የብርቱ ጥፋት ሤራዎች!! – ቴዎድሮስ ጌታቸው /ድሬዳዋ

‹‹ብዥታዎችን መግፈፍ››፣ ‹‹ክፉ ትንቢቶችን መቀልበስ››፣ ‹‹ሕዝብና ሀገር ማዳን›› ጊዜ የለም!!

ted የብርቱ ጥፋት ሤራዎች!!   ቴዎድሮስ ጌታቸው /ድሬዳዋ
ቴዎድሮስ ጌታቸው /ድሬዳዋ

ክቡር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር! ገና ያልጨረሱት ሥራ አለ!! ስለዚህ ከማንኛውም የግል ውሳኔዎ መታቀብ ይኖርብዎታል!! በቀጥታ ወደጉዳዩ ልግባ!! የፖለቲካ ትንቢት /Political Prediction/ እና ፖለቲካዊ ሴራ /Political Conspiracy/ ልዩነት የሚታይባቸው መስለው ይታያሉ፤ ሁለቱ ፖለቲካዎች ግን በአዙሪት ወይም Vicious-Circle ውስጥ እንዴት እንደሚገናኙ ዛሬ እንመለከታለን፤ የፖለቲካ ትንቢት ራሱን ተአማኒ አድርጎ ለማስቀመጥ፤ ፖለቲካዊ ሴራን እያገላበጠ ይመረምረዋል፤ መነሻ የሚያደርገው የቅርብ ጊዜ ፖለቲካዊ ሴራን ነው፤ ይህ መነሻ ቀደም ሲል ለተከናወነ ወይም ለታሪካዊ ሤራ ምርመራ ይጋብዘዋል፤ ፖለቲካዊ ትንቢት እነዚህን ማስረጃዎች ይዞ ወቅታዊውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከታዘበ በዃላ፤ ቀጣዩን ክስተት ግልፅና በማያሻማ መንገድ ያስቀምጣል፤ አንድ ምሣሌ ልጥቀስ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም /ነ.ይ./ ‹‹እንዘጭ እንቦጭ›› በሚለው መጽሐፋቸው፤ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያስቀመጡት አደገኛው ፖለቲካዊ ትንቢት፤ ሊፈፀም ጥቂት ወራት ሲቀሩት የኢትዮጵያ መንግስት በወሰደው ፈጣን እርምጃ እንዲከሽፍ ተደርጓል፤ ፕሮፍ የፈለጉትም ኢሄን ነበር! ፕሮፌሰሩ በዚሁ መጽሐፋቸው ስለኢትዮጵያ ሕዝብ የተናገሩት አደገኛ ትንቢት አለ! አሁን ድረስ ይህ ትንቢት አስተዋይ ተመልካች አጥቶ ውስጥ-ውስጡን እየሸረሸረን ይገኛል፡፡ ለዛሬ በአገራችን በወራት ውስጥ ሊፈፀም የታቀደውን ‹‹አደገኛ ፖለቲካዊ ሤራ›› አገላብጠን እንመረምራለን፡፡ እንሆ፤

‹‹ስኬት ያገኘው ፖለቲካዊ ሤራ›› በምልሰት!

ከታሪክ ጓዳችን ገብተን የተሳካውን ፖለቲካዊ ሤራ መመልከት ያስፈለገው፤ በቅርብ ወራት ሊተገበር የታቀደውን ፖለቲካዊ ሤራ፤ በሚገባ ለመረዳት እገዛ ስለሚያደርግልን ነው፤ በ1902 የምኒልክ አልጋወራሽ ሆኖ በአገራችን ሊተገብራቸው ያሰባቸውን እውን ሳያደርግ፤ ተዋክቦ ሥልጣኑን የተቀማው ልጅ እያሱ፤ ከቆየው የአገዛዝ ስልት /ልማድ/ መውጣት ካቃታቸው ሹማመንት ጋር፤ የነበረው ያለመግባባት /ቅራኔ/ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ልጅ እያሱ የሚከተላቸው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎቹ፤ ፈረንሳይና እንግሊዝን በመሰሉ ቅኝ ገዢ አገራት በስጋት የሚታይ ነበር፡፡ ከንጉሰ-ነገስት ምኒልክ ጋር ለበርካታ ዓመታት ያሳለፉት ሹማምንቱ ከልጅ እያሱ ጋር የነበራቸው ቅራኔ የሚመነጨው፤ ልጅ እያሱ አዲስና ተራማጅ ኃይል ይዞ ለመውጣት ካለው እሳቤ ነው የሚሉ አሉ፤ ሌላኛው ልጅ እያሱ ላይ ቅሬታ ካስነሳበት አንዱ፤ የአገራችን የምስራቁ ክልል መሀል አገር ካለው አገዛዝ ጋር የነበረውን፤ ከግብር ያልዘለለ የሩቅ-ለሩቅ ግንኙነትን በማሻሻል፤ በባህል፣ በኢኮኖሚና በዝምድና የማስተሳሰር ዘመናዊ ሀሳቡ ነው ተብሎ ይታመናል፤ የቅኝ ገዢዎቹ ስጋት መነሻ ተደርጎ የሚወሰደው ደግሞ፤ ከሚኒልክ ጋር በተደረገ ውል በፈረንሳይ ከተያዘችው ጅቡቲ፤ በእንግሊዝ ሥር ከነበረችው ሶማሊያ የጎሳ አመራሮች ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያደርገው ጥረት ነበር፡፡

ቅኝ ገዢዎቹ የውጭ ኃይሎች፤ የፖለቲካ ሤራቸውን ተግባራዊ ለማድረግ የተንቀሳቀሱት፤ በሹማምንቱ እና በልጅ እያሱ መሀል የተፈጠረውን ቅራኔ ክፍተት በመጠቀም ነው፤ ሹማምንቱን ጮቤ ያስረገጠ ሀሰተኛ ማስረጃ የተገኘውም ከነዚሁ የውጭ ኃይሎች ነው፤ እውነት ለመሆኑ የማያጠራጥር የፖለቲካ ሤራ! ያ ማስረጃ የተቀናበረው በግብፅ ካይሮ ሲሆን ልጅ እያሱ መስለሙን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ነበር /ሰልሟል ለማለት/፤ በዘመኑ መለኮታዊ ሽፋን የሚጠቀመው አገዛዝ፣ ሹማምንቶች እና በነሱ ሥር ለሚያድረው ሕብረተሰብ፤ እንዲህ ያለውን ተግባር የማይቀበለው ቢሆንም፤ ለውግዘት ከመነሳቱ በፊት ‹‹እስኪ እናጣራ›› ለማለት ጊዜ የሰጠ አልነበረም፤ በወከባና በጥድፊያ የልጅ እያሱን ትልቅ ሕልምና ልጅነቱን ለመቅጠፍ፤ ለጦርነት ዘመቻ መረባረብ ብቸኛ አካሄዱ ነበር፡፡ በዚህ የጥድፊያ ውሳኔ ‹‹ልጄን አፋልጉኝ›› ከሚሉት ንጉሥ ሚካኤል ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነት ተካሂዷል፡፡ ይህ የውጭ ኃይሎች የቀመሩልን ‹‹ታሪካዊ የፖለቲካ ሤራ›› ጠባሳችን ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወደአዲሱ የፖለቲካ ሤራ ሊያሸጋግሩ የሚያስችሉ ክፍቶችን እንመለከታለን፡፡ እንሆ፤

በመንግስት ቤት!

በአገራችን የፌዴራሉን መንግስትና የክልል መንግስታቶችን አሰላለፍ ስንመለከት፤ የፌዴራሉ መንግስት አብሮ ለመጓዝ ያለውን ዝግጁነት በተግባር ሲያሳይ፤ የክልል መንግስታቶች ደግሞ ለየቅል የመጓዝ ዝንባሌ ይታይባቸዋል፤ ለምሳሌ ፌዴራሉ በክልላቸው አስፋልት ሲገነባላቸው ክልሎቹ ደግሞ ልዩ ኃይል በመገንባት ገንዘብ ያባክናሉ፤ የትምህርት ተደራሽነት እንዲኖር በማሰብ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ሲገነባላቸው፤ ክልሎቹ ደግሞ የልዩ የልየ የልዩ ኃይላቸውን ደረጃ ያሻሽላሉ፤ ፌዴራሉ መብራት፣ ውሃና የመሳሰሉትን መሠረተ ልማቶችን ሲያስፋፋ፤ ክልሎቹ ደግሞ ጉልበተኛነትን እና የፖለቲካ ወንጀሎችን ያስፋፋሉ፤ በሌሎች ኢ-መደበኛ ጉልበተኞች የፖለቲካ ወንጀል እንዲፈፀምም ይፈቅዳሉ፤ ይህ አልበቃ ብሎ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ-መንግስት የተደነገገውን የሥልጣን ወሰን ሽፋን በመጠቀም፤ የፌዴራል መንግስቱን የሚፈታተኑ ሆነው ይታያሉ፡፡

ከላይ ለተጠቀሰው ሀሳብ ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ማሳያ የሚሆነን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው፤ ለዚህ መነሻ ሀሳብ የሚሆነን ደግሞ የኦነግ ሊቀ-መንበርነቱ አሁን አጠያያቂ የሆነው ኦቦ ዳኦድ ኢብሳ ይሆናል፤ ኦቦ ዳኦድ ከአሐዱ ቴሌቪዥን ጋር በነበረው ቆይታ፤ ‹‹ኦነግ ሸኔ ታዛዥነቱ በቀጥታ ለአቶ ዳኦድ ኢብሳ ነው ይባልል›› በሚል ከጋዜጠኛዋ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፤ ‹‹ኦነግ ሸኔ የሚለውን ስም እነሱ እንዴት አርገው እንዳወጡት አናቅም፤ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብለው ራሳቸውን ይጠራሉ፤ እኛም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት…ኢሄ ኃይል በደቡብና በምእራብ በድርጅቱ ሥር የነበረ ነው፤ እኛ ስንገባ የተስማማንበት እንትን አለ ተስማምተናል በአስመራ ባደረግነው ስምምነት፤ እዚህ ስንመጣ የጋርዮሽ ኮሚቴ አቋቁመን፤ ባለው የፀጥታ መዋቅር ውስጥ እንዴት አርጎ ሪ-ኢንተገሬት /እንደሚደባለቅ/… ፕሮሰስ አለው እሱ፤ ወይም ደግሞ ዓለም አቀፍ የሚከተለው እንትን ይህንን ነበር የተስማማነው…››፤ እንትኑን እንተወውና ኦቦ ዳኦድ ወደአገር-ቤት ሲገባ በቅድሚያ ሠራዊቱን ለአባ-ገዳ አስረክቧል፤ በመቀጠል ‹‹ከዚህ በዃላ በትጥቅ የሚታገል ሠራዊት የለኝም›› የሚል ደብዳቤ ፅፎ፣ ፈርሞና ማህተም አርጎ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሰጥቶታል /ኦቦ ዳኦድ ‹ማድረግ አልነበረብንም› ይላል/፡፡

ይህን የኦቦ ዳኦድ ንግግር በኦ.ቢ.ኤን. እና በሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች ሥምምነቱ ሲፈፀም በተግባር ተመልክተነዋል፤ በዚህ መልኩ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከኦነግ ኃላፊዎች ጋር ስምምነት ላይ ከደረሰ፤ ታጣቂዎቹን በቁጥጥር ስር የማድረግ ኃላፊነት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስቱ እንደሆነ ግልፅ ነው፤ ክልላዊ መንግስቱ ቡድኑን ትጥቅ የማስፈታት አቅም ቢያጣ እንኳ ቁርጠኝነቱ ቢኖረው፤ የፌዴራል መንግስቱን እገዛ ጨምሮ መፍትሄ ሊያበጅለት ይችል ነበር፤ ይህን ባለማድረጉ ኦሮሚያን የንፁሀን ዜጎች እልቂት ማዕከል በማድረግ፤ ክልላዊ መንግስቱ ለበርካታ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ በኦሮሚያ ክልልላዊ መንግስት ምን-አገባኝነት ነገር ግን እውቅና የተሰጠው በሚመስል መልኩ እየተፈፀመ ያለው የፖለቲካ ወንጀል፤ በቢንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስትና በደቡብ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት አሁን ደግሞ በአማራ ክልል እየተፈፀሙ ከሚገኙ የፖለቲካ ወንጀሎች ጋር ተዳምሮ፤ እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚታየው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የጀመረው ዓለም-አቀፍ የዲፕሎማሲ ጫና ሲጨነርበት፤ አገራችን ኢትዮጵያ በተለይ የፌዴራሉ መንግስት ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እዳና ክሰ እንዲጫንበት ያደረገ፤ በአገር ህልውና ላይ አደጋ የጋረጠ እና አብሮ በመኖር እሴቶቻችን ላይ ከሽንቁር በላይ ሰፊ ክፍተት የፈጠረ ‹‹አደገኛ ስህተት›› ሆኖ ይታያል፡፡

በመንፈሳዊው ቤት!

በመንፈሳዊው ቤት ያለው ነገር መንፈስ-ቅዱስ የራቀው መስሎ ይታያል፤ በአገራችን መለኮታዊ ሽፋን ከሚጠቀመው የንጉሰ ነገስት ሥርዓት መፍረስ በዃላ፤ የመንግስት አስተዳደር ሥርዓታችን ስሙ ሴኩላር ይባል እንጂ፤ እጁን ከመንፈሳዊ ቦታ መዶሉን አልተወም፤ መንፈሳዊ ተቋማቱም ከዓለማዊው መንግስት ጋር መተሸሸቱን ቀጥለዋል፤ ይህ በሁለቱ ብዙ ተከታይ ባላቸው እምነቶች ተቋማት የሚታየው ችግር፤ ከፌዴራል እስከ ክልል ድረስ የሚታይ ነው፤ አገራዊ የፖለቲካ ለውጡን እየመራ የሚገኘው መንግስትም፤ የለውጥ ሂደቱ እንዳይስተጓጎል ተቀዳሚ ሥራው ካደረገው ውስጥ አንዱ፤ በሁለቱ የእምነት ተቋማት ውስጥ ለሚታዩት የውስጥ ችግሮች፤ የመፍትሄ አካል ለመሆን እጁን ማስገባት ነበር፡፡ ለዚህ የመንግስት ተግባር በወቅቱ የመንፈሳዊው ቤት ምስጋና ከማቅረቡ ባለፈ፤ በሐይማኖት ተቋማቱ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ግለሰቦች፤ ከመንግስት ጋር የመቀራረብ ፍላጎቶች የተስተዋለበት ነበር፡፡

መሆን የነበረበት በመንፈሳዊ ተቋማቱ ውስጥ የታዩት ችግሮች፤ በሙሉ ወይም በከፊል መፍትሄ የተገኘለት ሲመስል፤ ዓለማዊው ተቋም /መንግስት/ ንፁህ እጁን ቀልጥፎ ከመሰብሰብ ነበር፤ ነገር ግን እጁን በመንፈሳዊው ተቋማቱ ማክረሙና የጉዳዩ ተዋናዮችን ማቅረብ መፈለጉ፤ አሁን በመንፈሳዊ ተቋማቱ ለሚታየው መልሶ ማገርሸት፤ ተጠያቂነቱን መንግስት እንዲሸከመው ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ተዋናዮች እንዲበራከቱ ምክንያት ሆኗል፡፡ የለውጡን መንግስት ተወቃሽ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ያለው የመንፈሳዊው ቤት ተዋናይ፤ የቀድሞው አገዛዝ ‹‹እርቅ ለመፈፀም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች መሰቀል አለባቸው›› በሚል ይዞት የነበረውን አቋም፤ ዞር ብሎ በመመልከት አሁን ካለው የለውጥ አመራር አቋም ጋር እንዳያነፃፅር፤ የገባበት የውስጥ ችግር ጋርዶት ይታያል፡፡

በማህበራዊው ሚዲያ ቤት!

አገራዊው የፖለቲካ ለውጡን ተከትሎ በርካታ ማህበራዊ ሚዲያዎች፤ በአገራችን የፖለቲካ እንቅስሴ ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፤ ማህበራዊ ሚዲያው ማሕበረሰብን በማንቃት ረገድ ያበረከተው አስተዋፅኦ የላቀ ስለመሆኑ፤ መሬት ላይ ያለው እውነታ ያረጋግጥልናል፤ ሚዲያው ኃላፊነት የሚሰማቸው ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ተንታኞችን በሥሩ ያካተተውን ያህል፤ ትንታኔያቸው በሕዝብና ሀገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ውጤት ከግምት የማያስገቡ፤ በብዛትም መኖሪያቸውን በውጭ ያደረጉ ግለሰቦችን የሚያሳትፍ፤ በአገራችን የሚገኘውን ሰፊ የሕዝብ ቁጥር ተከታይ ያደረገ የቴክኒዮሎጂ መረብ ነው፡፡ በመሆኑም በሕዝብ ላይ ብዥታ የመፍጠርና ብዥታ የመግፈፍ፤ ሕዝብ ሀገሩን እንዲገነባ እና ሀገር ከመገንባት እንዲዘናጋ የማድረግ፤ በአገር ውስጥ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እና አገር ውስጥ ቀውስ እንዲቀሰቀስ /እንዲቀጣጠል/ ማድረግ የሚያስችለውን፤ ሁለት አይነት መሣሪያ የሚያስታጥቅ ቴክኒዮሎጂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ባጠቃላይ ግን ማሕበራዊ ሚዲያዎች እንደአገር ያሉብንን ክፍቶች የምናይባቸው ናቸው፤ ክፍተቶች እንዳሉብን ካሳዩን የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት፡፡ እንሆ፤

 1. ‹‹አቢይ አህመድ በዳያስፖራው ያለው የፖለቲካ ቅቡልነት የፍፃሜ መጀመሪያ ደርሷል…፤ከዚህ በዃላ ምንአልባት ሠላማዊ ሰልፍ የሚወጡ ከሆነ፤ ኤርትራውያን ናቸው ለአቢይ አህመድ ሠላማዊ ሰልፍ የሚወጡት፤ እነሱን ደግፈው የተወሰኑ ሆድ በል የሆኑ…ጥቅም ያገኙ ኢትዮጵያውያን ሊኖሩ ይችላሉ…›› /ኤርሚያስ ለገሰ በኢትዮ-360 ‹‹ገዳዮችን የማጋለጥ ዘመቻ›› በሚለው ተገቢ ዝግጅት ላይ የሸነቆረው ሀሳብ April 06, 2021/
 2. ‹‹በዘመነ ህ.ወ.ሓ.ት. ቀጣዩ ተገዳይ ማን እንደሆነ፤ በወቅቱ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን፤ በብዕር ስማቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገፅ ሶስት ላይ ይፅፉሉ ከሚባለው ፅሑፋቸው ነበር የሚታወቀው፤ አሁን ደግሞ የተወሰኑ ግለሰቦች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህንን ሚና ተክተዋል፤…ከነዚህ መሰሎቹ መካከል አንዱ የሆነው ግለሰብ ከሚያሰራጨው መራጃ እንደምንገምተው፤ ቀጣዩ ሴራ በሙስሊሞች መንደር መሆኑን በግልፅ ለመረዳት ይቻላል፡፡…›› ኡስታዝ አህመዲን ጀበል /ኬዎቭን ያስገደለው…ስታሊን ነው/ በሚል ርዕስ ያሰራጨው መልዕክት በፊዳክ ቲዩብ ከተላለፈው ውስጥ በጥቂቱ የተወሰደ March 26, 2021 /
 3. ‹‹ባንዳነት እዛ ሠፈር ባህል ነው፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች ከመጡ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብረው ለመሥራት አይናቸውን አያሹም፤…እኔ ማስበው ባንዳነትን ባህል አርጎ የሚኖርን ማህበረሰብ፤ የኢትዮጵያ አካል አርጎ መቀጠል ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን ከዛ ማህበረሰብ ገንጥሎ ማኖር ነው፡፡ ኢትዮጵያን ከትግራይ መገንጠል ነው እኔ ምፈልገው፡፡…›› /ስዩም ተሾመ በየኔታ ቲዩብ ካስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሸነቆረው ሀሳብ፡፡/
 4. ‹‹ወላሂ በዚህ ወቅት እንኳን ለሮመዳን ዝግጅት የሚደረግበት እንጂ፤ እንዲሁ ላይቭ ገብቶ የሚወራበት ወቅት አልነበረም፤ ነገር ግን እጅግ በጣም በሚያሳፍር ሁኔታ ሰሞኑን የተፈፀመውን ነገር አይታችሁአል፤ ሁላችሁም ሰምታችሁአል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በደምብ አይታቹአል፤ ከክፍለሀገር ተሰባስበው የመጡ ትልልቅ ኡለሞቻችን በረንዳ ለበረንዳ እንዲንከራተቱ ነው የተደረገው፤ በዚህ በብልፅግና ማለት ነው፤ …ደህንነቶች እየተከታተሉ..ሰሞኑን እያያችሁ ነው፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ የሚወሰንበትን የጠቅላላ ጉባኤ እንዳይካሄድ መንግስት ካድሬዎቹንና ደህንነቶቹን መድቦ፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚያከብሮአቸውን ኡለሞቻችንን ሲያንገላቱ ነበረ ማለት ነው፤ መጅሊስ ውስጥ ተደብቆ መሀተም እየደበቀ ሲያወናብድ የነበረን ሰው ጭምር አገዱ ማለት ነው፤… ትናትና ህ.ወ.ሓ.ትን የሸኘነው ትናትና ህ.ወ.ሓ.ትን የታገልነው ለዚህ ነው ወይ ብለን እንጠይቃለን ማለት ነው፡፡…›› /ሙሃጅሩ በፊዳክ ቲዩብ ካስተላለፈው መልእክት የተወሰደ April 11, 2021/
 5. ‹‹አብይ አህመድን የሚደግፈው የአማራ ልሂቅ፤ የአማራ ሕዝብ ዋናው አስጨፍጫፊ ነው›› /ቴዎድሮስ ፀጋዬ በርዕዮት ሚዲያ የውይይት አጀንዳ ያደረገው ሀሳብ April 5, 2021/
 6. ‹‹ዓብይ አህመድ የኦሮሙማ ጠቅላይ ሚኒስትር›› /ኤርሚያስ ለገሰ በኢትዮ-360 የውይይት አጀንዳ ያደረገው ሀሳብ April 2, 2021 /
 7. ‹‹እነዚህ የዴሞክራሲ አጋፋሪ ነን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነን ይሉ የነበሩ ሁሉ…፤ እ…አንድ አባባል ነበረ ‹ጣሊያንም ይሄድና ሊሬውም ያልቅና፤ ያስዛዝበናል ይሄ ቀን ያልፍና› እንደተባለው፤ እነኚህ ባንዳዎች ዘንድሮ እምናያቸው እምንተዛዘብበት ጊዜ ይመጣል፤…›› /ክፍሉ ሁሴን በርዕዮት ሚዲያ ለጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ምስጋና ለማቅረብ፤ የለውጡን ደጋፊ የገለፀበት (የፈረጀበት) ሀሳብና ማስጠንቀቂያ April 17, 2021/
 8. ‹‹ኢትዮጵያ በእውነት በአሁኑ ሰዓት አለች ማለት አይቻልም፤ እየፈራረሰች ያለች አገር ናት መንግስት አለ ለማለት አይቻልም፤ ምንአልባት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አራት ኪሎ አካባቢ ብቻ ይመስለው ይሆናል አገር ማለት፤ በተቀረ ግን እሳት ያልተለኮሰበት አካባቢ የለም፤ ኢሄ የሚያሳየው ፌይልድ ስቴት መሆኗን ነው፡፡…›› /ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ በርዕዮት ሚዲያ ካቀረበው ትንታኔ በጥቂቱ የተወሰደ April 17, 2021/
 9. ‹‹አቢይ አህመድ አነሳሱ ከእርኩሳን መናፍት ነው ብዬ ነው የማምነው፤…አቢይ አህመድን የሚነዳው የሰው ደም እንደመስዋእት የሚቀርብለት እኩይ መንፈስ ነው፡፡ የንጹሀን እልቂት በአይኑ ፊት የቀለለው ለዚህ ነው፡፡›› /ማርያማዊት ሃይሌ በርዕዮት ሚዲያ ከሰጠችው አስተያየት በጥቂቱ የተወሰደ April 11, 2021/

በውጭ ኃይሎች ቤት!

አሁን ደግሞ አገራችን ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ሱዳንና ከአረቧ ግብፅ ጋር በቅርቡ እያከናወነች ያለውን ፖለቲካዊ ትግል እንመርምር፤ ከግብፅና ሱዳን ጋር እንደአገር የገባንበት የፖለቲካ ትግል፤ በዋናነት የመሬትና የውሃ ነው፤ መሬትን በተመለከተ ሱዳን የድንበር ወረራ በመፈፀም ‹‹ጉልበት ካልተፈታተሸን ሞቼ እገኛለሁ›› በማለት፤ የአገራችን ኢትዮጵያን ብርቱ ክንድ እየተጠባበቀች ስትገኝ፤ የውሃው ፖለቲካ ደግሞ ከግብፅ የሚሊተሪ ማስፈራሪያ ጋር ታጅቦ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ የኮንጎው ኪንሻሳ የድርድር ሂደት ከተቋረጠ በዃላ ‹‹ምን ሊያስከትል ይችላል›› ለሚለው ጥያቄ፤ ሁሉም በመሰለው መንገድ ቀጣዩን ሂደት ቢገምትም፤ አሜሪካን ግን ከግምት ያለፈ እርምጃ ሄዳለች፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደአፍሪካ ቀንድ ልካ፤ የቀጣይ ሂደት ዝንባሌዎችን ከየአገራቱ ለመረዳት ሞክራለች፤ ሱዳን በአሜሪካን በኩል ለኢትዮጵያ ያቀረበችው ጥያቄ ትኩረት ይስባል፤ የሱዳን ጥያቄ ‹‹ኢትዮጵያ የግድቡን ሙሌት ወደመስከረም ብታሻግረው?›› የሚል ነው፤ በፖለቲካ ሤራ መርማሪው በኩል የሚነሳው ጥያቄ ደግሞ ‹‹ለምን?›› የሚል ነው፡፡ እንቀጥል!

ግብፅ የውሃውን ጉዳይ በፍላጎቷ ልክ ለማስፈፀም እየሄደችበት ያለው አቅጣጫ፤ አንድ ወይም ሁለት አይደለም በርካታ የሚባሉ ናቸው፤ ያም ማለት ከሶስትዮሽ ድርድሩ ባለፈ በአገራችን ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ኃያላን አገራትን መጎትጎት፤ ጎረቤት አገሮች ከአገራችን ኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ትብብር ወደራሷ የመሳብ ጥረቷ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ግብፅ ከነዚህ ጥረትና እንቅስቃሴዎቿ አልፋ ‹‹ቀይ-መስመር›› የረገጠችበት፤ አገራችን የህልውና አደጋ ውስጥ እንድትወድቅ እየሸረበች ያለው ሤራ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ልብ ሊባል የሚገባው ይሆናል!! ከነዚህም ውስጥ አገር-አቀፍ የፖለቲካ አሰላለፋችንን የማዘበራረቅ እና መንፈሳዊ እምነታችንን ከፖለቲካ ጉዟችን ጋር አደባልቆ ብዥታ ውስጥ በመክተት መንግስትን ማስጨነቅ፤ ግብፅ የውሃ ፍላጎቷን ከግብ ለማድረስ የምትከተላቸው አቅጣጫዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ሀሳብ ማስረጃ ሆኖ የሚቀርበው፤ የግብፅ የእርሻ ሚኒስትር የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ በካይሮ በነበረ ውይይት ላይ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የራሱ ሕዝብ ይነሳበታል›› በማለት ያስተላለፈው መልዕክት ነው፡፡ እኛም የግብፁን የእርሻ ሚኒስትር ንግግር ግብፅ በምን መንገድ ልታስፈፅመው እንደምትችል ለመመርመር እንገደዳከን!!

የቤይሩቱ መልዕክት!

በቅርቡ ከቤይሩት የሰማነው ዜና የቤይሩታውያን ጉዳይ አይደለም፤ የኢትዮጰያውያንን ቅስም የሚሰብር አሰቃቂ ተግባር ነው፤ አንዲት ኢትዮጵያዊት አካሏን በመቆራረጥ (በመከፋፈል) የተፈፀመ ግድያ! የተቆራረጠውን አካሏን በፌስታል ውስጥ ተጠቅልሎ አገኘን የሚሉት የቤይሩት ፖሊሶች፤ ‹‹እንዲህ ያለ ሰቅጣጭ ድርጊት ካየን በርካታ ዓመታት ሆኖናል›› ይላሉ፤ ከተቆራረጡት አካሏ ከፊሉ አልተገኘም፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ሴት ልጅን እንደእናት፣ ሚስትና እና እህት ከማየት ባሻገር፤ ሴትን በመሬት እና በአገር ጭምር እንመስላታለን፤ ያ ማለት ሴት ሁሉነገራችን ናት!! የአረብ አገራት ተምሳሌት ከሆነችው ቤይሩት! በሴት ልጃችን አማካኝነት ለኛ ለኢትዮጵያውያን ወይም ለአገራችን መንግስት ሊተላለፍ የተፈለገው መልዕክት ምንድን ነው? ይህ የግብፅ መልእክት ይሆን? ብለን እንጠይቃለን!!

የተጋባዡ መልዕክት1 ‹‹ማኮብኮብ!››

በተለያዩ የነፃ ሀሳብና የሥነ-ጽሑፍ መድረኮች ላይ እየተገኙ፤ ልዩ እይታቸውን ለታዳሚያን ሲያካፍሉ የምናያቸው፤ መጋቢ ሐዲስ አለማየሁ እሸቱ፤ ተፈሪ አለሙን ለማመስገን በተዘጋጀ አንድ መድረክ፤ የሚከተለውን መልዕክት አስተላለፉ፤ ‹አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙ የቸገረው፤ መረጃና ኑሮው አልመጣጠን ብሎት ሊቀውስ ነው…ብዙ ሰው ሊያብድ እያኮበኮበ ነው፤ አልነገሯችሁም እንጂ ብዙ ፕሮግራም የያዙ አሉ ሊያብዱ፤ በሚቀጥሉት አመታት ብዙ ሰው ያብዳል በርግጠኝነት ነው የምነግራችሁ፤ ኢሄን ለማወቅ ነቢይም ፃድቅም መሆን አይጠይቅም፤ ሰው የሚያገኘው መረጃና የሚኖረው ኑሮ አይገናኝም፤ ሰው ደግሞ ኑሮውና መረጃው ካልተጣጣመ አቋርጦ ነው የሚያብደው…››፡፡ የመጋቢ ሀዲስ መልዕክት ለያዝነው ጉዳይ በዋዛ የሚታለፍ አይደለም!!

የተጋባዡ መልዕክት2 ‹‹በዓለም ላይ ያሉ አጋንንቶች!››

ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ ነፃ ሀሳብ በሚንሸራሸርበት መድረክ ተገኝተው፤ በሚያስተላልፉት ጠቃሚ መልዕክቶች ይታወቃሉ፤ በቅርቡ ያስተላለፉት መልዕክት ግን ለየት ይላል፤ በጥቂቱ እንመልከት ‹‹አንድ ጊዜ ስልክ ተደወለልኝ…የደወለልኝ ሰው ‹ከትግራይ ከኢሮብ ወረዳ ከአሲምባ ተራራ ነው ምደውልልህ› አለኝ፤…እሺ ምንድነው አልኩት ‹አባ ዘወንጌልን እያገለገልኳቸው ነው› አለ እሺ ‹መስቀለ-ክርስቶስ የሚባል ቤተክርስቲያን እያሰሩ ነው› አለ እሺ ‹ቤተ-ክርስቲያኑን ይጨርሱታል› እሺ ‹ከጨረሱት በዃላ እሳቸው ይሰወራሉ›…እሺ ‹ከዚያ በዃላ የኢትዮጵያ መከራ /ምጥ/ ይጀመራል› አለ፤ በጨዋነት አዳመጥኩት ሄደ፤…መስከረም ወር ላይ ‹መስቀለ-ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተመረቀ› የሚል ዜና አየሁ፤ ወር ባልሞላ ጊዜ ‹አባ ዘወንጌል አረፉ› የሚል ዜና ሰማሁ፤ አሁን ደነገጥኩ! ልክ ያለኝ ነገር ነው የሆነው፤ ከተፈፀመ ነገርየው! የሚቀጥል ነገር አለ ማለት ነው፤ ሶስት ዓመት መከራ ይሆናል ብሎኛል፤ 2015 የኢትዮጵያ ትንሳኤ ይሆናል!..፤ 2012 እና 2013ን ሳይ እስከዚህ ድረስ፤ ሰይጣን በየሀገሩ በየኮንቲኔንቱ ያሉትን ሰራዊቶች በሙሉ፤ አጋንንቶችን በሙሉ ሰብስቧቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያመጣቸው ነው የሚመስለው…››፤ ‹‹ኢሄን ስታዳምጡ መንፈሳዊ የሆናችሁ በመንፈሳዊ አዳምጡ፤ መንፈሳዊ ያልሆናችሁ በፓራ-ሳይኮሎጂ አዳምጡ›› ብለዋል ዶ/ር ወዳጄነህ፤ ስለኢትዮጵያ ያላቸውን ተስፋም ገልፀዋል-ዶ/ር!! በዚህ ጉዳይ ግርታ እንዳይፈጠር አፍታተን መመልከት ይኖርብናል፤

ክፉ ትንቢቶች የሚነገሩት ለምንድን ነው? በኦሪቱ ዘመን ወይም ከኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ በፊት በነበረው የይሁዲ እምነት፤ ነቢያቶች በእስራኤል ሕዝብ ላይ የሚመጡ መከራዎችን አስቀድመው ይነግሯቸው እንደነበረ፤ ከእስልምና እና ከክርስትና ቅዱሳት መጻሕፍቶች ውስጥ ለመረዳት ይቻላል፤ በነቢያቶች በኩል ለሚመለከታቸው ማለትም ለሕዝቡና ሕዝቡን ለሚመራው ንጉሥ ወደፊት ስለሚገጥማቸው መከራ የሚያስተላልፉት መልዕክት/ትንቢት፤ ‹‹ቅድመ-ማስጠንቀቂያዎች›› ናቸው፡፡ መልዕክቱ የደረሰው ሕዝብ ወይም ንጉሥ ‹‹ይህ ፍዳ እንዳይደርስብን ምን ብናደርግ ይሻለናል?›› ብለው የመፍትሄ ሀሳብ የሚጠይቁት፤ ክፉ ትንቢቱን/ማስጠንቀቂያውን ካስተላለፈው መልዕክተኛ ወይም ነቢይ ነው፡፡ በመሆኑም የመከራና ፍዳ ትንቢት የሚነገረው፤ የተነገረው መከራና ፍዳ እንዳይደርስብን የመከላከያ ሥራ እንድንሰራ ነው ማለት ነው፡፡ እውነታው ይህ ቢሆንም ዶ/ር መሀረነ ‹‹ይህ ፍዳ እንዳይደርስብን ምን ብናደርግ ይሻለናል?›› ብለው ለአባ ዘወንጌል መልዕክተኛ ስለመጠየቃቸው እና ለዚህ መልስ ስለማግኘታቸው የተነገረን ነገር የለም፡፡ ስለዚህ የትንቢቱን እውነተኛነት በጥልቀት መመርመር እጅግ አስፈላጊ ይሆናል!! ምክንያቱም፡-

 1. በመንፈሳዊ ቅን አማኞች ዘንድ፣ እንዲሁም በአገራዊው የፖለቲካ ለውጥ ደጋፊዎች ዘንድ የሚፈጥረው የአመለካከት ተፅእኖ ቀላል ባለመሆኑ እና ከውጭ ኃይሎች ለሚቀናበርልን ሤራ አጋዥ መሣሪያ ሊሆን ስለሚችል፤
 2. ዶ/ር መሀረነ ተላከልኝ ያሉትን ትንቢት ታጣቂ ቡድኖች ለንፁሀን ግድያና ሰቆቃ ወይም ለዕኩይ ዓላማቸው ማስፈፀሚያ እንደመልካም አጋጣሚ የሚጠቀሙበት በመሆኑ፤
 3. መንግስት /አገራዊው የለውጥ አመራር/ በአገራችንና በሕዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ክፉ ተግባር፤ የማስቆም/የመቀልበስ ግዴታውን እንዲወጣ የሚያስችለውን ፍንጭ የሚያገኝበት በመሆኑ ነው፡፡

የወሎው ሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢቶች፤ በክርስትና እስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ያላቸው ቅቡልነት ቀላል አይደለም፤ ብዙ ትንቢታቸው የተሳካ ስለመሆኑ የሚመሰክሩ ሰዎች ቁጥር በርካታ ነው፤ አሁን በምንገኝበት ዓመት ደግሞ ‹‹አንድ ንጉሥ ይመጣል›› በሚል የሚሰራጨው መልዕክት፤ ሰፊ የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ ሆኖ ይገኛል፤ ይህን መልዕክት አምኖ ከተቀበለው የማህበረሰብ ክፍል ውስጥ፤ አንደኛው ንጉሱ የሚቀባው ዶ/ር ወዳጄነህ በተናገሩት ‹‹መስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው›› ሲል፤ ሁለተኛው የለም ‹‹ባሕር ዳር ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ነው››፤ ሶስተኛው ‹‹ከድሬዳዋ በቅርብ ርቀት ከሚገኘው ኤረር ነው››፤ አራተኛው ‹‹ንግሥናውን የሚቀበለው ከደብረ-ብርሃን ነው›› በሚል የሚያምኑ ናቸው፤ ለንጉሱ መምጣት በዋናነት እንደምልክት የሚጠቀሙት ደግሞ፤ አሁን በአገራችን የሚታየውን ግድያና መፈናቀል ያስከተለውን የፖለቲካ ቀውስ፣ በሽታና አለመረጋጋትን ነው፡፡ እነዚህ ማህበረሰቦች በኢትዮጵያ በአራቱም ማእዘናት የሚገኙ፤ የተለያዩ ብሄረሰቦችና የሁለቱም ሐይማኖቶች ተከታዮች የሚገኙበት ነው፡፡ ማህብሰቦቹ በአካሄድ ይለያዩ እንጂ ንጉሥ እንደሚመጣ በማመን አንድ በመሆናቸው፤ ‹‹የንጉሥ ተጠባባቂዎች ቤት›› የሚል ስያሜ ሰጥተን ወደሚቀጥለው ፖለቲካዊ እይታ እንሸጋገር፡፡

ዶ/ር ወዳጄነህ የተነገራቸውን መልዕክት/ትንቢት በሚያስተላልፉበ ጊዜ፤ ‹‹ትንቢትን አትናቁ ሁሉን መርምሩ›› በሚል የጠቀሱትን ሀሳብ ተቀብለን፤ አንዳንድ ኩነቶችን እንፈትሻለን፤ ከዛሬ 100 ዓመት በአገራችን በተከሰተው ወረርሺኝ የብዙ ሰው እልቂት ያስከተለ ነበር፤ በተለይ አዲስ አበባ በሽታው ባስከተለው ሞት ከፍተኛ ተጠቂ ነበረች፤ በዚህ አስከፊ ጊዜ አንድ ኩነት ተፈፅሟል፤ ያም ነዋሪነቱ መራቤቴ የሆነ አንድ ግለሰብ ‹‹ንጉሥ ሆኜ ይህን ችግር የምቀርፈው እኔ ነኝ ተከተለኝ›› የሚል አዋጅ አስነገረ፤ አምኖ የሚቀበለው ሕዝብ ቁጥርም በአጭር ጊዜ ተበራክቶ፤ ጭፍሮቹን ይዞ ወደአዲስ አበባ ሲገሰግስ በንጉሱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የታሪክ ሰነዶቻችን ይጠቁማሉ፡፡ እንግዴ ንጉሥ ቴዎድሮስን ከመራቤቴም መፍጠር እንደሚቻል ይህ ግለሰብ አሳይቶናል፡፡ እንቀጥል!

በዘመነ ህ.ወ.ሓ.ት. የቀድሞው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፤ ሥልጣኑ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ማጣቱን ተከትሎ፤ በአንድ አዳራሽ ውስጥ በነበረ ስብሰባ ጠ/ሚኒስትሩ ውይይቱን በሚመሩበት ወቅት፤ በአዳራሹ ውስጥ ተሰብሳቢ የነበረው አንድ ቄስ የሰጠው አስተያየት በሕዝብ ዘንድ ተፅእኖ የፈጠረ ነበር፤ ቄሱም ‹‹ይመጣል ተብሎ የሚነገርለት ንጉሥ ቴዎድሮስ እርሶ ኖት›› በማለት አዋጅ በሚመስል መልኩ ተናገረ፤ ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ይህ የሚያስረዳን ‹‹ይመጣል›› ተብሎ የተነገረለትን ‹‹ንጉሥ ቴዎድሮስ››፤ በቀላሉና በቅፅበት በአንድ አዳራሽ ውስጥ መፍጠር እንደሚቻል ነው፡፡

ለዚህ ነው! ለዶ/ር ወዳጄነህ ከኢሮብ ወረዳ የተላከላቸውን መልዕክት እንድንጠራጠርና /ዶክተሩን አይደለም/ በሚገባ እንድንፈትሽ የሚመከረው፤ ለዚህ ነው! ትንቢቱን አምኖ ከመቀበልና ከመከተል በፊት፤ የህ.ወ.ሓ.ት. የመጨረሻው ስትራቴጂና ስልት መሆን አለመሆኑን ማጣራት የሚያስፈልገው፤ ለዚህ ነው! ህ.ወ.ሓ.ት. መልሶ ራሱን ሕዝብ ላይ ለመጫን የሚያደርገው አልሞት ባይ ተጋዳይነት ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጥያቄ ቀድመን መልስ ማግኘት የሚገባን!!

ለነዚህ ጥያቄዎችና ጥርጣሬዎች መልስ ሊያስገኝልን የሚችለው፤ መንፈሳዊ የሚመስለው መልዕክት/ትንቢት ለዶ/ር ወዳጄነህ የተላከበትና እንዲረስ የተደረገበትን ሁኔታዎች በመፈተሸ ይሆናል፤ ዶ/ር መልዕክቱ ደረሰኝ ባሉት ጊዜያትም የሰው ሞት፣ መፈናቀልና ጩኸቶች በነበሩበት ጊዜ ነው፤ ሌላው ለዶ/ር ወዳጄነህ መልዕክቱ የደረሳቸው በየመድረኩ የሕዝብ ትኩረት የሚስቡ ንግሮችን በሚያደርጉበትና የሕዝብ ተቀባይነት ባገኙበት ጊዜ በመሆኑ፤ ትንቢት የተባለው መልዕክት ለሳቸው እንዲደርስ የተደረገበት አካሄድ፤ ከመንፈሳዊ ትስስር የመነጨ ሳይሆን፤ የዶክተሩን የሚዲያ እንቅስቃስ ውጤታማነት ገመረግሞ ውሳኔ ላይ በደረሰ ድርጅት ወይም ቡድን፤ በአስገዳጅነት በመልዕክት አድራሹ በኩል የተላከ ፖለቲኮ-ትንቢት ሊሆን ይችላል፡፡

በሌላ መንገድ ስንቃኘው ቤተክርስትያንን የሚያንፅ መነኩሴ ወይም አባት የሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች/ትንቢቶች ሁሉ ትክክል ሊሆኑ እንደማይችሉ ማሳያ አሉ፤ ከነዚህ ውስጥ አባ ገብረመስቀል ተሰማ የተባሉ መነኩሴ፤ በሰሜን ወሎ ‹‹ዳግማዊ ላሊበላ›› የተባለውን ቤተ-ክርስቲያን ከአንድ ወጥ አለት የፈለፈሉ ናቸው፤ አባ ይህን እውቅናቸውን ተጠቅመው እህተ-ማርያም በመባል የምትታወቀውን እህት ‹‹በቀጣይ የምትገለጥ የኢትዮጵያ ንግስት ናት›› ብለው ትንቢት የተናገሩላት ቢሆንም፤ እውነትነት ያለው ትንቢት ሳይሆን፤ ልዩ ቅንብርና ወንጀል ጭምር ያካተተ ሆኖ እንደተጠናቀቀ፤ የቅርብ ጊዜ መነጋገሪያችንም እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም ህ.ወ.ሓ.ት. መንፈሳዊ ነገሮችን ለዓለማዊ ፍጆታው አይጠቀምበትም እንዳንል፤ ለቁሳዊ ጥማቱ ሲል የዋልድባን ቅዱስ ገዳምና መነኮሳቱን የደፈረ ቡድን በመሆኑ በሁላችን የተገለጠ ነው፡፡ ስለዚህ ከፖለቲካዊ ምስቅልቅሉ ባላነሰ በዚህ መልኩ ሕዝብ ላይ የተፈጠረው ብዥታ፤ በአገራችን ላይ ከሚታዩ ክፍቶች አንዱ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡

ከላይ ጀምረን እስከዚህ ድረስ ያየናቸው መረጃዎችን፣ እሳቤዎችንና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ፤ ለአንድ ሰው ብናሸክመው ከኑሮው ጋር አልመጣጠን ብሎት፤ ለማበድ የማኮብኮቢያ ጊዜና ቦታ እንደማያባክን ለሁላችንም ግልፅ ነው፤ በሌላ በኩል ከላይ ያሉትን መረጃዎች ከነእንቅስቃሴያቸው ተሸክማ የምትገኘው ሌላ ማንም ሳይሆን አገራችን ኢትዮጵያ ናት፤ በመሆኑም አገራችን ኢትዮጵያ በቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ልንረዳ ይገባል!! ስለዚህ ፅሑፍ አቅራቢው እንደአንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ፣ ደራሲና የፖለቲካ ተመልካች፤ ለዚህ አገራዊ ቀውስ በራስ ተነሳሽነት የሚከተሉትን እርምጃዎች ይወስዳል!! ሁሉንም መረጃዎች ሰብስቦ መተንበይ፣ የማጠቃለያ ሀሳብና የመዝጊያ ሀሳብ መስጠት፡፡ እንሆ፤

ሰብስቦ መንበይ!

ከ106 ዓመታት በፊት የውጭ ኃይሎች ያቀናበሩትን ሤራ የተሳካ ያደረገው፤ በመንፈሳዊው ጎራ ያሉትና ተራማጅ አስተሳሰብን የሚቃወሙ ሹማምንቱ በአንድነት፤ ልጅ እያሱ አራምዶት በነበረው የአገዛዝ ስልት በታየው ልዩነት ምክንያት በተፈጠረው አገራዊ ክፍት ነው፤ ከቀድሞው የተለየ መልክ ይዞ የምናየው አሁናዊው አገራዊ ክፍተት፤ የውጭ ኃይሎች ሊጠቀሙበት በሚያስችላቸው ሁኔታ ዝግጁ ሆኖ ይገኛል፤ ታሪካዊ ሤራውም ራሱን ሊደግም ከፊታችን ተደቅናል!!

የውጭ ኃይሎች አሁን ባለው የአገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የሚያቀናብሩት ሤራ፤ በልጅ እያሱ ላይ አቀናብረውት ከነበረው ሤራ የሚለየው በቅርፁ ብቻ ነው፤ ነገር ግን የውጪው ኃይል በእስልምና ወይም በክርስትና ምክንያት ሤራ ሊጠነስስበት አይችልም፤ ምክንያቱም በመንግሰታዊ አስተዳደሩ የሚከተለው ሤኩዩላሪዝም ስለሚከያሽፈው ነው፤ ስለዚህ ሤራው የሚጠነሰስበት መንገድና አካሄዱ አዲስ ይሆናል ፤ ያም ‹‹የሰይጣኖች አለቃ የሉሲፈር ተከታይ ነው›› በሚል የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊጠራጠረው የማይችል የቪዲዮ ማስረጃ ማቀናበር!!

ለዚህ የውጭ ኃይሎች ሤራ መነሻ ተደርጎ የሚወሰደው፤ የህ.ወ.ሓ.ት. ቃል አቀባይ የነበረው ጌታቸው ረዳ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚመሩት መንግስት የሰጠው ‹‹ጉግማንጉግ›› የሚለው ስያሜ/ፍረጃ ሲሆን፤ በውጭ ኃይሎች የሚቀናበረውን የቪዲዮ ሤራ በተስፋ ከሚጠብቁት ታጣቂ ቡድኖች ውስጥም፤ ይኸው ጌታቸው ረዳ እየተሳተፈ የሚገኝበት ቡድን እንደሆነ ይታመናል፤ ይህ የቪዲዮ ሤራ የሚቀናበረው ከግብፅ እንደሆነ እና የመሰራጨቱን አይቀሬነት የሚያረጋግጥልን፤ የአገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ ባነጣጠረ መልኩ፤ የግብፅ የእርሻ ሚኒስትር ‹‹የራሱ ሕዝብ ይነሳበታል›› በሚል ያስተላለፈው እርግጠኝነት የተሞላበት ንግግሩ ነው፡፡

በቪዲዮ የሚቀናበረው የውጭው ኃይል ሤራ! ተፈፃሚ/የሚሳካ እንደሚሆን ከሚታዩ ምልክቶች መገንዘብ ይቻላል፤ እንመልከታቸው፡-

 1. የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ቀደም ሲል ሲሄዱበት ከነበረው የሴኪዩላር ፖለቲካ ትንታኔ አፈንግጠው፤ አሁን የሚገኘውን አገራዊ መዋቅርና መንግሥታዊ ሥርዓት በመንፈሳዊ እይታ ለመተንተን የሚያደርጉት ሙከራ፤ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ነጥሎ የመፈረጅ ዝንባሌ ሲሆን፤
 2. ሌላኛው በአገራችን በፖለቲካ መጠላለፍ ምክንያት እየተፈፀሙ ያሉ ብሄር ተኮር ግድያዎችና መፈናቀሎች፤ የሕዝብን ልብ የሚያደሙ፤ ባለው በመንግስት ላይም ተጥሎ የነበረውን ተስፋ የሚያማጥጡ መሆናቸው እርግጥ ቢሆንም፤ ሕዝብ ‹‹የፖለቲካ ወንጀሎች›› መሆናቸውን ከመረዳት እና ‹‹መንግስት የፖለቲካ ወንጀሎቹን በማስቆም ሊፈታው ይገባል›› የሚል ጠንካራ አቋም ከመያዝ ይልቅ፤ ዓለማዊው ችግር በመንፈሳዊ መንገድ እንዲፈታ እያሳየ ያለው ዝግጁነት ነው፡፡

በመሆኑም የውጪው ኃይል! ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሙሉ ልባቸው ሊፈርጁት በቃፍ ለሚገኙት ማህበራዊ ሚዲያዎች፤ የሤራውን ቪዲዮ በመበተንና ለሕዝብ እንዲያስተጋቡ በማድረግ፤ ወደፊት /በቅርቡ ማለት እንችላለን/ እኩይ ተልዕኮ ያነገበውን ሤራ በቀላሉ የተሳካ ሊያደርገው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩል ‹‹ሠላምን የሚያሰፍን፣ ሕዝብን በእኩልነት የሚያስተዳድር ንጉስ ይመጣል››፤ የሚለውን ትንቢታዊ ንግርት አምኖ የተቀበለው፤ የየትኛውም እምነት ተከታይ የሆነው የሕብረተሰብ ክፍል፤ በተስፋ የሚጠብቁት ንጉሥ ንግስናውን የሚፈፅምበት አካባቢና ቤተ-ዕምነት ላይ የተለያየ እሳቤ ያላቸው መሆኑ አሳሳቢ ያደርገዋል፤ ይህ እሳቤም የሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም የሚያስከትል፤ በተለይ ‹‹ንጉሥ ይመጣል›› የሚለው ተስፋ በእምነት በበቁ ሰዎች የሚመራ ሳይሆን፤ እሳቤው በእምነት ባልበቁ፣ የፖለቲካ አይዲዎሎጂ በታጠቁና በማሕበራዊ ሚዲያ በሚያነቁ ሰዎች የሚሰራጭ በመሆኑ፤ የውጭው ኃይል ሤራ ተጨምሮበት የአገር ህልውናና አንድነትን የሚያሳጣ ይሆናል፡፡ እናስተውል!!

በአዙሪት ውስጥ የመገናኘት ዕድል!

ወደብርቱ ጥፋት ሊያመሩን የሚችሉ፤ እንቅስቃሴዎችንና ክፍተት የፈጠሩ መልዕክቶችን ከላይ በዝርዝር ተመልክተናል፤ አሁን ደግሞ እነዚህን እንቅስቃሴዎችና መልዕክቶች እያገጣጠምን ምስል በመፍጠር፤ በአገራችን ሊከሰት በሚችለው ያልተገባ እንቅስቃሴ ውስጥ፤ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ /በመተዋወቅም ሆነ ባለመተዋወቅ/ ወይም የዓላማ አንድነት ኖሮአቸውም ሆነ ሳይኖራቸው፤ ተዋናዮች የሚፈጥሩትን አሠላለፍና መገናኘት እንመለከታለን፤

 1. አገር አቀፉ ምርጫ ተግባራዊ እንዳይሆን ለማድረግ በማሰብ፤ የምርጫ ጣቢያዎችን የሚያቃጥሉና የሚያወድሙ ታጣቂ ቡድኖች፤ ‹‹ንጉስ ይመጣል›› በሚል ቀቢፀ ተስፋ ውስጥ የሚዋልለውና ‹‹አገርአቀፍና ክልላዊ ምርጫ አያስፈልግም›› ከሚለው ማህበረሰብ ጋር ባይተዋወቁም ‹‹በአዙሪት ውስጥ›› ይገናኛሉ፡፡
 2. አሁን የሚገኘውን የለውጡን መንግስት ‹‹ጉግማንጉግ›› በማለት የሚጠራው የህ.ወ.ሓ.ት. ታጣቂ ቡድን፤ ‹‹አቢይ አህመድ አነሳሱ ከእርኩሳን መናፍት ነው ብዬ ነው የማምነው…›› ከሚለው የርዕዮት ሚዲያ-ዘመቻ፤ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ መንፈሳዊ ሽፋን በመጠቀም የሚሰራጨውን ፀረ-መሪ ትንታኔን አምኖየተቀበለው ማሕበረሰብ፤ የጋራ ዓላማ ባይኖራቸውም ‹‹በአዙሪት ውስጥ›› ይገናኛሉ፡፡
 3. ‹‹እኔ ዋናው አላማዬ ኢትዮጵያን ከትግራይ መገንጠል ነው›› የሚለው የስዩም ተሾመ ሀሳብና ይህን ሀሳብ በስሜታዊነት የሚደግፈው ማህበረሰብ፤ ‹‹የትግራይ ሪፐብሊክ እንመሠርታለን›› ከሚለው የህ.ወ.ሓ.ት. የፖለቲካ ክንፍ ጋር፤ እውቅና ባጥሰጣጡም ‹‹በአዙሪት ውስጥ›› ይገናኛሉ፡፡
 4. የአገራችንን ጠቅላይ ሚኒስትር ለብቻው ለመነጠል በማሰብ ‹‹የራሱ ሕዝብ ይነሳበታል›› ያለው የግብፁ የእርሻ ሚኒስትር፣ ብሄር ተኮር ዘግናኝ ጭፍጨፋና ማፈናቀል የሚያካሂዱ የተደራጁ ታጣቂ ቡድኖች፤ እንዲሁም በወገኖቹ መጨፍጨፍ ልቡ የደማውና በመንግስት ላይ ጥሎት የነበረው ተስፋና ትዕግስቱ የተሟጠጠው ሕዝብ ‹የሚያሳየው የመሪ ጥላቻ›፤ እንዲሁም በኢትዮ-360 ሚዲያና በርዕዮት ሚዲያ ተዋናዮች የሚያካሂዱት ‹መሪን ከሕዝብ የመነጠል እንቅስቀሴ›፤ ዓላማቸው ለየቅል ቢሆንም የኢ.ፌ.ዴ.ሪን ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻውን የመነጠል እንቅስቃሴ ውስጥ ‹‹በአዙሪት›› ይገናኛሉ፡፡
 5. አገራዊ የፖለቲካ ለውጥ ደጋፊውን ለማሸማቀቅና ከሂደቱ እንዲወጣ ለማድረግ በማሰብ ‹‹እነኚህ ባንዳዎች… እምንተዛዘብበት ጊዜ ይመጣል!›› የሚለው የክፍሉ ሁሴን ሀሳብና ይህን ሀሳብ የሚደግፉ ግለሰቦች፤ እንዲሁም ህ.ወ.ሓ.ት. ጠቃሚ አገር-አቀፍ ሀሳብ የሚያራምዱትን የትግራይ ምሁራንን ‹‹ባንዳ›› በሚል ከያዘው የፍረጃ-አቋም ጋር፤ ‹‹በአዙሪት›› ውስጥ ይገናኛሉ፡፡
 6. የአራችን ጠቅላይ ሚኒስትር በውጭ ዲፕሎማሲው የሚያራምዳቸው ጠንካራ አቋሞችን ለማክሸፍ፤ የሤራ ቪዲዮውን ለማቀናበር የምትገደደው ግብፅ፤ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰው ደም እንዲያፈስ መንፈሱ ይፈልጋል›› ለሚለው መላ-ምታቸው ማረጋገጫ ከተጠሙት ማህበራዊ ሚዲያዎች ጋር ‹‹በአዙሪት›› ውስስ ይገናኛሉ፡፡
 7. ‹‹ዛሬ ነገ ሳይባል ችግሮቼ ይፈቱ›› የሚለው የሐይማኖት ተዋናዮች ቡድን፣ ‹‹በቅርቡ ንጉሥ ይመጣል›› የሚለውን፤ መንፈሳዊ ሽፋን የተሰጠውን መልዕክት የሚቀበለው የማሕበረሰብ ክፍል፤ በታጠቁት መሣሪያ ወንጀል እየፈፀሙ ‹‹የካይሮውን ሤራ›› በተስፋ የሚጠባበቁት ቡድኖች /የህ.ወ.ሓ.ት.፣ የኦ.ነ.ግ. እና የጉሙዝ ታጣቂ ቡድኖች/፤ ከአገራዊው የፖለቲካ ለውጡ ጀምሮ አሁን ድረስ እየተፈፀሙ ያሉ ወንጀሎችና ዓለማዊ ችግሮች፤ በመንፈሳዊ መንገድ ይፈታል ብሎ ተስፋ ያደረገው ማሕበረሰብ፤ ፍላጎታቸው ለየቅል ቢሆንም በዚሁ ‹‹አዙሪት›› ውስጥ ይገናኛሉ፡፡

የማጠቃለያ ሀሳብ!

አንድ ጊዜ ከምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ማሊ ከቅርብ ዓመታት የታሪካ ጓዳዋ ጎራ እንበል! ጄነራል አማዱ ቱሬ ተብሎ የሚጠራ መልካም ሥም ያለው ወታደር፤ ራሱን ከሚሊተሪነት አሰናብቶ ሲቪል በመሆን ለማሊ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ለመወዳደር ራሱን አዘጋጀ፤ የማሊ ሕዝብም ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ አማዱ ቱሬን ፕሬዚደንት አደረገው፤ ፕሬዚደንቱን የቀድሞው መልካም ሥሙ እንደጠቀመው ይታመናል፤ አማዱ ቱሬ ለሁለተኛ ጊዜ በሕዝብ ተመርጦ ጊዜውን ከጨረሰ በዃላ፤ የማሊን ሕገ-መንግስት አክብሮ በቀጣይ ምርጫ የመወዳደር ፍላጎት እንደሌለው ግልፅ አደረገ፤ በቀጣይ በሕዝብ ፕሬዚደንት ሆኖ ለሚመረጠው ሥልጣኑን ለማስረከብም ዝግጁ ሆነ፤ ምን ዋጋ አለው! ቅሬታ አለን በሚሉ ወታደሮች ቅፅበታዊ ውሳኔ የመንግስት ግልበጣ ተደረገበት፤ መፈንቅለ-መንግስቱ የተፈፀመው በአንድ በኩል በሰሜን የሚገኙ ታጣቂ ቡድኖች ‹‹በደቡብ ማሊ ከሚገኙ ሕዝቦች ጋር በሐይማኖት ካልሆነ በዘር አንገናኝም፤ ስለዚህ የሰሜኑን ክፍል እንገነጥላለን›› በሚል ጦርነት አውጀው በሚታኮሱበት! በሌላ በኩል በኢያድ ጋሊ ይመራሉ የተባሉትና ‹‹የሼሪያን ሥርዓት በማሊ እንዘረጋለን›› የሚሉ ታጣቂ ቡድኖች ከአልቃኢዳ ጋር በመተጋገዝ፤ ማሊን በጦርነት እያንገበገቧት በነበሩበትና አጣብቂኝ ውስጥ በወደቀችበት ጊዜ ነው፡፡

ወታደሮቹ መፈንቅለ-መንግስት ለመፈፀማቸው እንደምክንያት የሚያነሱት፤ አንደኛ ‹‹በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱትን ቡድኖ ስንዋጋ መንግስት አስፈላጊውን ስንቅና ትጥቅ አላቀረበልንም፤ ስለዚህ እንድንሸነፍና እንድንዋረድ ተደርገናል፤ የቱሬ መንግስት ጦርነትቱን ለመግታት ፍላጎቱ የለውም›› የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ‹‹የዕፅ ዝውውርን ለመቆጣጠር ያለው ዝግጁነት ደካማ ነው›› የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን ወታደሮቹ በኃይል ሥልጣን ነጥቀው፤ በውስጥ የሕዝቡን! በውጭ የምዕራብ አፍሪካውን ሕብረት /የኢካዋስን/ ጫና አልፈው፤ ሥልጣናቸውን ለማደላደል በዋና ከተማዋ ባማኮ ሲተራመሱ፤ የሰሜኖቹ ታጣቂ ቡድኖች የአገሪቱን ግማሹን ግዛት ተቆጣጥረው ነፃነታቸውን አወጁ! በአልቃኢዳ የታገዙት ታጣቂዎችም በቀላሉ በተቆጣጠሩት ቦታ የሼሪያን ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ አልተቸገሩም፡፡ ከወታደራዊው መንግስቱ ጋር ለመነጋገር ፍላጎቱ እንዳላቸው የተጠየቁት ታጣቂ ቡድኖች መልስ ሲሰጡ፤ ‹‹ለመነጋገርም ቢሆን እኮ ከሚታወቅ ሰው ጋር መሆን አለበት፤ እነዚህን ማን ብለን ነው ምናነጋግራቸው!››፤ ኢኸውላችሁ አገር የምትፈርሰው በነዚህ እውራዊ ተግባሮች መነሻነት ነው!! መፈንቅለ-መንግስት ፈፃሚ ወታደሮቹ አለን የሚሉትን ቅሬታ፤ በቀጣይ ተመራጭ ፕሬዚደንት እንዲፈታ ማድረግ እየተቻሉ፤ በዚህ መልኩ ራሣቸውን ለውርደት አገራቸውን ማሊንም ‹‹ከድጡ ወደማጡ›› እንድትማስን አድርገዋል፡፡/ይህ አሰፋ እሸቴ በሸገር ኤፍ ኤም ከተረከልን በአጭሩ የወሰድኩት ነው/፤ ኑ! አሁን ወደአገራችን እንግባ!!

አገራችን ኢትዮጵያ ብንገባም፤ በፍጥነት እየተጋዝን ያለነው ወደፊት ሳይሆን፤ በአዙሪት ውስጥ 17 ዓመታት ወደዃላ! ወደ2004ቱ የማሊ ቀውስ ነው!! አሁን በአገራችን የፖለቲካ አመራሮች፣ ፖለቲከኞች፣ ፖለቲካ ተንታኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ሐይማኖተ-ፖለቲከኞች እና ታጣቂ ቡድኖች፤ እየተከናወነ የሚገኘውና ማሕበረሰቡ ውስጥ የሰፈነው ብዥታ የሚያመላክተን ይህንኑ ነው!! አንድን ጠቅላይ አመራር፣ አንድን ሕዝብ፣ አንዲትን አገር አጣብቂኝ ውስጥ መክተት!! ይህ ጉዳይ እንዴት ባለ መሰሪነት እየተፈፀመ እንደሚገኝ ለሕዝብ ግልፅ ማድረግ ይገባል፡፡ እንሆ፤

መሰሪነት በማህበራዊ ሚዲያ-1

አንዳንድ ምልከታዎቹ በበጎ ጎን የሚወሰድለት የርዕዮት ሚዲያ አዘጋጁ ቴዎድሮስ ፀጋዬ፤ በአንድ በኩል ‹‹አብይ አህመድን የሚደግፈው የአማራ ልሂቅ የአማራ ህዝብ ዋናው አስጨፍጫፊ ነው›› በማለት፤ የአማራውን ልሂቅ ከአማራው ሕዝብ ጋር ያለውን የማይበጠስ ሰንሰለት ለመገዝገዝ ሲጣጣር፤ እግረ-መንገዱን የአማራው ልሂቅ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ቁጭ ብሎ መፍትሄ የሚያበጅበትን መገናኛ መንገዶች ለመዝጋት ይሞክራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አማራውን ለበርካታ ዓመታት ገድሎ፣ አቃጥሎና ሰውነቱን ቆራርጦ ያልረካውን የህ.ወ.ሓ.ት. እብቅ ቡድን፤ በሽምቅ ውግያ አሁን እያደረሰ ያለውን ጥቃት ይደግፋል፤ በሚዲያው ግብዣ ያደረገለት ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ የህ.ወ.ሓ.ት. ሽምቅ-ውጊያ ደጋፊ፤ ጁንታው በሽምቅ ውጊያው እያገኘ ያለውን ድል ሲገልፅለት፤ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ደስታውን ከተመልካቾች ለመደበቅ ሲጣጣር የተመለከትነው ቪዲዮ በቂ ምሥክር ነው፤ በተመሳሳይ ክፍሉ ሁሴን የተባለ ጤናማ የማይመስል ሰው በዚሁ ርዕዮት ሚዲያ ላይ የለውጡን ደጋፊዎች ‹‹ባንዳ›› በማለት ከተሳደበ በዃላ፤ ‹‹ከወያኔ ጋር ድል አድርገን ስንገባ እንገናኛለን›› የሚል ይዘት ያለውን ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ፤ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ለማስጠንቀቂያ ሰጪው የወያኔ ተላላኪ ድጋፍ ሲያሳይ ታዝበናል፤  በዚሁ የሶስትዮሽ የርዕዮት ሚዲያ ፕሮፓጋንዳ፤ የወያኔው ልዑክ ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ‹‹ኢትዮጵያ ፈርሳለች›› በማለት ትዕዛዝ መሰል ሀሳብ ሲሰጣቸው፤ ቴዎድሮስ ፀጋዬና ክፍሉ ሁሴን ‹‹አዎ ፈርሳለች›› እያሉ የጥፋት ምኞቱን በዜማ ሲቀበሉ የሚያሳየውን ቪዲዮው ተመልክተናል፤ እንግዲ እንዲህ ያሉ መሰሪዎች ናቸው የአማራ ተቆርቃሪ መስለው፤ ከኦነግ ታጣቂዎች ባልተናነሰ አማራን ወደባሰ እልቂት እየወሰዱት የሚገኙት፤ የነዚህ ግለሰቦች በዚህ አቋም ውስጥ መገኘት፤ አንድም ወያኔ በሽምቅ ውግያ ውጤት አጊኝቶ የመንግስት ስልጣን ይቆጣጠራል ከሚል የእብዶች ተስፋ ነው፤ ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆነው የኢትዮጵያ ፈርሳለች ዜማ ተቀባዩ ክፍሉ ሁሴን ‹‹ድል አድርገን ስንመጣ እንገናኛለን›› በማለት ለለውጡ ደጋፊዎችና ለአማራ ልሂቃን ያስተላለፈው ዛቻ ነው፤ የእነዚህ የሶስትዮሽ የርዕዮት-ሚዲያ የፕሮፓጋንዳ ፊት-አውራሪዎን ተግባር ስንፈትሽ፤ ከእግድ በተረፈው፣ እየተሟጠጠ በሚገኘውና በሌብነት በተሰበሰበው የወያኔ ዶላር ላይ የሚያሳዩት ‹‹ለሀጭ ማዝረክረክ›› ሆኖ እናገኘዋለን፤ ባጠቃላይ እነዚህ ግለሰቦች ጥቁር አፍሪካውያን እህትና ወንድሞች በባርነት ተግዘው፤ በጉልበታቸው በገነቧት አገር አሜሪካን ውስጥ ቁጭ ብለው የሚያስላልፉት መልዕክት፤ ነፃነቱን አስጠብቆ ለመኖር በቆረጠው ሕዝብና አገራችን ላይ ከሚያደርሰው ጥፋት አንፃር፤ ‹‹የብርቱ ጥፋት ሤራ›› አካል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

መሰሪነት በማህበራዊ ሚዲያ-2

ኢትዮ-360 ሚዲያ ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ተንታኞች የሚያስተላልፉት ፕሮፓጋንዳ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና አገራችንን ኢትዮጵያ ወዴት ሊመራት እንደሚችል ቆም ብለው ራሳቸውን ሊፈትሹ ይገባል፤ ለምሳሌ ‹‹ዓቢይ አህመድ የኦሮሙማ ጠቅላይ ሚኒስትር›› በሚል ያሰራጩት ፕሮፓጋንዳ፤ ሁለት ዓላማዎች ያነገበ ሆኖ ይታያል፤ አንደኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ከሕዝብ መነጠል ሲሆን፤ ሁለተኛው ብቻውን ማስቀረት ነው!! ይህ ፕሮፓጋንዳ በሚዲያው የተሰራው ‹‹ኦሮሙማን እንዳናራምድ መሰናክል የሆነብን ዐቢይ አህመድ ነው›› የሚሉ ቅሬታ አቅራቢ ቡድኖች ባሉበት እውነታ ውስጥ ሲሆን፤ የኢትዮ-360 ዋና ግቡ ያደረገው ጠቅላይ ሚስትሩን በጥርጣሬ የሚመለከት ተጨማሪ ኃይል በመፍጠር፤ የጠቅላዩን ቅቡልነት የሚሸረሽር ውጤት ማግኘት ላይ ነው፡፡ የኢትዮ-360 ተንታኞች ሊረዱ ያልቻሉት ይህ ውጤት የሚያስከትለውን ውጤት ነው፤ የ‹‹ኦሮሙማ›› አራማጆች ቅሬታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚጠራጠር ተጨማሪ ኃይል ከተፈጠረ፤ አንዲሁም ጠቅላዩን ብቻውን የመነጠል ሙከራው የተሳካ ሲሆን፤ ቀጣዩ የሤራ-ድርጊትና የሚያስከትለው ውጤት ግልፅ ነው!! ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የግድያ ጥቃት ማስፈፀምና እና ለጥቃቱ በሚሰጥ ምላሽ ውስጥ የመንግስት መፍረስ ጅማሬን ማወጅ ይሆናል!! እንዲህ ያለው መሰሪነት በመንግስቱ ኃይማሪያም ጊዜ ምን ውጤት እንደነበረው ከማናችንም የተሰወረ አይደለም!! ችግር የሆነው የፖለቲካ ተንታኙም፣ አክቲቪስቱም፣ ታጣቂ ቡድኑም በዚህ ፀያፍ አዙሪት ውስጥ መደንዘዙ ነው፡፡

የኤርሚያስ ለገሰ ‹‹ከዚህ በዃላ ለአቢይ አህመድ ሠላማዊ ሰልፍ የሚወጡት ኤርትራውያን ናቸው ፤…የተወሰኑ ጥቅም ያገኙ ኢትዮጵያውያን ሊኖሩበት ይችላሉ›› የሚለው ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክትም፤ የሚያስከትለው ውጤት ከዚያው ከአበዮቱ አዙሪት ውስጥ ጎትቶ የሚጥለን ነው፤ በቀላሉ የኤርሚያስ ለገሰ መልዕክት ነገ በተስህቦ መልክ ወደአገር-ቤት ሲመጣ የሚያስከትለው ውጤት!! ‹‹የዐቢይ አህመድ ደጋፊ ባንዳ ነው›› የሚለውን ፍረጃ አሰጥቶ፤ ‹‹የአቢይ ደጋፊ›› በተባለው ላይ የግድያ ጥቃት የሚያስከትል፤ ‹‹አታስገድሉን አስታጥቁን›› በሚል መንግስትን በእሪታ የሚጎተጉት ቡድን የሚፈጥር ይሆናል፡፡ እንቀጥል!

ሌላው በዚሁ ኢትዮ-360 ሚዲያ የሚቀርበው የዋህ ሀሳብ የሚመስል፤ ነገር ግን በውስጡ መሰሪነት የመሸገበት ትንታኔ ነው፤ ከኢትዮ-360 የፖለቲካ ተንታኞች አንዱ የሆነው ሀብታሙ አያሌው፤ ብሄራዊ መግባባትና እርቅን ከልደቱ አያሌው በውጭ አገር የልብ ሕክምና የመከታተል ፍላጎቱ ጋር ማገናኘቱ ነው፤ በኢትዮ-360 ቤት የሚገኙ ተንታኞች ያልተረዱት አንድ ነገር አለ፤ ያም ‹‹ብርቱ ጥፋት›› በአገራችን አንዴ ከተለኮሰ በዃላ! የተለኮሰው እሳት በአግቡ እስኪጠፋ፤ አቶ ልደቱም ሌሎችም ምክንያት የሆኑበት የአገራችን ምስቅልቅል እስኪስተካከል! ማንኛውም ፖለቲከኛ ከአገር አይወጣም!! ለዚህ ማሳያ የሚሆነን ህ.ወ.ሓ.ት በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ብርቱ ጥፋትቱን በለኮሰ ጊዜ፤ ቡድኑ ከአገር እንዳይወጣ ለማድረግ ድንበር በመዝጋት የተወሰደው አስቸኳይ እርምጃ ነው፤ የአገር መከላከያ ሠራዊት አርብ ሚያዝያ 15-2013 በድጋሚ አሄን አረጋግጧል፡፡ ተግባራዊ እየሆነ ያለውን ይህን አውነታ ማንኛውም ፖለቲከኛ ከየትኛውም እኩይ ተግባሮቹ አስቀድሞ ሊገነዘበው ይገባል!! ይህን በተመለከተ ሰኔ 2011 ባሳተምኩት ‹‹አልወልድም- የኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅጣጫዎች›› በተሰኘው ቅጽ1 መጽሐፌ ላይ፤ እንደአገር ሊያዝ የሚችለውን አቋም ‹‹ብርቱ ጥፋት›› በሚል ቀደም ብዬ ትንታኔ ሰጥቼበታለሁ /ገፅ 189-195/፡፡ የኢትዮ-360 ሚዲያ ተንታኞች በዚህ አደገኛ ተግባር ውስጥ እንዲዘፈቁ ያደረጋቸው፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ካላቸው ፍፁም ጥላቻ መነሻነት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እያሰራጩት ያለው ትንተናና ፕሮፓጋንዳ፤ በሕዝብና አገራችን ላይ ከሚያደርሰው ጥፋት አንፃር ሲታይ፤ ‹‹የብርቱ ጥፋት ሤራ›› አካል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

የለውጡን አመራር ይቅር የማያስብለው መዘናጋት!!

አሁን አንድ ነገር ተፈፃሚ መሆን ይኖርበታል!! ሕዝብ በሚፈፀሙ የፖለቲካ ወንጀሎች በመሰላቸቱና ተስፋ በመቁረጡ ምክንያት፤ አገር ለመገነጣጠል የተነሱ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያስተላልፉትን መልዕክት አምኖ እንዲቀበል የተገደደበትን፤ በዚህም ምክንያት ሕዝብ የፌዴራሉን መንግስት /በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን/ የቀጥታ ተጠያቂ አድርጎ እንዲነሳ የተደረገበትን ልዩ ስልት ለማጋለጥ፤ እንዲሁም አሁን የሚታየውን ለከት የለሽ የሤራ ፖለቲካና መንጀል ለማስቆም፤ መንግስት ራሱንና አካባቢውን ፈትሾ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ፤ በተለይ በዚህ ሤራ ዋነኛ ኢላማ ለተደረገው ለአማራ ሕዝብ በግልፅ ማሳወቅ የሚገባውን ተግባሮች ለይቶ ማውጣት ይኖርበታል፤ ከዚህ ውስጥ አንዱ ‹‹ንጋት›› ላይ የተከናወነውን ሤራ ነው!! የትኛውም አገር ወዳድና ንፁህ ፖለቲከኛ በዚህ ቃል ግራ ቢጋባ! እኔ ነኝ ግራ እምጋባው! ምክንያቱም በዚህ ቃል ግራ እሚጋባው የፖለቲካ ወንጀለኛ የሆነ ብቻ ነው!! እንሆ፤

የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032፤ የምንፈልጋት ኢትዮጵያ 50 ግለሰቦች ራሳቸውን፣ ተቋሞቻቸውንና የፖለቲካ ድርጅቶቻቸውን በመወከል፤ ለ11 ቀናት አብረው ውለው ለ8 ቀናትም አብረው አድረው ስለኢትዮጵያ ዕጣ-ፈንታ የመከሩበት ነው፤ ይህ ምክክር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሚስጥራዊ ነበር፤ በቀጥታ ወደ ‹‹ንጋት›› እንግባ፤ ‹‹ንጋት›› የአገራችንን ቀጣይ ብሩህ ጉዞን ያመለክታል፤ ‹‹የንጋት መርህ›› ከፈቀዳቸው አካሄዶችና አሰራሮች ውስጥ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ አመራሮችና ፖለቲከኞች በሚስጥር ወይም በህቡዕ መገናኘትን የሚፈቅደው አንዱ ነው፡፡ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ይህን ለቀጣይ የአገራችን ፖለቲካ መሻሻል ሲባል መግባባት ላይ የተደረሰበትን መርህና ዓላማ፤ ለዕኩይ አላማቸው ማስፈፀሚያ የተጠቀሙ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ አመራሮች፣ የመንግስት አመራሮችና ፖለቲከኞች አሉ ብሎ ያምናል፤ አማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ ጨምሮ፤ በቅርቡ የገጠሙን አገራዊ የፖለቲካ ምስቅልቅሎች የዚህ ውጤቶች እንደሆኑ ይጠረጥራል፤ በመሆኑም!! የለውጡ አመራር የሚከተሉትን ጉዳዮች ባስቸካይ እንዲመረምር ሀሳብ ያቀርባል፡-

 1. በሰላም እታገላለሁ ያለው ኦነግ ለምርጫ ቦርድ እጩዎችን የማሳወቂያ የጊዜ ሰሌዳ እንዲያልፍበት የሆነው፤ ድርጅቱ ሆነ ብሎ የፈፀመው መዘናጋት ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ይጣራ፡፡ ጊዜ የለም!!
 2. ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ /ኦ.ፌ.ኮ../ ምክንያት አስቀምጦ፤ ከምርጫው እራሱን ያገለለበት አካሄድ፤ ምክንያታዊ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ይጣራ፡፡ ጊዜ የለም!!
 3. የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አ.ብ.ን./ የቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስትርና የመንግስት አማካሪ የነበረው፤ አቶ በረከት ስምኦን በነበረው ህልም መሠረት የተቃቃመ/ የአቶ በረከት ህልም አስፈፃሚ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ይጣራ፡፡ ጊዜ የለም!!
 4. የፖለቲካ ድርጅቶችን በሚስጥር /በህቡዕ/ መገናኘት የሚፈቅደውን የ‹‹ንጋት›› መርህ፤ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም፤ ኦ.ነ.ግ.ና ኦ.ፌ.ኮ. ዓላማቸውን እንዲያስፈፅምላቸው ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በህቡዕ የሰጡት የፖለቲካ ውክልና አለ? ወይስ የለም? የሚለው ይጣራ፡፡ ጊዜ የለም!!
 5. ግድያ፣ መፈናቀል፣ መኖሪያ ቤትና ቤተ-እምነቶችን በማውደም፤ ባጠቃላይ የፖለቲካ ወንጀሎች በማቀናበርና በመፈፀም፤ ሕዝብን የማሰላቸት፣ ሕዝብ ‹‹ተለያይተን ብንኖር ይሻላል›› የሚል ድንዳሜ ላይ እንዲደርስ የማድረግ ሤራ ውስጥ፤ የኦ.ነ.ግ.፣ የኦ.ፌ.ኮ.፣ የአ.ብ.ን. እንዲሁም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፤ የተቀናጀ የዓላማ አንድነት አላቸው? ወይስ የላቸውም? የሚለው ይጣራ፡፡ ጊዜ የለም!!
 6. ሌላው!! ሉዓላዊነትን በተመለከተ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ-መንግሰት አንቀፅ 8 መሠረት፤ የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚገለፀው በዴሚክራሲያዊ ምርጫ በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት ነው፤ በመሆኑም በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ ክልልና በአማራ ክልል ውስጥ፤ የሚፈፀሙት ብሄር-ተኮር ግድያዎችና ከፍተኛ ማፈናቀሎች፤ የጥቃት ሰለባዎቹ በቦታው ሉዓላዊነታቸውን እንዳያረጋግጡ ለማድረግ ታልሞ፤ የሚፈፀሙ የፖለቲካ ወንጀሎች ናቸው? ወይስ አይደለም? የሚለው ይጣራ፡፡ ጊዜ የለም!!
 7. በተጨማሪም!! መንፈሳዊ-ንግርት /ትንቢት/ በሚል ሽፋን በመንፈሳዊ-እምነት ተከታዮች ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃን፤ ለፖለቲካ ፍጆታ /መሣሪያ/ እያዋለ የሚገኝ ኃይል /ቡድን/ አለ? ወይስ የለም? እንዲሁም ማንነው? የሚለው ይጣራ፡፡ ጊዜ የለም!!

የለውጡ መንግሰት እነዚህንና ሌሎች የፖለቲካ ሤራዎችን ፈትሾ ከውጤት ላይ በመድረስ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ ተፅእኖዎች ምክንያት የሰረፀበትን ብዥታ መግፈፍ፣ ክፉ-ትንቢቶችን መቀልበስ እና ሕዝብና አገር ማዳን ይኖርበታል፡፡ በዚህ ተግባር ውስጥ ከተለያዩ ክልሎች በኃይል የተፈናቀሉ የትኞቹም ዜጎች፤ ወደቀደመ መኖሪያቸው ተመልሰው /በድንኳን ተጠልለውም ቢሆን/ የሉዓላዊነታቸው ማረጋገጫ በሆነው ምርጫ ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ሊዘነጋ አይገባም!! ከዚህ አስቸካይ ተግባር ጎን-ለጎን የፖለቲካ አካሎች፣ የበጎ-ተፅእኖ ፈጣሪዎችና መንፈሳዊ አባቶች፤ በሕዝብ ላይ የሰፈነውን ብዥታ ለመግፈፍ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንዲያደርጉ እና ሕዝብ ወደመደበኛ ግንዛቤውና አኗኗሩ ገብቶ፤ በአገር-አቀፍ ምርጫው በመራጭነት እንዲሳተፍ የሚያስችለውን የምርጫ ካርድ እንዲወስድ ማድረግ፤ ምርጫ ቦርድም ሕዝብ ውስጥ በተፈጠረው ብዥታ ምክንያት የባከነውን ጊዜ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ የመራጮች ካርድ የመውሰጃ ጊዜውን እንዲያራዝም ከሚያስችለው ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ማድረግ አንገብጋቢ ተግባር ይሆናል፡፡ ጊዜ የለም!!

የመዝጊያ ሀሳብ!

ይህ መልዕክት የደረሳችሁ ኢትዮጵያዊ እህትና ወንድሞቼ!! በግልፅ እንድታውቁት የምፈልገው ማንኛውንም ጎራ መፍጠርም ሆነ ከየትኛውም ጎራ ውስጥ መካተት አልፈልግም!! እኔ ለራሴ የሰጠሁት ተግባርና ኃላፊነት የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን መመልከትና እይታዬን ለሕዝብ ማካፈል ነው! በመንፈሳዊ ማንነቴ ከተመለከታችሁኝ ከሁላችሁም የከፋ ሀጢአት የተሸከምኩ በደለኛ! በዓለማዊው ደግሞ በሚገባ ያልተማርኩ ነኝ! በእድሜ ከ37 ዓመት በታች ለሆናችሁ ታላቅ ወንድማችሁ፤ ከ37 ዓመት በላይ ለሆናችሁ ደግሞ ታናሽ ወንድማችሁ ነኝ!!

እባካችሁ!!  የትኛውንም እምነት የምትከተሉ እህትና ወንድሞቼ፤ ‹‹ሣልሳዊ ቴዎድሮስ›› በሚል በማህበረ-ቅዱሳን ሚዲያ የቀረበውን ትንታኔ በጥሞና እንድታዳምጡ፤ እንዲሁም ‹‹የተነበዩት አይፋለስም›› የሚባልላቸው የወሎው ሼህ ሁሴን ጅብሪል ‹‹ንጉስ አለ ብለህ አትወሳወስ በመርጫ ታልሆነ የለም የሚነግስ›› በሚል የገለፁትን መንፈሳዊ እይታቸውን ቆም ብላቹ እንድትመረምሩ እጋብዛችሁአለሁ፤ማንኛውም ‹‹ክፉ ትንቢት›› ቢኖር እንኳ የሚነገረው ተፈፃሚ እንዳይሆን ነው፤ አሁን በኢትዮጵያ ሕዝብና አገራችን ኢትዮጵያ ላይ እየተነገረ ያለው ክፉ ትንቢት፤ እውነተኛ ትንቢትና ከፈጣሪ በተላከ እውነተኛ ነቢይ የተነገረ ይሁን!! ወይም ሀሰተኛ ትንቢትና የህ.ወ.ሓ.ት. ጫና በደረሰበት መንፈሳዊ አባት የተነገረ ይሁን!! ወይም አገራችንንና ሕዝባችንን ውዥንብር ውስጥ በመክተት፤ መንግስት በውጭ ዲፕሎማሲው የያዘውን ጠቃሚ አቋም፤ እንዲለውጥ ለማድረግ በውጭ ኃይሎች የተቀናበረ ‹‹የሤራ-ትንቢት›› ይሁን!! ዞሮ ዞሮ ክፉው ትንቢት እኛው ላይ ነው የሚያርፈው!! በመሆኑም የክፉ-ትንቢቱን ውጤት ቁጭ ብሎ መመልከት? አማኝነት አይደለም!! የበይሆናል ዓለም /ዩቶፒያ/ ውስጥ ቁጭ ብሎም የሕዝብ ውክልና እንድንሰጥ የቀረበውን ዓለማዊ ምርጫ መግፋት? ከእምነት ጋር ጨርሶ አይገናኝም!! ስለዚህ በዓለማዊው ፖለቲካ ውድቀት የደረሰባቸው ቡድኖች፤ በመንፈሳዊው እምነታችን ላይ የፖለቲካ ቁማር እንዲጫወቱበት መፍቀድ ፈፅሞ አይገባም!! ማንንም ለምኜ ተለማምጬም አላውቅም! ዛሬ ግን ይህን ለማድረግ እገደዳለሁ!! በመሆም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ! ‹‹በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተነገሩ አስከፊ ትንቢቶችንና ፖለቲካዊ ሤራዎችን በማስተዋል ጥበብ እንለፋቸው›› ስል ልመና፣ ልምምጥና ተማፅኖ አቀርባለሁ፡፡ ጤና ይስጥልኝ፡፡

ቴዎድሮስ ጌታቸው

/ደራሲና የፖለቲካ ተመልካች/

ሚያዝያ 16/2013

/ድሬዳዋ/

ሠላም ለኢትዮጵያ ሠላም ለአፍሪካ

 

3 Comments

 1. በአንድ አንቀፅ መጠቅለል ትችል ነበረ ኮ፤ ይሄን ያህል መዛከር አያስፈልግም። My friend, ከተማኮ ነው እየወደመ ያለው?
  Failed state ምን ማለት እንደሆነ የሚጠፋህ አይመስለኝም። የአያ አሻግሬ መጨረሻ ወይ እንደ ጋዳፊ ዬሆናል፣ ብልጥ ከሆነ እንደ መንጌ ወደ ኤርትራ ይፈረጥጣል፤ Mark my WORD. ላለፉት ሶስት ዓመታት በአማራ ህዝብ የደረሰው መከራ በሰው ልጅ ታሪክ ደርሶ አያውቅም(እርጉዝ ሆዷ ተቀዶ ልጇ የተበላበት)። መንግስት እጁ የለበትም ብትል እንኳ ለመከላከል ፈቃደኛ አይደለም፤ ማውራት እንኳን አይፈልግም። ግን ከተጠያቂነት አያድነውም፣ ቁ 1 ተጠያቂው ደሞ ጠሚው ነው። MARK MY WORD፦አበይ የጋዳፊ ዕጣ ይደርሰዋል ወይም UAE OR SAUDIOR ERTIREA ይፈረጥጣል፤ እስከ አሁን የቆየው በአንድ መንገድ ብቻ ነበረ፣ አሁን ያን ገመድ በጥሶ አንገቱ ላይ አረጓል።

 2. ቤይሩት ውስጥ ኢትዮጵያዊት አካልዋ ተቆራርጦ ግማሽ የተቆራረጠው አካልዋ በፌስታል ተጥሎ ስለተገኘ ፤ በምን ሂሳብ ነው አረብ የቤይሩት ተወላጆች ናቸው ወንጀሉን የፈጸሙት ብለን ደምድመን አረቦች መልዕክት ላኩ ልንል የምንችለው?
  ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ህዝብ በወገን ኢትዮጵያኖች እየታረደና እየተከታተፈ በየቀኑ እያየን ፤ እቺን ሙዋች ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያዊት ገድሎ/ገደላት አካልዋን ቆራረጥዋት የሚለው እጅግ በጣም ሊታሰብበት የሚገባ ነገር ነው ።። ቤይሩት ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር አይልዋል። ባንክ ቤት የገባ ገንዘብ አይወጣም። ህዝቡ ካሽ በየፍራሹ ስር ነው የሚያጉረው፤ ባንክ ከከተተ መቼ ሊያገኘው እንደሚችል ምንም ማስተማመኛ ስለሌለ።
  ስለዚህ 1)ከባንክ ውጪ ያከማቸችውን ገንዘብ ለመዝረፍ ሌባ ገድሎዋት በህግ አስከባሪ እንዳይያዝ አካልዋን ለማስወገድ እንዲመቸው ቆራርጦ ጣላት የሚለው ይመስላል።
  2)ብዙ ኢትዮጵያውያን እንደሚያደርጉት የቤይሩት ሀብታም ፍቅረኛ እጮኛ ቅምጥ ከሆነችም ምናልባት ኢኮኖሚው ስለወደቀ በቤይሩት እንችን አልደግፍሽም የቤት ኪራይም ሌላ ተቆራጭ የምሰጥሽን አቋርጥብሻለሁ ካላት እርስዋም ክፈልልኝ አለበለዛ ለህጋዊ ባለቤትህ አጋልጥሀለው ብላው
  ከሆነ ከምታጋልጠኝ ብሎ ገድልዋትም ሊሆን ይችላል። ወይም የፍቅረኛዋ ሚስቲቱም ትሆን ይሆናል የገደለቻት።
  3) የኢትዮጵያውያን የዘር ጭፍጨፋ አራጆች (የታራጅ ዘሮች በቀልም) ሰለባም ልትሆን ትችላለች።
  እንጂ የአባይ ግድብ ስለተገደበ ተገደለች የሚለው ከሩቅ የተቀዳ Far Fetched ግምት ይመስለኛል በበኩሌ።

 3. The Silent majority

  Forget Ethio. 360 because they are against Dr. Abiy Ahmed starting from day one. They have no substance. All of them are trying to cover up all the bad things they have been doing in Ethiopia and also they are mercenaries bought by financiers such as TPLF and now Egypt and tomorrow someone else.

  Believe me, all of those who are so blinded by wrong theory will be ashamed very soon. Abiy is genuine and will serve Ethiopia effectively. Abiy will prevail. I don’t even think that he is concerned about this as they said the dogs are barking because it is their character but the camels are going.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.