የኢትዮጲያን ሉአላዊነት ለማስከበር የተጠራ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በካምቤራ-አውስትራሊያ

FB IMG 1615520583489 1

የኢትዮጲያን ሉአላዊነት ለማስከበር የተጠራ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በካምቤራ

በሜልበርን በታዝሜንያ በሲድኒእና በካምቤራ የሚገኙ የኢትዮጲያዊያን ኮሚኒቲዎች እንዲሁም የኤርትራ ኮሚኒቲ ባንድነት ያዘጋጁት የሀገርን ሉአላዊነት የማስከበር አውስትራሊያ አቀፍ ሰልፍ March 19/2021 ካምቤራ ላይ ይካሄዳል።

በሰልፉ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት እንዲሁም የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ መንግስታት በኢትዮጲያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን እንዲያቆሙ፣ ግብፅና ሱዳን ኢትዮጲያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ተፈጥሯዊ እና ህጋዊ መብቶች እንዲያከብሩና ሱዳን ከያዘችው የኢትዮጲያ ግዛት ባስቸኳይ ለቃ እንድትወጣ፣ ታላላቅ የሜዲያ ተቋማትና የግብረሰናይ ድርጅቶች የህወሀት ዲጂታል ሰራዊት እና ምንደኞቻቸው የሚፈበርኳቸውን ሀሰተኛ መረጃዎች ማሰራጨት እንዲያቆሙ የሚሉና በርካታ መልክቶችን ይስተጋባሉ። ስለሆነም በመላው አውስትራሊያ የምትገኙ ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን እንዲሁም ኤርትራዊያን በዚህ ታላቅ ሰልፍ ላይ እንድትገኙ በማክበር ተጠርታችኋል

ከሜልበርን ለምትሄዱ ኢትዮጲያዊያን የአውቶቡሶቹ መነሻ ሰአት ሀሙስ March 18/ 2021 በ11 PM ሲሆን
መነሻ ቦታው Cornar Of Irving & Albertt St
ከላሊበላ ሬስቶራንት ጀርባ ባለው አልበርት ስትሬት ፓርክ ፉትስክሬይ ይሆናል

ሰልፉ የሚኬሄደው March 19/2021 ሲሆን ቦታ ካምቤራ moonah Place ያራሩምላ በሚገኘው በአውስትራሊያ የአሜሪካ ኤምባሲና እና ፓርላመንት ድራይቭ ላይ በሚገኘው የአውስትራሊያ ፓርላመንት ሀውስ ፊት ለፊት ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ

0402 871 072
0401 331 652
0413 481 249 መደወል ይችላሉ

የኢትዮጲያ ማህበረሰብ ማህበር በአውስትራሊያ

Cambera australia

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ ... በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ን.ግ / ደ.ህ.ዴ. ን ክብረ በዓል ! (ነቢዩ ሲራክ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.