የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

fb image 1158በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት ።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሰው ፣የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ፣ም/ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ እና ሌሎች የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል ።

ብሔራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ከአረፋበት ሆቴል ተነስቶ በአዲስአበባ በተመረጡ ዋና ዋና ጎዳናዎች ለህዝቡ ደስታቸውን ይገልፃሉ ፤ ህዝቡም ለብሔራዊ ቡድኑ ያለውን ድጋፍ እና አክብሮት የሚገልፅ ይሆናል መባሉን ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኤፍ ቢሲ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.