መደመርና የ2013 ምርጫ – በአየለ ታደሰ (ዶ/ር)

አጭር ማስታወሻ

እ.አ.አ. 1995 ግድም ይመስለኛል። ምስራቅ አውሮፓ “ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ወደ ምዕራቡ ዲሞክራሲ” ለውጥ ባሳለፈች ማግስት ማለት ነው። በአሁኑ ጊዜ Big 4 በዚያን ጊዜ Big 6 ከሚባሉት Auditing Companies በአንደኛው ድርጅት ውስጥ እዚያው ምስራቅ አውሮፓ ውስጥ እሰራ በነበረበት ወቅት ያጋጠመኝን ታሪክ ላውጋችሁ።

በ1990 ዎቹ ወቅት ቢሮ “Office” ከሚባል ውጭ “Home Office” የሚባል ነገር አልተለመደም ነበር። ታዲያ በመስሪያ ቤታችን ውስጥ በአመራር ላይ የነበረ አንድ ግለሰብ በጠራን ስብሰባ ላይ “ከተወሰነ ዓመታት በኋላ እኛ ወደ ቢሮ መምጣታችን ይቀርና ቢሮው ወደ ቤታችን ይመጣል” አለን።

ከታዳሚው መካከል “ምን ማለትህ ነው?” ተብሎ ተጠየቀ።

አመራር ላይ የነበረው ግለሰብ መልስ ሲሰጥ “አሁን ያለው ባህል ልንገርህ። ወደ ቢሮ ከመምጣትህ በፊት ለስራ ትዘጋጃለህ፤ በማንኛውም ትራንስፖርት ተጠቅመህ ወደ ቢሮ ትገባለህ፤ ወደ ቢሮ ስትገባ ሰላምታ ትለዋወጣለህ፤ ከአለቃህ ጋር ትገናኛለህ፤ ለምሳ ትወጣለህ፤ ከዚያም ስራህን ከጨረስክ በኋላ ወደ ቤትህ ትሄዳለህ።”

በመቀጠልም “ቢሮው ወዳንተ መኖሪያ ቤት ሲመጣ ግን ቤትህ ቢሮም፤ መኖሪያ ቤትህም ይሆናል። ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ እስከ ቢጃማህ ወደ ስራ ትገባለህ። ምግብህን ለማዘጋጀትና ለመብላት ወደ ማድቤት ትገባለህ። ስትጨርስ ቲቪ ለማየት ወደ ሳሎን ክፍል፤ ከዚያም ለመተኛት ወደ መኝታ ክፍል ትሄዳለህ።”

ከዚያም አንደኛው “እኔ ማመን አልችልም። ይህ የእብድ (Őrűlt) አሰተሳሰብ ነው።” ሁላችንም በዚህ የአመራር ግለሰብ ዓይን ማየት ስለተሳነን ይህ እብደት ካልሆነ እንዲህ ሊሆን አይችልም አልን።

ከ22 ዓመታት በኋላ ግን ያ ግለሰቡ የተናገረው ነገር እውነት ሆነ። በኮቪድ 19 ምክንያት ቤታችን ውስጥ “Home Office”ን በማቋቋም ቢሮውና ስራችን መኖሪያ ቤታችን ድረስ መጣ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መንግስት ስለምን በሐይማኖት ጉዳዬች ጣልቃ ይገባል?

እንዲሁም በሌላ ታሪክ እ.አ.አ. 2019 ግድም አዲስ አበባ ላይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አንድ ተናጋሪ “መለሰ ጥላቻውን በግልፅ ነበር የሚናገረው አሁን የመጣው ጠ/ሚ ግን ጥላቻውን በሆዱ ውስጥ ይዞ … በአፉ ጤፍ የሚቆላ” ብሎ የተናገረው አይረሳኝም። እና ይህንን የሚለውን ግለስብም እንደ እብድ ቆጥሬው ነበር።

ይህንን መግቢያ ያነሳሁት ያለምንም ምክንያት አይደለም። የፅሁፉ መደምደሚያውን ስታነቡት ምናልባት እንደነዚህ ሰዎች “አብደሃል” እንዳትሉኝ። እኔ ግን ሙሉ ጤነኝነቴን አልጠራጠርም።

መልካም ንባብ!!!

አርዕስት አንድ 

“መደመር” በ”ሰብአዊነት” መነፅር

በመጀመሪያ መደመር ማለት ምን ማለት ነው? መደመር[1] ማለት “ከአራቱ የስሌት መደቦች አንዱ የሆነና ልዩ ልዩ መጠን ያላቸውን አሃዞች በአንድ ላይ አጠቃሎ የመቀመር ዘዴ ነው።” ብሎ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር መዝገበ ቃላት ይፈታዋል። አራቱ የስሌት መደቦች፤ መደመር፤ መቀነስ፤ ማባዛትና ማካፈል ናቸው።

የ”መደመር”ን መፅሐፍ አውዲዮ ሰማሁት።[1] መጽሐፉንም አነበብኩት። ታዲያ ይህ መጽሐፍ ለመተቸት ረጅም ጊዜ ይፈልጋል። “መጽሐፉ ከአካዳሚያዊ ዓለማ ይልቅ ለፖለቲካዊ ዓላማ የተጻፈ በመሆኑ አካዳሚያዊ አቀራረብን ሥራዬ ብሎ የተከተለ አይደለም።”[2] “መደመር” ለፖለቲካ ዓላማ የተጻፈ ሲባል የብልፅግና ፖለቲካ ፓርቲ “መመሪያ” ነው ማለት ነው።

“መደመር” እንደ “ፖለቲካ ዓላማ መመሪያ”

መደመር የ“ፖለቲካ ዓላማ መመሪያ” ሆኖ ወደ ሕዝቡ ሲወርድ ችግሩ ወለል ብሎ ይታያል። ጥያቄው ችግሩን በማን መነጽር ማየት ይሻላል ነው። ይህንን ዓለም ሳይወዱ በግዳቸው የተቀላቀሉና የተወለዱ ህጻናቶችን ሳስብ፤ ሳቅና ጨዋታ የሚያበዙት፤ ቢቆነጠጡ እንኳ ኩርፊያ የማያውቅት፤ ከየትኛውም ዘር ቢወለዱም፤ የአዳም ዘር ናቸውና አምላክ የሰጣቸው የመኖር ነፃነትና መብት ሊጠበቅላቸው ይገባል፡፡ በእነዚያ ቅን ህጻናቶች መነጽር “መደመር”ን ማየት ቃጣኝ። ምክንያቱም በመንግስት የጎሳ ፖሊሲ የተነሳ ብዙ ኢትዮጵያውን ህጻናቶች በተለይም የአማራ ህጻናቶች ያለቤተሰብ ቀርተዋል፡፡ እንዲሞቱም በመንግስት ተፈርዶባቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የበደል ድርድር - የቅጥፈት ውድድር። (ከሥርጉተ ሥላሴ)

አጤ ምኒሊክ “ድሃውን ገበሬዬ”ን አትንኩ” ለማለትም “ድሀው እወደደው እተመቸው ቦታ ይደር።”[1] ስላሉ በ”ድሀው ገበሬዬን አትንኩብኝ” መነጽር “መደመር”ን ማየትም ቃጣኝ። ምክንያቱም ብዙው ድሃው ህብረተሰብ ቤታቸውን፤ ቀዬያቸውን፤ እንዲለቁ፤ ከተማዎችን በማጥፋት ስራ መንግስት ተጠምዷልና። ከተማውም ተቃጥሎ፤ ቀዬውን እየለቀቀ ወደማያውቀው ቦታ ተሰዷልና።

እንግዲህ ያበጠው ይፈንዳ! በሚል ሁሉንም በሚጠቀልለው በ”ሰብአዊነት” መነጽር መደመር”ን ማየት ፈለግሁ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ እንደሚሉት “መደመር” እሳቤ ነው። መደመር አውራ ጎዳና ነው። “የመደመር ዋነኛ ዓላማ ሀገራችን ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበቻቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ድሎች ጠብቆ ማስፋት፤ የተሠሩ ስሕተቶችን ማረም እንዲሁም የመጻዒውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት ማሳካት ነው።[1] “እሳቤ ማለት ፅንሰ ሃሳብ ሲሆን ፅንሰ ሃሳብ ማለት ደግሞ ስለ አንድ ነገር በአእምሮ ውስጥ የተቀረፀ ግንዛቤ ማለት ነው።[2] “መደመር” ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ወደ ዲሞክራሲ አሸጋጋሪና የብልጽግና የፖለቲካ ፓርቲ “መመሪያና ፍኖተ ካርታ” ነው ብለዋል ጠ/ሚ ዐቢይ: እንዲያውምኮ “እኔ አሸጋግራችኋለሁ” ብለውናል። በ”መደመር” “መመሪያ” ላይ በመመረኮዝ ወደ ዲሞክራሲ የለውጥ ሽግግር ማለታቸው ነው። መደመር “ፍኖተ ካርታ” ነው ብለውናል።

—--ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ——-


 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.