ገጀራው የት ገባ? (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

ባለፈው ሰሞን በመንግስት ወይም በመንግሥታዊ ፈቃድ  ከተለያዩ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ በመቶ የሚቆጠሩ ገጀራዎች ጉዳይ ዘገባ ሕዝቡን አስደንግጧል።  አሸብሯል (አሳዛኙ ነገር አሸባሪ እየተባሉ የሚታደኑት በዙም(Zoom) ውይይት የሚሳተፉና የሕገ መንግሥት ረቂቅ የሚያወጡት እንጂ ገጀራ የሚያስመጡና የሚያከፋፍሉት አይደሉም) እነዚህ በዘገባዎቹ የተጠቀሱት ገጀራዎች የተደረሰባቸውና የተያዙት ናቸው። ያልተያዙትስ? እግዚኦ! ማለት ብቻ ነው እንጂ ስላልተያዙት ምን ማለት እንችላለን?

233
233

ስለተያዙት እናውራ። ወሬው አንድ ሚሊዮን ሰው ስለተጨፈጨፈበት ገጀራ የሚባል ሲዖላዊ ብረት ባይሆን ኖሮ የሚያስቅ ነገር ነበረው። ዜናው “ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ መቶ ምናምን ሺህ ገጀራ” ሞጆ ላይ ተያዘ ይላል። ሞጆ ሀገር ውስጥ አይደለም እንዴ? ያውም መሃል ሀገር። ቀይ ባሕር ላይ የያዙት ነው የሚያስመስሉት። የወያኔው አቃቤ ሕግ ኦህዴዳዊው ብርሃኑ ጸጋዬ አውስትራሊያ አምባሳደር ሆነው ሲመደቡ እምቢ እዚህ ጅቡቲ ያለውን ሰውዬ አንሱልኝና እኔ እዚያ ልሁን ብለው የተቀየሩት የገጀራን ጉዳይ እንዲያሳልጡ ነበር እንዴ?

ዐቢይ አህመድ በሩዋንዳ ቆይታቸው ጄኖሳይድን በሀገራቸው እንዳይመጣ ትምህርት ሲቀስሙ የቆዩ ሳይሆን ከሩዋንዳው ጄኖሳይድ እሳቸው ለነበራቸው የኦነጉማ ርዕዮት የሚጠቅሙ እና ለጄኖሳይዱ ሙሉ በሙሉ አለመሳካት ሳንካ የሆኑ ነገሮችን እንዴት መቅረፍና በኢትዮጵያ ከሩዋንዳ የከፋና የተሟላ የዘር ፍጅት ለማካሄድ ትምህርት ሲወስዱ የነበረ የሚያስመስሉ ተግባራዊ ሥራዎችን እየሠሩ ይገኛሉ።

gejera shipmennt mojo 2
gejera shipmennt mojo 2

ኢትዮጵያ የተጓዘችበት የሩዋንዳ መንገድ ባጋጣሚ የያዘችው ሳይሆን በምእራባውያን እና በኛ ባንዶች ሕብረት ሥራዬ ተብሎና በኃይል እንድትሳፈርበት የተደረገ የባቡር ሃዲድ ነው። ሶቪየት ዮኒየን እና ዮጎዝላቪያን ያፈራረሱ ሩዋንዳና ዮጎዝላቪያን ያጨራረሱ ሕገመንግሥትና  አፓርታይዳዊ የጎሳ ክልል ሥርዐት ለሙከራ በሚል ሳይሆን አፍራሽነታቸው በተግባር ታይቶ ነው ኢትዮጵያ ላይ የተዘረጉት። ሥርዐቱ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚኖረው የሚታወቅና ያ ውጤት ተፈልጎ በተግባር ላይ የዋለ ነው። ለዚህም የወደፊት አስፈጻሚ የሚሆኑ ሰዎች በተለያየ መንገድ ሥልጠና ሊደረግላቸው እንደሚችል መጠበቅ ይቻላል። የዐቢይ አህመድም የሩዋንዳ ቆይታና ከበሻሻው ግጭት ጀምሮ ያልተለየው የዘርና የሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋና ጽዳት ተሳትፎ ይህንኑ ያጠናክራል። ያለፉት ሦስት አመታትም ምን ከፍተኛ ጭካኔና ርኩሰት የታየባቸው ቢሆኑ አቢይ አህመድ ላይ ምንም የሐዘን ስሜት ሳይፈጥሩ ማለፋቸው የተያዘው ገና የማማሟቂያ ጭፍጨፋ እንጂ ዋናው ገና ነው የሚል አስደንጋጭ መልእክት እንዲያስተላልፍ አድርጎታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኦሮሞ ምሁር ሚኒልክ ሲገለፁ

gejera shipmennt mojoዐቢይ ወደ ሥልጣን እንደመጡ ሰሞን ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት የፈረንሳይ ጦር ከሥልጠናም ባለፈ የተወሰነ በኢትዮጵያ እንዲሠፍር ፍላጎት ነበራቸው የሚሉ ዘገባዎችን እናስታውሳለን። የፈረንሳይ ሠራዊት እንደሚታወቀው በሩዋንዳው ጭፍጨፋ ጊዜ እንዲጨፈጨፉ የተፈለጉት ቱትሲዎች ሲጨፈጨፉ በዝምታ ሲመለከት ቆይቶ የቱትሲ ጦር ጭፍጨፋውን ሊያስቆም ሲገሰግስ ጣልቃ በመግባት ጭራሽ መንገድ በመዝጋት ጨፍጫፊዎቹ እንዲያመልጡ አድርገዋል። ይቺን በመደመር ካልኩሌተር ስናሰላት የኦነጉማው ሠራዊት ያሻውን እንዲጨፈጭፍ በዝምታ ተመልክቶ ምናልባት ለአጸፋ የሚመጣ ካለ የፈረንሳዩ ሠራዊት ባለው መልካም ተሞክሮ መንገድ ዘግቶ ጨፍጫፊዎቹን እንዲያስመልጥ በማሰብ ይመስላል። የሆኖ ሆኖ ያ ሁሉ ያን ጊዜ ነበር። ገና ሕወሃትም ነብር እያለች። ገና ኦህዴድም ሰላሳ ዙር ሠራዊት ሳያሰለጥን በፊት። አሁን ለጄኖሳይዱ ጭፍጨፋ ገጀራ የታጠቀ ቄሮ ከተለቀቀ በኋላ ገጀራውን በገጀራ እመክታለሁ፣ ጥቃቱን አስቆማለሁ፣ አጸፋም እመልሳለሁ፣ የሚል ከመጣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ሸኔ በመባል የሚታወቀው የኦህዴድ ኢመደበኛ ሠራዊት በዘመናዊ ትጥቅ ድራሹን ለማጥፋትና ጄኖሳይዱን ለማሳለጥ ይችላል። ስለዚህ የፈረንሳይ መሣሪያዎቿ እንጂ ጦሯ ዛሬ ላይ እምብዛም ላያስፈልግ ይችላል።

 

ወደ ገጀራዎቹ ስንመለስ፣ ገጀራ በድሬዳዋ በሐረር ዙሪያ እና አዲስ አበባም አጠገብ ሞጆ ላይ አገር ገጀራ መያዙ ተነግሯል።  የት ገባ? ሠራዊቱ ተረከበው የሚባል ወሬ አለ። መቼ እና ለማን እንዲያድለው ነው ሠራዊቱ የተረከበው? ኦህዴድ የተቆጣጠረው ሠራዊት በዚህ ሰዐት በዘር ተኮር ጭፍጨፋ ጉዳይ የሚታመን እና ገጀራ እንዲጠብቅ አደራ ሊሰጠው የሚችል ነውን?  ምንም ደሃ ብንሆን ከገጀራ ጥቅም በሕይወት መኖር ይበልጥብናል  እና መተማመን በሌለበት በዚህ ወቅት በጊዜያዊነትም ቢሆን መፍትሔ የሚሆነው ገለልተኛ አካላት፣ ያገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ባሉበት ገጀራው ቢቃጠል ወይም ቢወገድ ነው። እርግጥ በዘላቂነት መፍትሔ የሚሆነው አፓርታይዳዊው የገጀራ ሥርዐት መወገዱ እንጂ በሕጋዊ መንገድ ወደ ሃገር የሚገባ በኮንቴነር ሙሉ ገጀራ እየተከታተሉ ማቃጠል ወይም ማስወገድ አይደለም። እስከዚያው ድረስ ግን መሰንበት ስለሚቀድም እነዚህ ልክ እንደሩዋንዳው ለልማት ነው በሚል ሽፋን ለድሬዳዋ ለሐረርና ለአዲስአበባ ሕዝብ አንገት ታስበው የመጡ ገጀራዎች የት እንደገቡ ተጣርቶ የሕዝብ ተወካዮች ባሉበት እንዲወገዱ ጥሪ ማቅረብ ይገባናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንተም ደመቀ መኮንን | ይድረስ ለማውቅህና ለማታውቀኝ የኢትዮጵያ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን | ከአንተነህ መርዕድ

የኛ ሀገር ጋዜጠኞችም እንዲህ ዓይነቱን ከሕዝብ ደህንነት እና የሀገር ህልውና ጋር የተሳሰረ አደገኛ ጉዳይ እስከፍጻሜው እልህ አስጨራሽ ክትትል ማድረግ ይገባቸዋል።

 

 

1 Comment

  1. ገጀራው ግብፅ ኢትዮጵያን ከወረረች ስለሚያስፈልግ ተብሎ ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ሲገዙ ፤ ገጀራውም ለመጠባበቂያ ይሆናል ተብሎ ታስቦ በጣም በርካሽ ገንዘብ እየተገዛ ከሌሎቹ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ጋር አብሮ ከውጭ ተገዝቶ እየመጣ የነበር ነው። አሁን ላይም ሁሉም ገጀራዎቹ በሙሉ በመከላከያ ሠራዊት መጋዘን ይገኛሉ። አንዳንድ ገበሬዎች ቢጠይቁም ገጀራዎቹን ለመዋስ ፤ ገጀራዎቹ ለግብርና እንዳይውሉ ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፍዋል። ከላይ በምስሉ የምታይዋቸው ሰዎች ፎቶግራፉም ፎቶሾፕ ነው እንጂ እውነት አይደለም ፤ እስቲ እውነት ከሆነ በግልፅ መንገድ ላይ እነዚህን ገጀራዎች ይዘው ያሳዩን ፤ ገጀራም ሆነ ጎራዴ መያዝ እኮ እጅግ በጣም ብዙ ባህላዊ ገጀራዎች እና ጎራዴዎች ባሉባት ኢትዮጵያ ውስጥ ህገወጥ አይደለም ፤ ህገወጥ ሆኖ ተደንግጎም አያውቅም ፤ አሁንም ህገወጥ አይደለም ። ህገወጥ የሚሆነው ወንጀል ከተፈፀመበት ብቻ ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.