/

ከደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በመጪው ግንቦት ምርጫ ለማካሄድ የመራጮች ምዝገባ እያከናወነች ትገኛለች፡፡ ፓርቲዎችም የምረጡኝ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡

niss 1

መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ እያካሄደ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ በጽንፈኞቹ የህወሓትና የኦነግ-ሸኔ ቡድኖች እንዲሁም በሌሎች ታጣቂዎች ላይም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በታለመለት ጊዜ ለማካሄድና በመጀመሪያው ዙር ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት እንዲጀምሩ መንግስት በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ ነው፡፡

ይሁንና እነዚህ አዎንታዊ ተግባሮች እየተከናወኑ ባሉበት በአሁኑ ወቅት መንግስት በሳይንሳዊና ገለልተኛ በሆነ መንገድ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በህግ አግባብ እንዲፈቱ አቅጣጫ አስቀምጦ እየሰራባቸው ያሉትን ከማንነት፣ ከአስተዳደር ወሰንና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማድበስበስ፤ ሀገሪቱን ወደ ግጭትና ትርምስ ውስጥ ለመክተት ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲፈጥር የውስጥና የውጭ ሃይሎች ተጣምረው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ መሆኑ በበቂ መረጃና ማስረጃ መረጋገጡን ከደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ አመልክቷል፡፡

ሀገራዊ ትርምስ ለመፍጠር የተዘጋጁ ሰነዶችና የጥፋቱን ተዋናይ አካላትንም የሚግልፅ መረጃ በደህንነትና በጸጥታ መዋቅሩ እጅ መግባቱንም ጠቁሟል፡፡

መንግስት መጪው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ካለው ፅኑ ፍላጎትና ከተጣለበት ሀገራዊ ሃላፊነት የተነሳ የጽንፈኛ ሃይሎችን ተግባር በሆደ ሰፊነትና በትዕግስት ሲከታተልና በአንዳንዶቹም ላይ የእርምት እርምጃ ሲወስድ መቆየቶን ያመለከተው መግለጫው፤ይሁንና እነዚህ ፅንፈኛ ሀይሎች በማህበራዊ ሚዲያው የሚታየውን ልቅነት ለእኩይ ሴራቸው በቅስቀሳ መሳሪያነት በመጠቀምና የእነሱ ግብረ አበሮች ከሆኑ የጥፋት ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ሰሞኑን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሞትና መፈናቀል ፈፅመዋል፡፡ይህም መላውን የሀገራችንን ህዝቦች አሳዝኗል፤አስቆጥቷልም፡፡ መንግስትንም በእጅጉ አሳዝኗል፡፡

ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረስብ አስተዳደር ዞኖች ከውስጥና ከውጭ የተደራጁ የጥፋት ሃይሎች በፈፀሙት ጥቃት ንጹኃን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ንብረት ወድሟል እንዲሁም በርካታ ሰዎች ከቀዬቻው ተፈናቅለዋል፡፡በዚሁ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቅማንት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃትም የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የንፁሃን ዜጎች ህይወት አልፏል፡፡ ንብረትም ወድሟል፡፡ በሌላም መልኩ በአፋርና በሱማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የንፁሃንን ሕይወት የቀጠፉ ግጭቶች አጋጥመዋል፡፡

በተመሳሳይ በቅንጅት የሚሰሩት የውስጥና የውጭ ጸረ ሰላም ሀይሎች የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በታለመለት ጊዜ እንዳይካሄድና እንዲስተጓጓል ለማድረግ የጉሙዝ ታጣቂዎችን አሰልጥነውና አስታጥቀው በአካባቢው በማሰማራት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰሩ ቢሆንም ድርጊታቸው ከመንግስት እውቅና ውጭ ባለመሆኑ ሴራቸውን ለማክሸፍ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የደህንነትና የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለፅ ይወዳል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ፀጥታን ለማስከበር እየተወሰደ ባለው እርምጃም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት ያለው የኦነግ-ሸኔ ታጣቂ ቡድን የመንግስትን ትኩረት ለመበተን በማለም በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈፅማቸውን ጥቃቶችና ግድያዎች ሙሉ በሙሉ ለማስቆም በቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃም ተጠናክሮ መቀጠሉን የጋራ ግብረ ሃይሉ ማሳወቅ ይወዳል፡፡

የውስጥና የውጭ ሀይሎች ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራቸውን ለማሳካት በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን እንዲሁም በዚሁ እኩይ ኣላማቸው የተጠለፉ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ አካላትንም ጭምር በመጠቀም፤ንጹሃንን በግፍ እየገደሉና እያፈናቀሉ ህዝባዊ ቁጣ እንዲቀሰቀስ በማድረግ የሀገርን ህልውና እንዲሁም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል እየተረባረቡ መሆኑን መላው ህዝባችን ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡ መንግስት ሀገራዊ ለውጡ እንዳይቀለበስ እንዲሁም የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ካለው ፅኑ ፍላጎት አኳያ እያሳያ ያለውን ሆደ ሰፊነትና ታጋሽነት ብሄራዊ ደህንነትን የሚፈታተን በመሆኑ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የጋራ ግብረ ሃይሉ መግለፅ ይወዳል፡፡

መንግስት ሀገራዊ ህልውናን አደጋ ላይ ለመጣል የሚሞክሩ የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎችን በምንም አይነት ሁኔታ የማይታገስ በመሆኑ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱ የፀረ ሰላም ኃይል ታጣቂዎችን እንቅስቃሴ በመረጃ፣ በደህንነትና የፀጥታ መዋቅሩ አማካኝነት በመከታተልና በመቆጣጠር፣ አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ የገለጸው ግብረ ኃይሉ፤ የሀገሪቱን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ፤ እየተወሰደ ያለው መጠነ ሰፊ ህግን የማስከበር እርምጃ ስኬታማ እንዲሆን፤ህብረተሰቡ የጥፋት ሀይሎችን ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ጥቆማ በመስጠትና በማጋለጥ እንዲተባበር የጋራ ግብረ ኃይሉ በታላቅ አክብሮት ይጠይቃል፡፡

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፤ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፤ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና የኢንፎርሜሽን መረብና ደህንነት ኤጀንሲ፡፡

ዋልታ

5 Comments

 1. Woyane 2: Where have you been when millions of Amharas were killed in Metekel, Wollega, Guraferda, central Shoa etc? You tell us this propaganda when Amharas say “BEKA”.
  Temesgen, the fake leader of the security apparatus, you better come to your senses and stand with your people, instead of continuing to serve as Abiy`s slave. It is not too late.

 2. ይቺ የተለመደች ማዘናጊያ ድለላ ናት። ለመሆኑ ስንት ጊዜ ነው ኦነግ ሸኔን ደመሰስን እያላችሁ ያሞኛችሁን? ከ እንግዲህ ወዲህ ብልጽግናን በ ምንም አይነት አናምንም። በቃ! ከ እንግዲህ ወዲህ አማራን አማራ ይታደገዋል። መንግሥት ተብዬው ዋናው ጠላቱ ነውና። የ ወያኔ ጊዜ የሚያስመኝበት ጊዜ ሆኗል እኮ። ኦነግ ተብዬው እራሱ የ አቢይ መንግሥት ነው። አቢይ የ ዘመኑ ተስፋፊ ሉባ ነው። አቢይ ዝርያዎቹ ኦሮሞዎች የተስፋፉበትን ፈለግ ተከትሎ ለመስፋፋት ባቀደው መርሃግብር ነው የ አማራ ህዝብ እየተፈጀ ያለው። ምንም አያጠያይቅም። አማራ ነቅቷል። ከዚህ በኋላ የሚመጣው የ ትግሉ ስልት አይነት ነው። ማንም ቢሆን እጅና እግሩን አጣጥፎ ከ እንግዲህ ወዲህ አይታረድም።

 3. የዘር ፓለቲካ በህግ ይከልከል። አሀን ያለው ቁዋንቁዋ ላይ የተመሰረተ አከላለል ፈርሶ በጥናት ላይ የተመሰረት ክፍለ ሀገሮች ይመስረቱ። የሚጠይቀውን መሰዋትነት ከፍሎ፣ ህገ መንግስቱ በአዲስ መንፈስ እና አላማ ፈርሶ በሌላ መተካት ። ከዚህ ውጭ ማድረግ Einstein እንዳለው የጎጥ ፓለቲካ እያቦኩ ፣ የዘር ጭፍጨፍን እናስወግለን ማለት ቢያንስ ራስን ማታለል ነው። ” Insanity is doing the same thing, over and over again, but exprcting different results.”

 4. አስቸኳይ መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ

  ይህቺ አገር አሁን ከበፊቱ የባሳ አደገኛ ሁኔታ ላይ ነች፡፡ ትህነግ ሲባል በዛ ኦነግ ሸኔ ይባላል፡፡ መተከል፣ ቤሻንጉል፣ ሱዳን ፣ ግብፅ ሲባል ሌላ ደግሞ ጉድ እየመጣ ነው፡፡ ስንት ኮንቴነር ገጀራ በባንክ ተፈቅዶ ቅድመ የጉምሩክ ዲክለራሲዮን ተሞልቶ ከወጪ አገር እዚህ እሲኪመጣ ምን አይነት ሰንሰለት ነው ያለው፡፡ በዚህ ቼን ላይ ያለ መስመር በደንብ መፈተሸ አለበት፡፡ ኡሁንም መንግስት በተለያየ እርከን ላይ ያለውን ውስጡን በደንብ ካልፈተሸ ገና አስቸጋሪ ሁኔታ ከፊት አለ፡፡ ያመለጠ ገጀራ አለ የተባለውንም በአስቸከይ ቤት ለቤት አሰሳ ሊደረግ ይገባል፡፡
  ይህ ሴራ አገሪቷን እንደ ሩዋንድ ፍጅት በማድረግ አፈራርሶ እንደ ግብፅ ያሉ እና የውስጥ ጠላቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመጠቀም ነው፡፡ በጣም አሳፋሪ ድርጊት ነው አየተሰራ ነው ያለው የመጨረሻ ውድቀት ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው ማንስ ነው ከዚ የሚጠቀም፡፡ አሁንም የደህንነት እና መረጃ መረቡ በጣም መጠናከር አለበት ትክክለኛ የመረጃ መስመር ያስፈልጋል ከውስጥ ችግር ፈጣሪ ስላለም፡፡
  መንግስት አሁን ማድረግ ትያለበት ምርጫው የግድ መካሄድ ካለበት፣
  1. የሰራዊት አባልን በአስቸኳይ ማጠናከር ስንት ወጣት በየክልሉ አዲስ አባበ ጭምር እና የቀድሞ የተገፉ ወታደሮች ለአገራችን እንውደቅ እያሉ ነው፡፡ ይህን ጥሪ ማፋጠን አለበት፡፡
  2. ያሉትን እውነተኛ የአገር ስሜት ያላቸውን የሰራዊት አባላት ወታደር፣ ፖሊስ በመለየት በየአካባቢው አልፎ አልፎ በመመደብ ከህዝቡ ጋር የጥበቃ ስራ በመሳሪያ ታዞ እንዲያከናውኑ ማድረግ፡፡
  3. በየወረዳው፣ ክፍለ ከተማ እና ክልል ወረዳዎች ያሉ የመንግስት አካለት፣ ፖሊስ ሃይል፣ መከላከያ ሰራዊት ቢሮ የተቀመጡት ጭምር እየወጡ ከህዝብ ጋር የተቀናጀ ስራ መስራት ሲስተሙ እንዲዘረጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቸኳይ ትዕዛዝ መስጠት፡፡ ይኽው አማራ ክልል እኮ አማራጭ ቢያጣ በጎበዝ አለቃ ለመመራት እየሞከረ ነው፡፡ መንግስት አሁን መተኛት የለበትም፡፡ ቀን ለሊት ከህዝብ ጋር መስራት አለበት፡፡ ነገ አዛኝ ከመመሰል አሁኑኑ ይሰራ ገዳፋው ደግሞ ለሁሉም ነው፡፡ አገርም ትፈርሳለች፡፡ መንግስት ምርጫው ይደረጋል እያለ ስለሆነ ህዝብ አካባቢውን ይጠብቅ ብች ማለት ዋጋ የለውም፡፡ አብሮ ከህዝብ ጋር መስራት አለበት በአስቸኳይ በደርግ ጊዜ እኮ ጥበቃ እየተባለ ቤት ለቤት ተዘርግቶ ነበር፡፡ በጣም ይታሰብበት፡፡ ህዝብ ከባድ ስጋት ላይ ነው ያለው፡፡ በመንግስት ስልጣን ውስጥ ተቀምጠው ሴራ የሚጠነስሱም ነገ ለነሱ ልጆችም መዘዘ እያመጡ እንደሆነ ቆም ብለው ሊያስቡበት ይገባል፡፡ መቼም የሩዋንድን፣ ሶሪያን የሚመኝ አንዴ ለይቶለት ስለበደ ከአሁኑ ያለው አማራጭ በሙሉ መሰራት አለበት፡፡

  4. በመጨረሻም የገጀራው ጉዳይ እንዲህ በቀላል የሚታይ አይደለም ሌላ ማጣራት መከናውን አለበት፡፡ መንግስት ከህዝብ ጋር መስራት ያለበት ወቅት ላይ ነው፡፡ በአስቸኳይ ስርዓቱ ቢዘረጋ ጥሩ ነው፡፡ ይህች አገር ጠላት እንደበዛበት ይታወቃል፡፡ ሁሉም ይተባበራል፡፡ በአጎረስኩኝ ሆነና የዚህች አገር ተስፋ፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.