ሰላም ሚኒስትር ወደ ሰላም ቡቲክ ተቀይሮ ሲውረገረግ ሳይነግሩነ – ጌታቸው ሽፈራው

174106473 4446456022050029 3511794698886931838 n
ስራችን ነው ያላችሁትን መስራት ተስኗችሁ ንፁሃን በየቀኑ እየታረዱ እናንተ ለልብስ ዲዛይን ስትጨነቁ ሰነባብታችሁ መድረክ ላይ ሸክ አድርጋችሁ ታውረገርጋላችሁ። ህፃናትና እናቶች በየቀኑ እያለቁ እናንተ በአደራሽ ወገብ ታወላግዱልናላችሁ። እውነትም ሀገር ተለያይተናታልኮ።
በቃ እንዲህ አማካሪ ይጥፋ? በቃ እንዲህ እቃ እቃ ሆነ የኢትዮጵያ ጉዳይ?
174046078 4446455878716710 8165909927046176622 n
ለሰርግ፣ ለቀለበት፣ ለልደት………ምናምን ብላችሁ ማስታወቂያ መልቀቅ ነው እንግዲህ! ፌስቡክ ላይ እናግዛለን።
አክቲቪስት እንኳን አዲስ ልብስ በለበሰ ቁጥር ፎቶ ይለቃል? ይለቃል እሱስ ከአክቲቪስት ለየት ለማለት ግን አጥባችሁ ስታሰጡትም፣ ሲደርቅ፣… እንዲያው አንዳንድ ፀረ ሰላም አይጥ ከበላውም …ምናምን አሳዩንማ። ልብሱም ሰላም መሆኑን ማወቅ አለብንኮ!

1 Comment

  1. ጌታቸዉ ሺፈራዉ አረ እግዜርን ፍራ የሰላም ሚኒስተሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት መሰሉኝ እንዴት እንዴት ነዉ ነገርህ ባንዴ ከስተዉ አንዲት ፍሬ ልጂ አድርገህ ፎቷቸዉን እየተዉረገረጉ ሲሄዱ የምታሳየኝ? መነጽሬንም ብቀያይረዉ መልስ አልሰጠኘም። ይሄ ፋሺን እየተባለ መወላገድስ ከምን የመጣ ነዉ? አዉሮፓና አሜሪካ ገበያ ያጣዉ ሸቀጥ እንዲሸጥ ልብ መስለቢያ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋጋዉን ይቀንሱለት እንጂ ገዢ መች አጣ? ወ/ሮ መአዛም እንዲህ አይነት ነገር ልባቸዉን እንደሚስበዉ ደጋግሜ ተመልክቻለሁ በዚህ በፍቅር ቀን ጋዜጠኛ ተከታትሎ ጉዳቸዉን ቢያሳየን መልካም ነበር። መቼም ህወአት አገሩን እንዳልነበረ አድርጎታል ባዘጋጀልን ቦይ መፍሰስ ነዉ።
    በተረፈ ያገሬ ሰዎች ይህን ነገር ወደናንተ የላኩት ሰዎች ሲያዩዋችሁ ሆዳቸዉን እስኪያማቸዉ ይስቁባችሗል ከነሱ በላይ እነሱን አትሁኑ ብትችሉ የሀገራችሁን ባህል አሳድጉት ገና አልተነካም።፡ወንዶች ጋዜጠኞችም አማረብን ብላችሁ ጸጉር ሳታበጥሩ ዉል ያለዉ ልብስ ሳትለብሱ የፈረንጅ ዱርዬ መስላችሁ እራሳችሁን አታዋርዱ።፡ፕሮቶኮል የሚባል ነገር መኖሩንም አትዘንጉ “It is good to look good than to be good ” የሚባል ነገር አለ ብትችሉ ሁለቱንም ሁኑ። እንዲህ ፈረንጅ ለመሆን መጨናነቅ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነዉ? ይህንንሰ norm ማነዉ ያወጣላችሁ? ከማንነታችሁ እየሸሻችሁ የት ትደርሱ ይሆን? አንተ ሰዉ እግዜር ይይልህ ያልሆነ አርእስት ጀምረህ ምን ዉስጥ ከተትከኝ?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.