የኢትዮጲያዊ ማንነት፣ የብሄረሰብ ማንነትና አራቱ አንኳር የመንግስታዊ ስርዓት አቅጣጫዎች

ዛሬ በሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ፍጅት ማለትም ግድያ፣ አካል መጉደል፣ ስደት ፣የንብረት ውድመት ፣የፍትህ መጓደልና የዕለት ተዕለት አስተዳደራዊ በደል ፣ምክንያቶቹ አሁን በስራ ላይ ያለው ሕገ መንግስት ፣ አግላዩ የክልል አውቃቀር ፣ እንዲሁም ‘የብሄር ማንነት’ ፖለቲካውና የመንግስት መዋቅር ውስጥ መሰንቀሩ መሆኑን የማይረዱ በርካቶች ናቸው። የብሄር ማንነቴ ከኢትዮጲያዊ ማንነቴ ተጋጭቶብኝ አያውቅም የሚሉ ጅሎች በቁጥር ቀላል አይደሉም። ችግሩ በግለሰብ ደረጃ ላይታይ ቢችልም ስርዓቱ የኢትዮጲያዊና የብሄረሰብ ማንነትን ሚዛን የጠበቀ አይደለም።ዜጎች በብሄረሰብ ማንነታቸው ብቻ የሚታረዱትም ለዚህ ነው። እውነታው ‘የብሄረሰብ ማንነት’ የመንግስትና የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ከገባ ማንነትና ኢትዮጲያዊነት ፊት ለፊት ይላተማሉ።ክልሌ ነው ውጣልኝ እና ሀገሬ ነው የትም አልሄድም ግጭት ላይ ናቸው።

መሬት ላይም የምናየው በአንድ በኩል ይህ ሕገ መንግስት ሃገር ሊያፈርስ ነውና ይወገድ የሚልና በሌላ በኩል አይ ለሕገ መንግስቱ ትህነግ ደምና አጥንቱን ግብሯልና ይቀጥል ከሚል ሰጣ ገባ በዘለለ፣ በተጨባጭ ያሉትን ሌሎች አማራጮችና ያሏቸውንም ጠቃሚና ጎጂ ጎኖች በዝርዝር ማወቅና መረዳት ትኩረት የተሰጠው አይመስልም። እዚህ ከማቀርበው የተሻሉ ሃሳቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ እየተገነዘብሁ፣ በኔ እይታ ግብ ግብ ውስጥ ያሉትና ሚዛናቸውን መጠበቅ ያልቻሉትን ፣ የኢትዮጲያዊ ማንነትና የብሄረሰብ ማንነት፣ በተለያዩ ጠርዞቻቸው ሲዋሃዱ የሚፈጥሯቸውን አራት አንኳር የፖለቲካ ስርዓት አማራጮችና የአማራጮቹንም ጠንካራና ደካማ ጎኖች በቀላል ሞዴል ለማሳየት እሞክራለሁ።

በሂሳቡ ዓለም የትስስር ወለል (coordinate plane) አዎንታዊ (+) እና አሉታዊ (-) ጠርዞች ባሏቸው በሁለት መስመሮች መተላለፍ የሚፈጠር፣ የጉዳዮችን ተዛምዶ መመርመርያ ቀላል መሳሪያ ነው። በአንዱ መስመር የብሄረሰብ ማንነትን፣ በሁለተኛው መስመር የኢትዮጲያዊ ማንነትን በማስገባት ፣ በመስመሮቹ የተለያዩ ጠርዞች ትስስር አራት ቀጠናዎች ይፈጠራሉ። እያንዳንዱ ቀጠና ሁለቱ ማንነቶች በተለያዩ ጠርዞቻቸው (+ & -) የሚፈጥሩት ስለሆነ ፣ ያሉትን ሁሉንም አንኳር የመንግስታዊ ስርዓት አማራጮች በአንፃራዊነት አንድ ገበታ ላይ እናገኛለን።ይህም ለተሻለ ሀገራዊ መደላድል የሁለቱ ማንነቶች ሚዛን በተሻለ የሚጠቀበቅበትን ለመምረጥ ቀላል ይሆንልናል። ሶስተኛ መስፈርት በመጨመርም ሊታይ ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ”

— ሙሉውን መግለጫ ላማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ—


 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.