖሩ ናቸው። አልገጥም ያለውን ጫማ ሳይሆን የእናታቸውን እግር በመከረከም፣ ባስም ሲል ገላዋን በመቆራረጥ ጫማው ውስጥ ሊያስገቡ ሲሞክሩ ዘመንም እድሎችም አምልጠው እዚህ ላይ ደርሰናል። እዚህ ላይ ተቆርቋሪነታቸው፣ መፍትሔ ለማምጣት መሞከራቸው፣ በዚሁም ተግባር ትጋታቸው የማያጠያይቅና ጊዜና ታሪክ የመዘገቡት እውነታ ነው። ግን አሳዛኙ ነገር ዛሬም አካሏን በማስተካከል ነው ጫማው እንዲሆናት እና ዘምና እንድትጓዝ የሚደክሙት። የእግሯን መጠን ለመለካት፣ የእግሯን ቅርጽ ለመረዳት ከዚያም በልኳ የሚሆናት ጫማ ለመስፋት ትኩረት ወደ መስጠት ሊሄዱ አልቻሉም። ከስታሊን ፋብሪካ የተሠራውን ጫማ ግራና ቀኝ እያዟዟሩ በደማውና በተቆራረጠው እግር ላይ በግድ ለመሰካት መሞከር ብቻ!
  ዶ/ር ብርሃኑ በመተከል ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ስላሏቸው “አማራና ሌሎች መጤዎች” ስላሉት
  በመተከል እንደሚታወቀው የአማራው እጅግ ቢከፋም አገው፣ ሽናሻ፣ ኦሮሞ የጭፍጨፋ ሰለባዎች ሆነው ከርመዋል። አማራን በተመለከተ እኔ ከመተከል አማሮች የዘር ሐረግ ስላለኝ በአንድ በኩል ነባርና ከየትም ያልፈለሰ የመተከል ባላባት አማራ ሕዝብ እንዳለ፣ በሌላ በኩል በሰፈራ ዘመቻ ተሳታፊ ስለነበርኩ ቤት ሠርተን ከወሎና ከትግራይ በሰባ ሰባቱ ዘመቻ ሰዎች እንዳሰፈርን ከነዚህም ውስጥ አማሮች እንደነበሩ ልነግራቸው እችላለሁ። አገዎችን በተመለከተ መተከል የቀደመ ስሙ አገው ምድር ይባል እንደነበረና አገዎች ለዚህ ቦታ ነባር እንጂ መጤ ሕዝቦች እንዳልሆኑ ከታሪክም ከግል የዘር ሐረግም በመነሳት ልመሰክር እወዳለሁ። የወንበራን ኦሮሞዎችን በተመለከተም በጎጃም ክፍለህገር ለመቶ አመታት የኖሩ ነባር ሕዝቦች እንጂ መጤ እንዳልሆኑ ከታሪክም ከዘር ሐረግም አጣቅሼ ልነግራቸው እወዳለሁ። በመጨረሻም ሽናሻዎች ከሕወሃት በተለይም ከብልጽግና ሥልጣን መያዝ ወዲህ በጉምዝ ታጣቂና ካድሬ የተገፉና የተጠቁ ቢሆንም በሌላ ቦታ የማይገኙ ነባር የመተከል ባላባቶች እንደሆኑ ይታወቃል። ታሪክም ይህንኑ ይነግረናል።
  ብዙ መቶ አመታት ወደ ኋላ ሄደን ከሆነ ‘መጤ’ ‘መጤ’ የምንባባለው ጉምዞች ከወለጋ በኦሮሞ ተገፍተው ወደ መተከል እንደገቡ፣ ኦሮሞዎችም ጥቂት ቆይተው ተከትለዋቸው ወደ መተከል እንደመጡ፣ በሥፍራው የነበሩ አገዎች ደግሞ የተወሰኑት ወደ ወይና ደጋውና ደጋው መተከልና አገው ምድር እንደተሸጋሸጉ የአካባቢው አፈ ታሪክ ይናገራል። የዶ/ር ነጋሶና የሌሎችም የታሪክ ጽሑፎችም ይህንኑ ይደግፋሉ። “መጤ” ለሚል አደገኛ ፍረጃ ብዙ መቶ አመታት ወደ ኋላ መሄድ ከተጀመረ ለማንም አያዋጣምና መጤ ባዮች ሁሉ እንዲጠነቀቁ ማስጠንቀቂያ መስጠት የግድ ነው። ለምሳሌ ዶ/ር ብርሃኑ ከጉራጌ ብሔረሰብ ናቸው። ከጉርዐ ኤርትራ ወደ ሸዋ የመጣ ሕዝብ። እኛም ከተለያየ ቦታ አዲስ አበባ ከመጡ የተወለድን ነን። ኦሮሞም ከቦረና ተነስቶ በመምጣት የዛሬዋን አዲስ አበባ አልፎ ወለጋና ከዚያም አልፎ እስከ ጣና የመጣና የሰፈረ ሕዝብ ነው።
  እነዚህ ቦታዎች ፈጽሞ ባዶ አልነበሩም። ነበሩ ማለቱ የልጅ ጨዋታ ይሆናል። ከግራኝ ወረራ በፊት ምን ዓይነት የሕዝብ ስብጥር እንደነበረባቸው ታሪክ መዝግቦታል። ከዚያም ቀደም ሲባል የሰው ልጅ መፈጠሪያ በነበረች ሀገራችን እየወጣ የሄደው ቢበዛም እዚሁ የነበሩና ብዙ ሺህ አመታትን ያስቆጠሩ ጋፋቶች፣ አገዎች፣ ማያዎች፣ ዳሞቶች፣ ቤጃዎች እና ሌሎችም ላይ ከሰሜን ደቡብ ከደቡብ ሰሜን ከምሥራቅ ምዕራብ በስደትም፣ በወረራም በሰፈራም ሕዝቦች እየተንቀሳቀሱ ዛሬ ያለውን መልክ ይዘዋል። ባለጊዜ ነኝ ብሎ ታሪክን እያጣመሙና ከሆነ የታሪክ አንጓ መርጠው እየተነሱ መጤ መጤ መባባሉ የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብና ወደ ድንጋይ ዘመን መላሽ እልቂትን የሚጠራ እንጂ ለሀገር የሚበጅ ሰላምም ሆነ እድገትን የሚያመጣ አይደለም።
  የዛሬ ኦሮምኛ፣ አማርኛና ትግሪኛ ተናጋሪ ወገኖች በእያንዳንዳቸው የቋንቋ ክፍፍሎች እጅግ ብዙ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ የነበሩ ነገዶችን በውስጣቸው ያዘሉ እንደሆኑ ለማወቅ በታሪክ ብዙም ሩቅ መሄድ የለብንም።
  ወደ ልቡናችን እንመለስ። ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በአንድ ወቅት የተናገሩትን ልብ ማለት ያስፈልጋል።
  “ሀገሩ ሰፊ ነው። ሀገሩ የጋራ ነው። ሀገሩ የእግዚአብሔር ነው።”
  ሀገርን በመገንባትም ሆነ ከወረራ በመጠበቅ ባደረጉት አስተዋጽኦ እናት አባቶቻችን ሀገሪቷን የሁላችንም አድርገዋታልና ማንም ከማንም የበለጠ ወይም ያነሰ ባላባትነት የለውም። ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት፤ ሁላችንም የኢትዮጵያ ነን።
  ታሪክንም እናስተውል። ታሪክንም እንወቅ። ግዙፍ የፖለቲካ አንድምታ ያላቸውን ለሕዝብ ግጭትና እልቂት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ፍረጃዎችን ከማድረግ እንቆጠብ። በተለይም የፖለቲካና የአደባባይ ሰዎች። ይኸው ነው ወገናዊ ምክሬ።
  እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልን።
  የኢትዮጵያን ትንሳኤም ያቅርብልን።

  • አሁን ዶር ብርሀኑ በየትኛው አውደ ውጊያ ነው እራሱን ለአደጋ አጋልጦ ያየኸው? በአንድ ሁኔታ ላይ መጠነኛ ግንዛቤ ቢኖረን ተሳስተን ሰውንም አናሳስትም።ብርሀኑ በአንድ መድረክ አንዱ ጠያቂ ስለ ወያኔ ግፍ አምርሮ ሲጠይቀው “ንግግርህን አለዝበው እኔ ማኪያቶ እየጠጣሁ የማራምደው ፖለቲካ ነው የምፈልገው” ነበር ያለው አስመራም አለን ያሉት ጦር ፈገግ አድርጎናል ገንዘብ መዝረፊያ ነበር ። ቢያንስ አውቃችሁ አታሳስቱን እዘኑልን

 2. በዜግነት ካባ የተሸፋፈነው ብርሃኑ ነጋ የኦነግ ፖለቲካ አራማጅ ነው ። በሄደበት ሁሉ መጤ ሰፋሪ እያለ አማራውን የሚተቸውና ቅስቀሳ የሚያካሂደው ከአማራ ጠልነቱ የመነጨ ነው ።ይህ አይነት ቅሰቀሳ ብዙ አማራ እንዲጨፈጨፍ ያደረገ ነው።

 3. hello Mr. MALAJI, do you read and listen amharic ? I THINK YOU ARE BELONGS TO THE GOJAM ACTIVIST
  millions of Ethiopians are heard what professor Berhanu said, plz. look something else at list closer to your lie

 4. Ahoon. ብርሀኑ ነህ ማለት ነው? ሲጀመር ብርሀኑና አንዳርጋቸው የሚመሩት ድርጅት አማራ ክልል ምን ይሰራል? የብርሀኑን አማራ ጠልነት ለመገልበጥ ይምታደርገው ሙከራ አንተኑን ይገለብጥህ እንደሆን እንጅ ሀቁን ፈቀቅ አያደርገውም። ወዳጅህ ከሆነ በቃህ አርጅተሀል ያለው ትውልድ ጋር አትተዋወቁም የተሸፈንክባት ፕሮፌሰር የሚሏት ነገር ነች።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.