አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ልዩ አስቸኳይ ጥሪ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ

women g

ዛሬ የአገራችን ኢትዮጵያን አገራዊ ህልውናን የሚፈታተን፣ ህዝቧንም በተለይም የአማራውን ህዝብ በባሰና በከፋ ሁኔታ ለሞት፣ ለእልቂትና ለመፈናቀል በሰፊው ያጋለጠ ወቅት ውስጥ መገኘታችን  የፈጠጠ ነባራዊ መራራ ሀቅ ነው።አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት፣ ይህንን መራራ እውነታ በጥልቅ በማስተዋል በቆራጥነት አገርና ህዝብን ለማዳን አስቸኳይና ፍቱን መፍተሄ መስጠት ዛሬ ነገ የማይባል የወቅቱ አጣዳፊ ተግባርና ታሪካዊ ሀላፊነትን የሚጠይቅ ነው ብለን እናምናለን።

ላለፉት ሶስት አመታት በአብይ አህመድ መንግስት እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለይም የአማራ ህዘብ በገዛ አገራቸው ተሰደዋል፣ ተፈናቅውል፣ ተግድለዋል፣ ጭካኔ ለተሞላበ ጥቃትና እልቂት  ተዳርገዋል፣በጥላቻ ታርደዋል። ነፈሰ ጡሮችና ህጻናት ቤታቸው በላያቸው ላይ ፈርሶና ተቃጥሎ መንገድ ላይ ወድቀዋል፤ በርካታ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ካህናት በቁም ተቃጥለዋል፣ በሰይፍ ተቅልተዋል፣ የተዋሀዶ ቤተ ክርስትያኖች ተቃጥለዋል። ዛሬም በአብይ አህመድ መሪነት በመከተል፣ በአጣየ፣ በሸዋ ሮቢት ወዘተ በአማራው ህዝብ ላይ ጦርነት ታውጆበት ሰላማዊ ህዘብ በመንግስት የጦር ሃይልና በኦንግ/ሸኔ ሽፋን በዘመናዊ መሳሪያ በታጠቁ ሀይሎች ያልታጠቀውን ሰላማዊ ህዝብን ሴቶችና ልጆችን እየገድሉና እፈናቀሉ ነው።  ሁለተኛ አመታቸውን ያያዙት በደንቢደሎ በአማርነታቸው የታፈኑት ወጣት ተማሪዎች ጉዳይ እስካሁን ድረስ መልስ አልተገኘም፤ ለእንዚህ ወጣቶች ህይወት፣ በአጠቃላይም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ አልበገር ባልው በአማራ ህዝብ ላይ በየእለቱ የሚፈጸመው  ግፍና አረመናዊ ተግባር መንግስት ነኝ ባዩ እያወቀው የሚደረግ ተግባር ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚያቀነባብረውና የሚመራው ሌላው የዘመናችን ናዚ/ሂትለር የኦንጉ አብይ አህመድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። ይህ ግንዛቤም ለምንሰጠው መፍትሄ ቁልፍ ነው። እንዲሁም ስልታዊ፣ ተመጣጣኝና ተገቢ ምላሽ በመስጠት ህዝባችንና አገራችንን በቶሎ እንታደግ ዘንድ ይረዳናል፣ ይህንንም እውን ለማደረግ በአንድ መንፈስ፣ ልበ ቁርጠኝነታችንን እናሳይ ዘንድ ወገናዊ የትብብር ጥሪ እናስተላልፋለን ።

ዛሬ አገራችን እንደ አንድ ነጻ አገር ያላት ህልውና በየቀኑ እይተሸርሸር መምጣትና ሀዝቧንም ለማያባራ አስቃቂ ግድያና እልቂት በሰፊው መዳረግ የአብይ አህመድ የጎሳ መንግስት መገለጫ ውጤት ነው። አገራችንና ሀዝባችንን ከዚህ አስከፊ የጥፋት መንገድ ለማዳን ወንጀለኛውን አብይ አህመድ በሙሉ ሃላፊነት ተጣያቂ በማደርግ በአስቸኳይ ከስልጣኑ መውረድ ቅድሚያ የሚሰጠው የመጀመርያው የአገር ማዳን ተግባር ነው።  በተጨማሪም ከዚህ አጥፊ አረመኔ መንግስት ጋራም በተለያየ መንገድ የሚተባበሩት ምሁራን፣ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችም ሆኑ ሌሎች ከታሪካ ተጠያቂነት አያመልጡም፤ አሰላለፋቸውን በቶሎ ወደ ህዝብ ወገን  እንዲያደርጉ አጥብቀን እናሳስባለን።

የአብይ መንግስትና መሰሎች ለኢትዮጵያውያን ሆነ ለአማራው ህዝብ ነጻነትና ደህንነት ይቆረቆራሉ ብሎ ተስፋ ማድረግ አደገኛ ሞኝነት ነው።  አብይ አህመድ መቶ ሺ ሰው በአንድ ቀን ማረድ እችላለሁ ብሎ የዛተና የደነፋ፣ ከፍተኛ የተክለ ሰውነት ቀውስ የተጠናወተው አረመኔ፣ ያሻገርናል ብሎ ተስፋ ማደረግ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንዲፈለፈል መጠበቅ እንደማለት ነው። የወያኔን አመራር በኦነጋዊ የጎሳ መንግስትና አስተሳሰብ መተካት ለኢትዮጵያ ህዝብ እውነትኛ ለወጥ አለመሆኑ በተግባር ተረጋግጧል፤ እንዳወም ከእሳት ወደ ረመጥ ሆኖል እንጂ፤ ይህ የጎሳ ክልል ስርአት ወገንን ከወገን የሚለያይ፣ አገርን የሚከፋፍል የርስ በርስ ጦርነት የሚጋብዝ፣ ህዝብን ለእልቂት፣ ለድህነት፣ ለመፈናቀልና ለባርነት የሚዳርግ ስልሆነ ባስቸኳይ መወገድ አለበት። በጎሳና በዘር ላይ የተመሰረተ ጸረ ኢትዮጵያ ‘ህገ መንግስት’ ላይ ተመርኩዞ፣  በህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቶ እልቂት በመፈጸም ምርጫ አካሂዳለሁ ማለት በህዝብና በአገር ላይ መቀለድ ነው። ስለዚህም ፍትሃዊና ነጻ ምርጫ ለማካሄድ ከተፈለገ በቅድሚያ የኦነግ/ሸኔ አላማ አስፍፈጻሚ የሆነውን አብይ አህመድን ከስልጣን አስወገዶ ኢትዮጵያዊና ህዝባዊ የሆነ የሽግግር መንግስት መመሰርት ወሳኝና አስፈላጊ የመፍትሄ ሂደት ነው።

የወያኔ/ኦነግ/ኢህአደግን መሰርታዊ አላማና ግብ ለማሳካት ብልጽግና ፓርቲ፣ (የኦነግ የዳቦ ስም፣ ኢትዮጵያውነት የተራቆተው አስምሳይ ድርጅትን) የሚመራው አብይ አህመድ በሰልጣን ለመቆየት ማንኝውንም አረመናዊ ተግባር ሁሉ እንድሚያድርግ በተደጋጋሚ ገልጾል፣ ይህ ተግባራዊ እንዳይሆን ማድረግ የእኛ የአገር ወደድ ኢትዮጵያውያን ሃላፊንት ነው።  የመላው ኢትዮጵያዊ ሰባአዊ መብት፣ የአማርውን ህዝብ ደህነንትና የአገር ህልውናን ማስጠበቅ የያንዳንዳችን ሃላፊነት ነው፣ ይህንን ሃላፊነት በቁርጠኝነት ከተቀብለን ግዴታችንን መወጣት እንችላልን፣ የማይቻል ነገር የለምና።

በአብይ መንግስትና በተባብሪዎቹ ላይ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሳዊ ማእቀብ እንዲደርግ በድጋሚ የትብብር ጥሪ እናቀርባለን። በያለንበት ቦታ፣ በሚያስፈልገው የትግል ዘርፍና አቅም ሁሉ ከወገኖቻችን ጎን እንድንቆምና ወሳኝ ትብብር እንድናደርግ በሙሉ ልብ ዝግጁ ሆኖ መገኘት ይጠበቅብናል። ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ዛሬ ኢትዮጵያ አገራችንና ህዝቧን  ከኦነግ/አብይ ናዚያዊ መንግስት የሚያደርሰውን ጥቃት እንድንከላከልና እናድናት ዘንድ ለመላ ኢትዮጵያውያን በተለይም ለመከራው ገፈት ቀማሽ ለኢትዮጵያውያን ሴቶች ይህን  ልዩ የትብብር ጥሪ እናቀርባለን። እኛ ኢትዮጵያውያን ሴቶች፣ እንደ ጀግኖች ቅድመ አያቶቻችን ተባብረን ከተነሣን አላማችንን ከማሳካት የሚያግድን ምንም ኀይል አይኖርም።

 

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ጀግንነት ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!!

አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት

ሚያዚያ፣ 2013።

2 Comments

  1. በትክክል በዚህ ሰዓት ህዝብ መገንዘብ ያለበት ይህንን ነዉ፤ከሞትን አይቀር ትርጉም ያለው ሞት እንሙት
    አለበለዚያ ልክ እንዳሁኑ ከዉሻ ሞት ያነሰ ሞት መሞታችን ይቀሬ ነዉ፡፡

  2. “…ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ማዕቀብ ..” ስንቶቻችንስ እናውቅበትስ ይሆን? እስከመቼ ድረስስ ነው ማዕቀቡን የምንገፋበት? ለማስታወስ ያህል በዳያስፖራ ኢኮኖሚያዊና ተመሳሳይ ማዕቀብ ተጥሎ ነበር በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመጨረሻ የስልጣን ወራት ዘመን። ኢህአዴጎች ወድያውኑ ኃይለማርያምን አስወግደው ሌላ የኢህአዴግ መሪ ተክተው አማለሉ ድያስፖራን ፤ የዳያስፖራ ማእቀብም ተነሳ ልክ አብይ ወደ ስልጣን እንደመጣ፤ ተቃዋሚ ከእስር ፈታ ፣ ከውጭ ሀገር ያሉ ተቃዋሚም ግቡ አለ እና ማእቀብ ተነስቶ ድል ተባለ። አሁንም ሌላ ማእቀብ ዳያስፕራው ከተጣለ እስከመቼ ነው ማእቀቡ የሚገፋበት? አላማችን ምንድን ነው? የሚለው ሊታሰብበት ይገባል። የአማራ ግድያ ዘር መጥፋቱ መቆም ብቻ ሳይሆን አላማችን ሊሆን የሚገባው ዘር ማጥፋቱ እንዳያንሰራራ የሚያደርግ አላማ ይዘን እንደምንገፋበት እርግጠኞች መሆን አለብን። ዘር ጨፍጫፊዎች እረፍት ውሰዱ ቫኬሽን ሂዱ እና ተመለሱ የሚያስብል ማእቀብ መሆን አይገባውም ።ዘር አጥፊ የተባሉትስ በምን ምክንያት ዘር ማጥፋታቸውን ያቆማሉ ማእቀብ ስለተጣለ? አብይ ከስልጣን ወርዶ ሰላም ቢሰፍንስ ዘር አጥፊዎቹ ሚስጥራቸውን እርስ በእርስ እያወጡ እየተወነጃጀሉ እንደማይከዳዱ በምን እርስ በእርስ ተማምነው ሰላም ያገኛሉ? ለማንኛውም የተጠራው ማእቀብ ትክክል ነው። ለሶስት አመት እና በላይ ጊዜ ያላቆማችሁም ግፉበት።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.