“በሁሉም ቦታ በደረሰው ጥቃት አጸፋ እርምጃ በክልልና በፌዴራል መንግስት ቅንጅት እየተወሰደ ይገኛል”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

New TPLFጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁሉም ቦታ በደረሰው ጥቃት አጸፋ እርምጃ በክልልና በፌዴራል መንግስት ቅንጅት እየተወሰደ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን፤ የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን ለሟች ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እንገልጻለን” ብለዋል፡፡”
ጠላቶቻችን በውስጥና በውጭ ተደራጅተው ንጹሀን ዜጎቻችንን በመግደል የጀመርነውን ጉዞ ለማሸማቀቅ እና ከመንገዳችን ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሥዋዕትነት እየከፈልንም ቢሆን የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክረን ጉዟችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
በሁሉም ቦታ በደርሰው ጥቃት አጸፋ እርምጃ በክልልና በፈዴራል መንግሥት ቅንጅት እየተወሰደ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ጥፋት ኃይሎች ወጥመድ ላለመውደቅ በማስተዋል እየተጓዘ፤ በእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ከመንግሥት ጋር ተባብሮ
ጥፋተኞችን ወደ ሕግ ለማቅረብ እና እንደዚህ ዓይነት ግድያዎች ፈጽመው እንዲቆሙ በትብብር ልንሠራ ይገባልም ብለዋል።
“ኢትዮጵያ በመሥዋዕትነት የቆመች፤ በመሥዋዕትነት የምትቀጥል ሀገር ናት። በትብብርና በአንድነት መንፈስ የኢትዮጵያን ጠላቶች ደግመው እንዳይነሡ አድርገን ማጥፋት አለብን” ሲሉም ነው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የገለፁት።

3 Comments

 1. Abiy ahmad is a liar and fraud. , mentally deranged individual who has been repeating the same lie over and over again in the hope that people will believe him. He was in Benshingul very recently , supposedly to stop the genocide. Instead he allowed those who commit the genocide to take over the meeting he was called to attend and the murderers used the platform to launch more genocide on the amhara living in the region. upto 200 people were murdered soon after Abiy left the region . Abiy did not even attempt to visit the genocide victims and to listen to their story. This is the first time ever in 3 months that Abiy said sorry to the victims families, when it is clear that the genocide was ongoing for the last 3 years.
  This announcement is not going to have any impact, infact it is a cover up for more genocide and a coded announcement for more genocide.
  We have seen all of the suspects of the Shasshmane and Arusi genocide suspects all released from prison without any single person being charged, No one has been charged or questioned for the last three years despite the fact that all the criminals who commit this viocious barbaric crimes are all known and could have been caught. There are 100s of thousands of local oromo militias , trained by the regime who could have been deployed to protect the public. Instead The militia assist olf murderers and allow them to hide or disappear without trace. This is known by the regime and the local representatives ofthe regime.

 2. የሰውዪው ውሸት የጀመረው የመጀመሪያ ንግግሩን በፓርለማ ያደረገ እለት ነው።አልገባ ያለን እኛው ነን። አሁንም የ3ኛ አመቱን ህዝብ እያለቀ ከአጎብጓቢዮቹ ጋር በግብዣ ሲንደላቀቅ እያየን ነው።. ነብስ የዘራባቸው የሌላ ሀገር መንግስታት መሪዎች ፣በዜጎቻቸው ጭንቅ ጊዜ አለንልህ ብለው ከጎናቸው ቆመው የሀዘናቸው ተካፋይ ይሆናሉ። ይሄ ጉድ ግን ከራሱና ከራሱ ሲጨመር ደግሞ ከኦሮሚያ ውጭ በኢትዮጵያ ምድር ሌላ ምንም ስሜቱን አይጎረብጠውም።
  የፈረደባት እናቱ ንጉስ ትሆናለህ ብላኛለች ብሎ ይኸው ኢትዮጵያን እንዳልነበረች እያደረገ ነው። የኔም እናት ጭራሹን ስም ስታወጣልኝ ንጉሤ ብላኛለች። እንደርሱ ቅዠትና ብዥታ ላይ አልወደቅሁም። ለሁሏም እናት ልጇ ንጉሧ ነው ። ምናልባት የፍቅሯ አገላለፅ አልገባው ይሆን። በጣም ይመስላል ።
  እግዚአብሄር ከዚህ ሰውዪ መቅሰፍት እንዲሰውረን እንማፀነው።

 3. ከአንጅት ካለቀሱ ይባላል ነገሩ!! እውነት ከውስጥ ያለ ችግርና ነቅሎ ማውጣት አዳግቶ ነው??? ብልፅግና፣ ኦዲፓ ውስጡን በደንብ መፈተሸ እና ማጥራት ይኖርበታል፡፡ የሰው ልጅን መግደል እና እነዚህ ሳይፈልጉ ወደዚህች ምድር የመጡ ሕፃናትን መፍጀት ምን ያህል የሰው ልጅ የመጨራሻ አውሬነት ደረጃ እንደደረሰ ማሳየቱን በግልፅ ያሳየ ነው ድርጊቱ ሲፈፀም የመጀመሪያ ባይሆንም፡፡ በየቦታው ያሉ አስተዳደር አካላትን ጨምሮ አሁንም በህውአት ርዝራዥ እና ኦነግ ሸኔ እየተባለ በተዘረጋ ሴራ ላይ መንግስት ስሩን በመበጣጠስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት ካልቻለ የባሰ ችግር እንዳይመጣም ምንም ዋስትና የለም፡፡ ተቻችሎ መኖር የሚችል ማህበረሰብ እሲኪፈጠር ካልሆነ የአማራ ክልል አስተዳደር ችግሩ ባለበት አካባቢዎች ያሉ አመራዎችን በእስቸኳይ መቀበያ በማዘጋጀት እንዲመለሱ ቢያደርግ ይሻላል ምንም እንኳን ብዙ አመታት በዛ የኖሩ ቢሆንም፡፡ ይህንን የሚፈልጉ ደስ ቢላቸውም ከመሞት ይሻለል፡፡ መስሎዋቸዋል ነገ በኔ ነው ነገሩ፡፡ ይህ ደግሞ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ተመላሾሾቹን በማቋቋም ደረጃም ባለሀብቶች እንዲሳተፉ የአማራ ክልል ማስተባበር ይችላል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.