በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ የተገነባዉ የወላጅ አልባ እና ለችግር ተጋላጭ ህጻናት የቅድመ መደበኛ ትምህርት እና እንክብካቤ ማዕከል ተመረቀ

ሚያዝያ 14 ቀን 2013 አዲስ አበባ

በዳያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በኩል ባበረከቱት ልገሳ ከሚካሄዱት ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነዉ “የወላጅ አልባ እና ለችግር ተጋላጭ ህጻናት የቅድመ መደበኛ ትምህርት እና እንክብካቤ ማዕከል”  ወይም Early Childhood Care and  Education Center (ECCE) for orphan and vulnerable children ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የተገነባዉ  ማዕከል የምርቃት  ስነስርአት ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ተወካዮች ፣ የክፍለ ከተማዉ እና የወረዳዉ አመራሮችና፣ ፕሮጀክቱን የሚተገብረዉ የህይወት የተቀናጀ የልማት ማህበር አመራሮችና ሰራተኞች፣የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም የማዕከሉ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑ የአካባቢዉ ኗሪዎች ተገኝተዋል፡፡

unnamed (11)

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ወይም Early Childhood Care and  Education ህጻናትን ለመደበኛ ትምህርት ከማዘጋጀት ባሻገር ለሁለንተናዊ እድገታቸዉ መሟላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለዉ  ቢሆንም  በሀገራችን በአቅም ማነስ ምክንያት ከ 50 በመቶ በላይ ህጻናት የቅድመ መደበኛ ትምህርት እድል አንደማያገኙ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ፈንድ (UNICEF) ጥናት ያመለክታል፡፡ ጥራት ያለዉ ትምህርትን ለሁሉም ማዳረስ ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች አንዱ ሲሆን ይህም የተሟላ የቅድመ መደበኛ ትምህርትና እንክብካቤን የሚያካትት ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ለዉጥ ለማምጣት ከሚሰራባቸዉ መስኮች አንዱ እና ዋናዉ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ነዉ፡፡ ለማዕከሉ ግንባታ እና በማዕከሉ ለሚታቀፉት400 ተማሪዎች አንክብካቤ እና ትምህርት ትግበራ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የ9,065,742 ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 6 የተገነባዉ ማዕከል ግንባታ በመስከረም ወር 2013 የተጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱን የሚተገብረዉ ህይወት የተቀናጀ የልማት ማህበር እንዲሁም የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እና የወረዳ 6 አመራሮች እና ባለሞያዎች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ እና ድጋፍ ግንባታዉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡  ማዕከሉ ለ400 ወላጅ አልባና ለችግር ተጋላጭ ህጻናት የተቀናጀ የቅድመ መደበኛ ትምህርት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የተማሪዎች ምገባ እንዲሁም የጤና እና የስነልቦና ክትትል እና እንክብካቤ ከትምህርት ጎን ለጎን  በማዕከሉ ዉስጥ ለህጻናቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች ናቸዉ፡፡  በማዕከሉ ከሚታቀፉት 400 ተማሪዎች መካከልም አብላጫዎቹ የተለያየ የአካል ጉዳትና የጤና እክል ያለባቸዉ ህጻናት እንደሆኑ የህይወት የተቀናጀ የልማት ማህበር  ዋና ስራ አስኪያጅ ሎሬት ሲስተር ጥበበ ማኮ ገልጸዋል፡፡  ማዕከሉ ለህጻናቱ አዕምሮአዊ፣ አካላዊና ስነልቦናዊ እድገት ከሚያበረክተዉ አስተዋጽኦ በተጨማሪ ወላጆችና አሳዳጊዎች ልጆቻቸዉን ያለሀሳብ በማዕከሉ አቆይተዉ ቀኑን በስራ ላይ ለመሰማራት ስለሚያስችላቸዉ ሰርተዉ ለመለወጥ እና ቤተሰባቸዉን ለመመገብ የሚያግዛቸዉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ይህን እና መሰል የልማት ፕሮጀክቶችን ለመተግበር እንዲቻል ለቀረበዉ  ‘በቀን የአንድ ዶላር’ ጥሪ ፈጣን ምላሽ ለሰጡት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን፣ ለአማካሪ ምክር ቤት አባላት እና በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም ለማዕከሉ ግንባታ አስተዋጽኦ ላያደረጉት አካላትን ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባልን፡፡ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት ያልተቆጠበ ድጋፍበማድረግ ላይ ያለዉን የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP)ን ለማመስገን እንወዳለን፡፡  በቀጣይም በከፍተኛ ድህነት ዉስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን ህይወት ለማሻሻል በዳያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የልማት አጋሮቻችን በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በኩል የሚያደርጉትን ልገሳ እና ድጋፍ አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ አደራ እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በዳያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለምንም የዘር፣ የብሔር፣ የቋንቋ እና የፖለቲካ አቋም ልዩነት ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቻቸዉ ያበረከቱት ልዩ ስጦታ ነዉ።

The Early Childhood Care and Education Center Funded by EDTF will serve 400 orphan and vulnerable children

 9e2ae5bc 42c1 4327 b135 e99277daf05c

22 April 2021, Addis Ababa

The Early Childhood Care and Education (ECCE) Center built for orphans and vulnerable children was inaugurated in Kolfe Keranio Sub-City, Addis Ababa on 22 April 2021.  The ECCE was funded by the Ethiopian Diaspora Trust Fund (EDTF).  The inauguration ceremony event was attended by representatives of EDTF, City and Woreda officials, the Hiwot Integrated Development Association leadership and staff (EDTF’s implementation partner), religious leaders as well as residents of Woreda 6 who will benefit from ECCE’s services.

Although early childhood care and education is critically important for the intellectual and psychological development of children, these services are not adequately provided in Ethiopia. A report issued by the United Nations Children’s Fund (UNICEF) estimates that more than 50% of children in Ethiopia do not have access to pre-school education for a variety of reasons, including the unavailability of early childhood care and education centers and facilities. Consistent with the United Nations sustainable development goals, access to quality education is one of EDTF’s priority intervention areas targeted to improve the lives of Ethiopians living in poverty. EDTF has donated 9,065,742 Ethiopian Birr for the construction of the ECCE center and the implementation of the integrated care and education services which will benefit children and their families. The construction of the ECCE was started in October 2020 and completed within a relatively short time considering the COVID-19 pandemic.

The ECCE Center will provide integrated early childhood education and care for 400 orphans and vulnerable children including pre-school education, school meals, health, and psychological monitoring and support services.  Sister Tibebe Mako, Executive Director of Hiwot Integrated Development Association explained that most of the children enrolled in the Center suffer from various forms of disabilities and health impediments. In addition to contributing to the mental, physical, and psychological development of the children, the Center allows parents and guardians to leave their children in a safe environment to engage in productive work to support their families.

The EDTF Board of Directors sincerely thanks all donors who responded to the ‘one dollar a day’ which has resulted in funding for the construction and implementation of the ECCE Center and similar development projects. We also thank EDTF’s leadership and volunteers as well as government and non-government partners who contributed to the successful completion of this important project.  Our deepest appreciation and gratitude also goes to the United Nations Development Programme (UNDP Ethiopia) for its generous support in financing the operation of the EDTF secretariat in Addis Ababa. EDTF calls for the continued and revitalized support of the Ethiopian diaspora community and development partners to improve the lives of Ethiopians in need.

The Ethiopian Diaspora Trust Fund is a gift of the Ethiopian Diaspora to the Ethiopian people.

1 Comment

  1. የተከበራችሁ የትረስት ፈንዱን ራዕይ አዳባሪዎች ፤
    እንደሚታወቀው ያለ እናንተ ምክር የትረስት ፈንዱ ቦርድ ብቻውን ትረስት ፈንዱን ውጤታማ ልናደርገው አንችልም። ምክርም ለትረስት ፈንዱ ቦርድ በጣም አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት እባካችሁ የትረስት ቦንዱን ቦርድ አማካሪ ለመሆን የምትሹ ከMay 15 2021 በፊት የትረስት ፈንዱን ቦርድ አማካሪ ለመሆን የሚያበቃችሁን ማመልከቻ በትረስት ፈንዱ ድረገፅ ላይ ማመልከቻውን ሞልታችሁ አመልክቱ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.