የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ! – በላይነህ አባተ

wewwምጣድ የፈጀውን ጩኸቱን ሊቀማ፣
የዓለም ጆሮ እስቲመግል የእንቅቡ ተንጣጣ!

ምጣድ ያሳረረው ላንቃውን ለጉሞ፣
ተእንቅብ ያለው ጮኸ አፉን አንቦርቆ!

ሲያምሱህ የኖርከው የሱፍ የስንዴ ዘር፣
በአብሮ መኖር ክዳን ፍጅት ስትሸፋፍን፣
ፈንጠር ፈንጠር ብለው ፈንድሻ ጎመንዘር፣
የዓለምን ቀልብ ሳቡ ያረሩ በመምሰል፡፡

ጥደው የሚቆሉህ የሱፍ የስንዴ ዘር፣
ተዋልደን ተዳቅለን ድስኩር ስደሰኩር፣
ተቃጥለህና አረህ ተምጠፋ ታገር፣
ተንጣጣ እንደ መውዚር ጠንጥን እንደ ጠጠር፣
አንደበት ይኑርህ ምጣዱንም ስበር፡፡

ፍርደ-ገምድል ምድር ተድሮውም ከፍታ፣
ተበዳዩ በዳይ ክፈል ተባይ ካሳ!

ዓለም ስለምትወድ አፈ ሰፊ መርጣ!
የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
መጋቢት ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም.

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቤት ውበት! (ዘ-ጌርሣም)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.