ድንገተኛ መከራ ድንገተኛ ሴራ የለም – ማላጅ  

162795442 4134618073226456 4286982535628240428 oለምን ለዘመናት የሆነዉን እና እየሆነ ያለዉን የብሄራዊ አንድነት ፣ሉዓላዊነት እና የዜጎች ደህነት አደጋ ላይ በመጣል  የስልጣን እና መሬት ቅርምት ሴራን ዕዉን ለማድረግ በተለያየ ጊዜ በተለያየ አካላት እንደ ደራሽ ዉኃ ድንገተኛ ለማድረግ እንደሚፈለግ አይገባንም ሊገባንም  አይችልም፡፡

ኢጣሊ እ.አ.ኤ.1888 ሆነ ከ 40 ዓመት በኋላ የቅኝ ግዛት ወረራ የዓመታት ዝግጅት በማድረግ ባህር ዉቅያኖስ አቋርጣ ከሰሜን አዉሮፓ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገር ኢትዮጵያ ስትመጣ የራሱን ምኞት እና ህልም ዕዉን ለማድረግ በዉስጥ እና ዉጭ ተባባሪወች በመመካት የ40 ዓመት ዝጅጅት ይዛ እንጅ ድንገቴ ሆና አልነበረም ፡፡

በዘመኑ የነበሩት ጅግኖች እና የጥቁር  ዓለም የነጻነት ቀንዲል ፋና  ወጊ የነጻነት አባት ዕምየ ምኒሊክ ድንገት እና ሳናስብበት ነዉ ብለዉ በከንቱ ቀቢፀ ተስፋ ጊዜ እና ትንፋሽ ማባከን አልፈለጉም ነበር ፡፡  ለዚህም የተጋድሎ ዉጤት የዘመናት የጥቁር ዓለም መመካት እና ኩራት ዓርማ ሆነዉ ስማቸዉ ከመቃብር በላይ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል ፡፡

ይህን ብርቱ ኢትዮጵያዉያን እንደሚያዉቁት ጠላት እና መከራ አዋጅ አያስነግርም ፤ በጋ ክረምት አይልም አድብቶ እና አዘናግቶ ይከሰታል እንጅ  እንጅ ፡፡

እኛ ግን የትናንቱን ትተን የዛሬን እያለባበስን የነገን በጭፍንፍን የሕልም ሩጫ ሆኖብን በየጊዜዉ የትናንቱን ችግር እና ምክነያት እየደጋገምን እንደክማለን ፡፡

አንድ አበባል አለ ያቆሰልከዉን አዉሬ አትመነዉ…… ይህ እንግዲህ ለጎሽ ይሆናል ለምን ጎሽ  ለልጇ ተወጋች ይሏል  አበዉ ፡፡ እኮ ለምን ይሆን ያቀሰልከዉን አዉሬ አትመን ለተባለ የገደለዉን እና የሚገድለዉን  ዞትር አሜን እያለ መኖር ይህ ፅድቅ ነዉ ኩነኔ …. ማነዉ የዚህችን አገር ዕንቆቅልሽ የሚፈታዉ ?

ርግጥ ነዉ በእምነት እና ዕዉነት የሚኖር እና የሚያስታርቅ ጠፋ እንጅ  ብዙ እና ለዓመታት የተሰራባቸዉ ብዙ ዓይነት በየዓይነት  የማዘናጊያ እና የማዛጊያ አደረጃጀቶች መብዛታቸዉን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ  የሆነ ሁሉ የሚያዉቀዉ ነዉ ፡፡

በተለይም በ1967/8 ዓ.ም. ጀምሮ በነጻነት ትግል ስም ፀረ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያን  እና ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ሰይፍ መዞ ህዝብን እና አገርን ከሚያጎሳቁል የግማሽ ክ/ዘመን የሞት እና ስደት ታሪክ ሳንማር እየተዘነጋን እና እየዛግን ላለፉት 27 ዓመታት በትኩረት እና በቅንጅት የሚሰራበትን የአገር አንድነት እና ሉዓላዊነት የማዳከም ክፉ እና ዕኩይ ስራ ድንገተኛ ማለት ዘበት ነዉ ፡፡

በርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብም ከተጫነበት አዚም በአንድነት እና በቁርጠኝነት ለመላቀቅ ምን እንደያዘዉ ማሰብም አንድ ወቅታዊ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያ ታሪካዊ እና ብሄራዊ የዉጭ እና የዉስጥ ጠላቶች ኢትዮጵያን ከምደረ ዓለም ለማጥፋት ብቸኛ የከፋፈይ መሳሪያ አድረገዉ የሚጠቀሙበት የአማራ የበላይነት /ገዥ መደብነት ከ18ኛዉ ክ/ዘመን ጀምሮ የቅኝ ግዛት እና ወራሪዎች እና የተስፈኞች የአገር አንድነት እና ታሪክ የመናድ ከፍርሃት ፣ የታችነት  እና ክፋት  ስሜት  ያስከተለዉ  የቅዠት ትርክት ነዉ ፡፡

ለዓመታት ይሙት፣ሞተ፣ ተገደለ፣ ተሳደደ፣ ተዋረደ …….ኢትዮጵያዊ( ዓማራ )  ሞተ ፣ ተሰደደ፣ ተዋረደ…..ዛሬም ተወረረ ….ተባረረ ማህበራዊ ሠላም  ተነሳ  እያሉ መደጋገም ከመድከም ባለፈ አገርን ከዉድቀት ፤ህዝብን ከሞት አይታደግም ፡፡

አስከ መቸ ነዉ የአንዲትን አገር ህልዉና አደጋ ላይ የሚጥል ድብቅ የጥፋት ሴራ እየተዘራ በገመራ እና መከራ በተከሰተ ቁጥር ኢትዮጵያዊዉ /ዓመራ ……እያልን የምንቀጥለዉ ፡፡

ጠላት ዓማራ የሚሉት ኢትዮጵያዊ መሆኑን አሳምረዉ ሲያዉቁት የዚህች አገር ችግር እና መከራ ሁሉ ለዓማራ  የሚገፉት ኢትዮጵያዉያን ግን ሞኝነት እና ጥፋት መሆኑን ዛሬም ሊታያቸዉ አለመቻሉ የሞት ጊዜዉን ከማዘግየት ዉጭ ስቃይ ከመጨመር እና መከራ ማራዘም የተለየ ነገር አይጠበቅም ፡፡

አበዉ “ የጨዉ ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል …..ብልህ ያለቅሳል ” እንዲሉ ለዘመናት “ሞት ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ” የሚሉት ታሪካዊ

የ፩በ፩  ወይም ሶስት በአንድ የሚያተኩሳቸዉ የጥላቻ ጌኛዎችን (phobia)  የዉሸት ጨቋኝ እና ተጨቋኝ መደብ ፈጠራ ለሚነዛ እና ህዝቧን ለሚገፋ የትፋት ኃይል  ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በተባበረ ክንድ ከነ መርዛማ አሚኬላዉ መንቀል እና ማቃጠል ተስኖት የዚህችን አገር የነበር እና የሚኖር ሁለንተናዊ ችግር ለአንድ ማህበረሰብ “አማራ ” መስጠት ዕድሜ ለመግዛት መሞከር አስከ መቸ እንደሚቀጥል ባይታወቅም አሁንም ጠላት ከጫነብን የክፋት እና ጥላቻ ቀንበር ለመላቀቅ ከማንቀላፋት ለመታቀብ አለመትጋት አሳዛኙ የጊዜዉ  ዕዉነታ ነዉ ፡፡

በሰሞነኛዉ“ የመከራ እና ሞት ነጋሪት ሳይጎሰም ንጋት እና ለሊት በማይተካኩባት ” ምድር ዛሬ በሰሜን ሸዋ እና ወሎ (ከሚሴ) አካባቢ ስላለዉ የአካባቢ የፅጥታ መደፍረስ እና የማህበራዊ ህይዎት ቀዉስ  መንስዔ እና ዉጤት ድንገተኛ ማለት ከፍላጎት ማጣት እና ከኃላፊነት ዝንፈት የሚመነጭ ካልሆነ ዉሃ ቋጣሪ ፤ ታሪክ አመሳካሪ አይሆንም ፡፡

ለዚህም ወደ ኋላ ስለ 18ኛዉ ክ/ዘመን የነጻነት እና ሉዓላዊነት ተጋድሎ ስናማትር የቅርብ ጊዜ ቁስልን  መረሳት እና በቁስል ላይ መርዝ ለሚጨምር ጠላት ለሚያደርሰዉ ተደጋጋሚ ጥቃት  ድንገት ማለት  ከችግር ፈችነት ችግር አብስ ፣ ህዝብ አስለቅስ እና አገር አፍርስ ስለሚሆን እና ይህም በተለይም ከ1987 ዓ.ም አካባቢ ጀምሮ( ህገ መንግስት ፣ ክልል አስተዳደር……) የአገሪቷን የግዛት አስተዳደር አደረጃጀት ፣ ወሰን አከላል እና የሰዉ ኃይል አሰላለፍ ማየት በቂ እና ከበቂ በላይ ለሆኑት እና እየሆኑ ላሉት ብሄራዊ አንድነት እና ደህንነት አደጋ አመላካች ናቸዉ ፡፡

የኢትዮጵያን የድንበር እና የጎረቢት አገር አዋሳኝ ክፍለሀገር ግዛት ስያሜ እና አከላል የተቀየረበትን ዘመን እና ምክነያት ወደ ኋላ ለሚቃኝ ለኢትዮጵያ ዉድቀት ፣ለህዝቧ ድህነት ፣ ስደት ፣ሞት እናዕንግልት ለሚመኙት ምኞት ማስፈፀሚያ ሲባል  ምን ያህል በጥልቀት እና በርቀት እንደተሰራበት በተግባር እየታየ ያለ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ ፡፡

ከነዚህም መካከል በተለይም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን ለማክሰም የሰሜን ጎንደር ፣ ሰሜን ወሎ ፣ ምዕራብ ጎጃም( መተከል አዉራጃ) ግዛቶችን (ይዞታወች ) ከድንበር አስከ ታሪክ ማወናከር ፣ማሳከር እንዴት ፣ለምን እና በማን እንደ ተሰራ ማየት በቂ መተማመኛ ነዉ ፡፡

ከዚህም ሌላ ፡-

 • የላቀ እና ገላጭ ኢትዮጵያዊ እና መልካ ምድራዊ ስያሜ ሳይጠፋ አማራ ክልል ማለት ፣
 • ከወረዳ አስከ ክልል የነበረ የፖለቲካ ስልጣን ከክልሉ ዉጭ ከተመለመሉ ጉዳይ አስፈታሚ ታማኝ አገልጋዮች ተይዞ የነበር እና ይህም በመንግስት አስተዳደር ብቻ ሳይሆን በቤተ ክህነትም ሳይቀር በግላጭ መሆን እና ይህን ዕምቢ ያለ ገለልተኛ አካል አለመኖር ፣
 • ነገር ግን በሌላ የአገሪቷ ክፍል በፖለቲካ ስልጣን ርከን መሳተፍ አይደለም መወለድ ምን ያህል እንደ ወንጀል ይታይ እንደነበር ለማንም ግልፅ ነበር ነዉ ፣
 • በራሱ በክልሉ ዉስጥ ኢትዮጵያዊነት ጠላትነት ሆኖ በህይዎት የመኖር እና ያለመኖር ስጋት ሆኖ ለረጅም ዓመታት መቀጠል ፣
 • በኢትዮጵያ አገረ መንግስት ታሪክ ከ ሁሉም ኢትዮጵያዉያን ጋር በግንባር ቀደምትነት በሁሉም የአገሪቷ ማዕዘናት ከጥንት አስከ ኢትዮ -ኤርትራ ጦርነት ኢትዮጵያ የሚልን ህዝብ በስያሜ እና በግዛት አስተዳደር መወሰን /ማጣበብ፣
 • በአገሩ በየትኛዉም ግዛት የመኖር ተፈጥሯዊ መብቱን በመገደብ ከየት እና ለምን መጣህ በሚባልበት ፣
 • በኢትዮጵያ የግዛት አስተዳደር የብሄረሰብ አስተዳደር በብቸኝነት ያለዉ አማራ ክልል አካታች እና አሳታፊ ሆኖ እያለ በሌላ በየትኛዉም ክልል ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ መኖር አይደለም ማሰብ ጥፋት ሆኖ የሚቆጠርበት  ፣
 • በክልሉ ከፍተኛ የስራ አጥነት እና የመልማት ችግር ስር ሰዶ እና ተንሰራፍቶ እያለ የስራ ማስኪያጃ ገንዘብ የሚተርፈዉ እና ለሌች በግድ የሚለግስ እንዲሁም ሠራተኛ ከሌላ አካባቢ ቅጥር የሚያስተናግድ ፣
 • በተለይም በወሎ ከሚሴ በአካባቢዉ ብቁ የሰዉ ሃይል እና ከፍተኛ ስራ አጥነት መኖሩ እየታወቀ ዛሬ እና ትናንት ለደረሱ የአካባቢ መናጋት አመቻች አደረጃጀትትን አስቀድሞ የፈጠረ እና ያዳበረ ፣
 • በኃይማኖት እና በተለያዩ ሽፋኖች በአካባቢዉ የነበረ እንቅስቃሴ ከአካባቢ፣ ክልል እና ብሄራዊ ስጋት መሆን በላይ ለጥፋት መልዕክተኞች መንጠላጠያ እና መረማመጃ መንገድ መሆን ሲታወቅ ፣
 • ይህም የዞን መስተዳደሩ በዉስጥ ያለዉን ተደጋጋሚ አደረጃጀት አዉቆም ሆነ ሳያዉቅ ለደረሰ ተደጋጋሚ ጥፋት እና ዕልቂት ተጠያቂ አለመሆን ፣
 • ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በሚደረግ ኢትዮጵያን በአዲስ እና በተቀናጀ ስልት ለማፍረስ እና የዜጎቿን ሠላማዊ ህይዎት ለማደፍረስ ለሚሰራ ኃይል አፍሪካን መምራት እንችላለን ለሚል የኢትዮጵያ መንግስት የዓመታት የዉስጥ አንድነት እና ደህንነት ለመከላከል አለመቻል ወይስ አለመፈለግ ? ለሚያይ የኢትዮጵያም ሆነ የአካባቢዉ ጉዳይ ድንገተኛ ሳይሆን ሁነኛ ሴራ ለመሆኑ  በህዝብ እና አገር ኪሳራ የሚኖሩ ወንጀለኞች ዋጋ ስለማይጠየቁ እና ስለማይጨነቁ ጊዜ እና ሁኔታ እያዩ የጥፋት የዓላማቸዉ ተደጋጋሚ ማሟሻ እና መዳረሻ  የህዝብ ሠላም እና ህይወት ዕጦት እና የአንድነት መናጋት ቢሆን እንዴትስ ድንገተኛ ይሆናል ፡፡

ለመሆኑ  አፋር …..ሶማሊያ……አማራ….ሞተ ከሚል የዞትር አዙሪት እና የክፋት ጥግ ወጥተን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን እየሞቱ ነዉ ይህም ሲደመር በጥላቻ “የአገር  እና ተዉልድ መሞት” በቃ የምንለዉ መቸ ነዉ ፡፡

ዕዉነት ዕዉነቱን ስንነጋገር ድንገተኛ ሳይሆን አገር ኢትዮጵያ ፣ ማንነት ሠዉነት እና ኢትዮጵያዊነት ፣ ዕምነት ከርስትና ፣ የራስ ሆሄ እና አሀዝ፣ የራስ ብሄራዊ ዓርማ /ሰንደቅ ዓላማ የሚል ኢትዮጵያዊ አይደለም ራሽያዊ ፣ ፈረንሳዊ፣ ቻይናዊ፣ አሜሪካዊ….. ትምክተኛ፣ ነፍጠኛ …ወይም በኢትዮጵያዊነት ጥላቻ ልክፍት ለተቀፈደዱት የተሰጠዉ ትርጉም ዓማራ /ኢትዮጵያዊ ነዉ ፡፡ ይህን እኔ የተረዳሁት በ1980/90 ዓ.ም. አንድ ቀልፍ/ቁንጮ ከፍተኛ የኢህዴግ /ትህነግ ባለስልጣን እና የቀድሞዉ አዲስ አበባ የኒቨርስቲ ተማሪዎች ሊቀ መንበር የነበረዉ እና በአሁኑ ስዓት አዉስተራሊያ የሚኖር ብቁ ፣ ደፋር እና የምር ኢትዮጵያዊ ሠዉ ካደረጉት የፊት ለፊት ዉይይት  ነበር ፡፡

ይህን ድምፁን ማየት ይቻላል …. ርግጥ ነዉ ብዙ ማለት ይቻላል ኢትዮጵያ ከነስሟ ቀስሟን  ለመስበር የተደረገዉ ጥረት እና ስኬት ሁሉ በራሷ ልጆች እና አስተዳዳሪዎች መሆኑ በዓለም የክፍለ ዘመናችን  ለገዛ አገር እና ህዝብ ዉድቀት እና ሞት በርትቶ የሰራ በሌላ ዓለም እና አገር  ስለመኖሩ አላዉቅም ፡፡

እንደ አለመታደል “ሆኖ ክፉ ሞቶም ይገድላል ” እንዲሉ አበዉ ይህን በልዩ ሁኔታ  ብሂሉን ክፉ እየኖረ ይገድላል ፤እየገደለ ይሞታል ፤ እየሞተም ይገድላል …… ብለን በጥላቻ እና በቂም ተፀንሶ፣ የተወለደ ፣ ያደገ እና የዛገ ስብዕና ከበታችነት እና ከራስ ወዳድነት ዉጭ ሊሆን እንደማይችል አለሁለት የሚለዉን ህዝብ ሳይቀር እኔ ሞቸ ሠላም ዉሎ አይደር ፣ በህይዎት እንዳይኖር ….የሚቀር ቢኖር  ከወገን ጋር በፍቅር እና በይቅርታ ባይነት እንዳይኖር በጥላቻ  ግርሻት እና ቅርሻት እየበከለ መሆኑን አየን…..አየን፡፡

…….መረረን….. መረረን ፣

በዚህ በሁዳዴ  በዓርባ ቀናት ሡባዔ ፤ በዓብይ ዐፅዋማት ፣

ዓምላካችን ሆይ ዕምየ ኢትዮጵያን ህዝቧን እና ምድሯን አብዝተህ ጠብቃት ፣

ከጥላቻ ደዌ ከሚማቀቀቁትም በሽታዉ እንዳይተርፍ በምህረትህ ጎብኛት  ፡፡

እናት ኢትዮጵያ ለዘላም ትኑር ”                                                

                                                                                                                                                   ማላጅ

                                                                                                                

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.