ስለ ዶክተር ዝናቡ እርገጤማ አለመናገር አይቻልም! – አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

Abiyወደን የማንስቅባቸው ብዙ አጋጣሚዎች መኖራቸውን “ወደው አይስቁ” የሚለው ፈሊጥ ያረጋግጥልናል፡፡ አዎ፣ አንዳንዴ ተገደንም ቢሆን እንስቃለን፡፡ አንገቱ የተቆረጠ ሰው – አሉ ነው – ከሰውነቱ የሚለዬው ጭንቅላት በሣቅ እየተንከተከተ ለተወሰነ ጊዜ ራሱን ችሎ ይንቀሳቀሳል ይባላል፡፡ ይህ ግን የውዴታ ሳቅ አይደለም፡፡ እናም ሆዳችን እያረረ የምንስቅባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ – ልክ እንደማሽላዋ፡፡

ዶ/ር ዝናቡ እርገጤ ሕዝበ አዳምን በሣቅ ጦሽ ማድረጉን እንደቀጠለ ነው፤ ግሩም ተዋናይ እኮ ነው! በዚህ የሣቅና ስላቅ ሂደት የሚያሳዝኑኝ አንዳች ድግምት የተዞረባቸው የሚመስሉት ጭፍንና ምናልባትም የዋህ ደጋፊዎቹና ተከፋይ አክቲቪስቶቹ በነሀብታሙ አገላለጽ ውታፍ ነቃዮቹ ናቸው፡፡ “አውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም” – ትክክል ነው፡፡ ውታፍ ነቃዮቹ መተዳደሪያቸው ኅሊናን ሸጦ በሚገኝ ሶልዲ በመሆኑ የተፈለገውን ያህል እውነት ቢነገርና ቢለፈፍ ጆሮ የላቸውም፡፡ በቆረቡበት ውሸትን የማራገብ የሆድ አደርነት ተግባር እንደተሰለፉ እስከህቅታቸው ማብቂያ ይዘልቃሉ፡፡ በገንዘብ የተለወጠ ኅሊና ወደ ሆድ ወርዶ ስለሚሸጎጥ ሰውን መግደልና ማረድም ለነሱ ጽድቅ እንጂ ኩነኔ አይደለም፡፡

ዶ/ር እርገጤ ማነው ዝናቡ እርገጤ “በጎጃምና በሰሜን ሸዋ ዝናብ ያዘነብኩት እኔ ነኝ” እያለ ነው – ይህ ልጅ ጊዜ ካገኘ እንደ ሊቀ ሣጥናኤል እኛን ጭምር “አነ ፈጠርክክሙ በአምሳሊየ ወበአርአያየ” ሳይለን ይቀራል ብላችሁ ነው? እንዲያውም ይህን ዝናብ የማዝነብ ጥበቡን ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆኑንም “አብሥሮናል” – አሃ! ግን ቴሌ ባለአራት ጂቢ ብሮባንድን በኦሮሚያ ሲያስጀምር “ዝናብ” በሚል ኮድ ባላጡት ሥፍራ በአማራ ክልል የተጀመረው ዝናብን የማዝነብ የመንዝ ደብተራ ድግምት “አልጋ እንዲረጋ ለሰይጣን ግብር የሰው ደም ማፍሰስ” ለማለት እንደሆነስ ቅኔው እንዴት ሊገባን ይችላል? ለማንኛውም ጆሯችን ጤንነቱን አይጣ እንጂ እርገጤ ገና ብዙ ጉድ ያሰማናል፡፡ ታስታውሱ እንደሆነ ወደሥልጣን እንደመጣ ሰሞን በቲቪ መስኮት ብቅ ብሎ በሀገራችን የነዳጅ ድፍድፍ መገኘቱንና ወደምርት ልንገባ ጫፍ ላይ መድረሳችንን ነገረንና በነዳጅ አምሮት የተቃጠለውን ምላሳችንን ምራቅ በምራቅ አደረገው፡፡ እስካሁን ድረስ ግን ወፍ የለም፡፡ እንዲያውም ያን ጊዜ የነበረው የነዳጅ ዋጋ አሁን ዕጥፍ ድርብ አድጎ በነዳጅ ውድነትና እርሱን ተከትሎ መጣ በተባለው የኑሮ ውድነት ሀገር ምድሩ እየታመሰ ነው፡፡ ታሪክ ከታቢዎች የእርገጤን የየዕለት ውሸት ዘግቡና ለታሪክ አቆዩት እባካችሁን፡፡ ወደፊት በታሪካችን “እንዴ! እንዲህ ዓይነት መሪም ኢትዮጵያ ነበራት?” ተብሎ ትውልዱ እንዲማርና በነባራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ሳይሆን በስሜት ከሚነዳ ወፈፌ መሪ እንዲጠነቀቅ ሀገርን እንርዳ፡፡

ሰሞነኛውን የኦነግ/ኦህዲድ በአማራ ሕዝብ ላይ የተካሄደና አሁን ድረስ ያልቆመው ጦርነት መንስኤው የአማራ አልጠግብ ባይነትና በኦሮሞ ላይ ያለው ጥላቻ የወለደው እንደሆነ በብጥለው ገለበጠኝ ከኦነጋውያን እየሰማን ነው፡፡ አለማፈርን ከሸጡ አይቀር እንደዚህ ነው፡፡ የአጣዬና ማጀቴ ሕዝብ ነቅሎ ወጥቶ ሆሮ ጉድሩ ላይ የሚገኝን ኦሮሞ ሲጨፈጭፍ የተገኘ አስመሰሉት፡፡ ይሉኝታንና ሀፍረትን መሸጥ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም፡፡ ዶ/ር ኮሎኔል ሎሬት እርገጤም ተደርቦ “አማራና ኦሮሞ ድብድባችሁን አቁሙ” ዓይነት ንግግር በአሻንጉሊት ፓርላማው ፊት ሲናገር ተደምጧል አሉ፡፡ ማን ተንኳሽ ማን ጥፋተኛ እንደሆነ ልቦናው እያወቀ ጥፋትን ለንጹሓን ጭምር ማጋራት ወይም ማከፋፈል የተንኮለኞችና የሤረኞች ጠባይ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ አማራን በደለኛ ለማስባል የሚሄዱበት ርቀት እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የኦነግ/ኦህዲድ በቀቀኖች ያጠኑትን ንግግር በፓርላማ ተብዬው የኦህዲድ ብልግና ፓርቲ የባለጌዎች ሠርግ ዳስ ውስጥ ሲዘላብዱ የሰማቸው ሁሉ ተደንቋል፡፡ ካበዱ አይቀር እንዲህ ነው፡፡

ዶ/ር እርገጤ ማነው ዝናቡ እርገጤ የዚህ ሁሉ ድራማ ደራሲ መሆኑን ለመረዳት በቅርቡ የተከበረውን 125ኛ የዐድዋ ዝክረ በዓል ማስታወስ በቂ ነው፡፡ መስቀል አደባባይ ላይ አክራሪ ኦሮሞዎች ያሳዩት ነውር የተሞላበትና የደጃች ባልቻ አባነፍሶ ቤተሰብ ማኅበርም አጥብቆ የተቃወመው የበዓል አከባበር ለዚህ ለሰሞኑ ዕልቂት የዋዜማ ዝግጅት ጠቋሚ ነበር፡፡ ያን አንዳችም ኢትዮጵያዊነት ያልተንጸባረቀበት በዓል የታዘበ ሰው እነዚህ ሰዎች የሽመልስ አብዲሣን ንግግር ተግባራዊ ለማድረግ ቀን ከሌት እየተራወጡ እንደሆነ መረዳት አይከብደውም፡፡ ሕዝበ አዳም ግን የተደገሰለትን ያወቀ አይመስልም፡፡ አብዛኛውን ሕዝብ ስታዘበው በአገር አማን ምንም ሳይመስለው ኑሮውን ይገፋል፡፡ ግርምቲ አዲ!

ካለፈው ተነስቼ መጪውን እያወቅሁት “እገሌ እንዲህ በል፤ እነገሌ እንዲህ አድርጉ” ማለት አልፈልግም፡፡ ለነገሩ ምን ጥልቅ አደረገኝ?

6 Comments

 1. Excellent observation dear writer! Whether we like it or not the truth is this one, the one expressed by Ambachew. What a marvelous piece of writing, really! Short and precise.

 2. በተለያዩ ወቅቶች ከአምባቸው ደጀኔ ( ከወልዲያ) እየተባለ የሚወጡ ጽሁፎችን ተመልክቻለሁ ቢሆንም ዶ/ር ዝናቡ እርገጤ በማለት የቀረበው ግን የጠቅላይ ሚንስትሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያቀረቡት እውነታ በምድሪቱ የሚካሄደውን ገጽታ የሚያንቋሺሽ ነው።በመሆኑም ንግግራቸውን በስነ ሥራት ተከታትያለሁ ከነዚህም ውስጥ አንዱ የአምባቸው ደጀኔ ወቀሳ በሰው ” ሰራሽ ዳመና ዝናብ የማዝነብን ጥበብ ” ነው።ይህንን በተመለከተ እንድሚታወቀው የሲና በረሃ የተፈጥሮ ዝናብ የማያገኝ በአሸዋ የተሞላ በርሃ ላይ እስራኤል በሰው ሰራሽ ዳመና በመፍጠር ዝናብ በማዝነብ በእርሻ ልማት ከዓለም ቀደምትነቱ ይዛ ትገኛለች።ታዲያ በሰው ሰራሽ ዳመና ተፈጥሮ ዝናብ የሚገኝበት ጥበብ መገኘቱን ለህዝብ ማብሰሩ ጠቅላይ ምኒስትሩን የሚያስወቅስ እና በሓጥያተኛነት የሚያስፈርጅ ምኑ ነው? በጽሁፉ በገዕዝ ስለ ሊቀ ሣጥናኤል ተጠቅሶአል ጥቅሱ ያለቦታው ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን ይህ ጽሑፍ እነተጋሩ የደረሰባቸውን የውድቀት ወጋግራ ለማቅናት የተውረገረገ ዛኒጋባ ነውና ይህ ጌዜ እስክያልፍ ከመጻፍ መጻህፍትን መንበቡ ይመረጣል፡፡

  • ውድ የሰማው፧ ሃሣብን በሃሣብ መሞገት ጥሩ ነው። ልታሥተምረኝ የፈለግኸውን በጨዋ ደምብ ከነገርከኝ በኋላ “አርፈህ ተቀመጥ፤ ከመጻፍ ይልቅ አንብብ” ማለትህ አፈና ነው። “አንብቡ” ማለት በራሱ መልካም ነው። “ስለ እገሌ ከመጻፍ ይልቅ አርፋችሁ ተቀመጡ” ማለት ግን በልጆች ቋንቋ በሰው ሞራል መረማመድ ነው፤ እንዲህ አይባልም – ነውርም ነው።
   አቢይን መደገፍ መብት ነው፤ መቃወምም። ግን የምወደውን ሰው የተቃወመብኝን ሁሉ ከመሬት እየተነሣሁ “ከምትቃወም አርፈህ መጽሐፍ አንብብ” የማለት የሞራል ብቃት ሊኖረኝ አይችልም። ከዚህ በላይ ብል ነውርን መካፈል ይሆንብኛልና ይቅርብኝ… ስለ አሥተያየቱ ግን ምሥጋናየ ከልብ ነው፣

 3. አንዳንዴ ሳስበው ሰውየው ለሌላ አምስት አመታት ተመልሶ እንዳይመረጥ እራሱን ሆን ብሎ ሳቦታጅ እያደረገ ነው እንዴ? ብዬ እራሴን መጠየቅ ጀምርያለሁ። እንደ ኃይለማርያም አልቻልኩበትም በቃኝ ለማለት ወኔው ስለሌለው ፖርቲው በቃህ ብሎት ከዙፋኑ እንዲያነሳው ሆን ብሎ ይሆን እንደዚህ የሚያደርገው ?

  ኧረ ፖርቲው እባካችሁ ብዙ ሳያጠፋ ፍላጎቱን አጢናችሁ እንደተመኘው በቃህ በሉት።
  ከእዚህ በላይ ምን ጥፋት ያድርግ ፖርቲው እንዲሽረው? አሳውቁት እና ምን ቢያደርግ ከስልጣን እንደምታገሉት ቶሎ ያንኑ ፈፅሞ ስልጣኑን ያስረክብ።

  እንደ ደመቀ መኮንን እና እንደኃይለማርያም ደሳለኝ በመሪነቱን አልፈልግም አልችልበትም ለማለት peer pressure , his previous boastful speeches እና ጭፍን አፍቃሪዎቹ ስለከለከሉት ፓርቲው በቃህ ውረድ እንዲለው እየቡዋጠጠ የሚገኝ ይመስለኛል። ችግሩን የሚረዳለት ቢገኝ በቶሎ ሀገር ከማጥፋቱ በፊት አስቡበት። ምን ያድርግ እስቲ? ደንብ አውጡና በግሉ አሳውቁት ያለ አይመስለኝም መለስም ሆነ ኃይለማርያም እንዲህ አይነት ነገር ለውይይት የሚያቀርቡ አልነበሩም። በሪፎርም በብልፅግና ፓርቲያችሁ ደንብ ካለ መቼ መሪ እንደሚሻር ቶሎ አሳውቁት ፡።

 4. አቶ የሰማው ፣ያልሰማኸውን ለህዝብ እንደእውቀት ታቀርባለህ። ዝናብ ከሰው ሰራሽ ደመና ሳይሆን. ያለውን የደመና ቅሪት.ዮድ የድህነትና እንዲዘንብ ይደረጋል ይባላል ። ግን ይሄ እውነት ለመሆኑ አሁን ድረስ ሣይንቲስቶች ይጨቃጨቃሉ። በእውነት ትክክል ቢሆን ስንት ባለፀጋ ነገራት ሀገራቸውን ለም ባደረጉት ነበር።
  በጭፍን ሰውዪውን ከማምለክ አለን ብሎ ማሰብ ከኋላ ፀፀት ያድናል።
  ዲክታተር ናደጋፊዎቻቸዉ ሁሌም ሲዋረዱ አይተናል። ለኛ ደርግና ህወሃት በቂ ምስክር ናቸው።

  • ውድ ከፈይ፣ ክብር ይሥጥልኝ! ከሥንቱ ‘ውታፍ ነቃይ’ ጋር እንደምንታገል እንግዲህ ሰው ይወቀው። ዝናቡ እርገጤ ማለት ከነእዩ ጩፋ መንደር የተላከ አንዱ የአጋንንት ልዑክ ነውና አጫፋሪውና የጥቅም ተጋሪው ብዙ ነው። ያለንበት ጊዜ እጅግ አደገኛ ነው፤ ገንዘብ የሚመለክበትና ሆዳምነት የገነነበት የዘመን መጨረሻ ውሥጥ ነን።
   በል አንዱ መጥቶ “ኮሜንት ላይ መጻፉን ትተህ ቁጭ ብለህ አንብብ” ሣይለኝ ልሰናበት ወዳጄ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.