ሕዝብን የሚያንጓጥጥ፣ የሚሳደብና የሚያስፈራራ ጀብደኛ መሪ – ምሕረት ዘገዬ

abiy 1 ሕዝብን የሚያንጓጥጥ፣ የሚሳደብና የሚያስፈራራ ጀብደኛ መሪ  ምሕረት ዘገዬብዙ ተሳዳቢና አሽሙረኛ መሪዎች በዓለማችን እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ ነገር ግን እንደአቢይ አህመድ በትዕቢት ተወጥሮ አንድን ሕዝብ በስድብ የሚሞልጭና በሾርኒ የሚያስፈራራ ያለ አይመስለኝም፡፡ ለጥጋቡና ዕብሪቱ ወሰን ሊያበጅለት አለመቻሉ የኛንም የሀገራችንንም ዕድለቢስነት ይጠቁማል፡፡ “ለአንድ ክልል ብለን ህግ አንቀይርም” ሲል በዚያን ሥልጣን በያዘበት ሰሞን ከ40 ሚሊዮን የማያንስ ሕዝብ ተሳደበ፤ ንቀቱንም በአደባባይ ገለጠ፡፡ የራሱን ክልል ሚሊሺያ በእንደራሴው በኩል በመቶ ሽዎች በየጊዜው እያሰለጠነና እያስመረቀ ከራሱ ኪስ አውጥቶ የሚመጸውት ይመስል “የምንመድብላችሁን በጀት ለልዩ ኃይል ሥልጠና እያዋላችሁ ምን እናድርግ?” ሲል በአማራ ክልል ተላላኪዎቹ ላይ ተዘባበተ፡፡ ይህ ሁሉ የትዕቢቱን ልክ ማጣት ያሳያል፡፡

ዛሬ ጧት ወደ ሥራ ስገባ መንገዱ ሁሉ በሞንታርቮ ድብልቅልቁ ወጥቷል፡፡ ብልግና ፓርቲ ከፍተኛ ቅስቀሳ ላይ ነው፡፡ በርሀብ አንታጀቸው የታጠፈ ትናንሽ ልጆች ለፈረንካ ሲሉ አይሱዙ የጭነት መኪና ላይ ሆነው ይሄን ጭፈራ ያስነኩታል፡፡ ድምጹ ግን ከተማዋን ክፉኛ እየረበሸ ነው፡፡ ቲያትሩን  ለሚመለከት ሞኝ ታዛቢ ቅስቀሳው እውነት ይመስለው ይሆናል፡፡

እንዲያው ግን ሊቀ ሣጥናኤል ይህን ምርጫ አጥብቆ የፈለገበት ምክንያት ምን ይሆን? ምርጫውን “እንዳሸነፈ” እያወቀ በግንቦቱ ምርጫ ፍጹም ፍትሃዊነት ይህን ያህል ሙጭጭ ማለቱስ የጤና ነው? “ና አይዞህ አልመታህም” አለው አንዱ ለአንዱ፡፡ “አሃ! ‹አልመታህም›ን ምን አመጣው! ይሄኔ ነው መሸሽ” አለና ሮጦ አመለጠው አሉ፡፡ ሊቀ ሣጥናኤል አቢይም አለነገር አይደለም በዚህ ምርጫ ላይ ክችች ያለው፡፡ ከዚያ በኋላ ያሰበልን ከእስካሁኑ የከፋና የከረፋ ዕልቂት እንዳለ መጠርጠር ይገባል፡፡ ለማንኛውም ውጭ ያላችሁ በዚያው ቆዩ፤ ሀገር ውስጥ ያላችሁ ለማይቀረው አርማጌዴዖን ተዘጋጁ፤ በርትታችሁም ጸልዩ፡፡ ቄስና ጳጳስ የለም፡ ፓስተርና ነቢይ የለም፡፡ ሁሉም የሊቀ ሣጥናኤል ተባባሪና አሸርጋጅ ሆኗል፤ ለሥጋው የሚያድረው ከቀን እቀን እየበዛ ነውና ጊዜው የአጭቤዎች መሆኑን እንረዳ፡፡ የመጨረሻው ቀን ሲመጣ ብቸኛው አዋጭ ነገር ወደ ፈጣሪ መዞርና ጭዳ ላለመሆን አቅም በፈቀደ መጠን ተዘጋጅቶ መጠበቅ ነው፡፡ በከተሞች ያላችሁ እርስ በርስ ተነጋገሩ፤ የአደጋ ጊዜ መገናኛ ዘዴን ፍጠሩ፡፡ መንደራችሁን ከፀጉረ ልውጦች ጠብቁ፡፡ ይህ ሰውዬ ይህን ምርጫ ካለፈ በኋላ የወንድሙን የሽመልስ አብዲሣን ንግግር ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ይለውጣል፤ አሁን በግማሽ ልብ ነው፡፡ ኋላ ግን ምርጫውን እንዳሸነፈ አድርጎ ያውጅና የልቡን ለመሥራት ይበልጥ ይመቸዋል፡፡ ያ የፈረደበት “ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ”ም የራሱ ጥቅምና ፍላጎት አይነካ እንጂ በሩዋንዳ አይተነዋል፤ በሶማሊያ አይተነዋል፤ በኢራቅና ሦርያ ለክተነዋል፤ በሊቢያና የመን ገምግመነዋል፤ ሚሊዮን ጥቁር ቢያልቅ ከዝምብም አይቆጥሩን፡፡ የጠ/ሚኒስትር ዊሊያም ውሻ በመኪና ተገጭታ ብትሞት የቢቢሲ መሪ ዜና ነው፤ አቢይ አህመድ አንድ ሚሊዮን አማራ በአንድ ጀምበር ቢጨፈጭፍ ግን ለግርጌ ዜናነትም አይበቃ (news bar)፡፡ የሰውን ልክ የማያውቁ የተማሩ ደደቦች ናቸው፡፡

ሊቀ ሣጥናኤል ምርጫው በሃቅ እንደሚካሄድና ከተሸነፈ ለአሸናፊው ወገን ወንበሩን በክብር እንደሚያስረክብ የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ይመስል ሳይጠየቅ ጭምር እየወተወተ ነው፡፡ ለማያቁህ ታጠን በሉት፡፡ በሀሰት ንግግር ከመለስ ዜናዊ በዕጥፍ የሚበልጠው ይሄ ግልገል እስፊንክሳዊ ጁንታ ምርጫውን አስቀድሞ በልቶታል፡፡ የሚያካሂደው ቅስቀሳ ለይምሰል ነው፡፡ እነኢዜማም ይህን ያውቃሉ፤ ግን ቀብድ ስለበሉ አጃቢነቱን ይቀጥላሉ፡፡ ለኢትዮጵያ የሚበጅ የለም፡፡ ሁሉም ውሸት ነው፡፡

የዚህን እስፊንክስ የውድመት ፓርቲ የሚመርጥ ከእርሱና ጥቂት አጫፋሪዎቹ በስተቀር አንድም ዜጋ አይገኝም፡፡ ወያኔን አስታውሱ፡፡ በ1997 ምርጫ በቤተ መንግሥት ሲጨፍርና ሲደንስ ከነበረው ያ ሁሉ ባለሟል ወያኔ/ኢሕአዲግን የመረጠው 200 ገደማ ብቻ ነበር፡፡ ሰዎች በግልጽ ብታታልላቸው በሥውር ይሠሩልሃል፡፡ ወያኔዎች ያን ክስተት ማመን አቅቷቸው ነበር፡፡

ይህኛው የኦሮሙማ ወያኔም ልክ እንደዚያው ነው፡፡ ይሁንና ይህኛው ከፊተኞቹ ተምሮ ብዙ ነገሮችን ከወዲሁ አስተካክሎ ጨርሷል፡፡ አንደኛ በየትም ሀገር የሌለ በሣምንት ልዩነት ሁለት ምርጫዎች እንዲኖሩ ብኩርናዋን ሸጣ በበላችው ብርቱካን ሚዴቅሣ አማካይነት ትልቅ ሥራ ተሠርቷል – ይህ የዘረኝነት አባዜ ኢትዮጵያን ክፉኛ እየተፈታተናት እንደሆነ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሚገባ እየተረዳሁ መጥቻለሁ፤ ስንትና ስንት የሀገር ዋልታና መከታ የነበሩ የጋራ ልጆቻችን ኤሣውን እየሆኑ ለቁራሽ እንጀራ እየሸጡን ነው፤ በዚያም ምክንያት ለዘመናት ያካበቱትን ማኅበረሰብኣዊ ቅቡልነት (ሶሻል ካፒታል) እያሽቀነጠሩ በመጣል የገማ የዘረኝነት አረንቋ ውስጥ ገብተው መርመጥመጥን መርጠዋል፡፡ ይሄ እነብርቱካን የጽናት ፈተናቸውን የወደቁበት የሁለት ጊዜ ምርጫ ጉዳይ እጅግ አሣፋሪ ነው፡፡ ይህ አካሄድ መራጮች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ውድመት ፓርቲን በተደጋጋሚ እንዲመርጡ ዐይን ያወጣና ይሉኝታን እንዳወጣ ቸብችቦ የበላ ቅጥፈት ነው፤ “ማን ምናባቱ ያመጣል!” ከሚል ትዕቢት የሚመነጭ ዕብሪት ነው – በመራጮች ምዝገባም በግልጽ ታይቷል፡፡ በጊዜ ሂደት ትልቅ ዋጋ ቢያስከፍላቸውም ዕቅዱ ትልቅ ድፍረት የተሞላበት ሕዝብን የመናቅ ውጤት ነው፡፡ ሁለተኛ ሕዝብ እንደማይመርጣቸው በደምብ ያውቃሉ፡፡ ስለሆነም ኮረጆ ገልባጭ ሠራዊት ማዘጋጀታቸው የማይቀር ነው፡፡ ስለዚህ በምርጫው ለውጥ እናያለን ብሎ የሚያስብ ካለ ከትንኝም ያነሰ ጭንቅላት ያለው ጅል ነው ወይም ብአዴንን የመሰለ አጋሰሰና ሆዳም የቤት ውልድ ነው፡፡ አማራ በዚህ ድርጅት እንዴት እንደሚያፍር ይታያችሁ፡፡

ተመልከት – ትግራይ ምርጫ የለም፤ እንኳንስ ምርጫ ሊኖር በሕይወት ለመኖርም በተፈቀደላቸው፡፡ የአማራን ሕዝብ ባለፈው ሰሞን አይተነዋል፤ እሳት ልሶ እሳት ጎርሶ የሊቀ ሣጥናኤልን አጋንንታዊ መንግሥት እንዴት በአደባባይ እንዳዋረደው ታዝበናል፡፡ ከዚያ አካባቢ አንድም ድምጽ እንደማያገኙ ሕዝቡም፣ ሊቀ ሣጥናኤል ራሱም፣ ሎሌዎቹ ብአዴኖችም፣ ለአቅመ ፖለቲካ የደረሰ የመላው ዓለም ዜጋና የምርጫ ታዛቢም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ ብቸኛው የሊቀ ሣጥናኤል የምርጫ ማሸነፊያና የሚጀነንበት መኩራሪያ ብልሃቱ ብልጠቱ ነው፡፡ ይቺን ብልጠቱን ደግሞ የውጭ ጌቶቹም ጠንቅቀው ያውቁለታል – በለበጣ እየሳቁ ሊያውም፡፡  በሥልጣንና በጥቅም አንዴውኑ የታወረ ደግሞ እንኳን የለበጣ ሳቅ ጥይትንም ይቋቋማል፡፡

አማራን በስድብና ንቀት በተሞላበት የማንጓጠጥ ውርጅብኝ እንዴት እንዳጥረገረገው አይታችኋል፡፡ ይህ ሕዝብ በገዛ ገንዘቡ አራት ኪሎ አስቀምጦ የሚቀልበው ይህ ሊቀ ሣጥናኤል “ይህን መንገድ አልፈንበታል፤ በደምብ እናውቀዋለን፡፡ በመንጫጫትና በመጮህ የሚሆን ነገር የለም፤ በምርጫ ብቻ!” እያለ ሲሳደብ ምርጫውን ከጠፈር የመጡ ሰዎች ድምጽ የሚሰጡበት ይመስል በሕዝብ እንዴት እንደቀለደ አስተውለናል፡፡ እንግዲህ በሕዝብ እንዲህ ተሣልቆ ማን ሊመርጠው እንደሚችል ካልተረዳ እኔም እንደሱ ባለጌ እንድሆን ይፈቀድልኝና ይህ ሰው ራሱ ጀዝባና ሰገጤ ባላገር ነው ማለት ነው፡፡ (አንድን የሕዝብ አካል የሆነ ጋዜጠኛ ባለፈው አንድ ቃለ መጠይቁ መድረክ ላይ “ጀዝባ” ብሎ መሳደቡንና ነውረኝነቱ እንዳይታወቅበት ስድቡን “ትቆርጠዋለህ” በማለት ጨዋ ለመምሰል መሞከሩን የምናስታውሰው ነው፤ ግን አንድዬ ምን ዓይነቱን ዱርዬ ሰይጣን ነው የሰጠን!  ትንሽ የርህራሄ መንፈስ ያለው የተሻለ ሰይጣን ፈልጎ አጥቶልን ይሆን ወይንስ የኛ ኃጢኣት ገዝፎ ትልቁን ኃይለ አጋንንት አስፈረደብን? አዎ፣ ለክፉ ሕዝብ እኮ ክፉ መሪ ነው የሚታዘዘው፡፡ ስለዚህ እርሱም ዐረመኔ የሆነው ወዶ ላይሆን ይችላል፡፡)

የትግራይንና የአማራን ምርጫ ያዝክልኝ አይደል? ወደ ኦሮሞው እንሂድ፡፡ ኦሮምያ የሚባለው ግዛት የፍልፈሉም የጃርቱም የአቦሸማኔውም እንደልብ መፈንጫ በመሆኑ እንኳንስ ምርጫ ማካሄድ ቤትን ዘግቶ በሰላም መቀመጥም አልተቻለም፡፡ በዚያ አካባቢ ሜንጫ እንጂ ምርጫ አይታሰብም፡፡ ደቡብን ያየን እንደሆነም ከኦሮሚያው ባልተናነሰ እዚያም ክልል እንደልብ የሚፈነጩት የኦሮሙማ ግልገሎችና ቄሮዎች ናቸው፡፡ እሱንም እንተወው፡፡ ሶማሌና አፋር ዕድሉን ካገኙት ማንን እንደሚመርጡ ግልጽ ነው፡፡ አማራ ወንድም እህቶቻቸውን በጅምላ የሚጨርሰውን የሊቀ ሣጥናኤል የውድመት ፓርቲ እንደማይመርጡ ግን በጣም እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ ቤንሻንጉል ጉሙዝንም እርሱት – ያው በሽመልስ እጅ ሥር ከወደቀ ሰነበተ፡፡ በድብቅ በወጣው ንግግሩም በግልጽ ነግሮናል፡፡

ማን ቀረ? አዲስ አበባና ድሬዳዋ፡፡ ለነዚህ ከተሞችም አንዳች መላ አስቀድሞ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ የነዚህ ከተሞች ሕዝብ ማንን እንደሚመርጥ ስለሚታወቅ በሚሊዮኖች የሚገመት ቀድሞ የተዘጋጀ ድምጽ ይቆጠርና ውድመት ፓርቲ አሸነፈ ይባልልሃል፡፡ ይህ አጭበርባሪ ልዝብ ሰይጣን ሙሉ ጊዜውን የሚያውለው ሸርና ተንኮል በመጠንሰሱ የሤራ ፖለቲካ ላይ በመሆኑ ከዚህ የምርጫ ሽርጉድ በተጓዳኝ ብዙ ግድያዎችና እሥራቶች እንደሚኖሩ ከአሁኑ ብዙ ፍንጮች እየታዩ ነው (“አበረ አዳሙን ያዬ ከአቢይ ጋር ሰፋጣ አይገባም!” ሲሉ ሰማሁ ልበል የፖለቲካ አራዶች?)፡፡ ሰውዬው ልማቱንና የመልካም አስተዳደር ግንባታውን እርግፍ አድርጎ ጥሎ የሌት ከቀን ቅዠቱ በሆነው ሥልጣን ላይ እየተረባረበ ነው፡፡ መላው የሀገሪቱ ሀብትም ለዚህ ሰይጣን የሥልጣንና የቅዠት ትልሞች ስኬታማነት እየተመዠረጠ ለሌላው ለምሣሌ ለህክምና፣ ለትምህርትና ለመንገድ የሚሆን ገንዘብ እየጠፋ ነው፡፡ አንድ ዐይና በአፈር አይጫወትም ነበር፡፡ የአቢይ ኢትዮጵያ ግን ሁለት ዐይኖቿም ጠፍተው በአፈርና በሚጥሚጣ እየተጫወተች ትገኛለች፡፡ ደግነቱ ይህም ያልፋል፡፡ ሲያልፍ ግን እንደዘመን መለወጫ ቀን በፌሽታና በሆታ እንዳይመስልህ፡፡ ብዙ አሣር አብልቶ ነው፡፡ መጪው ዘመን ከብልግና ፓርቲ ጋር ብሩኅ ሣይሆን ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡ ጸሎት ትልቅ መሣሪያ ነው፤ ወጪ ቆጣቢም ነው – ዱዲ አታወጣም፡፡ የሚያስፈልገን ንጹሕ ልብና እንዴት እንደምንጸልይ ማወቅ ብቻ ነው፡፡ ብዙ አፄ በጉልበቱዎች ከተሰቀሉበት የዕብሪት ማማ ወርደው የሚፈጠፈጡት በጦር መሣሪያ ብቻ ሣይሆን በጸሎትና በዕንባም ነው፡፡ ግፍና በደል የበዛበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከክፋት ርቆ በአንድ ልብ ቢጸልይ የነሽመልስ ኦሮሙማ ዕድሜ በሣምንታት የሚቆጠር ነው፡፡ ይህች ታላቅና ታሪካዊት ሀገር ወደቀድሞ ክብሯ መመለሷ አይቀርም፤ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ እኛ ግን ወደፈጣሪ እንመለስ፡፡ ወደፈጣሪ መመለስ ብዙ ጥቅም አለው – ከተነገሩ ውድመቶች ብዙዎቹ ሊለዝቡ ይችላሉ፤ የመከራና የስቃይ ጊዜያት ሊያጥሩ ይችላሉ፤ የጠፉ መልካም ዕሤቶች በቶሎ ሊመለሱ ይችላሉ፤ ራሳቸውን ሳይሆን ሕዝብንና አገርን የሚያስቀድሙ ብልኅና አስተዋይ መሪዎችን ልናገኝ እንችላለን …. ስለዚህ ከመጥፎ ሥራዎች በመቆጠብና እርስ በርስም በመዋደድ፣ አንተ እንትን አንቺ እንትን ከሚለው የዘር ቆጠራና የዘውግ አስተሳሰብም በመቆጠብ ከተጋን ችግራችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ታሪክ እንደሚሆን እንመን፡፡  በል ያለኝን አልኩ፡፡ በቃ፡፡

8 Comments

 1. ልብ ያለው ልብ ይበል! ግሩም ወቅታዊ ትንታኔ ነው፤ ሰሚ ጠፋ እንጅ። ብቻ እግዚኣብሔር ይራዳን።

 2. ሦስት ነጥቦች።
  1። “አልመታህምን ምን አመጣው?’ ሳይሆን “አልበላሽምን ምን አመጣው” ነው፣ ተዋናዮቹምም “አንዱ ላንዱ” ሳይሆን “ጦጣና አንበሳ” ናቸው። ጦጣ ዛፍ ላይ ወጥታበት። አንበሳ “ነይ ዉረጅ አልበላሽም” ሲላት የሰጠችው መልስ ነው።
  2። “………. እንዲኖሩ ብኩርናዋን ሸጣ በበላችው ብርቱካን ሚዴቅሣ አማካይነት ትልቅ ሥራ ተሠርቷል – ይህ የዘረኝነት አባዜ ኢትዮጵያን ክፉኛ እየተፈታተናት እንደሆነ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሚገባ እየተረዳሁ”
  የዘረኝነት የመጨረሻው ጥግ ማለት ይህ ነው። ወጣቶቹ “ነፍ” የሚሉት ዓይነት። ብርቴን ለመወንጀል ብቸኛው ምክንያት የአባቷ ስም “ሚደቅሳ” መሆኑ ነው። “አይ ሰው ያለማወቅ?’ ያለው ማን ነበር? “ቃሌ” የሚለውን ታሪካዊ መጣጥፍዋን ፈልግ/ጊ እና አንብብ/ቢ። እንደው በ44ቱ፣ ብርቴን ለቀቅ!!
  በምርጫ ብቻ!

  • ወንድም ከድር ሰተቴ፦ 3 ነጥቦች ብለህ በ2 መቆምህ አሳስቦኛል – ምነው ሣይጨርሥ በጅምር ተወው?በሚል።
   ሌላው ቀላል ነው። ተረቱን ተወው፥ነገር ማድመቂያ እንጅ ዋናው ጉዳይ እሱ አይደለም። ቢሆንም ተረቶችና አባባሎች የተለያዩ አካባቢያዊ ልዩነቶች እንዳሏቸውም እንረዳ። ከዚህ አንጻር የኔም ያንተም ትክክል ናቸውና በዚህ በኩል ሃሣብ አይግባህ ወንድማለም።
   ሥለብርቱካን ሚዴቅሣ ያነሣኸውም የአሁኗ ብርቱካንና የበላችውን ቃሏን ስትጽፍ የነበረችው ብርቱካን አንድ እንዳልሆኑ የዱሮው አጌናና (ሲሣይ) የአሁኑ አጌና አንድ አለመሆን አንዱ አሥረጅ መሆኑን ኅሊናህ ካልታወረ አንተም ታውቀውለህና የሰውን በሽታ ወደኔ በከንቱ ለማጋባት አትሞክር። ሃቁን ነው የተናገርኩት – ማንም የሚያውቀውንና የሚለውን። ጥፋቴ እውነትን እንዳለች መናገሬ ነው። ይህ ደግሞ 44ቱን ታቦት ካረፉበት የሚቀሰቅሥ ጥፋት አይደለም – ተራ እውነት እንጅ። መማማር ጥሩ ነው፤ “ምርጫ ብቻ!” የምትላት አጃቢ አዝማችህ ግን ደሥ ትላለች፤ የአለቃህ የዘወትር ጸሎት መክፈቻ ናት። ምርጫው ግን አልቋል። የሚቀረው አሸናፊውን ማወጅ ብቻ ነው። ይህን መሠል የቂል ትያትር የሚሠራበት ማኅበረሰብ አባል መሆን ራሱ መፈጠርን ያሥረግማል። አንተ ግን ታድለህ! እውነትን ውኃ በማያሰኝ የወቴ ጫማ እየረጋገጡ በሀሰት ማማ ዧ ብሎ መተኛትና ሃቅን ላለማየት ዐይኔን ግምባር ያ’ርገው ማለት በርግጥም በእንደገና መፈጠር ብቻ ሊገኝ የሚችል መታደል ነው። ምነው አንተን ባ’ረገኝ!

   • ይቺ የ60ዎቹ የማሸማቀቅ ፖለቲካህን ወደዚያ ጣለት። አልፈንበታል! በብርቱካን ላይ ያገኘሀው ጥፋት የአባቷን ስም ብቻ ነው። ዉስጥህ ያለውን የዘረኝነት ጥግ ብ”frustration” መቆጣጠር አቅቶህ ገንፍሎ ወጣ። ለማኛውም በምርጫ ብቻ! ከዚያ ዉጭ ምን አለ? እንደ ጁንታው በጉልበት? አይሆንማ! ቢያንስ አዲስ አበባን እና አማራ ክልልን ህዝብ ካልፈለገ ብልጽግናን በአብን እና ባልደራስ ለመተካት ከፈለገ ሊያስቆመው የሚችል ሃይል የለም። ሰበብ አታብዛ። ህዝብ ጥቅሙን ያውቃል። ዛሬ የረመዳን አካባበርን አየሀው? ሰለሰላም እና ግድባችን ብቻ። ደስ አይልም?
    መቼም፤ ምንም ይሁን፣ በምርጫ ብቻ!

    • ድንጋይ ላይ ውኃ ማፍሰስ ነው የሆነብኝ።
     ምን ያላለፋችሁበት አለ በሦሥት ዓመት ውሥጥ!
     ጥሬ እውነትን መናገር በየትኛው ሂሣብ ነው የ60ዎቹ የ100ዎቹ ማሸማቀቅ ሊሆን የሚችለው ደሞ? የሚሸማቀቅ ነገርሥ አላችሁ ከመነሻው? ገዳይ እኮ ማፈሪያም መደንገጫም አካል የለውም፤ አታናግረኝ እንጂ አብዮቴ!

 3. የኢትዮጵያን መንግስትን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠረው የብልፅግና የፖለቲካ ፓርቲ ልጆችን በከባድ መኪና ጭኖ ሲያስጨፍር የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንዴት ዝም ይላል ? እድሜያቸውስ ለሥራ ብቁ ነውን? የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የሀገር ውስጥ ገቢስ ስለእነዚህ ልጆች ለአደጋ የተጋለጠ የሥራ ቦታ ሁኔታ እንዴት ዝም ይላል? በብልፅግና አሠራር ውስጥ ስለ ህጉን የተከተለ የመቅጠር እና የማሠራት ምሳሌነት ለመሆን አለመካተቱ ምን ይባላል? በአደባባይ እያዞረ እንደአጋሰስ ሲያውረገርግ የደሀ ልጆችን ምነው ዝም ማለታችን?
  የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርስ ምን ይላል ስለየሚጨፍሩት ልጆች ለኮሮና ስለመጋለጣቸው እና ሌላውንም ህብረተሰቡን ለኮሮና ስለማጋለጣቸው? አንድ ልጅ እንኳን ኮሮና ካለበት ፤ ኮቪድ 19 በመኪናው በጠቅላላ ትሰራጭቶ ኮቪድ 19 በተለቀቀበት የሙዚቃ መሳሪያ ስፒከር እየነፉ በርቀት እያስፈነጠሩ ከተማዋን ሲዘዋወሩ ሊውሉ ነው ማለት ነው። ስፒከር እኮ እንደፋን ነው ፤ እየርን ርቀት ያስወነጭፋል ፤ ኮቪድ 19 ያለበት አንድ ሰው ካለ ኮቪድ 19 መኪናው ላይ ያሉ ሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን የሚተላለፈው ፤ ከጭነት መኪናው አልፎ በስፒከሩ ንፋስ በመታገዝ መንገዱ አቅራቢያ ያሉ ህዝቦችንም መበከሉ አይቀሬ ነው። በእዛ ላይ አፍጥር በአደባባይ ሲበላም የሚተላለፈውንም እናስብና ከአንድ ወር በኋላ ጀምሮ ስንት ሰው በመዲናችን እንደሚሞት ታዘቡ ተገንዘቡ። ለትራፊክ አደጋም ስለሚጋለጡት ደናሾች ልጆች እንዴት ዝም ይባላል?
  እድሜያቸው እንኳን ለሥራ ብቁ ነው ብለን ብንገምት ፤የከፍተኛ ድምፅ እያወጣ ካለ ስፒከር አጠገብ ሆነው ኮቪድን ከተነፈሱ፤ ወደ ውጭ ከስፒከሩ በሚወጣው ንፋስ ከፍተኛ ርቀት ደርሶ እየተፈነጠረ የሚጓዘው ኮቪድ 19 በአከባቢው ባለ ሰው ጭምብልንም አልፎ ኮቪድ 19 ሊተላለፍ ይችላል። ስፒከሩ በሚያወጣው ንፋስ ከተማን መበከል ለምን? በቅርቡ አዲስ አበባ በላፍቶ ክፍለከተማ ምርጫ ካርድ የወሰዱት የኦሮሚያ ነዋሪዎች በብልፅግና አይሱዙ ተጭነው ስለመጡ ለማስተባበል? ከኦሮሚያ በብልፅግና ካድሬዎች አይሱዙ ተጭነው መጥተው አዲስ አበባ ላይ ለምምረጥ ለምርጫ የተመዘገቡትን የኦሮሚያ ነዋሪዎች ቄሮዎችን ጉዳይ ለመሸፋፈን የተደረገው ይህ የብልፅግና ዘዴ ፤ ህፃናትን በአይሱዙ እየጫኑ እያስደነሱ በከተማዋ የማዞር የብልፅግናዎች የድንብር ሥራ መዘዙ ብዙ ነው የሚሆነው በአስቸኳይ ካልተገታ።

  • “ በኢትዮጵያ በብዛት የመንግስት ሰራተኛ የሚሰራው 5 ሰዓት እንኳን አይሞላም ” – የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገ/የስ።

 4. አይ ዘመን መኖር ብዙ ያስተዛዝባል ? ህዝብን በማሳነስ ተቃዋሚን ስብእና በመንካት ዐቢይ ከመለስና ከኮሎኔል መንግስቱ በለጠ? ዘመኑ ውሸት የነገሰበት በፕሮፓጋንዳ ሀገርን ለማፍረስ በየአቅጣጫው ጫጫታ የበዛበት ነው:: አማርኛ የሚችል ሁሉ ለመሞጫጨር እድልና መድረክ ያገኘበት የስራፈቶች ዘመን:: አቦ አታደንቁሩን

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.