ታዋቂው ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

fb image 144ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ደጋፍ ለማቅረብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ። አቤል ተስፋዬ በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በረሃብ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበረ በአሜሪካ የአለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።

ዘ ዊኬንድ አሁን ላይም በትግራይ ክልል የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የገለፀው በአሜሪካ የአለም ምግብ ፕሮግራም በድምፃዊው የተደረገው ድጋፍ ወሳኝ ነው ብሏል። ድጋፉ የአለም ምግብ ፕሮግራም በመጪው ስድስት ወራት የአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።
https://amharic.zehabesha.com/the-weeknd-donates-1-mil-for-2-million-meals-to-help-ethiopians/
ኤፍ ቢ ሲ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጉደር አምቦ ጸጥታው ደፍርሷል::ምርጫው ቆሟል::

1 Comment

  1. ለሌሎችም አርዐያ የሚሆን ግለሰብ በመሆኑ እጅግ የላቀ አክብሮት እና ምስጋና ይገባዋል። የላከው ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም በግል ድጋፍ ለማድረግ እየፈለግን ለነበርን አይናችንን ስለገለጠልን እናመሰግነዋለን። በማን በኩል ላኩ ፣ በማን እርዳታ ሰብሳቢ በኩል እርዳታ አትላኩ እየተባልን ግራ ተጋብተን ሳለ ግርግር እና ሁካታ በሌለበት መርዳት እንደምንችል ስላሳየን አቤል ባለውለታችን ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.