ዐማራ የተጋረጠበትን መንግስታዊ ጥቃት፣ ጭፍጨፋና የከተሞችን ውድመት ለማስቆም በጋራ ቆርጦ መታገል አለበት – ሞረሽ ወገኔ

mreshሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ዓርብ፣ ሚያዚያ ፲፭፣ ፪ሺ ፲፫ ዓ.ም. (Apr. 23, 2021)
ቅጽ ፰ ቁጥር ፫

ለሀያ ሰባት አመት በወያኔ ማኒፌስቶ ጥቃት ሲደርስበት የኖረው የዐማራ ሕዝብ፤ ዛሬም ጥቃትና ጭፍጨፋው፣ በለውጥ ስም ከወያኔ ኢህአዴግ ወደ የኦሮሙማ ብልፅግና በተቀየረውና በአብይ አህመድ ድጋፍ በሚደረግለት ፀረ ዐማራ ኃይል ከመቸውም በበለጠ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እንደሚታወቀው ኦነግ 40 አመት ሙሉ በቆራጥነት ታግሎ አንድ መንደር ተቆጣጥሮ አያውቅም። ኦነግ የሚታወቀው በጭካኔ፣ መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃንን ገድሎ በመሰወር ነበር። አሁን ግን በመላው ኢትዮጵያ የኦነግ ጦር በኦሮሞ ብልጽግና መንግስት ይሁንታ ተጠናክሮ ግድያውን የሚፈፀመው ድሽቃና ስናይፐር የሚባል አልሞ ተኳሽ መሳሪያ ታጥቆ ነው። በተለይም በዐማራ ሕዝብ ላይ ያለማቋረጥ የሚፈፅመው ጭፍጨፋ፣ ከቤትና ንብረት ማፈናቀል አልፎ ከተማ እስከማውደም የደረሰው፤ አረመናዊው ወረራና ጥቃት መንግስታዊ መዋቅር ሰራሽ እንደሆነ የችግሩ ሰለባዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚታዘዘው የመከላከያ ሰራዊትም የሀገራችንን ሉዐላዊነት በጎንደር በኩል በሱዳን ሲደፈር ወደጦርነት አንገባም የሚል የውሳኔ ሀሳብ በጀኔራል ባጫ አንደበት በአደባባይ ተነግሯል። ሰሞኑን የአጣዬ ሕዝብ በየኦነግ / ኦዴፓ ሲጨፈጨፍና ከተማው ሲቃጠል ሕዝብና አገር ከጥቃት ይታደጋል የተባለው መከላከያ ሰራዊት ጉዳዩ ከአቅሜ በላይ ነው በማለት ህዝቡን ለመንግስታዊው ሽፍታ አሳልፎ በመስጠቱ፣ ሕዝቡን በጭካኔ እንዲፈጅ፣ የአጣዬ ከተማም በቃጠሎ እንዲወድም ሙሉ ትብብር አድርጓል።

በዐማራ ሕዝብ ላይ ሰብዓዊ ፍጡር ያደርገዋል ተብሎ የማይገመት ወንጀል እየተፈፀመ ለድፍን ሶስት አመት ቀጥሏል። ጥቃቱ በህፃናት፣ በእናቶች፣ በእናት ማህፀን ውስጥ ባለና ባልተወለደ ፅንስ ላይ ሳይቀር አሰቃቂና ታሪክ ይቅር የማይለው አገዳደል ተፈፅሟል። በጅምላ የሚጨፈጨፉት ንፁሀን ከኢትዮጵያ ባህል ውጪ በጅምላ እንደቆሻሻ ተዝቀው የሚጣሉትና የአውሬ ራትና ምሳ የሚሆኑበት አገዛዝ ላይ ወድቀናል። የንፁሀንን ደም የሚታደግ መንግስትም እንደሌለ በተከታታይ ዐማራው በሚደርስበት በደል ሁሉ አረጋግጠናል።

ብአዴን / አዴፓ የወያኔ አሽከር ሆኖ አብዮታዊ ዲሞክራሲን እያቀነቀነ 27 ዓመት እያስገደለ የኖረ፤ የዐማራን ሕዝብ ስነልቦና ያልተላበሰ፤ ስለሰብዓዊ መብት ግንዛቤ የሌለው፤ ሎሌ እንደሆነ ይታወቃል። አዴፓ ዛሬም ጌታ ቀይሮ የአብይ አህመድን የመደመር (ገዳ፣ሞጋሳ) የወረራ ሥርዓት ተሸካሚ ሆኖ የጨፍጫፊው የኦዴፓ/ ኦሮሞ ብልፅግና ጉዳይ አስፈፃሚ በመሆን ስለሚሰራ፤ ከሽመልስ አብዲሳ የወረራ አካል ጋር ስምምነት ላይ ደረስን እያለ ከማዘናጋት ውጪ እንደ ዐማራ ክልል መንግስት ሕዝቡን እንደማይታደግ በተደጋጋሚ አስመስክሯል።

ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ ማዘናጋት የኦሮሙማ አንዱ የቁማር ስልት ነው። ኢትዮጵያን እየቦረቦሩ የሚያጠፏት የኦሮሞ ፓለቲከኞች በጋሞ ህዝብ ጭፍጨፋ ጀምረው፤ ዐማራውን በወለጋ፣ በመተከል በሰሜን ሸዋ፣ አጣዬ፣ ካራቆሬ፣ አዳይቱና ወ ዘ ተ፣ በደቡብም በአማሮ፣ ጌዲዮ፣ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ወላይታ ወ ዘ ተ ነገዶች ላይ በኦሮሚማ መንግስት መራሹ ወራሪ ኃይል ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። ነገር ግን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚስትር አብይ አህመድ ሆነው ሳለ፣ ጥቃት የሚያደርሱት “ሸኔ” የሚል የዳቦ ስም የሰጧቸው መንግስታዊ ሽፍቶች ናቸው እንድንል ከሚያስገድደን ከብዙ በጥቂቱ፣

 • ጨካኙና ገዳዩ ሠራዊት በአደባባይ ድንኳን ጥሎ፣ ስንቅና ትጥቅ ተሟልቶለት የሚሰለጥን ስለሆነ፤
 • የሠራዊቱ አባላት አንዳንዴ የመከላከያ፣ አንዳንዴ የልዩ ኃይሉ አንዳንዴ የኦነግ አልባሳት ስለሚለብሱ፤
 • አሸባሪው ሠራዊት ዲሽቃ፣ ስናይፐርና ብሬን የታጠቀና ሙሉ የሎጂስቲክ አቅርቦት የተሟላለት ስለሆነ፣
 • ሠራዊቱ በብዛትም፣ በትጥቅም፣ በመሳሪያም የተጠናከረ ስለሆነና መከላከያውም ከአቅሜ በላይ ነው ማለቱ፤
 • በተለይም የብልፅግናው መንግስትና ጠቅላይ ሚንስትሩ አንድም ቀን ሌላው ቢቀር የህፃናትና የሴቶች በግፍ መገደል ጉዳዬ ስለማይላቸው።
 • ኮማንድ ፓስት የሚታወጀው ለሟቾች ሳይሆን ለገዳዮቹን ሽፋን ለመስጠት ነው። ምክንያቱም ኮማንድ ፓስቱ ዐማራን ከዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ለመታደግ እንዳልሆነ በመተከል ስላየን፣ በኦሮሙማው ተስፋፊ መንግስት ተስፋችን ተሟጧል።

ዐማራው ራሱን ከጊዜው ጋር በተጣመረ ሁኔታ መደራጀትና መመከት ይኖርበታል። የዐማራው መዳኛ አንድና ብቸኛው መንገድ በሕብረት ቁሞ የህልውና ትግል ማድረግና ስልጣንን የህዝብ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው። ዐማራው እየተፈጸመበት ያለውን ወንጀል የሚመጥን ትግል ውስጥ መግባት የግድ ይላል። ዐማራው የመግደል ዓላማ ባይኖውም ላለመገደል መከላከል ግን ተፈጥሯዊ ግዴታው ነው። ኢትዮጵያን የሚጠሉ ፋሽሽቶች እጃቸው የወደቀውን የመንግስት ስልጣን ተጠቅመው ዐማራው ላይ በሰፊው የሚያደረጉት ወረራና ጭፍጨፋ በሂደት ሁሉንም የኢትዮጵያ ነገዶችና ጎሳዎች የሚያዳርስ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህም በመሆኑ ሞረሽ ወገኔ የሚከተሉትን ወቅታዊ ጥሪዎች ያደርጋል።

 1. ዐማራው ከብአዴን/አዴፓ የበለጠ ጠላት የለውም። ብአዴን ቀደም ሲል የሕውሃት ተላላኪ ነበር። ዛሬ ደግሞ የኦዴፓ ሞግዚት ሆኖ ዐማራውን እያስጨፈጨፈ ነው። ዐማራው ምንም አይነት የመንግስት ውክልና እንደሌለው ግልጽ ከሆነ ሰንብቷል። ስለሆነም ሕዝባዊ ቁጣውን በሙቱ አዴፓ ላይ አተኩሮ ወደማይቀረው መቃብሩ ገፍቶ መጣል አለበት።

 

 1. ዐማራው ለገዳዮዎች የሚከፈለውን ግብር መክፈል ማቆም አለበት። ዐማራው በዛሬይቷ ኢትዮጵያ ከትምህርት፣ ከስራ፣ ከኢኮኖሚ ልማት፣ ከጤና ተቋማት ምስረታ ከተነጠለ 30 ዓመታት አልፈዋል። በመሆኑም ገዳዮችን አሰልትኖና አስታጥቆ ለሚልክበት አገዛዝ ግብር መክፈሉን በእንቢተኝነት ማሳየት ይኖርበታል።

 

 1. ሊገመት በማይችል ደረጃ ዐማራው በራሱ በወገኑ በዐማራ ተክዷል፤ አብዛኛው የዐማራ ምሁር በወገኑ ላይ የሚደርስን ሰቆቃ፣ ፍዳ፣ ግድያና መሰደድ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል። ይህን ሁኔታ ለመለወጥ እንደ እሳተ ገሞራ የተነሳው ትውልድ፣ የዐማራ ምሁራንንና የአገዛዙ ተለጣፊዎችን አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ አስፈላጊውን ጫና ማድረግ ይኖርበታል።

 

 1. በኦዴፓ/ኦሮሙማ ሠራዊት ልጁን፣ እናቱን፣ አባቱን፣ ወዳጁን፣ ዘመዱን አጥቶ የተፈናቀለው የዐማራ ሕዝብ እንደፈረደበት በሀዘን ላይ ርሀብ፣ እርዛት ታክሎበት ያለመጠለያ ወድቋል። ስለዚህ አዴፓ “አበለፅጋለሁ”፣ የሚለውን ቧልት ትቶ በአስቸኳይ ተፈናቃዮቹን በመንግስት በጀት አስፈላጊውን ሁሉ አሟልቶ ወደቅያቸው እንዲመለሱ እንዲያደርግ፣ ግፊት ማድረጉ የዐማራ ሕዝብ ትግል አካል መሆን ይኖርበታል።

 

 1. ዐማራው በፋሽሽታዊ አገዛዙ አውራ ጠላት ተደርጎ ለዘር ማጥፋትና ለዘር ማጽዳት ወንጀሎች በሰፊው የተጋለጠው ኢትዮያዊነትን መለያው በማድረጉ ነው። የጣልያንና የሌሎች የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችን ፍኖተ ካርታን የፖለትካ ፕሮግራማቸው ያደረጉት የትግሬ/ወያኔና ኦነግ በሀገር ላይ የጫኑት አራዊተ ሕገ መንግስት ዐማራን ለማጥፋት የተዘጋጀ ሰነድ መሆኑ በገሃድ ሲታይ ሶስት አስርተ ዓመታት ሊሆነው ነው። ይህ የአፓርታይድ ስርአት የተቀየሰበት ኢትዮጵያን የማድከምና የማፈራርስ ጉዞ በአብይ አህመድ አሊ የሦስት አመት አጭር የነውጥ ጊዜ እየተፋጠነ ነው። በውጭም ሆነ በውስጥ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ህልውና ፈተና ላይ ወድቋል። ስለሆነም ይህን ህገ አራዊት መቀየር አለበት፣ የሚሉ የዐማራና ህብረ ብሄራዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ከአገዛዙ የምርጫ ትያትር እራሳቸውን አግልለው፣ የአብይ አህመድ የኦሮሚማ ካምፓኒ ከስልጣን ወርዶ ሁሉን አሳታፊ የሽግግር መንግስት ይመሰረት ዘንድ በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ እናቀርብላቸዋለን።

 

 1. አብይና የኦሮሙማ አገዛዙ የሚፈጽመው መንግስታዊ ጭፍጨፋና ግፍ ሞልቶ በመፍሰሱ፣ በተለያዩ የዐማራ ከተሞች የታየው ሰፊ ሕዝባዊ ቁጣና አስፈላጊና ጊዜው የሚጠይቀው ነው። ይህ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ቀጣይነት እንዲኖረውና የሚፈለገውን መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ይችል ዘንድ ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበና በወጣቱ የሚመራ መሆን ይገባዋል። የሙቱ ብአዴን / አዴፓ ቱባ ባለስልጣኖች የኦሮሙማ የሎሌነት

ሚናቸውን ለመወጣት ሲሉ ይህን ሕዝባዊ ቁጣ ከማይቀረው የፖለቲካ መቃብራቸው የሚያድናቸው መስሏቸው የአብንን ወይም ሌላ ህዝባዊ ድጋፍ ያላቸውን ድርጅቶች አመራርና አባላትን ለማሳደድ ቢሞክሩ፣ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ለሕዝብ ቅርብ የሆኑት የብአዴን / አዴፓ የበታች ካድሬዎችና አባላት ከሕዝባቸው ጋር እንዲቆሙ ጥሪያችን ይድረሳቸው።

በመጨረሻ ዐማራ ወገናችን እንዲያውቅ የምንፈልገው የተጋረጠብህን ተከታታይ የዘር ማጥፋት የህልውና አደጋ በዘላቂነት ለመቅረፍ ይቻልህ ዘንድ፣ ገበሬ፣ ወታደር፣ ምሁር፣ ተማሪ፣ ቄስ ፣ ሸህ፣ ወዘተ ሳትል፣ እየተናበብክና እየተደራጀህ፤ ራስህንም ሆነ ኢትዮጵያን ከጥቃት የሚያድን ሌላ አስተማማኝ የመንግስት አካል እንደሌለ አውቀህ፣ ጠላቶችህን በሚገባ ለይተህ፣ እራስህን ከተጋረጠብህ አደጋ በጽናት በመከላከል፣ ከአለመኖር ወደመኖር በትግልህ መሻገር ግዴታህ እንጂ ምርጫህ እንዳልሆነ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ወቅታዊና ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል።

 

አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፤ ሁሉም ዐማራ ለዐንድ ዐማራ!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

www.moreshwegenie.org[email protected]

 

3 Comments

 1. አማራ አንድ ሆኖ መነሳት አለበት። የ አማራ ክልል መንግሥት አልባ እንዳይሆን ጥንቃቄ መደረግ አለበት። አዴፓን ለ አማራ እንዲቆም ግፊት ማድረግ እና ቀስ በ ቀስ መተካት ነው እንጂ እንዲሁ ማፍረስ ህዝባችንን ለ አደጋ ያጋልጣል። ከ ሞረሽ ወገኔ የ አማራ መንግሥትን አስወግዱ የሚል ምክር መስማቴ አሳዝኖኛል። ከ ምንም መንግሥት ያለው መንግሥት መኖሩ ይሻላል። ረፎርም ማድረግ ነው ቀጣይነት ያለው።
  የ አማራ ህዝብ ህልውና የሚረጋገጠው ወጣቱ ሁሉን ነገር ትቶ ልዩ ሃይሉን ሲቀላቀል እና የ አማራ መንግሥት ሲኖር ነው። ይሰመርበት።

 2. ሞረሽ እንደጠራው የአማራ ህዝብ “ሆ ብሎ ተነሳ” እንበል? ምን እንዲያደርግ ነው ትዛዝ የምትስጡት? ሊያደርግ የሚችለውስ ምንድነው?
  1። ብልጽግናን በምርጫ ከአማራ ክልል ማስወገድ እና አብንን (ሌላ የለም!) ወደ ሥልጣን ማምጣት። ይቻላል!
  2። በአብን መሪነት እንደጁንታው በጉልበት መንግስት መገልበጥ መምከር። ከዚያስ? ሌላውን ህዝብ በጉልበት መጨፍለቅ። አያስኬድም!
  3። በአብን መሪነት አማራ ከፌደሪሽኑ እንደሚወጣ ረፈረንደም ማመቻቸት (እንደ ብሬግዚት!)። ይቻላል!
  4። አብን ወያኔ ላይ ነፍስ ዘርቶባት መተባባር እና እስከ አጼ ዮሃንስ ድረስ የነበረውን የአቢሲኒያ [አማራና ትግራይ] መንግስት መመስረት። በአጭር ጊዜ ላይሆን ይችላል። ግን “ኦሮሙማ”ን ፍራቻ ወይም በእልህ በሂደት ሁለቱ ለጊዜውም ቢሆን ሊቀራረቡ ይችላሉ። ችግሩ በአቢይ ቦታ ጃዋርን ብታስገቡት ወያኔ ጃዋርን ትመርጣለች (መቼስ ታስሮ አይቀር!}። ከምርጫ ዉጭ በፈለጋችሁት መንገድ አስቡት አያዋጣም፣ ማንንም አይጠቅምም፣ ተነስ ያላችሁትን የአማራ ህዝብ ጨምሮ። ፍርድ አዋቂው የአማራ ህዝብም ይህ አይገበዘብም ማለት አይቻልም። ለዚህም ነው የዚህ አይነቱ “ተነስ፣ ታጠቅ፣ ዝመት” ጥሪዎች መሬት ላይ ጠብ የማይሉት።
  በምርጫ ብቻ!

 3. ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ አስተያየቶች ለሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጂት፤ለአብንም ሆነ ለሌሎች የአማራ ድርጂቶች ጠቃሚ እና ፍሬአማ ምክር ነው። የአማራ ድርጂት የሚባሉት ሁሉ ይህንን የመሰለ ምክር እና ተቀብሎ ተግባራዊ ቢደረግ ለአማራው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ይጠቅማል። እንዲሁም በተለያየ ስም ማሰሪያው አማራ በሚል የተቋቋሙ ድርጂቶች ከልብ የመነጨ ለአማራው ተቆርቋሪነቱ ካለ ልዩነታችሁን በማስወገድ በአንድ ላይ ብትታገሉ ለሁሉ ይበጃል እንጂ አይጎዳም ።እስካሁን ባለው ሁኔተ ግን አማራው እየተጎዳ ያለው ባለው መንግሥት እና ኦሮሙማ ብቻ ሳይሆን ግንባር መፍጥር አቅቶት በየራሱ በአማራ ስም የተደራጁ ድርጂቶች ነው። አንድም የአማራ ድርጂት ነኝ የሚል ድርጂት የተፈናቀለን አማራ አበላ አጠጣ አቋቋመ የሚል መግለጫ እና ማሳሰቢያ የሰጠ የለም። ሌላውን ወቅሶ መግለጫ እና መሳሰቢይ በሚዲያ ከመለጠፍ ጎንም የተደረገውን እርዳታም አሳወቁ እኔም በአማራ እነቴ የምችለውን ልተባበር።ስለሆነም ከላይ የተሰጡትን ምክር እና አስተያየቶች ተቀበሎአቸው ።ዝውዱ እና ከድርም ይህንን የመሰለ አስተዋይነት የሞላበት እና አመርቂ ምክራችሁ አይለየን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.