ቅዱስ ፓትርያርኩ ለeotc ቴሌቪዥን የሰጡት ከ1 ሰአት በላይ ቃለመጠይቅ እንዳይተላለፍ በማን ተከለከለ? – ብርሃኑ ተክለያሬድ

176345115 4232006450154284 2036013590367727349 nሴራውን ገለጥለጥ ለማድረግ ያህል

እነ ታዬ ደንደአ ቤተክርስቲያን “አብይ አህመድና ግራኝ አህመድ አንድ ናቸው” ብላ ስትሰብክ ነበር በማለት በቤተክርስቲያን ላይ ጦርነት እያወጁ ነው።

ኦሮሙማ በቤተክርስቲያን ላይ እጁን አስረዝሞ የማፍረስ አባዜውን ከዘረጋ ቆይቷል። እውነቱ በገሐድ የሚታይ ቢሆንም ከልክ ያለፉ ብልግናዎችን በሂደት እንገላልጣቸዋለን። ለመነሻ ያህል ጥቂት ጥያቄዎችን እናንሳ

-የቅዱስ ፓትርያርኩን የጥበቃ ሀላፊ አስሮ ፓትርያርኩን በሰላይ ያስከበባቸውና የፈለጉትን ሰው እንዳያገኙ የከለከላቸው ማነው?

-በፓትርያርኩ ሊሰጡ የነበሩ 2 መግለጫዎችን ፖሊስ ልኮ የከለከለው ማነው?

-ጥቅምት 26 ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፓትርያርኩ ቢሮ ድረስ ሔደው አቡነ ማትያስን ከፍ ዝቅ አድርገው በሀይለ ቃል የተናገሯቸው በየቱ ስልጣን ነው?

-ቅዱስ ፓትርያርኩ ለeotc ቴሌቪዥን የሰጡት ከ1 ሰአት በላይ ቃለመጠይቅ እንዳይተላለፍ በማን ተከለከለ? ከቀናት በፊት በቴሌቪዥን በሚተላለፍ ፕርግራም የሰበኩት ስብከትስ ለምን ታገደ?

-(ስማቸው ይቆየንና)ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ “ቤተክርስቲያን ሊቃጠል ነው ተነሱ ብሎ አነሳስቷል”ብለው ከመጋረጃ ጀርባ ለመመስከር 3 ሰዎችን የመለመለው ማነው?

እግር በእግር እየተከታተልን ነው በቅርቡ ሁሉም ግልጥልጥ እያለ ይመጣል።

ከቤተክርስቲያን እጃችሁን አንሱ!!!

ብርሃኑ ተክለያሬድ

4 Comments

  1. ሌላው ይቅር እንዴት ቢሆን ነው አዳነች አቤቤ አቡነ ማትያስን ከፍ ዝቅ አድርጋ በሀይለ ቃል የምትናገራቸው? የማይመስል ነገር!

  2. ከድር ያንተ እህት አይደለች ምን ችግር አለባት? ከአውድህ ወጥተህ ቢያይህ እኮ ነው ይልቃል አይኑን ማመን የከበደው።

    • አዎን እህቴ ነች፤ ለዚያም ነው እምነቷም ባይሆን የተዋህዶን እምነት መሪ ያህል ደፍራ ሃይለቃል መናገር አይደለም እንደማታስበው አውቃለሁ። የአንተ አይነቶቹ ችግር እኮ “ኢትዮጵያዊነት ከኛ ዉጭ ላሳር” ማለታችሁ ነው። ስህተትን መንቀስ ያባት ነው። ይህን ያህል የታወረ ጥላቻ ግን አይጠቅምም!

      • እሱዋ የምታስበውን ከወቅህ አንተ ሰው አይደለህም ለእሷ ፈጣሪዋ ነው የምትሆነው ። ችግሩ ኦርቶዶክስ መብቶአን ስትጠይቅ እኔ ብቻ ነኝ ኢትዮጵያዊ እያለች ነው በሚል ጠማማ አውድ የምትረዱ አንተና መሰሎችህ እንዲሁም አዳነች አቤቤ አይነቶቹ በጭራሽ ግራ እና ቀኙን መመልከትና ሚዛናዊ አቁዋም የላችሁም ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.