ኦሮሚያ ዉስጥ የሚካሄደዉ ጀኖሳይድ ሊቆም አይችልም ምክንያቱም – ሚክይ አማራ

welega

 1. በተለይም ጨለማን ተገን አድርጎ የኦሮሚያ መንግስት የሚያካሂደዉ ጭፍጨፋ በመሆኑ መቼዉንም አይቆምም፡፡
 2. የኦሮሞ ኢሊቶች፤ አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች እስከዛሬዋ ድረስ ህዝባቸዉን ሞቢላይዝ እያደረጉት ያሉት በየአካባቢዉ አማራዉን ጠላት አድርገዉ እንዲያዩት በመሆኑ ጭፍጨፋዉ አይቆምም፡፡
 3. አይደንቲቲ ሁሌም ቢሆን የሚሰጥህ እና ዲፋይን የሚያደርግልህ የሚገድልህ ጠላትህ ነዉ፡፡ አማራ አይደለሁም ብትለዉም ገዳይህ ዲፋይ አድርጎሃል፡፡ ከአካባቢዉ ባህል ጋር አሲሚሌት ማድረግም ሆነ ወይም በፖለቲካዉ ፓሲቭ መሆን ለጀርመን ጀዉሾች፤ ለሩዋንዳ ቱትሲዎች፤ ለአዘር ባጃኖች አልሰራም፡፡ በ50 እና በ100 ግድያዎች ተነስቶ ቀስ በቀስ እስከ ስድስት ሚሊየን የጅምላ ግድያ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ ኦሮሚያ ዉስጥ ያለዉ አማራ በፖለቲካዉ ፓሲቭ ቢሆንም ማንነቱንም ለመቀየር ቢሞክርም ከመታረድ አልዳነም፡፡

ከዚህም በመነሳት የህዝብ እልቂትን ለመታደግ ከፍተኛ ችግር ያለባቸዉን እና ሪሞት የሚባሉትን እንዲሁም ለተደጋጋሚ ጥቃት ተጋላጭ አካባቢዎች የሚኖረዉን ህዝባችን ማንቀሳቀስ እና ማስፈር (population transfer) አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ህይወትንም መታደግ ነዉ፡፡

Population transfer በተለያዩ ሀገራት ጥቅም ላይ የዋለ እና የህዝቦችን ህይወት የታደገ ነዉ፡፡ ለምሳሌ

 1. ኦሮሚያ ክልል ትልቁ ድክመቱ የነበረዉን እስከ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጋ ኦሮሞወች ከሶማሌ ክልል የተወሰኑ ቦታዎች ላይ በማስወጣት ዛሬ ላይ የተሻለ ሰላም አላቸዉ፡፡ ቢያንስ የሚገደል ህዝብ የለም፡፡
 2. የሶማሌ ክልልም ከ 50 ሽህ በላይ የሚሆኑ ከኦሮሚያ ሁለት እና ሶስት አካባቢዎች በማስወጣቱ ከጭፍጨፋ አድኗቸዋል፡፡
 3. በሰሜን ናይጀሪያ ኢቦዎች ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በተደጋጋሚ ሲካሄድ የሀገሪቱ መንግስት ከ 1ሚሊየን በላይ የሚሆኑትን በሰሜኑ ክፍል ይኖሩ የነበሩትን ወደ ሌላ አካባቢ አንቀሳቅሷል፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ለጄኖሳይድ የቀረበ ጭፍጨፋ አላጋጠማቸዉም፡፡
 4. የታሚል ዘር የሆኑ በሲሪላንካ ከተማ ኮሎምቦ አካባቢ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በየጊዜዉ ሲያጋጥማቸዉ በመቶሽዎች የሚቆጠሩት ወደ ሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተዛዉረዋል፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ለጄኖሳይድ የቀረበ ፍጅት አላጋጠማቸዉም፡፡
 5. በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሰርቦች ከስሎቬኒያ እና ክሮሽያ ክፍለግዛቶች በመዉጣት ህይወታቸዉን አትርፈዋል፡፡
 6. እስከ ሁለት ሚሊየን የሚደርሱ ጀርመኖች ከኢስተርን ኢሮፕ ሀገሮች በመዉጣት ከጭፍጨፋ ድነዋል፡፡
 7. ከ 2 ሚሊየን በላይ ራሽያዎች በ1990ዎቹ ከተገነጣጠሉት ሀገራት ወደ ራሽያ ግዛቶች ገብቶ በማስፈር ከጭፍጨፋ ተርፈዋል፡፡
 8. 200 ሽህ ሃንጋሪዎች ከሰርቢያ አንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ በመስፈር ከጅምላ ግድያ ተርፈዋል፡፡
 9. ቡልጋሪያ፤ ግሪክ፤ ቱርክ ዉስጥ በየጊዜዉ የሚረጉ ዘርን መሰረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎች አንዱን ወደ አንዱ በማስፈር ዘር ተኮር ጅምላ ጭፍጨፋን አስወግደዋል፡፡

በመሆኑም በተደጋጋሚ እና ከፍተኛ ችግር የሚያጋጥምበትን አካባቢ በመለየት በተለየም በምእራብ ወለጋ ህዝባችን ከአካባቢዉ የማስወጣት ስራ መስራት አስፈላጊ ነዉ፡፡ ከእነዚህ አካባቢዎች የሚወጡትን ለከተሞች ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች ማስፈር፡፡ ለአዲስ አበባ ቅርብ በሆኑ እንደ ሰሜን ሽዋ አካባቢ ባሉት ዙሪያዎች ማስፈር፡፡ ወንዝ ያለበት አከባቢ ማስፈር፡፡ በተለይም መጠነኛ ግድቦች የሚሰሩባቸዉ እና በትንንሽ መሬት በአመት ሶስት እና አራት ጊዜ የሚያመርቱብት አካባቢ ማስፈር፡፡ ሰፋፊ ቦታዎች እና ከፍት የእርሻ መሬቶች ያሉበት አካባቢ ማስፈር ለምሳሌ ቋራ አካባቢ፤ ጃዊ፤ ምእራብ ጎንደር፤ ማእከላዊ ጎንደር (ዳንሻ ወልቃይት)፤ ወልደያ አካባቢ እና የመሳሰሉት፡፡

ባለሃብቱ ተባብሮ በ10 ሽህ የሚቆጠሩ ቤቶችን በመስራት እንዲያግዝ ማድረግ አስፈላጊም ከሆነ ለአመት እና ለሁለት አመት ብቻ የሚቆይ ልዩ የገቢ ግብር በመጣል ለዚሁ ተግባር ማዋል፡፡

እኛም ባናጓጉዛቸዉ አሁን ላይ በዱር በገደል እያሉ ግማሹ እየሞተ፤ ግማሹ እየቆሰለ፤ ንብረቱ ተበትኖ እየወጡ ነዉ ያሉት፡፡ ይሄን ለ 40 አመት ማስቆም ካልቻልን እነዚህ ለተደጋጋሚ ጭፍጨፋ ተጋላጭ የሆኑትን በመምረጥ በስርአቱ ከእነ ሃብት ንብረታቸዉ ማጓጓዝ ዉጭ ሌላ መፍትሄ የለዉም፡፡ ከዚህ ዉጭ ጨፍጫፊ መንግስት ላይ የቱም ያህል ጫና ብታደረግ ሊያቆም አይችልም፡፡

ለህዝባችን ሀገር እናወርሳለን ብለን ሞትን ልናወርስ አይገባም!

ሚክይ አማራ

 

 

3 Comments

 1. I strongly agree that as long as the dirty and deadly political system of EPRDF /Prosperity keeps going without being challenged and forced either to die it’s natural or otherwise, there will never be any meaningful stability at all!!

 2. በጣም ጥሩ የመፍትሔ ሃሣብ ነው። ግን የተጠቀሱት የውቭ ሀገራት ህዝቦች ከዕልቂት የዳኑት የኔ ነው የሚሉትና የኛ ላቸው የሚላቸው ህዝብና መሪ ነበራቸው። የኛ ከዚያ ይለያል። ህዝቡ ነፍዟል፤ ነሁልለናል። የአማራ ክልል ተብዬው የሆዳም አሽከሮች ጥርቅም በመሆኑ እንደምንም ብለው ከዕልቂት አምልጠው የሚሄዱትንም ”እዚያው ወደነበራችሁበት ሄዳችሁ እለቁ እንጂ አነሥጠጋችሁም” እያላቸው እንደሆነ እያየን ነው። በጣም እጅግ በጣም የጨነቀ ነገር ገጥሞናል። ጸሎትና ምህላ እንኳን እንዳንይዝ አንድም የሃይማኖት አባት የለንም፥ ሁሉም በዓለም ጠፍተዋል፤ በአጋንንት ተጠፍንገዋል።
  ምን ይሻለናል? ትልቅ ጥያቄ ነው። እግዚአብሔር ይሁነን ከማለት ውጪ ሌላ የተሻለ አማራጭ ለጊዜው አይታየኝም፤ እርግጥ ነው በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። እሱም ጥጋበኞች የጃቸውን ማግኘታቸው የማይቀር መሆኑ ነው። መቼ? ከፈጣሪ በስተቀር ጊዜውን ማንም አያውቅም፤ መገመት ግን አይከለከልም።…

 3. የፀሀፊው ሀሳብ በተራ አስተያየት አማራጭ ይመስላል ግን አይደለም። እንምሳሌ የተጠቀሱት ሀገራት ህዝቡን ያንቀሳቀሱት. በአንፃሩ ከሌላ ባእድ ሀገር ነው ። ለምሳሌ በአረብ ሀገር የሚሰቃዩት የሚንገላቱትና የሚታሰሩትን ወደ ኢትዮጵያ መመለስና በሃገሩ ኢትዮጵያ የሚኖርን አንድ ኢትዮጵያዊ ጋር ማመሳሰል ፣እነ ሽመልስ አብዲሳ የሚፈልጉትን መጤዎች ሰብስቦ ወደ አማራ ክልል ማጓጓዝ ሕልማቸውን መደገፍ ነው።በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት ወደ አማራ ክልል ሸሽተው የመጡትን የአማራ ክልል በድኖች አልቀበልም ተመለሱ ብሎ አባሮ ለሌላ ጭፍጨፋ ዳርጓቸዋል። አንድ ህዝብ በሀገሩ ኢትዮጵያ መኖር ካልቻለ ጥፋቱ የመንግስት እንጂ የንዋሪው ህዝብ አይደለም። አሁን እንደታወቀው ጨፍጫፊው የኦሮሞ ልዩ ሀይል የሚባለው ሲሆን፣ቀጥታ ሀላፊነቱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሲሆን በበላይነት የሚቆጣጠረው አፈ ጮሌው አብይ ነው። እርግጥ የኦሮሚያ ክልል የሚባለው ኢትዮጵያ አይደለሁም ካለ፣ እንደ ህወሃት አይነት የቅጣት ዘመቻ በመሪዎቹ ላይ ማካሄድ አስገዳጅ ይሆናል።
  ለሚገደሉት ወገኖቻችን የሞራል ድጋፍ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ እርዳታና ራሳቸውን እንዲከላከሉ በፍጥነት ማደራጀት ብቻ ነው አማራጩ። እነዚህ ነብሰገዳዮች የሚገባቸው አንድና አንድ ብቻ ነው ። መክቶ ግምባር ማሳየት ብቻ ነው። ግራህን በጥፊ ሲልህ ቀኝህን ስጠው የኦሪት አነጋገር. በ21ኛው ክፍለ. ዘመን አይሰራም ።አለመስራቱንም በኦሪት ዘመን አስተሳሰብ ቆሞ የቀሩትን የኦሮሞ መሪዎች የታሪክ ዝቃጭ መሆናቨውን ያሳዩበት ጊዜ ነው።
  ህዝቡን ከዘር ማንዘሩ ከኖረበት ማሸሽ ለኢትዮጵያውያን አስከፊ ምሳሌ ማድረግ ነው። እነ ለማ መገርሳ ለምን በሱማሌ ልክ አንስተው ወደ አዲስ አበባ ና ዙሪያ ለምን እንዳሰፈሩ ምክንያቱንም ሳይደብቁ በግሀድ ነግረውናል። አልገባ ያለን እያጎበደድን እኛ አማሮች ብቻ ነን።
  አላህ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.