ባህር ህዳር ላይ መንግስት የጀመረው የሃይል እርምጃ መነሻው አንዳንድ ሰዎች ሲፅፉ እንደማየው ወጣቱ ስሜታዊ ስለሆነ አይደለም

177033512 4235389769815952 6469339722182145349 n

መስከረም አበራ

ምክንያቱ ወዲህ ነው ፤ መንግስት የጠበቀው ህዝባዊ ቁጣው (ለታገቱ ተማሪዎች እንደተደረገው) ለአንድ ቀን ተደርጎ ወደቤት የሚገባ እና ህይወት እንደነበረው ይቀጥላል የሚል ነበር። ሆኖም ተቃውሞው ስለቀጠለ ሄዶ ሄዶ ለወንበርም ሊያሰጋ ይችላል የሚል ስጋት ስለያዘው ነው።

ሰልፉ የቀጠለው በሌሎችም ከተማዎች ሆኖ ሳለ የሃይል እርምጃው በባህርዳር የተጀመረው ከተማዋ ክፉኛ የተጠላው የክልሉ መንግስት በስስት የሚያየው ዙፋኑ ዋና መቀመጫ በመሆኗ የዋናውን ዙፋን ስጋት ለማቃለል ነው።

ሆኖም ተቃውሞው ቀጣይነት በኖረው ቁጥር የሃይል እርምጃው ወደ ሌሎች ከተሞችም መሻገሩ አይቀሬ ነው።

ስለዚህ አካሄድን በጥንቃቄ እና በተቀናጀና በተናበበ መንገድ ማድረግ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ዛሬ ባህርዳር ላይ ስራ ማቆምም አደባባይ መውጣትንም በአንድ ላይ ማድረጉ ትግሉን የተናበበ እንዳይሆን ከማድረጉም ሌላ አደባባይ የወጡትን ለይቶ ለአደጋ ያጋልጣል።

መንግስት የሃይል እርምጃውን ገፍቶ ፀጥ ለማድረግ መሞከሩ ስለማይቀር አደጋን ሊቀንሱ የሚችሉ የተለያዩ የትግል ስልቶችን በመቀያየር መተግበርም አስፈላጊ ነው።

በተረፈ መንግስት የአፈና እርምጃ መጀመሩ የትግሉ መጠለፍ ፣መበላሸት አድርጎ ማቅረቡ የፀጥታ ብላችሁ ተገዙ ባይ ወዳጅ መሳይ ጠላቶች የህዝቡን ትግል ለማኮላሸት የሚቀባጥሩት ማስመሰል ነው። ከታጋዩ ህዝብ የሚጠበቀው ፍፁም ሰላማዊነት፣የሃይል እርምጃውን ተገቢ ከሚያስመስሉ ስሜታዊ እርምጃዎች መታቀብ ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.