እጩዎች በምርጫና በሜንጫ ይከላሉ!!! የኮነሬል አብይ የጦር አበጋዝ መንግሥት በዓለም መንግሥታት ይገለላል!!! – ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

et677‹‹ማን ፈርሚ አለሺ፣ ማን ምረጪ አለሺ
በነጩ ወረቀት፣በአለንጋው ጣትሺ!!!››

የኮነሬል አብይ የጦር አበጋዝ መንግሥት በምርጫም በሜንጫም የ2013ዓም ስድስተኛውን ዙር ምርጫ  አሸንፎል፣ ለኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ የአምስት ዓመት የሥልጣን ኮንትራት ህዝብ አልሠጥም ብሎል!!!በምርጫም በሜንጫም Ballot and Bullet

ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ 2432 ዕጩዎችን በማስመዝገብ የስድስተኛውን የኢትዮጵያ ምርጫ ማሸነፉን አረጋግጦል፡፡

የይስሙላ ምርጫው ለኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ የአምስት ዓመት የሥልጣን ኮንትራት ውል እንድንሠጥ ነው  እየተጠየቅን ያለንው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና ጠወዳዳሪ ፓርቲዎች ያለውን ሁኔታ ገምግማችሁ በምርጫው መሳተፍ ወይም አለመሳተፍችሁን በጋራ በመወያየት ለህዝብ አቆማችሁን ማሳወቅ ይጠበቅባችኃል፡፡ ለኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ለሚቀጥለው አምስት አመት እንዲገዛን በትረ ሥልጣኑን ፈርመን ከሠጠን፣ የኦሮሚያ ጂኦ ፖለቲካ ካርታ በኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ መልክ ይሠፋል፣ በምርጫው ብልፅግናን ከመረጥክ አንተም አንቺም ተስማምታችኃል ማለት ነው፡፡ ማን ፈርሚ አለሺ ማን ምረጪ አለሺ!!! የሶስቱ ዕጩዎች ድምር 4390 ሲሆን በመቶኛ ስናሰላው አሸናፊው ፓርቲ ኦዴፓ ብልፅግና ሲሆን አሮሮጮቹ (Pacemakers) ደግማ ሁለተኛው መናጆ  ኢዜማ ሦስተኛው መናጆ እናት ፓርቲ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

ለህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ጠቅላላ ወንበር ብዛት 547 ሲሆን ለክልል ምክር ቤቶች ጠቅላላ ወንበር ብዛት 1,900  ለሁለቱ ምክር ቤት 2447 (ሁለት ሽህ አራት መቶ አርባ ሰባት) እጩዋች ማቅረብ ተወዳዳሪዎች ይጠበቅባቸዋል፡፡

 • ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ከ2447 (ሁለት ሽህ አራት መቶ አርባ ሰባት) ለሁለቱ ምክር ቤት (ለፌዴራልና ለክልል) ማቅረብ ከሚጠበቅበት ውስጥ 2432 (ሁለት ሽህ አራት መቶ ሠላሳ ሁለት) ዕጩዎችን በማስመዝገብ ማለትም 99.4 (ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ አራት) በመቶ የምርጫ ዕጩዋችን አቅርቦል፡፡ በዚህም መሠረት የስድስተኛውን የኢትዮጵያ ምርጫ ማሸነፉን አረጋግጦል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ በምርጫው አሸናፊ መሆኑን ከምርጫው በፊት አረጋግጦል፡፡
 • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)  ከ2447 ለሁለቱ ምክር ቤት (ለፌዴራልና ለክልል) ማቅረብ ከሚጠበቅበት ውስጥ 1385 (አንድ ሽህ ሶስት መቶሰማንያ አምስት) ዕጩዎችን ብቻ በማቅረብ ማለትም 56.6 (ሃምሳ ስድስት ነጥብ ስድስት) በመቶ የምርጫ ዕጩዋችን ብቻ በማቅረብ ተሸናፊነቱን አረጋግጦል፡
 • እናት ፓርቲ ደግሞ ለሁለቱ ምክር ቤት (ለፌዴራልና ለክልል) ማቅረብ ከሚጠበቅበት 2447 ውስጥ 573 ዕጩዎችን ብቻ ማለትም 4 (ሃያ ሦስት ነጥብ አራት) በመቶ የምርጫ ዕጩዋችን ብቻ በማቅረብ በመዘረር ተሸናፊነቱን አረጋግጦል፡
 • ኢዜማና እናት ፓርቲ ዕጩዎች ተደምረው 1958 ሲሆኑ ብልፅግና ዕጩዎች 2432 በመሆኑ በ474 ዕጩዎች ይበልጣል፡፡ ስለዚህ በዕጩዎች ብዛት ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በፎርፌ አሸናፊ መሆኑን ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ የሚታረደው ህዝብ በዚህ ምርጫ የሚፈለገው አራጁን ለማንገስ ነው እንላለን፡፡ ካለዛ በምርጫው ብንሳተፍም ባንሳተፍም ተሸንፈን በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ለሚቀጥለው አምስት አመታት ‹‹ማን ፈርሚ አለሺ፣ ማን ምረጪ አለሺ….በነጩ ወረቀት፣በአለንጋው ጣትሺ!!!›› እያለ ይዘፍንልናል፡፡

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 50 ሚሊዮን መራጮች 18 ሚሊዮን ብቻ በመመዝገብ ምርጫውን ከወዲሁ አክሽፎታል!!!

የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይህን በመረዳት ከምርጫ መሳተፍ የሚገኘውን ጥቅምና ጉዳት በማመዛዘን ከምርጫው መውጣት ጠቄሜታው ስለሚያመዝን የኮነሬል አብይ አህመድ መንግስት እውቅና በመንሳት ለዓለም ህብረተሰብ በማጋለጥ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡፡  የአውሮፓ ህብረትና የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ መንግሥት  የብርድ የእርዳታ ተዓቅቦ አድርገውበታል፡፡ ሃገራችን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ሊደረግባት ይችላል እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 50 ሚሊዮን ሰዎች በመራጭነት ይመዘገባሉ ተብሎ 18 ሚሊዩን መራጮች ብቻ ተመዝግበዋል፡፡(ከመጋቢት 16/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል ሐሙስ ሚያዝያ 14/2013 ዓ.ም ድረስ 18 ሚልዮን 427 ሺህ 239 ዜጎች የተመዘገቡ ሲሆን 41,659 ምርጫ ጣቢያዎች መራጮችን እየመዘገቡ እንደሚገኙ ተገልጿል።  በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የመራጮች ምዝገባ አርብ ሚያዝያ 15/2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት ነበር። የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እንደተናገሩት በተለያዩ ክልሎች ተከፍተው ድምጽ ሰጪዎችን ይመዘግባሉ ተብለው ከታቀዱት 50 ሺህ ያህል የምርጫ ጣቢያዎች መካከል ምዝገባ እያካሄዱ የነበሩት ግማሽ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን ተናግረው ነበር። ምርጫው ከወዲሁ መክሸፉ በዚህ መረጃ መሠረት ታውቆል ተፎካካሪ ፓርቲዎች የመራጩን ህዝብ የልብ ትርታ አዳምጣችሁ ውሳኔችሁን አሳውቁ፡፡

በምርጫው ከሚሳተፉት 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማቅረብ በኩል ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ቀዳሚ ደረጃን ይዟል። ከብልጽግና በመከተል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች ያስመዘገቡት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና እናት ፓርቲ ናቸው። ሦስቱን ፓርቲዎች ጨምሮ በምርጫው ለመወዳደር በፓርቲና በግል ለመወዳደር ከስምንት ሺህ ሁለት መቶ በላይ ዕጩዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።››       (1)

 

የኦሮሚያ ክልላዊ  መንግሥት መር ሽብርተኛነት

‹‹የኦሮሚያ ህጻናት ወታደራዊ ሥልጠናው ተጠናክሮ ቀጥሏል…*…… ዐማራ የአያትህን ጡት ቆርጧል፣ ዐማራ ስታይ እንዳታልፈው ግደል፣ ሚኒልክ መሬትህን ወርሮ ይዟል፣ ለማስለቀቅ ታገል። ደሃ የሆንከው በሰፋሪ ምክንያት ነው፣ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ቄስ፣ ዲያቆን መነኩሴ፣ አማኝ ስታገኝ አትለፈው። እረድ! ዐማራ ሆኖ እስላም የሆነም ስታገኝ ጨፍጭፈው፣ ለዘር እንዳታስቀር! አንተ ኢትዮጵያዊ አይደለህም! ተብሎ የጥላቻ መርዝ እየተጋቱ ከሚያድጉ ህጻናት  ከአራጅ ሌላ ምን ሊሆንላችሁ ፈልጋችሁ ኑሯል?  …… በትግራዩ ጦርነት የሚማረኩ የትግሬ ህጻናት ወታደሮች ቆስለው እንኳ ህክምና እየተደረገላቸው ምግብ ሲቀርብላቸው አሻፈረኝ ይሉ እንደነበር ሰምተናል። ምክንያታቸውም በጦርነቱ ቆስላችሁ ከተማረካችሁ ” በመርዝ ” ይፈጇችኋል ተብለው ፀረ ዐማራ ሥልጠና ስለተሰጣቸው ነው። ሃኪሞች ምግብ እየቀመሱ ነው ታካሚዎቹን ሲያበሏቸው የከረሙት።

… በኦሮሚያና በትግራይ ለዘመናት የተዘራው ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ትርክት አድጎ እና ጎምርቶ፣ አሽቶም ፍሬአፍርቶ ለዚህ ደርሷል። እነ ሽመልስ አብዲሳም የዚሁ ፍሬ ውጤቶች ናቸው። ” ሸረሪቷን ገድለናታል። የሚቀረን የሸረሪቷን ድር ማጽዳት ነው” አይደል ያለው። … አንዳንዱ ምስኪን ዐማራ የኦሮሚያ ፖሊስ ሲያይ ሩጦ ‘አድነኝ ” ይለዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ምላሽም  ‘ነፍጠኛ ልጠብቅ አይደለም የቆምኩት…”  “ኦሮሞ ኦሮሞን አይገልም” አለ ዐቢይ አሕመድ…… በኦሮሚያም በኢትዮጵያም የምትኖሩ ዐማሮች ግን ፈጣሪ ይሁናችሁ።›› (2)

ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ የምትመርጠው ምን ስለሠራ ነው?

ከመጋቢት ሃያ አራት 2010 እስከ 2013ዓ/ም  ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ መሪ የዶክተር አብይ አህመድ አገዛዝ ዘመን ምድሪቶ በደም ታጠበች፣ በህይወት የመኖር መብት ጠፋ ጣረ-ሞት በኢትዮጵያ እንዳንጃበበ ይገኛል፡፡

 • ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ካማሽ፣ መተከልና አሶሳ ዞኖች ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም ውስጥ 750 ሰዎች ስጋቸው ተበልቶል ደማቸው ተጠጥቶል፣ 265405 የአማራ ህዝብ ብዛት የነበረ ሲሆን በሦስት አመታት ውስጥ 221347  አማራዎች ተፈናቅለዋል፣ 2581 ተገድለዋል፣ 905 የቆሰሉ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 40572 አማራዎች በክልሉ ውስጥ ይኖራሉ፡፡
 • በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወለጋ፣ አርሲ ዞን፣ባሌ፣ ኢሉባቡር፣ ጅማ፣ ዝዋይ ኢተያ ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም 2465 ሰዎች ተገድለዋል፣ 1905 ሰዎች ቆስለዋል፣ 839645 ሰዎች ተፈናቅለዋል
 • በደቡብ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም 641 ሰዎች ተገድለዋል፣ 209 ሰዎች ቆስለዋል፣ 105000ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ (3)
 • በትግራይ ክልላዊ መንግስት 52000 ሰዎች ተገድለዋል፣ ሦስት ሽህ ሃያ አራት ህፃናት ወላጆቻቸው እንደጠፉባቸው እንዲሁም ስምንት መቶ ሴቶች ተደፍረዋል፣ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ በትግራየይ የገጠር ከተማዎች ነዋሪዎች መሠረታዊ አቅርቦቶች እንደማይደርሳቸው ዩኒሲኤፍ ሪፖርት አድርጎል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ  መንግሥት መር ሽብርተኛነት

‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ›  በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኜ፣ በዝዋይና በባሌ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የተካሄደው ጥቃት፣ ባመዛኙ የአማራና ሌሎችንም “መጤ” ተብለው የተሰየሙ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞችንና የዕምነት ቤቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው።

ትንቢተ ኦሮሙማ ዕቅድ በአምስቱ ዓመታት እንዲፈፀሙ ትፈቅዳላችሁ?

ሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ አንድም ሦስትም ናቸው!!! ኢትዮጵያን ለዘመናት ለማፍረስ በጋራ የነደፉት የትግል ስልት  አንኳሮቹ ውስጥ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ኤርትራን፣ ትግራይን ኦሮሞን ደቡብ ኢትዮጵያን፣ ሱማሌን፣ አፋርን፣ ቤኒሻንጉልን፣ ጋምቤላን፣ ወዘተ በቅኝ ግዛትነት ገዝታለች ስለዚህ ነው በፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል ያደረግነው ይላሉ፡፡ በዚህም መሠረት በዘር ላይ የተመሠረተ ነፃ አውጪ ድርጅቶች በመመሥረት በሃገሪቱ የጦር አበጋዞች መንግሥት የተፈለፈሉት፡፡ የጦር አበጋዞቹ ድንበር የማስፋፋት ፖሊሲ ስትራቴጂና ታክቲክ ሃገሪቱን ወደማያባራ ጦርነት ውስጥ ከቷል እንላለን፡፡ አቶ አያሌው መንገሻ የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የደህንነት ሹም የነበሩ (ቪዲዬውን ይመልከቱት) ከህብር ራዴዬ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ  የተገኘ መረጃ መሠረት፡-

ሌንጮ ለታ፣ ሌንጮ ባቲ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ግርማ ብሩ፣አብይ አህመድ፣ አባዱላ ገመዳ፣ታዬ ደንደአ፣አዲሱ አረጋ የሻሸመኔ፣ የመተከል፣ የወለጋ፣ የሰሜን ሸዋ  የአማራ አራጆች ለፍርድ ይቅረቡ!!!  እነዚህ አዲሶቹ የኦሮሚያ ሹማምንቶች በኢትዮጵያን ሃገረ መንግሥት በአንድ በኩል በህጋዊነት እየገዙ በሌላ በኩል በህገወጥነት ውስጥ ውስጡን በመንግስት ውስጥ ስውር መንግሥት በማቌቌም ህጋዊ ያልሆነ የግንኙነት መረብ በመዘርጋት በዘር ላይ የተመሠረተ አደረጃጀት፣ አንድ ለአምስት በማደራጀት የኦነግን ኦሮሙማ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፍኖተ-ካርታ ዘርግተው በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኦሮሚያ ከልልን በሁሉም አቅጣጫ በማስፋፋት አዲሱን የኦሮሙማ ካርታ ከትግራይ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ሀረሪ፣ ድሬዳዋ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እስከ ኬንያ የሚዘልቅ መሆኑን ካርታውን ከላይ ማየት ይቻላል፡፡ “Deep State:-A deep state is a type of governance made up of potentially secret and unauthorised networks of power operating independently of a state’s political leadership in pursuit of their own agenda and goals.” Wikipedia የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) የኦሮሞ ህዝብን በስብዓዊ ጋሻነት አፍኖ በመያዝ ሰው በማረድ፣ ህፃናት በመግደል፣ ሴት በመድፈር፣ ህዝብ በማፈናቀል ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ፈፅመዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የኦነግ ማፍያ ቡድን ሊታገለው ይገባል እንላለን፡፡

 

ከምርጫ በኃላ ኦሮሙማና የህገመንግስት ማሻሻያ አይኖርም  (ብልፅግና አንቀፅ 39 አይሻርም!!!) 

‹‹የኢትዮጵያ የሰላም ችግር ምንጩ፣ የአገሪቱ ህገ-መንግስት የፈጠረዉ የፖለቲካና የአስተዳደር ስርአት ነዉ። ሌሎች የሚደረደሩ ምክንያቶች ቢኖሩ አንድም ማደናገሪያ ናቸዉ፣ ሌላም ሚናቸዉ ዉስን ነዉ። መፍትሄዉ ግን በአጭርና በረጅም ጊዜ ተከፍሎ የሚደረግ መሆን ይኖርበታል። በረጅሙ ጊዜ (ከምርጫ በኋላ በሚኖሩ አመታት) ህገ-መንግስቱ መቀየር/መከለስ ለዘላቂ ሰላም በቸኛዉ አማራጭ ነዉ። ይህን ተልእኮ ጠ/ሚሩም ሆነ የሚመራዉ የብልጽግና ፓርቲ ይፈጽመዋል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። በህገ-መንግስቱ ጉዳይ ላይ ያላቸዉ አቋም ከህወሃት-ኢህአድግ የተለዬ እንዳልሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። ስለዚህ የህገ-መንግስት ለዉጥ ለማየት የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ምርጫቸዉን ከዚያ አንፃር ያደርጋሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ያም ሆነ ይህ፣ የህገ-መንግስት ማሻሻያ ዛሬ የሚደረገዉን የግፍ ግድያ ዉድመትና ዋይታ ለማስቆምና የአገሪቱን ህልዉና ከስጋት ለመታደግ አይደርስም። አሁን የሚያስፈልገዉ፣ መንግስት አሁን ባለዉ ህገመንግስት ጭምር የተደነገገዉን ሰላምን የማስከበር ሃላፊነቱ በአግባቡ ለመወጣት መቻሉ ነዉ። ስሞታና ወቀሳዉም ይህን ኃላፊነት መንግስት እየተወጣ አይደለም የሚል ነዉ።››       (4)

 • ‹‹በትግራይ ስላለዉ ጦርነት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያዉቀዉ ጦርነቱ በሶስት ሳምንታት የተቋጨ መሆኑን ነበር። በቅርቡ ግን ያ ቀርቶ ጦርነቱ በስምንት ረድፍ እንደቀጠለ ጄ/ል ባጫ ደበሌ ገልጿል። ከሁሉም በላይ የትግራይ ወጣት ልብ መሸፈትና የተረፉ የህወሃት ተዋጊ ሃይሎችን ለመቀላቀል መፈለጉ የሰብአዊ ቀዉሱንና የወገን ስቃይ ያራዝመዋል፣ ከዉጭ ጫና ለመፍጠር ለሚያቆበቁቡ ኃይሎችም መልካም ሰበብ ይሆናል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የጠ/ሚሩ ወይም የመንግስት ክፍተት ጦርነቱ ስላለበት ሁኔታና በተለይም የትግራይ ህዝብ እያለፈበት ስላለዉ ችግር ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰጡት መግለጫ አለመኖሩ ነዉ። ጦርነቱ በትግራይ ህዝብና በሌላዉ ኢትዮጵያዊ መካከል የፈጠረዉን መራራቅ መካድ አይቻልም። ይህ መራራቅና መቃቃር ጊዜያዊ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ምንም ይሁን ምን፣ የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ አካልና የነፍስ ክፋይ ስለሆነ፣ ያ ህዝብ ስለሚያልፍበት ሁኔታና ቀጣይ ምልከታዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ማስረዳት የጠ/ሚሩ ኃላፊነት ነዉ። ያን ሃላፊነት ግን በአግባቡ እየተወጣ ነዉ ማለት አይቻልም።››
 • ‹‹ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ የወልቃይትና የራያን እጣ ፋንታ ለመወሰን ለጊዜዉ መንግስት እየሄደበት ያለዉ አቅጣጫም ቀደም ሲል ህወሃት/ኢህአዲግ ያሰመረዉ አቅጣጫ ስለሆነ፣ ዉሎ አድሮ የሚፈነዳ ቦምብ እንደሆነ መገመት ቀላል ነዉ። ከትግራይ ዉጭ በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ያለዉ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ እየተሻለዉ ሳይሆን እየባሰበት እንደመጣ ከጠ/ሚሩ ዉጭ ሁሉም ልብ የሚለዉ ይመስለኛል። ባለፉት ስድስት ወራት እንኳ በምእራብና ምስራቅ ወለጋ፣ በመተከል፣ በቻግኒ፣ በጉራ ፈርዳ፣ አሁን ሰሞኑን ደግሞ በአጣየና አጎራባች ከተሞች የተፈጸሙት ግድያዎች፣ የንብረት ዉድመቶች፣ መፈናቀሎችና የንጹህ ኢትዮጵያዉያን ስቃዮች በእዉነት የደህንነትና የጦር ሃይል ያለዉ መንግስት በሚኖርበት አገር ይፈጠራል ብሎ ለመገመት ይቻላል። ሁሉም ቦታዎች ሊባል በሚችል መልኩ የተፈጠረዉ እልቂት የመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑን ልብ ስንል ደግሞ በመንግስት ላይ የሚደረገዉን ወቀሳና ሂስ ይበልጥ አግባብ ያለዉ ያደርገዋል።››
 • ‹‹ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከጎጃምና ወለጋ በተወሰደ መሬት ህወሃት-ወያኔ የፈጠረዉ ክልል ነዉ። በዚህ ክልል የሚገደሉት የአማራ፣ የአገዉና የሺናሻ ማህበረሰቦች በቁጥር አናሳ አይደሉም። ገዳዮቹ ወጡበት ከሚባለዉ የጉሙዝ ብሄረሰብ ጋር ሲወዳደር የአማራዉ ቁጥር ከፍተኛ ነዉ። ግድያ አድራጊዎቹ በቁጥር የበዙት ላይ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋና ማፈናቀል የሚያደርጉት የክልሉ መስተዳድር በግልጽም ሆነ በድብቅ በሚያደርገዉ ድጋፍ እንደሆነ ብዙ ማስረጃ ቀርቧል። ወቀሳዉ የፌዴራል መንግስቱ አስቸኳይ እርምጃ በመዉሰድ ተጠቂዎችን ከተቀነባበረ ግድያ ሊታደጋቸዉ አልቻለም የሚል ነዉ። አግባብም ያለዉ ወቀሳ ነዉ። የመንግስት ዳተኝነት ሰዎች በቀልን በእጃቸዉ ዉስጥ እንዲያስገቡ በማድረግ በቅርቡ በቻግኒ የታየዉ አይነት ጸያፍ የደቦ ፍርድ እንዲታይ ያደርጋል።››
 • ‹‹በኦሮሚያ ለሶስት አመታት የዘለቀዉ የኦሮሞ ብሄረተኞች ተግዳሮት የጠ/ሚሩ የአመራር ድክመት ዋናዉ መገለጫ ነዉ ማለት ይቻላል። የዛሬ አንድ አመት ግድም በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ በጅማ፣ በአሩሲ ነገሌና ሌሎች ቦታዎች በተመሳሳይ ወቅት የደረሰዉ መጠነ ሰፊ ግድያ፣ የሰዉ ጉዳትና የንብረት መዉደም በታሪክ ሊረሳ የሚችል አይደለም። ታዲያ ያን ያዬ መሪና መንግስት፣ ሰሞኑን በአጣዬ ከተማ ላይ ከወረደዉ ጥፋት እጁን እንደጲላጦስ አጥቦ ወንጀሉን ሁሉ ኦነግ-ሸኔ ላይ ሊጭን ይቻለዋል? የኦሮሞ ብሄረተኝነት ስትራቴጂ የአማራዉን ማህበረሰብ በብሶት እንዲነሳ በማድረግ የፌደራል መንግስትን አቅም ማሽመድመድ ነዉ።››

የኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ  ወድቃ ትገኛለች በሃገሪቱ  በኮማንድ ፖስት በትግራይ፣  በቢኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ክልል ወዘተ የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ሥር በኮነሬል አብይ አህመድ ወታደራዊ አገዛዝ  ቀንበር ተጠምዳ ትገኛለች፡፡ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ተሸመድምዶል፣ የሸቀጣ ሸቀጥ የዋጋ ንረት፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረት፣ የብድርና የእዳ ጫና፣ የውጪ ንግድ ገቢ መቀነስ፣ የአውሮፓና አሜሪካ አገሮች እርዳታና ብድር እቀባ  ወዘተ አገሪቱን በኦነግ የፈንጂ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ከቶታል፡፡

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በግማሽ ክፍለ ዘመን ትግሉ አንድ መንደር ነፃ አላወጣም፣ ዛሬ ሁሉ ነገር በብልፅግና ፓርቲ የኦነግ ሠራዊትን በኢትዮጵያ ሠራዊት ስም በመመልመል መላ ሃገሪቱን በምርጫና በሜንጫ ለመቆጣጠር በቃ፡፡ ለኦዴፓ ብልፅግና የኢትዮጵያ ህዝብ በህዝባዊ እንቢተኛነትና በሰላማዊ ትግል፣ ህዝባዊ ጥያቄ ያቀርባል፡፡

 • በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣የፖሊስ ኃይል፣ ልዩ ኃይል በሻሸመኔ፣ አጣየ ፣ ወዘተ ህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ በተመሳሳይ
 • በሃገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ የውስጥ ተፈናቃዬች አስቸኮይ የስብዓዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው
 • የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ማድረግ ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ከሱዳን ዳርፉር ያለው አራት ሽህ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል ሃር ቤት ገብቶ በትግራይ፣ ወለጋ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሸዋ ወዘተ ገብቶ ሠላም እንዲያስከብር ማድረግ፡፡
 • የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦነግ ለተቃጠሉት ከተሞች፣ ሻሸመኔ፣ጅማ፣አርሲ፣አጣየ፣ ሸዋ ሮቢ፣ ካራ ቆሬ፣ወዘተ ኃብትና ንብረታቸው ለወደመባቸው አስፈላጊው ካሣ እንዲከፈላቸው፡፡
 • ካማንድ ፖስት ኦሮሚያ ውስጥ ላሉ ኦነግ ሽፍታ እንጅ ላልታጠቁ የአማራ ሰላማዊና ንፅህ ዜጎች ላይ መሆን የለበትም፣ ካማንድ ፖስቱ ከሰሜን ሸዋ ይውጣ!!!
 • የአማራ ክልላዊ መንግሥት አዴፓ ብልጽግና ፓርቲን የምርጫ ድምፅ ካርድ በመንፈግና ባለመምረጥ ከስልጣን እንዲወርዱ ማድረግ እንዲሁም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከምርጫው ራሳቸውን እንዲያገሉ በማድረግ የኮነሬል ዐብይ አህመድን ወታደራዊ መንግሥት እርቃኑን በማስቀረት ለዓለም ህብረተሰብ ማጋለጥ የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው እንላለን፡፡
 • የህሊና እስረኞች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ እስክንድር ነጋ አመራሮቹ ይፈቱ! የዴሞክራሲ አብሪ ጥይት በመላ ሃገሪቱ ይቀጣጠላል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ መንግሥት ከወያኔ ውድቀት አልተማረም …ኦሮሙማ አይማርምም!!! ያልሠለጠነ አራጅና አውዳሚ ኃይል ነውና!!!

ምንጭ፡-

(1) ምርጫ 2013፡ 18 ሚሊዮን ድምጽ ሰጪ ተመዝግቦበታል የተባለው ምዝገባ ተራዘመ

(2) ‹‹የኦሮሚያ ህጻናት ወታደራዊ ሥልጠናው ተጠናክሮ ቀጥሏል… ዘመድኩን በቀለ/ | 13/03/2021

(3) ኦነግ ሽኔን ያቋቋመው ‘አብይ ነው ‘ የደህነቱ ሹም አቶ አያሌው መንገሻ ይናገራሉ | Hiber Radio with Ayalew Apr 1,2021|Ethiopia – YouTube (ቪዲዬውን ይመልከቱት)

(4) ጠ/ሚ አብይ አህመድ ላይ የሚሰነዘሩ ወቀሳዎችና ክሶች – ሺፈራዉ አበበ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All (zehabesha.info)

2 Comments

 1. እናቱ ገበያ የሄደችበትና እናቱ የሞተችበት ልጆች በተመሳሳይ አይነት ስሜት ና አኳኋን ምርር ብለው ያለቅሳሉ ይባላል፥፥እናንተ ልትገድሉ ሲትሄዱ የደፏቹ ለታ አማራ ተጨፈጨፈ ትላላቹ፥፥ሌላው ፖለቲካ ትርፍ ብለው እየረሸኑዋቹ ያሉትን የአማራ ሊሂቃንን ትርክትና ዱለታ መላልሳቹ ታሰሙናላቹ፥፥ከንግዲ ወዲህ ከአማራ ጋር ተጋሩ ህብረት የላቸውም፥፥እኛ የብቀላ እርምጃ ይወሰድ ብለን ስለ ጅምላ ጭፍጨፋ አንናገርም ተፅዕኖ የፈጠረብንም አካል የለም፥፥(ጦርነቱ በትግራይ ህዝብና በሌላዉ ኢትዮጵያዊ መካከል የፈጠረዉን መራራቅ መካድ አይቻልም። ይህ መራራቅና መቃቃር ጊዜያዊ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ)ስላልከው የተስፋ ዳቦ እየጋገረ እንዳትበላው ነግሮ ያሸከመህን ብልፅግናን ጠይቀው፥ትንሽ እንድትገምጠው ቢፈቅድልህ፥፥ኢትዮጵያዊነት ማዕተቤ አማራ፥ኦሮሞ ሌላው ሌላው ማህበረሰብ ህብረብሔር ሁሉ ወገኔ ብለን በኩራት ከስድስት ወራቶች በፊት በልበ ምሉነት በኩራት ስንገር ነበር፥፥አሁን ግን ለልጅ ልጆቻችን የምናስተላልፈው መልዕክት የተለየ ነው፥፥የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል ይባላል እናንተ የናንተው ጉዶች የአማራ ልሂቃን ለፖለቲካ ትርፋቸው ኦሮሞን ና ተጋሩን ለማስጠላት የኛን ወገኖች ዕልቂት ለማለባበስ(የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ማድረግ ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ከሱዳን ዳርፉር ያለው አራት ሽህ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል ሃር ቤት ገብቶ በትግራይ፣ ወለጋ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሸዋ ወዘተ ገብቶ ሠላም እንዲያስከብር ማድረግ፡፡)እንዳልከው ከትግራይ ናከኦሮሞ እኩል ተጎጂ መስሎ ለመታየት ከምታሴሩት በቀር መከራቹ ተጀመረ እንጂ እንዳላለቀ የሚስማሙ የሚናገሩ ንታኞች ብዙ ናቸው፥፥ሳይነኩት ግን ገና የተገሩት ለታ እንደሚያለቅስ ልጅ እናንተ የአማራ ልሂቃን ሳፋ አስደቅናቹህ በየ አደባባዩ በየከተሞቹ ትጮሃላቹ ታለቃቅሳላቹ፥ነጃሳ ናቹህ በዙሪያቹ ያለን ሁሉን ሕብረ ብሄር ተተናኮላቹህ ፥፥አላህ መከራዉንያቅልላቹ፥፥እኛ በሕዝብ እልቂት ንጠቀምም ፥ያለቀው ወገናችን በዋልጌው በአረመኔው ፋኖና አማራ ሚሊሻ የተገደሉ ሕፃናት ና ሴቶች እቶች እህቶችና ልጆቻችን አይሱም፥አምላክ በእቅፉ ይቀበልል የተቀሩትን ይታደግልን፥፥

  • To the traitor woyane who inscribed the above nonsense:

   What did you expect from Amhara elites? To rally in support of woyane? To say save woyane the fascist? If you expect this, you must be dumb. During the 30 years of woyane rule (during woyane 1 for 27 years and during woyane 2 for three years), Amharas have been killed indiscriminately for being an Amhara. Despite the unabated genocide of Amhara people for 30, with the exception of quite a few individuals such as Tedi REYOT, no tigrian, stood by the side of the victims; they were rather enjoying the theft and privilege. So do you have the moral right to expect the support of Amharas when ahmed waged war on you? The answer is a big no.
   However, a lot of Amharas, including me, are still against the killing of innocent Tigrians. But we feel that TPLFites deserve what they get from ahmed.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.