ምክረ ሃሳብ ለጎስቋላው ወገኔ – ሰማነህ ታምራት ጀመረ

altaye

ውድ ወገኖቸ፤

በተደጋጋሚ በአጣየ፤ ጉራ ፈርዳ፤ ወለጋ፤ ቤንሻንጉል፤ መተከለ፥ ወዘተ በአማራው ኢትዮጵያዊ ላይ የደረሰው ግፍ እንኳን እናንተ በቅርብ ሁናችሁ የምታዩትንና የምትሰሙት ቀርቶ ከባሕር ማዶ ሆነን ለምንሰማው እጅግ ይቀፋል። ይህ አስቆጥቷችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ድምፃችሁን ማሰማታችሁ ትክክል ነው። ይህን እያያችሁ ሰልፍ ባትወጡ ነበር የሚገርመው። ላደረጋችሁት ሁሉ ከመቀመጫየ ብድግ ብየ ምስጋናየን አቀርባለሁ።

ያ! የእኔ ትውልድ በስሜት ግራጁን አንስቶ መንግስትን መውጫ መግቢያ በማሳጣት ሕዝባችንን ከድህነት ሳያወጣ የተሳከረች ኢትዮጵያን ያስረከብናችሁ መሆኑን ሳስብ እጅጉ እቆጫለሁ። ለፀፀት መልስ የለውምና ከእኛ ስህተት እንድትማሩ ግን አደራ እላለሁ።

ስለሆነም ከስሜት ወጣ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። ድምፅ ማሰማት ትክክልና መብት ብቻ ሳይሆን ተገቢም ነው። ሰልፍ ስትወጡ ደግሞ ጥርት ያለ ዓላማና ግብ ሊኖራችሁ ግድ ይላል። የሰልፉ ዓላማ መንግስትን ለማስጨነቅ ከሆነ ግቡን መቷል። ከማስጨነቅ አልፎ ለዚህ ሁሉ ቀውስ መንግሥት ተጠያቂ መሆኑንም ሰልፋችሁ በሚገባ አንፀባርቋል። ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት ከሆነ ዝግጅት ባልተደረገበት ሁኔታ የሚገኝ ለውጥ ስርአት አልበኝነትና የከሸፈች ሃገርና ክልል መፍጠር ነው። ይህ የሚአስደስተው ቢኖር የውስጥና የውጭ ጠላቶችንና ኢትዮጵያ ጠል የሆኑ ጽንፈኞችን ይሆናል። ተረጋግቶና አስተውሎ መንቀሳቀስ ለደህንነታችንና ለሃገራችን መፃኢ እድል ይበጃል። አገር ከፈረሰ ሁሉም ነገር አብሮ የሚፈርስ ይሆናል።

የሌሎች ሃገራትን የመፍረስ ሁኔታ እናንተ በዜና እኔ ደግሞ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስሰራ በነበረበት ወቅት በአካል የአፍግሃኒስታንንና የኢራክን መፍረስ አይቻለሁ። ቃላት የሚገልጸው ስላልሆነ እንኳን ለሃገሬ ኢትዮጵያ፤ ለውብ ከተሞሞቻችን ባሕር ዳር፤ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፤ ደሴ፤ ደብረ ማርቆስ ወዘተ ቀርቶ ለቀንደኛ ጠላትም አልመኝለት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ - በአብርሃ ደስታ

እስካሁን ባደረጋችሁት ስልጡንና ሰላማዊ ሰልፍ አኩርታችሁናል። ያነገባችሁት መፈክር በራሱ አስተማሪ ሲሆን የናንተንም ብስለት አሳይቷል። ስልጡን ሕዝብ መሆናችሁን ወዳጅም ጠላትም እንዲአውቀው አድርጋችሗል። ለምሳሌ ፍሬ ሕይዎት ሙስጦፋ የተባለች የፌስቡክ ታዳሚ ‘ነገ ጥኋት ከተማችንን በማፅዳት ለከተማችን ሰላም ዘብ የቆምን መሆኑን ብናሳይ ምን ይመስላችኋል’ ያለችው ጥሪ ልብ ይነካል። ወጣቱም ለዚህ መልስ እንደሚሰጥ ጥርጥር የለኝም። ከዚህ በፊት አርጎ አሳይቶናልና አሁንም እንደሚአደርገው ጥርጥር የለንም። ስለሆነም ጎበዝ ጭንብላችሁን አርጋችሁ ሆብላችሁ ውጡና አፅዱት። ለሕዝብ፤ ለሰላማችሁና ለጤናችሁ መጠበቅ ደጀን መሆናችሁን አስመስክሩ። የእህታችንን ጥሪ እንደ እናት ጥሪ አርጋችሁ ተቀበሉት። የሴት አስተዋይና ደግ ንጉስ አታሳጣን። አልፎ አልፎ የናንተን የብዙሃኑን ዓላማና ፍላጎት ለመረበሽ የሚፈልጉ ሰልፈኞች የነበሩ መሆኑን ተገንዝባችሁ እርምት መውሰድ መቻላችሁ ይበልጥ አስደንቆኛል:: ይህን አለማድነቅ እንደምን ይቻለናል። ሰላማችሁ፤ ፍቅራችሁ፤ አንድነታችሁ እንዲበዛና እንዲጠነክር ከባሕር ማዶ ሆነን የምንፀልይላችሁ ብዙ ነን።

የባህር ዳር ከተማም ሆነ ሌሎች የአማራ ከትሞች ከፍተኛ የሆነ ስራአጥ ያለበት ክልል መሆኑን እናስተውል። በከተሞች ዙሪያ የሚኖረው ገበሬ ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ በመሆኑ ችግር መፍጠር እንደሚችል እንገምት። በተለይ የባሕር ዳር፤ የጎንደርና ላሊበላ ከተሞች ኢኮኖሚ የተገነባው በቱሪዝም፤ በፓርክ፤ በሐይቅ፤ በፏፏቴ፤ በውቅር አብያተ ክርስቲያናትና፤ መስጂዶች ወዘተ የቱሪስት መስህብነት ስለሆነ በንዚህ የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥረት አድርጉ። ይህን ማውደም ሕዝቡን ለርሃብና ለቀውስ መዳረግ ይሆናል። በእነዚህ እሴቶች እና በወገኖቻችችን ሃብት ላይ በምንም ዓይንት ቢሆን ጉዳት እንዳይደርስ መከላከል አድርጉ። ግርግር ከተፈጠረ መቋጫ ወደሌለው ቀውስ ውስጥ ያስገባልና።

ዛሬ በሌለ ዴሞክራሲ ትዊተር፣ ፌስቡክ፣ ሚዲያ እና ኢንተርኔት ላይ ድብልቅልቃችን ወጧል። በፖለቲካ ልሂቃን መካከል በሚደረገው የፖለቲካ እንቶ ፈንቶ ሁሉም አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት የሚአስችል የመግባቢያ ሰንድ ማቅርብ ተስኖት ይነታረካል። በቅርቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚአደርጉትን ክርክር ስታዩ በመካከላቸው ጉልህ የሆነ የፖለቲካ እሳቤና ልዩነት አይታይባቸውም። ከመቶ አመት በፊት በምኒልክ የተሸነፈው የምእራቡ ዓለም በቀሉንና ቁጭቱን ለመወጣት በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በትኩረት ይሰራል፡፡ እንደኦቦ ሸማኔ ጠቅልሎ ሃገርህን ሊውጥ አስፍስፎ እንዳለ ማወቅ ያስፈልግሃል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንኳን ሰው የበግ መንጋ እንኳን “ብኣኣኣ!” እያለ ሀዘኑን በአንድነት ይገልጣል! - በላይነህ አባተ

በመጨረሻም በውጪ ከምንኖር ዳያስፖራዎችም ለኢትዮጵያ ሉአላዊነትና አንድነት ከሚያቀነቅኑት ሌላ በለው፤ ግደለው፤ አውድመው፤ ፍለጠው የሚል ግፊት የሚአደርጉ ግለሰቦችና ቡድኖች እንዳሉ ይታውቃል። ስለእውነት ምከረን ካላችሁ ለሃገር ደህንነት መልካም ስራ የሚሰሩትንና መጥፎ ዓላማ ያላቸውን ለያይታችሁ በማጤን እንክርዳዱን ከስንዴው ለመለየት ጥረት አድርጉ። እኛ ዳያስፖራዎች ሁለተኛ ሃገር ያለን ስዎችነን። እናንተ ግን ያላችሁ አንድ ሃገር፤ አንድ ኢትዮጵያ ስለሆነ ተጠንቅቃችሁ ተንቀሳቀሱ። ማፍረስ፤ ማውደም ቀላሉ ስራ ሲሆን መልሶ መገንባት ግን ከባዱ ፈተና ነው።

አይዟችሁ- በዋሻው መጨረሻ ብርሃን ይታየኛልና በማስተዋል ኢትዮጵያን፤ ኢትዮጵያዊነትንና ክልላችሁን ታደጉ። ሁሉም እድል በጃችሁ ነውና እወቁበት። ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ። ተሳስቸ ከሆነ ከወዲሁ ይቅርታችሁን እጠይቃለሁ። መጪው በዓል የፍስሐ ይሁንላችሁ። አበቃሁ!

የባህር ማዶ ወንድማችሁ፤

ሰማነህ ታምራት ጀመረ

ኦታዋ፤ ካናዳ, ሚያዝያ 15 ቀን 2013

2 Comments

  1. እኔም የ ወንድሜን ምክር ሙሉ ለ ሙሉ ልመክራችሁ እወዳለሁ። ነገር ግን አማራ ህዝባችን የሚደርስበት ሰቆቃ መቆም አለበት። ይህም እንዲሆን ሁሉም ጎልማሳዎች ወገናችሁን ለ መታደግ መዘጋጀት አለባችሁ። አለበለዚያ አንድ በ አንድ ሳይሆን ከተማ በ ከተማ ያጸዷችኋል። በ አጣዬ፣ ካራ ቆሬ እና ሸዋ ሮቢት የሆነውን ልብ ይሏል። ከ ሁሉ በፊት ህልውና ይበልጣልና ቅድሚያ ስጡት። አንድ ህዝብ የሚከበረው በ ጉልበቱ ብቻ ነው። ያለው አቋም ልክነት ወይም ስብዕናው ቦታ የለውም። ስለዚህ በያላችሁበት በ ጎበዝ አለቃ ሥር ተደራጅታችሁ ከ ልዩ ሃይል ጋር በ መቀናጀት እራሳችሁን ማስከበር አለባችሁ። ጠላታችሁ ተስፋፊው የ አቢይ መንግሥት ነው። ከ እሱ ከለላ ከ መጠበቅ እራሱን መጠባበቅ አለባችሁ። አቢይ መገደላችሁን የሚሸሽግ እንጂ እናንተን የሚያድን አይደለም።

  2. ሰማነህ ታምራት ጀመረ

    Instead of pretending as a teacher of Gibre-Geb, tell us how Amara should defend it self from genocide? What are you doing to stop the Amara genocide?

    Your generation lead to the suffering of Amara and now you are blaming the Amara youth for fighting to defend itself. Classical opportunist.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.