ከማድበስበስ እና ከማለባበስ ወደ ዕዉነት መዳረስ ይበጃል !!! – ማላጂ

Ethiopian Politicsየእኛ አገር ፖለቲካ እያደር ከድጡ ወደ ማጡ የሚሆንበት ዋና ምክነያት በተጨባጭ እየታወቀ በይፋ ለህዝብ እና ዓለም አለመገለፅ የህዝብ መከራ እና ፍዳ እንዲራዘም አድርጎታል ፡፡

በኢትዮጵያ ኢትዮጵያዉያን ባለቤት መሆናቸዉን እየታወቀ  ኢትዮጵያዊነት ሆነ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አይኖሩም በሚል ትግል ለግማሽ  ምዕተ ዓመት  መኖሩ እየታወቀ ከልብ አገር የጋራ ሀይማኖት የግል መሆኑን አስረግጦ ከመናገር ይልቅ ፀረ ሠላም፣ ሕገ መንግስት….ወዘተ እያሉ ማለባበስ ለምን እንደቀጠለ ዛሬም አጠያያቂ መሆኑን እያየን ነዉ ፡፡

ለመሆኑ ፀረ አንድ እና ፀረ ሶስት አስተሳሰብ ይዞ በጋራ አገር ላይ የግል ርስት ለማድረግ የሚደረግ የዘመናት ሩጫ ለማስቆም በግልጥ  ፀረ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ፈለግ የሚከተሉት ለዘመናት በአገር እና በህዝብ ላይ ለሰሩት እና እየሰሩ ላሉት ግፍ ተጠያቂ በመሆን ዋጋ ላለመክፈላቸዉ መንስዔዉ የማለባበስ ጉዳይ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ቀንደኛ እና ታሪካዊ የብሄራዊ አንድነት እና የህዝብ ደህንነት ስጋት ናቸዉ እና በስማቸዉ እና በድርጊታቸዉ ልክ ይጠሩ፣ ይጠርጥሩ እና ከህዘብ መካከል ተለይተዉ ይመንጠሩ ሲል ጥቂት፣ የማይታወቁ፣ የማይሳካላቸዉ…..እየተባሉ የህዝብ ድምፅ ጆሮ ዳባ ማለት ጠላት የሚመኝልንን  ብሄራዉ ቀዉስ  ከነግሳግሱ ይዘን ዛሬ ካለንበት ደርሰናል፡፡

አሁንም ህዝብ እና መንግስት ለጋራ አገር እና ለአንድ ህዝብ ዕድገት እና ዘላቂ ህልዉና ለማስቀጠል አንድ አስከሆኑ ድረስ ፀረ አንድ እና ሶሰት ጠላቶች ታሪካዊ እና የረጅም ዘመናት የኢትዮጵያ ጠላት መሆናቸዉ ከነሙሉ ስም እና ምግበራቸዉ ለህዝብ እና ለዓለም ግልፅ  ሊሆን ይገባል ፡፡

ተግበራቸዉን ከነስማቸዉ አስቀድሞ ትክክል አለመሆኑ እየታወቀ  በህይወት ፣ ዘር ፍጅት ፣ በአገር ክህደት፣ የህዝብን ሠላም በማወክ  እንዲሁም የአገሪቷን ልዑላዊነት ስጋት ላይ በመጣል ለፈጸሙት ወንጀል አለመጠየቅ ለዛሬ ፈርጀ ብዙ እና የተንዛዛ ብሄራዊ ቀዉስ መከሰት ምክነያት ሆኗል፡፡

አሁንም ኢትዮጵያ ህዝብ ለይቶ በማሳደድ፣ በመግደል ፣ በማፈናቀል እና የአገር እና ህዝብ ሀብት በማዉድም የሚገኝ ጥቅም ለግለሰብ እና ቡድን ካልሆነ ለአገር ጥፋት በመሆኑ በግልፅ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

አገር እና ህዝብ በማጥፋት በአገር ፍረሰትም ሆነ በህዘብ ሞት የሚገነባ ነጻነት ምኞት ከመሆን ዉጭ ለማንም ስለማይበጅ ከማድበስበስ  ዕዉነቱን ተናግሮ ጨለማዉን አልፎ ከጋራ የንጋት  ብርሃን መድረስ ይሻላል፡፡

ዞትር በሚባል የተለመደ ማድበስበስ የትም እንደማይደረስ ከኋላ ታሪካችን ተምረን በጋራ እና በአንድነት እጅ ለእጅ በመየያዝ ለጋራ እና ለሁላችን ቤዛ ለተከፈለባት አገር በጋራ እንቁም፡፡

                                                                         ማላጂ

                                               “እናት ኢትዮጵያ ዛሬም እንደ ትናንቱ የኢትዮጵያዉያን ናት  ”

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.