“ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያን በማጥፋት የሚገኝ  ነፃነት ሳይሆን ባርነት ነዉ” –   ማላጂ

Ethiopiawinetኢትዮጵያችን በየዕለቱ እንደ ጨርቅ እያለቀች እና እየጠበበች ለድሆች ከመሆን ይልቅ የምታስጨንቅ ከሆነች እንዴት ለሁላችን ልትሆን እንደምትችል እጅግ ሊያሳስብ በሚችል ደረጃ ላይ መድረሳችንን ያሳያል ፡፡

በዉጭም ሆነ በዉስጥ በተከሰቱ የኢትዮጵያ ጥቃቶች ዛሬም እንደ ትናንቱ ቀድመዉ የደረሱት የብዙሃን ህዝብ የቁርጥ ቀን ጀግኖች የሆኑት  የመንፈስ እና ወኔ ባለፀጎች አገር እና ወገን ወዳዶች የወደቁለት እና እየተዋደቁ ያሉት ለመላዉ ህዛብ እና ወገን እንጅ ለአንድ ክፍል ወይም ቡድን አልነበረም አይደለምም  ፡፡

ለዚህም አብይ ምስክር የጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በትህነግ ጠባጫሪነት ተቀጣጥሎ የተቆሰቆሰዉን የአገር ክህደት እና ሉዓላዊነት ስጋት የነበረዉን የጥፋት ኃይል  ክንፍ የሰበረዉ የኢትዮጵያ ድኃ ህዝብ ልጅ ነዉ ፡፡

በጣሊያን ወረራ ….. ሀብት / ንብረት የሰበሰበ እና ድሀዉን ሲገፋ የነበረዉ ለስደት እግሬ አዉጭኝ ሲል ….እነ አባኮስትር……ጠላትን መግቢያ መዉጫ ያሳጡት ለህዝባቸዉ እና አገራቸዉ ሞት እና ዉድቀት እንዳልነበር እንዲሁም  በዕብሪተኛዉ ዚያድባሪ ፊዉታራሪነት የሶማሊያ ጦር ኢትዮጵያን ሲወር እና አገር ጭንቅ ስትገባ …… ፈጥነዉ ከተፍ ያሉት እና በእነ ኮ/ል አጥናፉ አባተ የተመለመለዉ እና የተዘጋጀዉ የኢትዮጵያ  ድሃ ሰርቶ አደር ልጅ እንደነበር እና ይህም በኢትዮ ኤርትራ ጦርነትም በዘመናችን የተገለጸ ዕዉነት ነዉ ፡፡

የሚያሳዝነዉ በጣሊያን ፣በሶማሊ፣ በኢትዮ ኤርትራ ሆነ በአሁኑ በትግራይ ጦር (ትህነግ) በተካሄዱ ጦርነቶች ሁሉ ከኋላ ሀነዉ ለዉጭ እና ዉስጥ ጠላት መሳሪያ ሆነዉ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ተጠልፈዉ የሚወድቁበትን ገመድ በመሸረብ እና ጉድጓድ በመማስ የጥፋት ተልዕኮ ( የህዝብን ሠላም እና ደህንነት ፣ህይዎት….አደጋ ላይ በመጣል) ፈጻሚ እና አስፈጻሚ የነበሩት ዛሬም ያንኑ ሲደግሙት እየታየ ስማቸዉ እና ተግባራቸዉ በዓለም ከሚታዩ ዘግናኝ እና አስነዋሪ ድርጊቶች በላይ ገላጭ ( በለይቶ ማጥቃት ፣ ፍጅት፣ ማፈናቀል፣ ኢሰባዊ ድርጊት….) ሆኖ ሳለ ኢትዮጵያን እየገደሉ አፈሯን መፈለግ ከጠላትነት በላይ ትዉልድ እና አገር ገዳይነት ነዉ አለማለት ለክፉ ሞኞታቸዉ ይሆናል የሚሉትን ጥፋት ሁሉ እያዩ እንዳላዩ መታለፍ በዕኩይ ጥፋት የህዝብ ነጻነት እና ማንነት ዋጋ በሚያሳጣ ተግባር ጠላት  እንዲገፉ ጉልበት ሆኗል ፡፡

የዘመናት የትዉልድ ተጋድሎ ለፀረ አንድነት እና ህዝብ ቡድን የስልጣን እና የጥቅም  ዘመን ማራዘሚያ እንዳልነበር የብዙዎች ዕምነት ቢሆንም በየጊዜዉ ከድል ማግስት ለህዝብ እና ለአገር ክብር የተደረገዉን መስዋዕትነት በመርሳትም ሆነ በመካድ መልሶ ህዝብ የመበደል እና የማግለል ልምድ ግን ዛረም በ21ኛዉ ክ/ዘመን በአገራችን መኖሩ ዕርግማን ይመስላል ፡፡

ይሁንና የኢትዮጵያዉያን ልጆች ለሞቱለት አገር እና ወገን ቁስላቸዉ ሳይሽር በጀርባ እና በህዝብ መሃል በመሆን ህዝብ  ለሚያደሙት የዉስጥ እና የዉጭ ጠላቶች  ትናንትም ፤ዛሬም ለሚዋደቁለት ቁርጥ ቀን ልጆች ለከፈሉት እና እየከፈሉ ላሉት የህይዎት እና የአካል መስዋዕትነት ዕዉቅና መንፈግ  ይመስላል ፡፡

  ይህም ኢትዮጵያዉያን መቸ እና እንዴት ካለፈ ታሪክ እና የህይዎት ልምድ እንደምንማር አጠያያቂ ቢሆንም ለዓመታት የተቦካ የብሄራዊ አንድነት እና የህዝቦች ማንነት ጥፋት ሴራ ቋያ እራሳችንን እስካላቃጠለን ምን ቸገረኝ በሚል የራስ ወዳድነት ድንዛዜ አበዜ እንደተጫን ዘመን አልፎ ዘመን ተተክቶ ይኸዉና ዛሬ ላይ በችግር እና በመከራ ቆፈን ዉስጥ እንደነበርን አለን ፡፡

ለዘመናት በአገር አንድነት እና የህዝቦች በጋራ መኖር የምኞታቸዉ ዕንቅፋት አድረገዉ የሚያስቡት ፀረ ህዝብ እና አገር  አቋም ይዘዉ በዉስጥ እና ዉጭ አጋሮቻቸዉ ድንጋይ አቀባይነት  ከመነሻዉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኢትዮጵያዊነትን በነርሱ የጥላቻ እና ጥፋት መዝገብ ፍች  ዓማራ የሚሉት ኢትዮጵያዊ ቀለም፣ ማንነት፣ አስተሳሰብ እና ባህል ያለዉን ህዝብ የሚደረገዉ የዓመታት ሴራ በቀላል አገላለፅ  ዐማራ የሚሉት የማህበረሰብ ክፍል ጠላታቸዉ ሆኖ ሳይሆን የዓላማቸዉ መዳረሻ ኢትዮጵያን መከፋፈል እና ድርሻቸዉን መሳላሰል መሆኑን እና ለዚህም ኢትዮጵያዊ ማንነትን መንቀል እና ማመሳቀል መሆኑን ለመናገር አለመፈለግ ወይም አለመቻል በህዘብ እና አገር ላይ በደል በበደል ሲጨመር ማየት አይገርም ፡፡

ይህ ሆኖ እያለ ድፍን ሶስት አስርተ ዓመታት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን ለማጥፋት በሚያስችል ሁኔታ መግደል፣ መነጣጠል፣ ማሳደድ ፣ ሰርቶ እንዳይኖር በራስ አገር መፃተኛ ማድረግ፣ ከስራ ማገድ ማፈናቀል (በመንግስትም ሆነ ስመ የግል ድርጅት ….በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የትህነግ /ኢህዴግ ይዞታወች በነበሩት እና ባሉት  ) ፣ አንዱ በሌላዉ በተለያየ መንገድ እንዲነሳ፣….. የማድረግ ስራ ሲሰራ ….. አማራ ስለነበር ፣ ሆኖ ስለረገኘ ……..እየተባለ ለዛሬ ስንደርስ …… አሁንም ቢሆንም ሀሶስት አስርት ዓመታት በኋላ ሰባዊነት ፣ዕምነት እና ኢትዮጵያዊነት ማንነት አለኝ የሚል ይህን ዕዉነት ሊደፍር አለመቻል የጥፋት ወላፈን ዕሳት  እኛን አይደለም ምንቸገረን ለሚሉት አድር ባዮች ላለመደረሱ ግን ማንም እርግጠኛ መሆን ቀርቶ መገመት አይቻለዉም ፤ የጥፋት ዕሳት ነፋስ ስለሚከተል እና የነፋስ አቅጣጫም መቀየር የሚችል ዕምነትም ሆነ ስብዕና ያለዉ ስለሌሎች አብዝቶ ይጨነቃል እንጅ ሌሎች ሞት እና ጥፋት አያስብም እና  ፡፡

ትናንት ኢትዮጵያዊነትን ከስሩ በማፍረስ በራሳቸዉ ምኞት እና ስሪት ለሚመሰርቱት አገር እንዲመች የኢትዮጵያዊነት ዛፍ መንቀል (ማፈናቀል) ብቻ ሳይሆን ማጥፋት ፣መግደል እና ታረክ እና ስም በመደለዝ እና በመበረዝ የራሳቸዉን ፍሬ አልባ ገድል የጥፋት እና ሞት   ለመጻፍ ሲባክኑ የነበሩት ለኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያ ጥፋት  ያዳፈኑትን እሳት እና ገለባ ይዘዉ ታች ላይ ለሚሉት ግብረ አበሮችም ሆነ ለቆሰቆሱት መዳረሱን እያየን ነዉ ፡፡

የአገርን ክብር እና ዳርድንበር አሳልፎ ለመስጠት ከሚደረግ የጠላት ግብ ግብ መፍሰሻ ቦይ ከመነሻዉ ሲቀየስ  ኢትዮጵያዊዉን አማራ እንደ መደብ ጠላት አደርጎ ከፈረጁበት ጊዜ አስካሁን ይህ  ፀረ አንድነት እና ህዝብ አመለካከት እንደነበረ እና እንደሆነ ከየትኛዉም የአገር እና ህዝብ ጉዳይ ይመለከተኛል ከሚል ሁሉ በግላጭ ሲነገር ሆነ ሲመሰከር አለማየት በአገር እና ህዝብ ላይ ከተደገሰዉ የጥፋት ሴራ  ስጋት ለመዳን የሚደረገዉን ብሄራዊ ጥረት እና ጥምረት የሚያግዝ አለመሆኑን በገቢር ከምናያቸዉ አሁናዊ አገራዊ ጉዳዮች እና ሆነቶች መረዳት ይቻላል ፡፡

እንደ አገር እና ህዝብ የአንድን ማህበረሰብ ማሳደድ ግፍ መስፈሪያዉ ሲሞላ ለሌላዉ መትረፉን በዕድሜያችን ከማየት በላይ ምን ምልክት እንደምንጠብቅ አሁንም በበዥታ ዉስጥ መሆናችን በአለፉት የጥልመት እና ሞት ዓመታት ዓለም ዉስጥ እንዳለን የሚያሳይ ተፅዕኖ መዳፍ ስር ስለመሆናችን ነዉ ፡፡

የአገር  ክብር እና ዳር ድንበር ሲከበር የሚያቀረሻቸዉ   ፤ አገር እና ህዝብ ሲዋረዱ ስለጥቅማቸዉ እያሰሉ በጥፋት እና ነዉር ጮቤ ለሚረግጡት የጥላቻ እና ክፋት ጌኛዎች ቢያንስ ዕኩይ ምኞታቸዉን ለመተግበር የሚየደርጉትን ሩጫ በመረዳት  ትናንት ተጀምሮ ዛሬ የቀጠለዉ  አገራዊ የጥፋት ዕሳት ሁላችንንም ተራ በተራ ሳይፈጀን በንቃት እና በህብረት መቆም መርጫ ሊሆን አይገባም ፡፡

አገር እና ህዝብ ሲጠፋ እያዩ እንዳላዩ ሆኖ ማለፍ ከሩቅ ያለዉን የበላ ዕሳት መሃሉን የማይደርስበት ምክነያት ስለማይኖር እና ይህም የአገራችንን ብሂል …የጨዉ ክምር ሲደረመስ ሞኝ ይስቃል ፤ ብልህ ያለቅሳል እንዲሉ ከትናንት አሰከዛሬ በአገር እና ህዝብ መታመስ እና ማልቀስ ለሚሳለቁ እና ለሚስቁ እነ ምንቸገረኝ ( እያዩ ምንአገበን፤ እየሰሙ ካልደረሰብን  ) ዙሩ መድረሱ አይቀርም እና ዕዉነቱን ለመናገር ፤የሆነዉን ለመመስከር ፣ ራስንን እና አገርን ለማስበር በአንድነት እና በጋራ መቆም ከአሁን የተሸለ ጊዜ አይኖርም ፡፡

ለአለፉት የጥልመት እና ሞት ዘመን በቀል እና በደል የተፈራረቁበትን ሠፊ እና ድኃ ሠርቶ አደር ህዝብ ላይ ዛሬም እንደ ትላንት ኢትዮጵያዊነት ዓማራ ብሎ የሚፈርጀዉ እና የሚያሳድደዉ ኢትዮጵያዊዉ ህዝብ ሁሉ በጠላትነት መፈረጁ አገራዊ ዉለታዉን በመርሳት ሳይሆን የመካድ እና የጥላቻ ትርክት ጉልበት ሰጪ የጥፋት ማቀጣጠያ በማድረግ የፖለቲካ ጥቅም እና ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ትንቅንቅ ነዉ ፡፡

 ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊነትን በመካድ እና በመናድ ምድረ በዳ አገር ላይ አፈሩን እና ሸንተረሩን ለሚመኝ እና የምኞት አገር ለመመስረት በህዝብ ደም እና ህይዎት ዋጋ የሚደረግ  መስዋዕት( ጥላቻ ፣ክህደት እና ጥፋት) መሆኑን ሁላችንም በመረዳት ራስን እና አገርን ለመታደግ በቀቢፀ ተስፋ ከማንቀላፋት የራስ ወዳድነት አስተሳሰብ በመዉጣት ሁላችንም የራሳችን እና የአገራችን ጉዳይ ከዕኛ በላይ ለእኛ ማን እንደ እኛ በማለት በህብረት እና አንድነት ድር ተሳስረን መነጋገር ፣ መደማመጥ ፣ መንቃት፣ መዘጋጀት  እና መደራጀት የሚኖርብን ጊዜ አሁን ነዉ ፡፡

በመጨረሻም በህዝብ እና አገር ላይ የመከራ ዘመን በማራዘም በነጻነት ስም ግፍ እና በደል ደጋግመዉ ለሚያደርሱ ሁሉ ዕዉነተኛ ማንነት እና ነጻነት ያለዉ ህዝብ በነጻነት ስም  ባርነት እና ጥልመትን አሜን ብሎ አይቀበልም ይልቁን የዛሬ ሞት የዳግም ትንሳዔ ጉዞ በአንድነት እና ህብረት ክንድ የሚታገልበት ጊዜ ላይ መሆኑን እንዲያወቁ በልማድ ንግግር ሳይሆን በተግባር ለማሳየት መነሳቱን ሊያረዳቸዉ ይገባል ፡፡

እየደጋገመ ለምናየዉ የአገር እና ህዞች ስቃይ በብሂል ልደምድመዉ !!!

 “እግር ነጣ ነጣ ፣እጅ ነጣ ነጣ ፣

እንዲህ አይደለም ወይ ቁምጥና ሲመጣ !!!

 

                                                ህብረት እና አንድነት ኃይል ነዉ                                                           

                                                               

                                                           ማላጂ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ተጋድሎ ከዚህ ወዴት?

1 Comment

  1. Ato Malaj,

    First, write in your real name. Who can trust a person who writes in fake name? A person who fakes a name is fake!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.