ኢትዮጲያውያን ሆይ፤ አብይ አሕመድ መቀመቅ እየከታት ያለችውን ሐገራችንን  በቶሎ እናድን! – ከሰርቤሳ ክ.

ከሰርቤሳ ክ.  5th May 2021

abiyየኢትዮጲያ ህዝብ  ያላመታከት አስክፊውን፣ ለ27  አመታት የቆየውን የሕወሓት  አገዛዝ በተለያዩ ያገራችን  ቦታዎች በሰላማዊ መንገድ ታግሏል። በዚህም ብዙዎች ህይውታቸውን ሰውተዋል፣ በመቶ በሺሂዎች ታስረው ተሰቃይተዋል፣ ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ወገኖቻችን  አገራቸውን ለቀው ተሰደው በአለም ማእዘናት ተሰደዋል። ያም ሆኖ ትግሉ ቀጥሎ  መጨረሻው ላይ በኢሕአዴግ ውስጥ ባሉ የኦሮሞ ፖልቲክኞችና በውጭ ሃገር ባሉ የኦሮሞ ሊሂቃን ተነጥቋል። ትግሉም ሕውሃትን ከመአከላዊ ስልጣን አስለቅቆ በቦታው እጅና ጓንት ሁነው ሲሰሩ የነብሩት የአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የኦሮሞ ሊሂቃን ህዝቡ ያልጠበቀውንና ያልገምተውን “ኦሮሙማ”  የሚባል ኦሮሞ ይቅደም የሚል ኦሮሞን በሌሎች ኢትዮጲያውያን ላይ በበላይነት የሚገዛ አዲስ ስርዓእትና አስተሳስብ ይዝው ከተፍ ብለው ለዲሞክራሳዊ፣ ለሁሉ ዜጋ እኩልንት የተድርገውን  የትግል ውጤት ቀምተዋል።

አብዛኛው አትዮጲያውያን በ 2018 (እአአ) የሽግግር መሪ ነን ብልው ባወጁ “መሪዎች” አስመሳይ ንግግርና የሃስት ቃልኪዳን ህዝቡን አጭበርብርዋል። እንደ ቀድምቶቹ ስራዓቶች አላማቸውንና ወገን ጠላቶቻቸውን ለየተው  ሳያስታውቁ  ዋና አላማቸውን ግን  በድብቅ ይዘው በሚያደርጉት ዲስኩር የኢትዮጲያዊነት ስሜቱን እይኮርኮሩ አፈዝ-አደንግዝ ውስጥ በመክተት የራሳቸው የሆነውን ኦሮሙማ  (ኦሮሞ ይቅድም) መሰረቱን በኢትዮጲያ ምድር ተከለዋል። 2016  በለንደንና በአትላንታ ከተማ  ተገናኝተው ያሴሩትን የኦሮሙማ ንድፍ ሃሳብን በኢትዮጲያ በተግባር አሳከተዋል። ዋናው ፍሬ ጉዳዩም በኦሮሞ የበላይነት የምትተዳደር ኢትዮጲያን መፈጠር ውይም ይሄ ካልተሳካ አዲስ ኦሮሚያ የምትባል ነፃ አገር ኢትዮጲያን በማፈርስ መመስርት ነው።

የትም  ሳይደርስ የቆየው 2014-2016  የኦሮሞ ወጣቶች ብቻ ተቃውሞ  ዳር ሊደርስ የቻለውና አስክፊውን የሕወሃት አገዛዝ ያንብረከከው ና ጠቅላይ ሚኒስትሩን  ሓይለማርያም ደሳለኝን  ስልጣን ያስለቀቀው የአማራ ወጣቶች በጎንድር፣ በባህር ዳር ላይ “የኦሮሞ ደም የኔ ደም ነው!  ኦሮሞ ወንድሞቻችንን  አትግደሉ”  ብለው ደረታቸውን  ለጥይት ስጥተው፣ ተሰውተው ሕውሃት የገናባችውን  የዘር ግርግዳ አፍራርሰው፣ በመላ አገሪቱ የትግሉን እሳት በተቀጣጠለ  ግዜ ነው። በሚያሳፍር ሁኔታ ኦሮሞ ኢሓዴጎች ‘የአማራ’ ኢሓዴጎችን አታለው የህውሃትን መንበረ ስልጣኑን በራሳቸው እጅ ማድርጋቸው ብቻ ሳይሆን፤  በውጭ ሃገር ይኖሩ የነበሩ የኦሮሞ ተቃዋሚን ሁሉ ጠርትው፤ በተለይ ብዙ አጥፊ ሰራዊት ያለውን ኦነግ (OLF)  ከነሰራዊቱና መሳሪያው  እንዲሁም መርዝኛ የዘር ጥላቻና ህዝብ ለህዝብ የሚያጋጨውን OMN  የሚባለውን ሚዲያ ያለ ህግ አግባብ አስግብተው  በህብርት ኦሮሙማ የተባል ፋሽስታዊ አምለካከትና አስተሣብ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ተከሉ። ይህንንም ተከትሎ ግዜ ሳይፈጅ በመላ  ሃገሪቱዋ በተለይ በምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማእክላዊ ኢትዮጲያ የንፁኃን ደም ማፍሰስ፣ ማፈናቀል፣ ባስከፊ ሁኔታ ሰው መግደል ዝርፊያ ማድርግ ማቃጠል  በተለይም የኦርቶዶክስ እምንት ተከታዮችን፣ የአማራ ጎሳ ተውላጆችንና ሌሎች  አናሳ ጎሳዎች ላይ መከራ አዝንበዋል።

ብዙ ኢትዮጲያን “የሽግግር መሪዎች” ነን ብለው ያውጁትን ወገኖችን  ጣፋጭ ንግግርን  በመስማት ለ27  አመታት ከወያኔው ጋ ሁነው ህዝቡን ሲያስቃዩና ሲያስሩት የነበሩትን እንዚህን ሰዎች ይቅር ብሎ፤ እምነት ጥሎባቸው ነበር። የትናንቶቹ የልጅ ወታደሮች፣ በኢትዮጲያውያን ላይ ለወያኔ ሲሰልሉ፣ ሲያቃጥሩ የነበሩ፣ ኋላ  ላይ ፖለቲከኛ በሆኑት አደራ በይዎች  ህዝቡን ኢትዮጲያ አገራችን እያሉ አታለው ኦሮሙማን ተከሉበት። ባአለም ዙሪያ ያሉትን የኦሮሞ ሊሂቃን ሁሉ ስብስበው የኦሮሙማን ስውር ደባ ሰርተው ሲያበቁ  ከተወስኑት ጋ ከነ ጃዋርና በቀለ እንዲሁም የተወሰኑ  ኦነጎች ጋ ያደርጉት ጸብ የስልጣን ይግባኛል  እንጂ በኦሩሙማ መሰርትና ሂደት ግን አይደለም።

እነ አብይ የኢትዮጲያን ህዝብ አፍዝ-አድንግዝ ውስጥ በንግግራችው ሲከቱ፤ ጓድኞቻቸው እነ ሽምልስ አብዲሳ ድምጽ ሳያሰሙ ኦሮሙማን መሰርት መሬት ላይ ተክለው ሲያሳድጉት ነበር። ህውሃት ይዛው የነበርውን የስልጣን ወንብር ሁሉ ጠራርገው በኦሮሙማ የሚያሙኑ ካዴሬዎች ተትኩ።ወሳኞቹ የፀጥታ ተቛማት፤ መከላⷋው፤ ደህንንቱን እንዲሁም የፖሊስ ሃይሉን በእጃቸው አስገቡት። ከሁሉ ኢትዮጲያ ከፍል የሚግኝ ጎሳ የሚኖባትን ትልቋን፣ አለም አቀፋዊ ከተማ አዲስ አበባን አብይ አህመድ ህግ ከሚፈቀደው ውጪ  የኦሮሙማ አቅንቃኝ የሆኑትን፤ በመጀምርያ ታከለ ኡማን፣ ቦኋላም አዳነችን ሾሟል። ይህንንም ተከትሎ የከተማዋ አስትዳድሮች፣ የንግድ፣ ኢኮኖሚ ማዋቅሮች ፤ የከተማዋ መሬት፣ ወሳኝ መዋቅሮች  ሁሉ በእጃቸው አስግቡ። በሚያሳፍር ሁኔታ ዛሬ እስር ቤት ጠባቂ ወታድሮቹ ሁሉ ከአንድ ጎሳ የሚወለዱ ኦሮሞውች ናቸው። በ አየር መንግድ፣ ባንኮች እንዲሁም የከተማው አስተዳድር ቦታዎች ሁሉ አዲሶቹ  ተትኪዎች ወረውታል። የኮንዶሚኒይም የጋራ ቤት ፕሮጀክቶችማ ኦሮሙማ ቆርቧል።

ክህውሃት መውደቅ ቦኋላ የሚደርግ ሽግግር ግዜ መፈፀም የነበርባቸው የሚከተሉት ዋና የሽግግር ግዜ ፖለ ቲካዊ ክንውኖች እንዳይደርጉ አብይና ግብራበሮች  ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፤

  • ቤሄራዊ የእርቀና የይቅርታ እንዲሁም የፍርድ ና የህብረትስብ መነጋግር  ጉዳይ ።  በ አብይ አገዛዝ የተከለከለ ፤
  • በትግሉ አስትዋጾ ያለቸውን በኢትዮጲያ ላይ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ ሃይሎችን እንዲሁም ሙሁራኖች፣ ያገር ሽማሌዎችን ያከተተ የሽግግር መንግስት መምስርት ሲገባው አብይና ጓዶች ራሳቸን አሽጋሪ ነን ብለው የህዝቡን ትግል ቀሙት፤
  • ወያኔ በኢትዮጲዋያን ላይ ከፋፍሎ ለመግዛት የተከለውን ህገ-መንግስትን ለመቀየር፣ ለመንጋገር ምንም ጥርት እንዳይደርግ በመከለከል፤
  • ወያን  ከፋፍሎ ለመግዝት ብሎ በዘፍቃድ ያሰመራቸውን ክልሎችንና ድንብሮች አሁንም የብዙ ህዝብ ድም አፍሳሽ ጉዳይን ዞር ባሎ አለማየት፤
  • የጸጥታ መዋቅሩን፣ መከላኪያውን፣ ፖሊስን የፍርድ ቤቱን እንዲሁም ወስኝ ተቋማትን በገለልትኝነት ማዋቀር ሲገባ አብይና ጓዶቹ  ለኦሮሙማ በሚያመች መልኩ ተዋቅⶂል፤
  • እርቅና ይቅርታ እንዲሁም ፍርድና ንግግር ሳይደርግ ወደ ምርጫ መግባት ውሃ-ቅዳ ውሃ-መልስ ቢሆንም የአብይ አገዛዝ ይህንን አድርጎ የሃስትኛ ምርጫ አዘጋጅቶ አሽንፌያለው የህዝብ መንግስት ነኝ ለማለት ተዘጋጅቷል።

ምንም እንኳ አብይና ግብራበሮቹ በጎሳ አልተውቀረም ብለው  ብልፅግና ፓርቲ አቁቁምናል ቢሉም እውነታው ግን የኦሮሙማ ፕርጅክት ማሳኪያ ትልቅ መዋቅር ነው። በዚህም ኦሩሙማ ሃያል  ሆኖ አዲስ ኢትዪጲያ የሃሰት ካባ ለብሶ  ታንኩንና ባንኩን ጥርስና ምላስ ይዞ ቀርቧል።

የኦሮሙማ ድብቅ የወታድራዊ ክንፍ የዘር ማፅዳት ስራ ወያኔው ላግዛዙ እንዲያመቸው ከልሎና አስምሮ በመስርተው ኦሮሚያ በሚባል ኢትዮጲያን ምድር  በማንነታቸው እየትለዩ በተለይም ኦርቶዶክስ ክርስትና  አማኞችን፣የ አማራ ጎሳ ተወልጆችን ባስቃቂ እየገደልና እያፈናቀለ፣ እየዘርፈ፣ ታላቅ የዘር ማጥፋት እርኩስ ድርጊት ላይ ተሰማርቷል። ይህ ወታደራዊ ክንፍ በዞን፣ በክልል አስትዳድርና የጸጥታ ሃይል የሚታግዛ ሲሆን በፌድራሉ የአገር መክላኪያ ባሉ የኦሮሙማ ጄነራሎች በድብቅ የሚታጠቅና የሚርዳ ወታድራዊ ሃይል ነው (የአጣዬውን ውድምት ልብ ይሏል)። ከዚያም አልፎ ተርፎ ከተወስነው ክልል አልፎ ሄዶ ሁሉ እልቂት እይፈፀም፣ ከተማ እያቃጠለ፣ አረምኔ እና ወደር የማይገኝለት ኢ-ሰባዊ ጭከና  እየተፈፀመ ነው። የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑት የተገድሉና የተሰደዱት ብቻ ሳይሆን የሚጠቅሙባቸው ወታዳሮችን አውሬ አድርጎ የሰውነት ባህሪያቸውን እያጠፉ ወደፊት ሁሉ ሊመስርቱት ለሚፍልጉት አገር እንኳን ሰው ሁነው የሚኖሩ እንዳይሆኑ አድርገዋቸዋል።

በጣም የሚያሳዝነው  በመላው የኢትዪጲያ ክፍል የሚገኙ ወገኖች  በተለይም በአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ፣ ሓረር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ አሰላ፣ ዲላ እንዲሁም በሌሎች  ከተማ ያሉ ኢትዮጲያውያን “አማራ ኢትዮጲያዋን ወንድሞቻችን ግድያ ይቁም!  የአማራው ደም ፣ደሜ ነው!”  ብለው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጡ የኦሮሙማ ባለስልጣኖች መክልከላቸው ነው። በተለይ ኢትዮጲያን  የሚወዱ ኦሮሞ ኢትዮጲያንን ከውንድሞቻቸው ሞት ሃዘናቸውን እንድይግልጡ አድርግዋቸዋል።

የኦሮሙማ ሌላው መንፍሳዊ ክፍል ደግሞ የፕሮቲስታንት ክርስትናን በመጠቀም ደጋፊዎቻቸው ባአግር ውስጥም ሆነ በውጪ ያለውን ቤተክርስቲያን ሁሉ በመቆጣጠር የአብይ መንግስት ከአምላክ የመጣ መልኮታዊ በማስመስል የእምንቱ ተከታዮችን  የአብይን መንግስት እንዲደግፉ ወይም ተቃውሞ እንዳያደርጉ ተጠቅሞባቸዋል።  በሚያስድንቅ ሁኔታ ደግሞ በተለያዩ  ውጭ አገራት  ያሉ አዲስ የኢትዮጲያን ስብስብ፣ማህበር፣ አገር አድን ስብስብ ሁሉ እንዚህ የዓብይ ፕሮቲስትንት ተከትዮችና የኦሩሙማ አምኞች የኢትዮጲያን ስም ካባ ለብሰው፣ ተቆጣጥረው የኦሮሙማን መንፍስና ድርጊት በህዝቡ ዘንድ አስራጭተዋል። እጅግ ብዙ ተከታይ  ያላትን የኢትዮጲያን  ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በመከፋፈል ደካማ አድርገውታል።  የእስልምና ሃይማኖት ተከትዮችን ባገራቸው ያልውን ሰቆቃ እንድይቃወሙ በተላያየ ወጥመዶች ይዘዋቸዋል። የሚያሳዝነው ስውር ደባቸው ደሞ ተዋልዶ ተፋቅሮ አብሮ በኖረው የትግራይና የአማራ ኢትዮጲያን ህዝብን በማጣላት፣ በማጋጨት  ያኔ  ወያ ኔ አማራውንና ኦሮሞውን በከፋፍለበት መንገድ አዲሶቹ የኦሮሙማ መሪውች ተክነውበት ወደፊት የተባበረ የህዝብ ተቃውሞ እንዳይገጥማቸው ትልቅ ስራ ሰርተዋል።

የኦሮሙማ መሪዎች በሚስጥር እይተስበሰቡ የሚያድርጉትን እቅድና ተግባርን  “የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት” ሆኖ በህግ ወጥ በአብይ የተሾምው ሽመልስ አብዲሳ ኦሩሙማ ተክታዮቹን ስብስቦ የሚሰሩትንና ያደርጉትን የገለጸባቸው  “አባይ ማዶ ተሻግርን አሳምነን ውይም አጭበርብርን”  “የፖለቲካ ቁማሩን  ጥሩ አድርገን በልተን”;  “አማራ  እየወረደ ኦሮሞ ወደ ላይ እንደወጣ”  ” ከ150  አመት በፊት ነፍጠኞች በሰበሩን ቦታ ሰብርናቸው”  የመሳሰሉትን ንግግርና፤  እንዴት አድርግው አዲሱን የብልፅግና ፓርቲ ለኦሮሙማ በሚያምች መልኩ እንዳቛቛሙት የተነግርውን መስማትና ማምዛዘን፤ ይህ አደገኛ ስብስብ የስልጣን ቁንጮ ላይ ሆኖ አገራችንን ወደ ለየት ያለ መቀመቅ እያወርዳት እንደሆነ ያሳያል። በሚጣፍጡ አማርኛ በማህብራዊ ሚዲያ ላይ የሚነዛ መርዝኛ የዘርና የእልቂት ፖሮፓጋንዳ የብልጽግና ፓርቲ ፕሮፕጋንዲስቱ ታዬ ድንዳአ የሚቀርበውን ማየት እንዴት አድርጎ ብልፅግና ፓርቲ አገራችንን ወዴት እይወስዳት መሆኑን እናያለን።

ዋናው የኦሮሙማ  አስፍፃሚና አድራጊ ፈጣሪው አብይ አህመድ በስልጣን ጥማት የታወርና ያበደ እጅግ አድግኛ ሰው ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ የተነገርውን ንጉስ ትሆናልህ  ትንግርት አምኖ ተዘጋጅቶበት ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ተጥቅሞ የስልጣን መስላሉ ጫፍ ላይ ተቀምⶏል። አብይ አህመድ ስልጣኑን መሎክታዊ ስልጣን አድርጎ  የእብድት እምነት ላይ ያለ ሲሆን  በስልጥኑ ላይ ለሚመጣብት ፈተና ያግሪቱን የፀጥት፣ መከላኪያና ፖሊስ  እንዲሁም የባድ አግር ሃይል ተጥቅሞ ሲመታ፤ ምስኪን ድሃ ኢትዮጲያውያን በማንንታቸው፣ በሃይማኖታቸው ሲጨፈጨፉ ፣ ሲሰደዱ፣ ትላልቅ ከተሞች ሲነዱ፣ ሲጠ ፉ ግን እጁን አጣጥፎ  የተኛ ወይም ይህን ድርጊት ያስፍፀመ ወይም ያመንበት ሰው ነው። በስልጣን እብድቱ መንግድ ላይ የመጣን ጠላትም ይሁን የቅርብ ወዳጅን ከማስወገድ አይምርም። ለዚህም ነው ወዳጆቹ እነ  ጃዋርን፣ በቀለን ፣ እንለማን ከፊቱ ዞሮ ያደርጋቸው።  ሌላውን የስልጣን ተግደርዳሪ ህውሃትን በጦር የገጠመውና የባእድ አገር ሃይል ሁሉ ተጠቅሞ በትግራይ ህዝብ ላይ መከራ የዘነበው።  እነ አሳምነው ፅጌና ዶ/ር አምባቸውን  ጂኔራል ሳእርን ልዮ በሆነ ሴራው ጠልፎ ያጠፋቸው። የኦሮሙማ ሴራውን ከሁሉ አስቅድሞ ያውቀውን ና በሰላማዊ መንግድ ሲቃወም የነበርወን ታዋቂውን ጋዜጠኛና የሰባዓዊ መብት ታጋይ እስክንድር ነጋ ወደ እስር ቤት ለ10ኛ ግዜ ያስገባው።

የሚድንቀው እስካሁን ብዙ  የዋህ ኢትዮጲያን አብይ አህመድን እውነታኛ መሪ አድርገው ይቆጥሩታል። አብይ አህመድ ባለው የንግግር ችሎታና የማይታወቅ የማታለል ክህሎቱ እንዲሁም የትኛውም የኢትዮጲያ መሪ  የማያድርገውን ለየት ያለ የህዝብ ቅርበት የሚምስል ድራማ ችሎታው ብዞዎችን ባድናቆት ሰመምን ውስጥ በመክተት አገራቸውን ከእጃቸው ፈልቅቆ ለኦሮሙማ እያስርክበባቸው መሆኑን አለመርዳታቸው ነው።

ያንድ መሪ ወይም አስትዳድር/አገዛዝ ስኬቱ የሚለካው በውጤቱ ነው።  ባልፉት ሶስት አመታት አገራችን ከድጥ ወድማጡ ነው የገባችው። መከራዋ እየጨመረ፤ ንጽሗን እይተጨፈጨፉ፣ እየተሰደዱ፣ ኢትዮጲያ እያልቀሰች፣ ሴቶችና ህጻናት እየታረዱ፣ ሴቶቻችን አስክፊ ሁኔታ እየተድፈሩ፤ የአገራችን ሉዕላዊነት የተደፈርበት በህዝባችን  መካከል ያለው ግንኙነት የሻከርበት፤ የእምነትና  የጎሳ ግጭቶች በመንግስታዊ ሃይል በመደገፍ ሃይል የሚፍፀመብት የእለት ተእልት ኑሮ ሆኗል። ይህን ሁሉ አብይ በህውሃት፣ግብጽ፣ ኦሌፍ ፣ እንድሁም መጥፎ ብልጽግና አባላት ተይዞ ነው በሚል  ሚዛን የማይደፋ  ፕሮፓጋንዳ  አይናችሁ በመሽፈኑ ይህ ያልታያችሁ የዋህ የአብይ ድጋፊዎች አይናችሁን ክፈቱ፣ ጆሮችሁን አቁሙ፣ አፍንጫችሁን ጠራርጋችሁ በኢትዮጲያ ምድር ያለውን ለቅሶ፣ ዋይታ ሞት እዩት፣ ስሙት  አሽትቱ። አብዛኞቻችሁ ላገራችሁና ለወገናችሁ ቅን ንጹሁ  ፍቅር ያልችሁ ዜጎች ናችሁና ከተኛችሁበት ሰመምን ንቁ።

በይትኛውም የኑሮ መስክ ያለን ኢትዮጲያዋይን ሁሉ፣ የየትኝውም ጎሳ፣ ሃይማኖት፣ፖለቲካ አመለካከት፣ ችሎታ ፣አቅም፣ የትምህርት ደርጃ፣ ጾታ፣ በመሳስሉት ያለን ወንድማምቾች እህትማምቾች ኢትዮጲያውያን ሁሉ፤  አገራችን እጅግ ትልቅ አደጋ ላይ ወድቃለች። “ኦሮሙማ”ወይም “ኦሮሞ ይቅደም” የሚለወን  አይዶሎጂ ስራ ላይ ያዋሉ ስልጣን ላይ ያሉ ወገኖች አገራችንንና ውስጣዊ ትሥስራችንን እይናዱብን ወደጥፋት መንግድ ገብተው ወደጥልቁ  ጨልማ እየግባን ነው። ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በዋና ሹፌርነት የሚዘውሩት  ፈጣን የጥፋት ባቡር ወደ ጥልቁ፣ መውጫ ወደሌለው ገደል በፍጥነት እይተጓዘ ነው። ፍፃሜው መስባብርና ሞት ስልሆነ ይህን የኦሮሙማ መንፍስና ድርጊት በቶሎ ማስቆም አለብን።

አናት፣ አባት፣ ልጅ፣ወንድም፣ እህት፣ አያት፣ አጎት አክስት ወድጅ ጓድኛውን ሁሉ የሚል የሚወድ ኢትዮጲያዊ  ባስቸኳይ ተንጋግርን ይህን እይፈጠነ ገደል የሚገባውን ባቡሩ ማስቆም አለበን። ባስቸኳይ  ተደራጅትን ምትክ የሌላትን አገራችንን እናድን። ለዚህም ለሚድርግ ጥርት ሁሉ እንተባብር።

እግዚሓቤር ህዝባችንና አገራችንን እናድን ዘንድ ይርዳን።

 

 

2 Comments

  1. የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ከተነሱ ሀይላት ጋር አቢይ አሕመድ እየሰራ ነው እያላቹ አዲስ ምክንያት በመፍጠር ኦርቶዶክሳዊያን የሆናቹ ሁሉ ጎሳ ብሄር ጎጥ መንደር ከተማ ሳይገድባቹ ከኛ ጋር ሆናቹ እንታገል ድምፅ እናሰማ እያላቹ እኛን ለመሸንገል የምትደክሙ ካላቹ ጊዜ አታባክኑ ስል ምክሬን እለግሣለሁ፥፥እንደ ክርስቲያን የማንንም ዕልቂት አልመኝም፥እየገደሉን ያሉ ወታደሮች እንኳ በፍርድ እንዲዳኙ ነው የምፈልገው፥፥ሕዝባችንን ምህረት በሌለው ከባለሥልጣናት የተላለፈ ትዕዛዝ ብቻ ሳይሆን በፅንፈኝነትና በጭፍን የብሔር ጥላቻ እየጨፈጨፈና በመጨፍጨፍ ላይ ያለው አብዛኛው የአማራ ፋኖ ና የአማራ ሚሊሻ እኮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኝ ስለመሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፥፥ብልፅግና ነው አቢይ አሕመድ ነው ጦር ያዘመተባቹ አማራ ከተጋሩ ጋር ናቸው ለምትሉ የማስታወስ ችግር ቢኖርባቹ እንኳ የናንተን ከአቢይ ጎን ስለመቆም የሚመሰክሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መጣጥፎች ምን አደከማቹ ኢንተርቴቱ ሳይቀር ያሳብቅባቹኋል፦፦የሚዋጣቹ ነገር እኛ ኮ በሥስት ቀንውሥጥ ጦርነቱን እንጨርሰዋለን ብለን ነው የጀመርነው ብትሉ ምህረት ታገኛላቹ፥፥ማጠፊያው ቢያጥራቹ ኦርቶዶክስ ተነሣ ፥ለሀገር ደህንነት ብሔርተኝነቱን ወደ ጎን ትተን አንድ እንሁን ወዘተ ጭንቀታቹህን መደበቅ የማትችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሳቹ ና የልብ ትርታቹ ከተለመደው ተፈጥሯዊው ሥጉምታ እንዳለፈ ተረዳን ፥፦፦ምንም እንኳን አምላክ ማስተዋሉንና ርህራሄን በውሥጣችን ቢጨምርም የሌላን ወገን ሕማምና ሲቃ ብሎም ሰቆቃውን እንደራሳሽን አድርገን ሊሰማንና ሊያመን የሚያስችል ስሜትን አልተሰጠንም፥፥ ስለሆነም ብዙዎቻችን በትግራይ ፥በኦሮሚያ ና በሌላው ክልል እየተፈፀመ ስለነበረውና አሁን ስላለው ሰብዊነት የጎደለው ግፍና የጅምላ ዕልቂት የእያንዳንችን በር እስካስከፈተበት ቀናት በፊት ጦርነቱን ከገንዘብ አንስቶ እስከ ደም ልገሳ አልፍም ልጆቻችንን ክቡር ሂወታቸውን ለ ብልፅግና አመራር ሀላፊዎች ሲገብሩ ቆይተዋል፥፥ ብልፅግናን የሚያስከዳ ኦርቶዶክስን እንደ ሽፋን ለመጠቀም የሚያስገድድ ታዳያ አሁን ምን ተገኘ?? ድሮም ተጋሩ እኮ ኦርቶዶክስ ነበሩ ፋኖንና የአማራ ሚሊሻ ስታዘምቱብን ኦርቶዶክስ መሳይ በሸንጎ በግ መሳይ ተኩላ ሆናቹሁብን እኮ ጃል !! አምላክ ብቻ የሰማዩን ነገር ያቅልላቹ ግራና ቀኙን የማያውቁ ልጆቻችንን ሕፃናትን፥ አባቶች ካህናትን ና መነኮሳትን እናቶቻችንና እህቶቻችን መነኮሳይያት ሴት ወይዛዝርትን ስትገድሉና ስትደፍሩ ፥ቤተክርስቲያናትንና ገዳማትን ስትዘርፉና ስታቃጥሉ እኛ ከአሁን ወዲያ የኦርቶዶክስን ካባ እንደ በግ ለምድ ካጠለቀ ኦርቶዶክስ መሳይ ጋር እንዳንተባበር መፅሐፍም ይከለክለናል፥፥በራድና ትኩስ ያልሆነ አንዴ ከፀረ ክርስትና ሀይላት ጋር አቅም ባነሰው ጊዜ ደግሞ ኦርቶዶክስ ነኝ ከሚል ጋር ሕዝባችንን ዳግመኛ አብሮ እንዲኖር አንገፋፋም : ደህንነቱ ተጠብቆ በሰላም እንዲኖር የሚችልበት የሚያስችል ዋስትና የለውም፥በሰላማዊ መንገድ ከኦርቶዶክስ መሰል ፀረ ክርስትና ከሆናችሁት መራቅ ብቻ ነው የሚመከረው ፥፥
    ንፁሓንን ብቻ ዘር ጎሣ የማይለይ አምላክ ነፃ ያውጣልን እናንተ ደግሞ ልሂቃኑና ጦር የሰበቃቹሁብንን ለፍርድ የምትቀርቡበትን መንገድ ይፍጠርልን፥፥ትግራይ በሀይለ አምላክ ትሥዕር አሜን !!! Ethiopia is in exile and soon gonna be destroyed !Where do amhara elites and mahibrekidusan gonna hide !please suggets a hideout for these goons!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.