የዴሞክራሲ ውርጃ፣ ጳጳሱ ታፈኑ! የኦዴፓ ብልፅግና መንግሥት ምሁራንን በ‹‹አሸባሪነትና ፅንፈኛነት›› ከሰሰ! – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

et56
et56

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣  የሐረርወርቅ ጋሻው እና ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ በትግራይ የሚካሄድ የአረመኔዎች ጦርነት ትግራዋይን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ያለመ መሆኑን፣ በኤርትራ ወታደሮች የተደረገውን የአክሱምን ህዝብ ግድያ እንደ ቅጠል የረገፈውን ሰዎች በመግለፃቸው ምክንያት በመንግሥት በተደጋጋሚ ድምፃቸውን እንዳያሰሙ መታፈናቸው ለዓለም አቀፍ ህብረተሰብ በድብቅ የተሠራጨው ቪዲዬ በኢትዮጵያ ያለውን ፀረ-ዴሞክራሲ ተግባር አጋልጦል፡፡

Abune Mathias, who is the Sixth Patriarch and Catholicos of Ethiopia and Archbishop of Axum, also spoke about the Axum massacre perpetrated by Eritrean forces, in powerful words likening the lives lost with “people left over the ground like leaves.” His remarks on the gruesome massacre that took place in Axum over a course of two days marks the first publicly available remark from the highest authority of the Church in its Holiest site, about which “the world is speaking about, but we are denied from doing so.” ……(1)

የኦዴፓ ብልፅግና መንግሥት በዲያስፖራ የሚገኙ ምሁራንን የሐረርወርቅ ጋሻው እና ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ  በአሸባሪነትና ፅንፈኛነት መክሰሱ ታውቆል፡፡የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፣ስድስተኛውንሀገራዊ ምርጫ ለማደነቀፍ በህቡዕ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች እኩይ ሴራ  ማክሸፍ በሚል በሰጡት መግለጫ ታዋቂዎቹን ኢትዮጵያዊያን የሃረርወርቅ ጋሻው እና ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ በአሸባሪነትና ፅንፈኛነት ፈርጀዋል፡፡

የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው ፖለቲከኛ፣ ፓን አፍሪካኒስት፣ የስብዓዊ መብቶች ተሞጋች፣ የስደተኞች መብት ተከራካሪ፣ ተዋናይ፣ ዴሬክተር፣ ፕሮዲዩሰርና ፀሀፊ መሆኖ ይታወቃል፡፡ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ዓለም አቀፍ ሞዴሊስትና ተዋናይ ናት፡፡ Politician PanAfricanist human rights activist advocate for African (Ethiopian) refugee’s rights actress director producer screenwriter. First Ethiopian international model and actress, first Black actress to appear on Dallas CBS Show TAFF Ambassador.

She featured as the first Black woman in the Popular Soap Opera ‘Dallas’. In 1988 she took up a role in a stage play ‘Backstreet’ in Dallas as an African woman married to an African American Hollywood music producer addicted to Drugs. President Bush recognized her campaign for the fight against drugs in a letter. She advanced her Anti-Drug campaign to Africa, meeting with President Mandela and President Mobutu in the 1990……….(2)

  • በ1999እኤአ የሃረር ወርቅ ወደ ኤርትራ በመጎዝ የኤርትራ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን በማግኘት የኢትዮጵያ የጦር ምርከኞች በቀይ መስቀል እርዳታ እውቅና አግኝተው ተፈተው ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ በ2000 እኤአ እስረኞች እንዲፈቱ አድርጋለች፡፡ In 1999, Yeharerwerk traveled to Eritrea and advocated for the freedom of Ethiopian Prisoners of War. After meeting with the President of Eritrea, Isaias Afwerki, in Asmara and shining light on the situation, restrictions on the Red Cross aiding the prisoners made by the Eritrean government were revoked. Due to her efforts, some of the POWs were released in 2000 and the rest in the years to come.
  • የሃረር ወርቅ ጋሻው የፓን አፍሪካኒስት አክቲቪስት በመሆን ለሳውዝ አፍሪካ ሮዲዤያን እና ሞዛምቢክ ነጻነት ትግል አድርጋለች፡፡ በ1990 እኤአ የሃረር ወርቅ ኒልስን ማንዴላንና ማርሻል ሞቡቱ ሴሴ ሴኮን በጎማ አየር ማረፍያ እንድትቀበል በመመረጥ ብሎም የማንዴላ በማጀብ የተለያዩ ቦታዎች በመጎዝ የፓን አፍሪካን አክቲቪስት በመሆን ትልቅ አስተዋፆኦ አድርጋለች፡፡ Yeharerwerk became a Pan-Africanist activist at the age of 12 in Addis Ababa in support of freedom in South Africa, Rhodesia, and Mozambique.[12] In 1990 she was selected to welcome Nelson Mandela by Marshall Mobutu Sese Seko at Goma Airport. While in Goma, she was appointed as Mandela’s assistant. She traveled with Mandela for some time assisting him with translations and organizing his visits within African countries as a Pan-Africanist activist.[13]
  • የሃረር ወርቅ ጋሻው  እንግዳ በመሆን የዛየር መንግሥት ማርሻል ሞቡቱ ሴሴ ሴኮና የአማፂው መሪ ጋር  የሰላምና እርቅ መርሃግብር አካሂዳለች፡፡ Yeharerwerk was the official guest of Zaire, now DR Congo, where she introduced her peace and reconciliation proposal to Marshall Mobutu Sese Seko in order for him and the rebel leaders Laurent-Désiré Kabila, Étienne Tshisekedi, and the rest of the oppositional leaders like Gerard Kamanda wa Kamanda to come together.
  • ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ Democratic constitution for Ethiopia 1996 እኤአ እንዲሁም Constitutional democracy for public self administration ሁለት መፅሃፍቶች ለኢትዮጵያዊያንና ለዓለም ያበረከቱ ምሁር ናቸው፡፡ ‹‹ተከሳሹ ፕሮፌሰር ስለ ክሱ ምን ይላሉ….›› ኢትዮ360 ልዩ ፕሮግራም በዩቲዩቨ ተከታትላችሁ ፍርዳችሁን እንድትሰጡ  እንጠይቃለን፡፡……(3)

 

Getachew Reda /ጃንዩወሪ 19 /በጌታቸው ረዳ፡ የቀረበውን እጭር ትንተና

ከዚህ በታች ያለውን ብታነቡት ትልቁ የኢትዮጵያ ችግሮች አራት ሲሆኑ ዋናዎቹን መሰሮቶቹን በጌታቸው ገለጻ ታዩታላችሁ። መልካም የጥምቀት ቀን እና ለሊት ለሁላችንም። አሜን። ከአክብሮት ጋር።

“በዙ ወጪና ጊዜ የሚሻማ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምሁራን ኢትዮጵያን እንዲያውቋት “ሃ” ብለው እንዲማሩ አዲስ ት/ምህርት ቤት ካልተመሰረተ አለን እያሉ አገሪትዋንም እየናዱ እነሱም በቁም የመፍረሳቸው ክስተት ቀጣይ ነው!”

(የኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው) 1/19/2021

ትንተና በጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethopian Semay

ጥቅስ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ፤ ተወናይና የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊት ዓለም አቀፍ ሞዴሊሰት የሐረር ወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው)

በርዕሱ የተመለከተው ጥቅስ የተናገረቺው ከላይ የተጠቀሰው የሐረር ወርቅ ናት።እንደምናውቀው ከ1966 ዓ፣ም ጀምሮ ወደ ፖለቲካው መድረክ የተከሰቱ የኢትዮጵያ ምሁራን ራሳቸውን ሲያዩበት የነበረው መስተዋት የትምህርት ቤታቸው ዘመናዊው መስተዋት እንጂ ያደጉበት ማሕበረሰብ መስተዋት አራሳቸውን አዋህደው ለመመልከት ሰላልጣሩ በኢስያ፤ በምስራቁና በምዕራቡ አገር የቀሰሙትን ትምህርት ብቻ በመመራት ሕዝባችን እርስ በርስ እንዲገዳደልና እንዲለያይ አድርገዋል።

አስረጅ የተባለ ሎስ አንጀለስ ሲታተም የነበረ የቆየ መጽሔት የኢትዮጵያ ምሁራን ምን እንደሚመስሉ የተነጋገሩትን ጠቅሼ ላስጨብጣችሁ፡ጥቅሱ እንዲህ ይላል፤

የሰሞኑ የሎስ አንጀለስ አካባቢ የኢትዮጵያውያን ውይይት ከኢሕአዴግ እንዴት ዲሞክራሲ ይገኛል የሚለውን ጉዳይ አስመልክቶ ነው። አንዱ የተሟጋች አይነት ‘ከወያኔ ዲሞክራሲ ይገኛል ብሎ ማሰብ ‘ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች እንደደተባለው፤ ነው፡” ብሎ ትችቱን ሊቀጥል ሲያዛጋ አንዱ የኢሕአዴግ ደጋፊ የስብሰባውን ሰብሳቢ ፈቃድ ሳይጠይቅ ከመቅጽበት ብድግ ብሎ “ወንድሜ ንግግርህ ልፊ ያላት ውርንጫ እናትዋን ተከትላ ገበያ ትወጣለች እንደተባለው አይነት ነው፡ ‘ቆለጥ’ አዲስ አበባ ላይ ወደቆ ይገኛልና ሞኝ አትሁን” ብሎ አደናገረው” ይላል መጽሔቱ ከስብሰባው የዘገበው ንግግር፡

እነሆ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ ባለ የእርስበርስ ልፊያ እየገቡ የሕዝቡን መከራ ለ30 አመት አስፍተው አባባሱት።ያኔ ‘ቆለጥ’ አዲስ አበባ ላይ ወደቆ ይገኛልና ሞኝ አትሁን” ያሉት እነሆ ዛሬ ከ30 አመት በሗላ ዝንጀሮ ዋሻ ውስጥ ገብተው በመጫኛና በቃሬዛ እየተጎተቱ ፍጻሜአቸው በእንሰሳት አለም የሚታይ ትራጀዲያዊ ፍጻሜ ሆነው ኢትዮጵያንም በሚያስጨንቅ የገደል ጫፍ አስቀምጠዋት እነሆ ለማመን በሚከብድ “አልጋ ቢሉዋቸው አፈር ተመኝተው” በአስገራሚ ስንብት ተሰናበትዋት። አገራችን እንዲህ ባሉ የምሁራን እንሰሳዎች እየታወከች እስከመቸ እንዲቀጥሉ በቸልተኛነት እንፈቅዳለን? በጣም ጥቂት ሰዎች አገራችን እየተናጋች ነች እያልን ጥቂቶቻችን ስንገልጽ ነበር። የጥቂቶች ድምጽ በማፈን ከፈተኛ ሚና የነበራቸው የዘመናዮቹ ባለሥልጣኖች ብቻ ሳይሆኑ በሚገርም ሁኔታ ከጠላት ጋር እየተሞዳሞዱ አሁን ላለነው አስቸጋሪ ሁኔታ የዳረጉን መሪ ተዋናዮቹ የነበሩት በተቃዋሚው በኩል የተሰለፉ ውጭ አገር የሚኖሩ የፖለቲካ መሪዎችና ብዙዎቹ የተቃዋሚ የዜና ማእከሎች/ሚዲያዎች ናቸው።

በወቅቱ እኔም ሆንኩ የሐረር ወርቅ በተደጋጋሚ ያሰሰብነው ነገር ቢኖር “ለውጥ ከመጣ እኛን የሚታገሉን ዛሬ ከኦነግና ከመሳሰሉ የነ ጃዋር አምላኪ አክረሪ እስላሞች ጋር እየተሞዳሞዱ በየ አዳራሹ ስለ አክራሪዎቹና አገር አፍራሾቹ “ስለ አፍቅሮተ ኢትዮጵያዊነታቸውን” እየሰበኩና እየመሰከሩ የነበሩ ፖለቲከኞችና የድረገጸና የራዲዮን ጋዜጠኞች የዲያስፖራውን ማሕበረስብ እያጃጃሉት ያሉት ክፍሎች ናቸው” ብለን ነበር! ያኔ ገና ይህ ለውጥ ከመታየቱ በፊት ዱሮ! ገና ድሮ!። እነሆ አንዳንዶቹ ወደ ትክክለኛው መንገድ ሲገቡ አንዳንዶቹ ግን አገር ቤት ካለው “ኢ ቲ ቪ” ብሰው የተረኞቹ የውጭ አገር” ኢቲቪ” ቱለቱላዎች ሆነው አረፉት። ይሆናሉ ብለን የተነበይነው ቃል እኛ ያልነው እውን ሆኖ አየናቸው! እነሆ ልክ እንዳልነው “አንዳንዶቹ የአጭባሪዎቹን መጫሚያ ጫማ ሰር ወድቀው”ሥልጣን ላይ እስካሉ እስከመጨረሻ ሕይወቴ አገለግለዎታለሁ” ብለው ቃል ገብተው ሲሳለሙ፤ዛሬ ያ ሁሉ ግፍ እየወረደም ቢሆን “ፈራ ተባ” እያሉ ድፍረት አጥተው ድምጻቸውን ላለማሰማት ድምጽ አልባ “አሽከርነትን” የመረጡ “ሁለቴ የታዩ” ማፈሪያዎች እና እንዲሁም ፤ ከነዚህ ማፈሪያዎች ጋር አብረው በየአገሩ አዳራሾች እየዞሩ ‘ኢትዮጵያ በኮሎኒ ይዛናለች’ ብለው ሲሉ የነበሩት ኦነጎች ሮጠው አገር በመግባት አሁን ላለው የኦሮሙማው መሪ አጋርነታቸው በመግለጽ ተረኛነታቸውን ለማጠናከር የፋሺሰቱ መሪ “የግል አማካሪ” ሆነው፤ እነሆ እኛን ሲያፍኑና የሕዝቡን ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ወደ ጭቃ እየረገጡ፤ የክርስትያን ማተብ በፖሊሶቻው እየበጠሱ እነሆ ሕዝቡ በተረኛው የጅማው አገር በቀል ቅኝ ግዛት መሪ ሥር ወድቆ እነሆ “ለሁለተኛ ዙር” ለዋይታና ለእሪታ ዳረግዋት።

እነሆ ጥቂት የቁርጥ ቀን ልጆች ወደ ወህኒ በተረኞቹ ታፍነው ታስረዋል። አብዛኛዎቹ ምሁራን ተብየዎች ግን ዛሬም ይህ ሁሉ የአገር ውርደት የባሰ ግፍና ልቅሶ እያዩ ጀሮ ዳባ ያሉ ብዙ በሚሊዮኖች ናቸው። ምሁራኖቹ በሕዝባቸው በነገዳቸው እንኳ ልዩ የዘር ጭፍጨፋ ግፍ ሲደርስበት ጭጭ ብለው ለ27 አመት ቃል ያለመተንፈሳቸው ሲገርምን፤ ዛሬም ሕዝቡን በማንቃትና ለዘመናት ሲሰበኩ የነበሩ የጠላቶች የውሸት ፕሮፓጋንዳ በሚያስደንቅ ብስለትና ምርምር ጠላቶቹን በሰላ ብዕሩ ያሸማቀቃቸው አቻምየለህ ታምሩ ከፌስ ቡኩ በተደጋጋሚ በሴራ እንዲታገድ ሲደረግ ምሁራኖች እና የሕግ ጠበቆች ተሰባስበው ይልተማረውን ማሕበረሰብ በመጥራት ፌስ ቡክ ዋና መ/ቤት በመምጣት ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ማድረግ አልቻሉም። እኛ ከምሁራን የምንጠብቀው የነሱ ወደ ግምባር መምጣትና እኛም በጥሪው መሰረት ድምጽ እንድናሰማ እና ሁኔታውም በሕግ እንዲታይ ያደርጉ ይሆናል ብለን ሰንጠባበቅ ዝምታን ለምን እንደመረጡ አስገርሞኛል።

የትግራይ ሕዝብ ማፈሪያ የሆኑ የወያኔ የነ አሉላ ሰለሞን የሩዋንዳ መሳይ ጥሪ በፌስ ቡክ ሲተላለፍ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሕግ እንድንጋፈጠው ጥሪ አቅርቦ አንድም ምሁር መልስ ሳይሰጥ በመቅረቱ ስመለከት እውነትም የዚህ አገር ምሁራን የኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው እንዳለቺው “በዙ ወጪና ጊዜ የሚሻማ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምሁራን ኢትዮጵያን እንዲያውቋት “ሃ” ብለው እንዲማሩ አዲስ ት/ምህርት ቤት ካልተመሰረተ አለን እያሉ አገሪትዋንም እየናዱ እነሱም በቁም የመፍረሳቸው ክስተት ቀጣይ ነው!”

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethopian Semay……..(4)

 

ምንጭ

(Yeharerwerk (YeEthiopiawerk) Gashaw – EverybodyWiki Bios & Wiki)

ESAT Menalesh Meti with prof Abera Meshesha June 29 2019 – YouTube

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.