አማራንም ኢትዮጵያንም ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም! – ሚኪያስ

ኢትዮጵያ ጠላቶችዋ በየፈርጁ ናቸው፣ ማዕከላቸውም ግብጽ ነች። ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያን ያመሰቃቀለችው የስብሃትመለስ ዕጅ ሥራ የሆነችው የባንዳዎች ስብስቧ ትህነግ ነች። ወያኔ በዝብዛ፣ በዝብዛ ሲበቃት– ኢትዮጵያን – የመምራትና የማስተዳደር ችሎታ ለሌለው ቀማኛ ቡድን አሳልፋ ሠጥታ – እርሷ ተደላድላ በወርቅ መቅረዝ በተሠራ ቤት ውስጥ ለመኖር ነበር ትልሟ። እግዚአብሄር ግን ቀድሞ ትቢያ አደረጋት። ወያኔ አማራን እንደ ርዕዮተ ዓለም በጠላትነት ፈረጃ በመርሃ ግብሯ አሰፈረች። ይህን አማራን አጥፍቶ ኢትዮጵያን የማዳከሙን ዕቅድ አተገባበር አስቀድሞ የተገነዘቡት ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ አማራው ራሱን መጠበቅ የሚያስችለውን መላ አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐህድመሠረቱ።

Save Amharaምዕራፍ አንድ – የትህነግ የብልጽግና ዘመን (ዘመነ ኤፈርትሜቴክ– የአማራ ፍጅት

– ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህድን) – ስብሃትና መለስ ገና በጠዋቱ አማራን ለማጥፋት ሲወጥኑ ትልቅ ብልሃት ሆነው ያገኙት ጥቅም ፈላጊዎችና ምርከኞችን አስባስቦ ኢህድን የተባለውን ድርጅት ጠፍጥፎ መሥራት ነው። የነ ስብሃት ምስለኔዎች እነ በረከት፣ ታምራት፣ አዲሱ፣ ወዘተ፣ የመጀመርያውን የአማራውን ጥቃት በበደኖ እና አርባጉጉ ላይ ጀመሩ። አቶ ታምራት ላይኔ ከክልሉ ውጭ የሚገኛ አማራ ሁሉ ነፍጠኛ ነውሲል ደሃው አማራ ላይ ሞት አዘነበበት።

– አማራ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አሕዴን)– ፕሮፌሰር አሥራት መላ አማራ ሕዝብ ድርጅት(መዐህድ) የሚለውን ለአማራ የሚቆረቆረውን ድርጅት ሲመሰርቱ ወያኔ – ኢህዴን – የተባለውን በ” ላይ የተጠቀሰውን ድርጅት ስሙን አማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (አህዴን) ብላ ቀየረችው። አህዴን ነፍጠኛ ብሎ የፈረጀውን አማራ ካለርኅራሄ መፍጀቱን ቀጠለበት። መዐህድ ፕሮፌሰር አሥራት ካረፉ በኋላ በቀኛዝማች ነቅዓ ጥበብ ሲመራ ቆይቷል። ኋላ ላይ አማራ በዘር ተደራጅቶ መሰባሰቡ ኢትዮጵያን ይከፋፍላል የሚል ሃሳብ መነጨ። ይህ አስተሳሰብ በመርህ ደረጃ ትክክል ቢመስልም ተጨባጩን ሁኔታ ግን ባለማገናዘቡ አማራው በአማራነቱ እንዳይደራጅ ትልቅ እንቅፋት በመሆን የፕሮፌሰ አሥራት ራዕይን ጋረደ።

-. ምርጫ 97- የተወሰኑ አባላት መዐህድን ለቀው መላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)የተባለውን ድርጅት አቋቋሙ። ይህ ድርጅት በኢንጂነር ኃይሉ ሻውል እንዲመራ ተደረገ። ከመዐህድ የተገነጠለው ሌላው ድርጅት በልደቱ አያሌው የሚመራው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – ኢዴፓ – ነው። በኢንጂነር ኃይሉ ሻውል የሚመራው መኢአድ፣ በአቶ ልደቱ የሚመራው ኢዴፓ እና በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው ቀስተ ደመና – “ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ” ተብሎ በምርጫ ተወዳደረ። ሆኖም ግን ኮሮጆ ገልብጦ አሸንፌአለሁ ያለው ወያኔ ወጣቱን ግንባር ግንባሩን በጥይት ከመታ በኋላ የኦህዴድን መቀመጫ ከናዝሬት አዳማ ወደ አዲስ አበባ በማዞር አማራውን ከማሸማቀቅ ባለፈ አዲስ አበባ በኦሆዴድ ሥልጣን ሱሰኞች እንድትወረር አደረገ። ከቅንጅት በኋላ ወያኔ የበቀል ጅራፍዋን አወፈረችው።

-. ድህረ ቅንጅት – አማራው እጅጉን የተጎዳው ከቅንጅት መሰባበር በኋላ ነበር። ሀገር ውስጥ የቀረው ፍርክርኩ ፓርላማ ሲያደምቅ እውጭ የወጣው ሌላኛው ክፋዩ ቅንጅት እንደገና ለሁለት ተከፈለ (Kinijit International Council (KIC) and Kinijit International league (KIL)። ቅንጅት ሲከፋፈልና ሁሉም በሚያመችው መንገድ የትግል ስልት ሲቀይስ አማራው ተረሳ። በተለይም ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት በርካታ አማራ ምሁራንን እንዲሁም የኪነትና ሥነ ጥበብ ሰዎችን በሥሩ በማቀፉ ለአማሮች ድምጽ የሚሆነው ቁጥር ሰለለ። የአማራ እልቂት ብሎም የኢትዮጵያን መፍረስ ያስከትላል የሚሉ ጥቂቶች ድምጽ ለማሰማት ቢሞክሩም የወቅቱን የፕሮፖጋንዳ በትር ማሸነፍ ተሳናቸው።

.- አማራው እንዳይደራጅ ማዘናጋት – ሰው በባህርይው ተታላይ ነው። መደለያ ሲሰጠው፣ ሹመት ሲቀጥሉለት ይዘናጋል። ማንም ሰው ለሃገሩ መታገል ግዴታ አለበት። ነገር ግን አንዱን እጅግ ጣርያ ሰቅሎ ማንቆለጳጰስ፣ ከስሙ ፊት የሙገሳ መጠርያዎችን መቀጠል፣ ሲራመድ ማጀብ፣ እርሱን ብቻ ጣራ ሰቅሎ ማጨብጨብና መሸለም፣ ወዘተ፣ ጤናማ ያልሆነ የውድድር ስሜትን ይፈጥራል። መልካም ያልሆነ የውድድር ስሜት መፍጠር ሌሎች የቻሉትን እንዳያደርጉ ማዳከም ነው። ብዙዎች ለጥቂቶች ከማጨብጨው አልፈው ለብዙሃን እንዳይቆሙ በተደናቂዎች ጫማ ልክ ብቻ እንዲራመዱ ሲደረግ የተበደሉ፣ የተጎሳቆሉ ይረሳሉ። ወያኔ ይህን አመቺ ሁኔታ እየተጠቀመ መደራጀት ያቃተውን አማራን ይፈጃል።

ምዕራፍ ሁለት – የኦነግ የብልጽግ ዘመን (ዘመነ ተረኝነት) – አማራን መጨፍጨፍ

ኦሮማራ – ዲያብሎስ መለስ ዜናዊ ወደ ሲዖል ከወረደ ወድያ ሕዝባዊው ትግል እጅግ ተፋፋመ። የአማራ ልጆች ፋኖ፣ የኦሮሞ ልጆች ቄሮ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች እጀቶ – እየተባሉ በአንድነት ተነስተው ትህነግን ቁም ስቅል አበሏት። ወያኔ ግድያውን በኦሮሞ ክልል ስታበዛ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው” አለ ወጣቱ ከጎንደር። ደጉ አማራ በቀለ ገርባ ይፈታ ሲል ጮኸ። የኦሮሞም ወጣት የአማራ ደም ደሜ ነው” በማለት ምላሹን ሠጠ። መሠሪዎች ይህን ትግል ሠርቀው ለኦኔግ ገጸ በረከት አረጉት። አማራው” ኢትዮጵያ ሱሴ ነች” በሚለው ምትሃት ሲዘናጋ ኦነጎች አራት ኪሎ ለመግባት ስልቶች አበጃጁ። ኦሮማራ በሕዝባዊ ትግል የተዳከመችዋንና በሙስና የተፍረከረከችዋን ወያኔ አባሮ ሥልጣን የመንጠቁ ምሥጢራዊ አካሄድ ሆነ። በአቶ ደመቀ የሚመራው አህዴን፣ በአቶ ለማ የሚመራው ኦህዴድ፣ በወይዘሮ ሙፈርያት የሚመራው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ – መክሮ ዘክሮ ምሥጢሩን ጠብቆ መቅኖ የራቃትን ሙሰኛይቱን ወያኔን በምርጫ ከፈጠፈጣት በኋላ ሥልጣኑን በስምምነት ለኦሆዴድ አስረከበ። ኦሮማራ የ ተረኝነት” መሠረትና አማራውን የመፍጀቱ የደደቢቱ ማኒፌስቶ ግልባጩ የሚጻፍባት ስውር ብራና ነበረች።

ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ – ብልጽግና)–  ዶክተር አብይ ወታደሮች ቤተ መንግሥት ድረስ መጥተው በከበቧቸው ጊዜ መንግሥታችን ተነካ ብሎ ሕዝቡ ከቡራዩ ሊመጣ ነበር” ሲሉ ምን ማለታቸው ነበርዶክተር አብይ ሥልጣኑን ከተረከቡ ጀምሮ ለሶስት ዓመታት ያለማቋረጥ አማራው ሲገደል ለምን ዝም አሉአንዳንዶች እሳቸው ምን ያድርጉ ከሥራቸው ያሉት አላሠራ ሲሏቸው ይላሉ። ግን እነ ብጄ አሳምነው ጽጌ ላይ ሲሆን እንደምን በረቱ? ወይም ምንም ወንጀል ያልሰራውን እስክንድር ለማሰር ሲሆን እንደምን ጨከኑበኦዴፓ ውስጥ አንድ ምሥጢራዊ ስብስብ እንዳለ ይታያል። ይህን ስብስብ ዶክተር አብይ ይወቁት፣ አይወቁት ማስረጃ ባይኖርም ኦዴፓ ግን የኦሆዴድ ቅጥያ በመሆን እነ ጄል አሳምነው ጽጌን፣ ዶክተር አምባቸውን፣ አቶ ምግባሩንና ሌሎችንም አስወግዶ አማራውን ካለ ተቆርቋሪ አስቀረ።

ምዕራፍ ሶስት – የብልጽግና ካባ የለበሰው ኦነግ የመጨረሻው ዕቅድ – አማራ ክልልን መውረር

እልቂት በትህነግ የታወጀበት አማራ፣ ቁም ስቅል ያየው አማራ፣ የሰው ልጅ የማይችለው መከራ የተፈራረቀበት አማራ፣ ገደል የተወረወረው አማራ፣ ወዘተ፣ – ሌላስ ምን ቀረ። የቀራቸው ሰሜን ሸዋ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ – እነዚህን ምድሮች ማጋየት ነው። አማራ ብልጽግና (አዴፓ) ተብሎ የተሰየመው ስብስብ አንዳች እርምጃ መውሰድ ያልቻለ የኢህድን ቅጥያ ነው። ኦነጎች ትህነግ የጀመረችውን አማራውን የማጽዳትና የዘር ፍጅት ተረክበው – ቡራዩ፣ ሻሸመኔ፣ ዝዋይ፣ አርሲ፣ ወለጋ፣ መተከል፣ ቤንሻንጉል፣ ወዘተ፣ ላይ ብዙሃን አማራን ከጨረሱና ንብረቱን ቤተ ክርስትያኑን ካቃጠሉ በኋላ ሰሜን ሸዋ አጣዬ ደረሰው ከተማዋን ሲያወድሙ አዴፓ አንዳች አልተነፈሰም። ተገንና ደጋፊ ያጣው አማራ፣ ጊዜው ደርሶ ነው – በቃ – ያለው። አማራው ምን መደረግ እንዳለበት ራሱ ያውቃል። እኔ እንደ አንድ ግለሰብ እነዚህን መፍትሄዎች ልጠቁም።

ምዕራፍ አራት – ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለማዳን የመፍትሄ ሃሳቦች።

አማራ ነፍጠኛ ነው። ዛሬ ለነፍጥ አዲስ የሆኑ ሁከተኞች ነፍጥ ይዘው ሲፈጁት ዝም ያለው ማህበራዊ ቀውስ እንዳይባባስ ጀግኖች የሞቱላት ኢትዮጵያ እንዳትመሰቃቀል እንጂ እሱም እንደነሱ ነፍጥ አንስቶ አጸፋ መመለስ አቅቶት አይደለም። አማራ ሃይማኖተኛ ነው፣ ብዙ ይታገሳል፣ ሠላም ይወዳል፣ ነፍጥ ካነገበም አጠቃቀሙን ያውቅበታል። አማራ ትምክህተኛ አይደለም፣ አስተዋይ እንጂ። አማራ ጠላቱ ኦህዴድ እንጂ የኦሮሞ ሕዝብ አይደለም። አማራ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰብ ይወዳል።

. – አማራ ቀድሞ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ እንዳቋቋሙት ባለ አንድ ድርጅት ሥር ዳግም መደራጀት አለበት። መከፋፈሉ ግብጽንና ልጆቿን እነ ኦነግን ጮቤ ያስረግጣል። መከፋፈሉ አማሮችን ለርህራሄ ቢሶቹ ሁለገብ ጥቃት ይዳርጋል። ኢትዮጵያ እግዚአብሄር ቃል የገባላት አገር ናትና አማራ በአንድ ልብ፣ በወኔ፣ በላቀ ስሜት ተደራጅቶ ዘሩንም ኢትዮጵያንም የማዳን አደራ አለበት።

. – የትግራይ ሕዝብ በባህል፣ በኃይማኖት፣ በሥነልቦና፣ በመልካዓ ምድር አማራን ይቀርባል። የትግራይ ልጆች የባንዳ ውላጆች የቀረጹትን ክፉ አስተሳሰብ እርግፍ አድርጎ ትቶ እንደ አጼ ዮሃንስ ኢትዮጵያን በማዳኑ ሥራ ላይ ሊሰማሩ ይገባል።

አገር ወዳዱ ጀግናው የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ራስ ጎበና አባ ዳጬ ተነስ። ኦሮሞ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነው። እነዚህ ለግብጽ አድረው በስሙ የሚነግዱበት ኦነጎችና መሰሎቹ ኦሮሞን ለማያልቅ እልቂት ዳርገው ሊምነሸነሹ አንዳሰቡ ልትገነዘብ ይገባሃል። በኃይማኖት፣ ጎሳና ነገድ የተከፋፋሉት የኦሮሞ ልህቃን እንኳንስ ሠፊውን የኦሮሞን ሕዝብ ሊመሩ ቀርቶ እራሳቸውን ማስተዳደር የማይችሉ ቅምጥሎች ናቸው። የአማራና ኦሮሞ ሀገር የማዳን ጥምረት የሆነውን ኦሮማራ የተበላሸው በነዚህ ቅምጥሎች ደባ ነው። የሸወዱ የመሰላቸው ሁሉ የተሸወዱት እራሳቸው ናቸው። ጀግናውን የኦሮም ሕዝብ የማይወክሉት የሥልጣን ቀበኞች ንዋይና በየሆቴሉ መሽቀርቀሩ ዓይናቸው ጋርዶት እንጂ ቢያስተውሉ ኖሮ ትህነግ ላይ የደረሰው መከራ ትምህርት በሆናቸው ነበር።

ኢትዮጵያን የምትወድ መላ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከአማራው ጎን ተሰልፈህ ኢትዮጵያን ማዳን አለብህ። ኢትዮጵያን ከዘመነ መሣፍንቱ ክፍፍል አላቀው የቀድሞ ማንነትዋ እንዲመለስ የወጠኑት አጼ ቴዎድሮስ ናቸው። ኢትዮጵያን ከቅኝ ገዥዎች ሠለባነት የታደጉት አጼ ሚኒልክ ናቸው። አጼ ሚኒልክ መላ ኢትዮጵያን በአረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ባንዲራ አጣምረው አፍሪካንና በምድር ዙርያ በቅኝ ገዥዎች የሚሠቃዩትን ነጻ ያወጡ ብልህና ጀግና መሪ ናቸው። ሃቁ ይህ ነው። አማራ ነፍጠኛ እየተባለ ሲገደል የቆየው ነፍጥ ይዞ አጼ ቴዎድሮስንና አጼ ሚኒልክን ተከትሎ ኢትዮጵያን ስላስዋባት፣ አብሮ መኖርን ስላስተማረ፣ ባርነትን ስላስቀረ፣ ወዘተ፣ ነው። ኢትዮጵያን ማዳን ዛሬም ግድ ይላልና መላ ኢትዮጵያውያን ከአማራ ትግል ጎን ልትሰለፍ ይገባል።

ኢትዮጵያ በአጼ ሚኒልክ ዘመን እንደነበረው ክልላዊ ፌደራሊዝም ወይም በመልካዓ ምድር የተካለለ ፌደራሊዝም – መርጦ ተወያይቶ ሥራ ላይ ማዋሉ የወደፉቱ የቤት ሥራ ነው። የዛሬው አፋጣኝ ሥራ እስላም ክርስትያኑ በፍቅር የሚኖርባትን ኢትዮጵያን ከግብጽ ሎሌዎች መዳፍ አላቆ ኅልውናዋን ማስቀጠሉ ነው። እነዚህ ሁሉ ሥራዎች ስንሰራ ብቻችንን አይደለንም፣ ኃያሉ እግዚአብሄር አብሮን ነው። እመብርሃን ትለምንልናለች። እኛ እንጀምራለን አምላካችን ይፈጽምልናል። አማራንም ኢትዮጵያንም ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም።

አማራ ያሸንፋል፣ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.