በአማራ ሕዝብ ላይ የሚካሄደው የዘር ፍጅት ይቁም ! ወንጀልም በሥሙ ይጠራ! – ጀርመን የውይይትና ትብብር መድረክ

Germanሦስት አስርት ዓመታትን ያስቆጠረው ቋንቋንና ጎሳን መሰረት አድርጎ የተገነባው የከፋፍለህ ግዛው የፖለቲካ ሥርዓት በሕገ መንግስት እውቅና አግኝቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተንሰራፋበት ጊዜ አንስቶ በበርካታ የሀገራችን ክፍሎችና በተለይም ኦሮሚያና ቤኒሻጉል ጉሙዝ የሚባሉት ክልሎች ነፍሰ ገዳዮች የሚፈለፈሉባቸውና ስርዓተ አልበኝነት የነገሰባቸው ክልሎች ሆነው ቆይተዋል። ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ የሚጨፈጨፉት፣ የሚደርስላቸው አጥተው እየታረዱ እሬሳቸው በየዱር ገደሉ የሚጣለው፣ ተዘቅዝቀው የሚሰቀሉትና በግሬደር እየተጠረጉ በጅምላ የሚቀበሩት በነኚህ ክልሎች ነው። እነዚህ መልካቸውን እየቀያየሩና የጭካኔ መጠናቸው እየጨመረ በተደራጀ መልኩ የሚካሄዱት ዘር ተኮር ጭፍጨፋዎችና የማፈናቀል እርምጃዎች አካባቢውን ከአማራና አማርኛ ተናጋሪ ከሆኑት ማህበረሰቦች የማጽዳት ዘመቻ አካል እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል።

— ሙሉውን መግለጫ ላማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ—–   


 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.