የበርማዋ እማሆይ ይፍቱኝ! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ber1 የበርማዋ እማሆይ ይፍቱኝ!  በላይነህ አባተታሪክ ደጋግሞ እንዳሳየው ነገ ጉርንቧቸውን ታንቀው መያዛቸው ላይቀር በበርማ ጭራቅ ገዥዎች ሕዝባቸውን በማረድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን አሰቃቂ ግፍ የሚፈጥሙትን ወታደሮች ተገዳማቸው ወጥተው የተጋፈጡት አንዲት መነኩሴ ምድርንም ሰማይንም አስገርመዋል፡፡ መነኩሴዋ ተሕዝቡ በፊት እርሳቸውን እንዲገሏቸው ተመጣነዋል*፡፡ እኒህ ተገዳማቸው ወጥተው ህይወት ለማትረፍ ጥረት ያደረጉ መነኩሴ ሳድግ አውቃቸው የነበረቱን እውነተኛ የኢትዮጵያ መነኩሴዎችና ካህናት አስታውሰውኛል፡፡

ይህ አድግ የሚባል የወሮ በሎች ቡድን ቤተመንግስት ገብቶ ክህነትን፣ ሽምግልናን፣ ህሊናን፣ ባህልንና በአጠቃላይም ሰውነትን ተማርከሱ በፊት በኢትዮጵያ ካህኑ ካህን፤ ሽማግሌውም ሽማግሌ፣ ሰውም ሰው ነበር፡፡  እውነተኛ ካህንና ሽማግሌ ታረቁ ብለው የማይፈጠም እርቅ፤ አትፈጽሙ ብለው የሚደረግ ድርጊት፣ ይሁን ብለው የማይሆን ነገር አይከሰትም ነበር፡፡ ይህ አድግ የተባለው የሳጥናዔል ተከታይ ቡድን ክህነትን በእነ አባ ገረመድህን ሽምግልናን ደግሞ በእነ ኤፍሬም ይሳቅ ገደል ተከተተው ወዲህ ክህነትና ሽምግልና ተሰው ደምና አጥንት የተሰራ ወጥ ማጠበቂያ እንጀራ ሆነዋል፡፡

አንዳንድ አስመሳዮች እነ አባ ገረመድህን እንደ አረም የዘሯቸው ካህናት ሲተቹ ተእኛ በላይ ተቆርቋሪ መስለው  ቤተክርስትያኗ የተወቀሰች አስመስለው ጅራታቸውን ተውዲያ ወዲህ እያወራጩ ቤተክርስትያኗን ተድጡ ወደ ማጡ ሲከቷት ይታያል፡፡  ቤተክርስትያን የቤተክርስትያኗን ራስ ክርስቶስን፣ አማኙን ሕዝብና የአምልኮቱን ሕንፃ ያጠቃልላል፡፡ ሕዝቡ የሚያመልክበት ሥፍራ በአሪዎሶች ሲቃጠልና  የቤተክርስትያኗን አሥራት ከፋይ ሕዝብ በአረመኔዎች ሲታረድ የአቦይ ማትያስ የካህናት ቡድን በቃጠሎው ሥጋውን እየጠበሰ ተዝካሩን ይዝቃል፡፡

ስለዚህ እንደ በርማዋ መነኩሴ ሕዝብን ተሞት ለማትረፍ ሳይሆን የቤተክስትያኗን አስራትና አርመኔዎች የጨረገዱትን ሕዝብ ተዝካር እየዛቀ ሕዝብ ሲጨፈጨፍ “ለቆ ጣለ” የሚልን ካህንና ጳጳሳትን መውቀስ በምን መስፈርት ክርስቶስንና ክርስቶስን አምኖ የሚኖረውን ሕዝብ መውቀስ ሊሆን ይችላል? በምን ሒሳብ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ለፍትህ የተሰውትን ብጹዕ ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ-ዘኢትዮጵያን ያፈራችውን ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን መውቀስ ሊሆን ይችላል? በምን ቀመር ደብረ-ሊባኖስ ፋሽሽትን በጠመንጃ ያርበደበዱትን አባ ገብረየሱስን ያፈራች ቤተክርስትያን መውቀስ ይሆናል? በምን ሚዛን በጦርነት ወቅት አርበኛ በሰላም ጊዜ መምህርና ጠሐፊ የነበሩትን መላክ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬንና አለማየሁ ሻሾን ያፈራች ጥንታዊት ቅድስት ቤተ-ክርስትያን መተቸት ሊሆን ይችላል? በምን ስሌት ዓለም ጨለማ በነበረችበት ዘመን ቀለም በጥብጠውና ብራና ፍቀው ሆህያትን፣ ሃይማኖትን፣ ፍልስፍናን፣ ስሌትን፣ ሥነ-ጽሑፍንና ሥዕልን ያስተማሩ ሊቃውንትን፤ እንደ መምህር አካለ ወልድ፣ አራት ዓይናው ጎሹ፣ መሀሪ ትርፌ፣ አቡነ ጎርጎርዮስና ሌሎችንም ያፈራች ቤተክርስትያን መውቀስ ሊሆን ይችላል? ማትያስ ሲደመር የማትያስ አገልጋዮቹ ይሆናል(=) ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሚል ቀመር ለመከራከር እጁን የሚያወጣ በየትኛው አቅጣጫ ሊታይ ይችላል?

የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስትያን መእመናን ሲረሸኑ፣ ሲታሰሩ፣ ሲገረፉ፣ ሲሰደዱ፣ በስደት ሲታረዱ፣ ሲራቡና ሲጠሙ መዋሉን ቀጥለዋል፡፡ አቦይ ማትያስና አገልጋዮቻቸው ግን አቦይ ማትያስ “ጵጵስናውን በገንዘብ ገዛው!” ሲሉ እንደከሰሱትና በኩልኩልቱ እንደ ታነቀው አባ መላኩ በእንጀራና በቁርጥ ታንቀው ዝም ብለዋል፡፡ መጽሐፉ ግን እስተንፋስ ያለው ሁሉ እንዲተነፍስ ያዝዛል፡፡ የአባ ማትያስ አገልጋይ ጳጳሳት ግን ይህንን የመጽሐፍ ቃል በመሻር የሕዝቡን እስተንፋስ ለመዝጋት በሰይጣን ተላላኪነት ተሰልፈዋል፡፡ ሰይጣን  እንደ እግዚአብሔር በአካል ባይታይም በጭራቅነቱ፣ በውሸታምነቱ፣ በከሐዲነቱ፣ በአታላይነቱ፣ በሌባነቱ፣ በስግብግብነቱ፣ በከፋፋይነቱና በክብር የለሽነቱ ይታወቃል፡፡ እነዚህ የሰይጣን ባህሪያት በባዕዳን ከወንበር የተጎለቱትን ባንዳ ገዥዎች ይገልጧቸዋል፡፡ ካህናት በተለይም “የኦርቶዶክስን ቤተክርስትያንና የአማራን ቋንጃ ሰብረናል” እያሉ በሚደነፉት የተሾሙት “ፓትርያሪክና” እርሳቸውን የተሸከሙት ጳጳሳት ለገንዘብና ለስልጣን ሲሉ አምላካቸውንና ሕዝባቸውን ክደው የቤተ-ክርስትያኗ ቋንጃ ሰባሪዎች ላሳደጓቸው ካድሬዎች ዛሬም ሲላላኩ ይታያል፡፡

ber12 የበርማዋ እማሆይ ይፍቱኝ!  በላይነህ አባተእነዚህ ካህናት የቤተክርስትያኗ ልጆች በመላ አገሪቱ በግፍ ሲታረዱ፣ ሲገረፉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲሰደዱና ሲራቡ አብረዋቸው ቆመው እንደማያዉቁ ይታወቃል፡፡  ዛሬም አስራት እያስገቡ እንደ ኮርማ የሚቀልቧቸው ምእመናን እየታረዱ በጅምላ ግኒደር ተቆፈረው ጉድጓድ እንደ ውሻ እሬሳ ሲጣሉ፣ አንገታቸው እየተቀላ በመንገድ ሲጎተቱና ከእነፍሳቸው ሲቃጠሉ እንኳን እንደ በርማዋ መነኩሴ “መጀመሪያ እኔን ግደሉ” ብሎ በገዳይና በተገዳይ መካከል የሚቆም በግፍ ለተገደሉት ድምጡን ከፍ አድርጎ ፀሎት የሚያደርስ ጳጳስም ማየት አንቀጥ ሆኗል፡፡

የይህ አድግ ዘመን ጳጳሳትና መነኩሴዎች ተገዳም የሚወጡት እንደ አምስቱ ዘመን የደብረ ሊባኖስ መነኩሳት ሰይጣን የላከውን ፋሽሽት ለመፋለም ወይም ደግሞ እንደ በርማዋ መነኩሴ ምእመናን ለማትረፍ ሳይሆን ገንዘብ ለማካበት፣ ፎቅ ለመስራት፣ ልጃገረድ ለማሳደድና አረመኔ ሲገል ተስካር ለመዛቅ ሆኗል፡፡

አቡነ ጴጥሮስን፣ አቡነ ሚካኤልን፣ አባ ገብረየሱስን፣ አድማሱ ጀምበሬንና አለማየሁ ሻሾን የመሳሰሉ ካህናት በአገሬ ምድር እስታገኝ  የበርማዋ እማሆይ ይፍቱኝ!

 

*Myanmar nun pleads with military not to shoot children: ‘Kill me instead’ https://www.independent.co.uk/asia/myanmar-protests-nun-military-coup-b1814532.html

መጋቢት ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም.

 

 

5 Comments

 1. ጉቦ አቀባባይ ሽጉጥ የሚታጠቁት ከመለስ ሰይጣናዊ ተከታትለው በቅርብ ጊዜ ርቀት የሞቱት የወያኔ ጳጳስ በፍርሀት አደንዝዘዋቸው ነው ፤ ህሊና ቢስ ልበ ቢስ አድርገዋቸው ነው።
  እንደ ሀይማኖታዊ ደንቦቹማ የኦርቶዶክስ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የሙስሊሙም ፣ የጴንጤውም …….ግድያዎቹን መቃወም ነበረባቸው።

  የሀገር ሽማግሌ /አሮጊት መላ ቢሉዋቸው ምን ነበረበት?

 2. I feel as if we living in the time of Lot in Ethiopia. None of is pious as was Lot in his time. Lot pleaded to God to lift the wrath which was to happen on Sodom and Gomorrah under some sort of negotiation that consists of availing some godly people other than himself. But he couldn’t bring forth anyone, for everyone was engaged in sinning. We know what happened next. Even the wife of Lot was not able to escape the wrath and she was turned to be a ‘statue of salt’ according to the bible.
  The copy-paste of that story is practically being seen in Ethiopia and elsewhere in the world too. The satanic popes and their Luciferian patriarch who stood among them are members of the executive committee of the netherworld government of Devil. But look that nun of Burma! She is a real token of Christ on Earth.
  These so called priests and bishops and pastors and sheikhs, etc. are tools of Satan. Believe me, we are in the endtimes after which the golden time will come into the scene and all the dirt we observe now will have been wiped out!!

  • ጎረቤታችን የሚኖሩ አንድ እናት አቀማጥለው ይሳደጉት አንድ ጎሮምሳ ልጅ ነበራቸው።ዘወትር ልጃቸው በአማሪኛ ሲያናግሩት መልስ የሚሰጣቸው በእንግሊዘኛ ነው።እናት መልሱን ሰምተው ሲጨርሱ ጥያቄቸው “ይህ ዝተትህ ደግሞ ምን ማለት ነው?”ይሉት ነበር።
   በአማሪኛ ለቀረበው መጣጣፍ አስተያየት በእንግሊዘኛ መስጠቱ የብዙ ውድቀቶች ምልክት ነው።አንዱ በራስ የመመካት ጉድለት።ከራስ ቋንቋና ባሕል አስበልጦ የባእዳኑን ማምለክ ነው።ሁለተኛው በኢትዮጵያና በሌላው ዓለም ያለው አማሪኛ ብቻ አንባቢ አሰተያየት ሰጪዎቹ እሳቤያቸው ውስጥ ያለማስገባት የአዕምሮ ጨቅላነት እንደሆነ እንገመት። በሦስተኛ ደረጃ ስለ ሰዶምና ገሞራ፣ ስለ ሳጥናኤሉ ፓትሪያርክ፣ባጠቃላይም ስለ ሞራል ውድቀት በእንጊለዘኛ ቋንቋ ሊያስተምሩን ሲሞክሩ ያልተረዱት ፣የራሳቸው ሞራል ውድቀት የሚጀምረው አማሪኛ ብቻ የሚረዳው ወገን ላይ ሲዘብቱ ነው።ስለ የራስን ቋንቋ ማናናቅን ብዙ ማለት ይቻላል።
   ሌላው አቢይ ጉዳይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለአንዳዶቻችን ማንነታችን የታነጸበት፣ኢትዮጵያዊነት የተላበስንበት ርዕዮተ ዓለማችን እንጂ ሃይማኖት ብቻ አይደለም።ይህንን አሳንሶ፣ ገንጥሎ፣ ለማኮሰስ፣ሃይማኖቱ ላይ ብቻ የሚደረገው ዘመቻ፣ ኢትዮጵያን ገነጣጥሎ የማዳከም ሴራ አካል ነው። ዛሬ ቤተ ክርስቲያኗን የማዳን ዘመቻ ይበልጥ ኃላፈነት ያለበት ምዕመናኑ ነው። ምን መደረግ አለበት? ጥያቄውን አንግቦ መደራጀቱ እንደ መለኮት ትዕዛዝ ሊቆጥረው ይገባል።

 3. The businesses opened on the Orthodox Church properties were signs of the interests the church leaders had for accumulating personal wealth.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.