ባንዳዎች ህክምና ሊፈቀድላቸው አይገባም!!! – ናትናኤል አስመላሽ

.
birhane GebreKirstosባንዳው ብርሃነ ገብረክርስቶስ(የቀድሞ የኢትዮጲያ አምባሳደር በአሜሪካ) ከጦርነት በፊት ታክሜ ልምጣ በማለት በሽምግልና፣ በሚስቱ ወንድም፣ በእህቱ ባል (አርከበ እና አዲስ አለም ባሌማ) ለምኖ ተፈቅዶለት አሜሪካ ከመጣ ቦሃላ፣ የአሜሪካ ባለስልጣናት በህወሓት የታወጀውን የህግ የማስከበር ሂደት፣ በህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀሙን ድሮ ለሚያቃቸው የውጭ ዲፕሎማቶች በለመደው ውሸታም አንደበቱ ሊያሳምናቸው ችለዋል። ከዚህም አልፎ በውጭ ጥቃቅን እና አነስተኛ ጁንታዎችን በማደራጀት የሃሰት መረጃዎችን ሲያቀብል ከርመዋል።
.
ብርሃነ ገብረክርስቶስ በስሙ(የኢፈርት) በአሜሪካ የተቀመጠውን አስር ሚልዮን ዶላር፣ ከሚስቱ ውጭ ሲማግጥ ተይዞ፣ ሚስቱ የፊቺ ክስ አቅርባ፣ የነበረው ቤት ለሚስቱ እና ለልጆቹ ተፈርዶ፣ በባንክ የነበረው (የኢፈርት) እነሱ እንደሚሉት የትግራይ ህዝብ ገንዘብ ባል እና ሚስት ተከፋፍሎውበት አምስት አምስት ሚልዮን ዶላር ደርሶባቸው፣ ፍርድቤቱ ፋይሉን ዘግቶታል፣ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ መፅሃፍ( የመለስ ልቃቂት ገፅ 83) ማንበብ ይቻላል።
.
ዛሬ የጁንታው ደጋፊዎች በትግራይ ህዝብ ስም የተቀመጠ ገንዝብ ባል እና ሚስት አምስት አምስት ሚልዮን ተከፋፍለው ሲያበቁ ይህንን ሁሉ ረስተው፣ ሴሰኛው ብርሃነ ገብረክርስቶስ መሪያቸው አድርገውታል፣ ጥፋቱ ለህክምና የፈቀደለት የደህንነት መስርያቤት ቢሆንም፣ በህክምና ምክንያት ፍቃድ ተሰጥቶዋቸው፣ ወደ ውጭ የሚወጡ የጁንታው ባለስልጣናት፣ ክህደቱ አያሌውን ጨምሮ ከአገር እንዳይወጡ የምንለው ለዚህ ነው። ክህደቱ አያሌው ምርጫ 97 በተጭበረበረበት (250 የአዲስ አበባ ወጣቶችበተረሸኑበት ) ወቅት ፣ ልቡ ያላመመው፣ ክህደቱ አያሌው ጁንታው ወደ መቃብር ሲሸኝ ልቡ አሞታል፣ ለነገሩ ልክ ነው! የቄስ አባቱ ህወሓት የተመታበት ልደቱ ልቡ ያላመመው ክህደቱ ማን ልቡ ያመዋል? ከጁንታው ሞት ቦሃላ ግን የኢትዮጲያ ህዝብ ልቡ ቅቤ ጠጥተዋል፣ ዛሬም እንደ ትናንትናው አመመኝ ላለ ሁሉ ህክምና የሚፈቅድ አካል፣ ከጁንታው ብርሃነ ገብረክርስቶስ ካልተማረ ከማን ይማራል? ለህዝብ እታገላለሁኝ የሚል፣ ለህዝብ አንዲት ደረጃዋ የጠበቀች ሆስፒታል ሳያሰራ እንዴት ውጭ ለመታከም ደፍሮ ይከራከራል? https://www.facebook.com/dimtsiweyane/posts/3721520011279481
.
ነገሩ ወዲህ ነው፣ ባሁኑ ሰአት አገር ቤት እንደ ፕሮፌሴር አስራት ወልደየስ መስዋእትነት መክፈል የማይፈልገው ክህደቱ፣ “ፖለቲካ አልገባው ለሚለው ህዝብ መስዋእትነት” ከምክፈል ይልቅ፣ የላፕቶብ ጦርነት ለማድረግ ህክምናን እንደ ሰበብ መጠቀም ስለሚፈልግ ብቻ ነው!!! ይህ ከሆነ ህወሓት ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ፣ ብርሃኑ ነጋ የላፕቶፕ ጦርነት አድርጎ ህወሓትን ማሸነፍ አይችልም ሲለን የነበረው ክህደቱ ዛሬ፣ ከጁንታው ሞት ቦሃላ እንዴት የላፕቶፕ ጦርነት ለማድረግ ቆርጦ ተነሳ? መልሱ ለናንተ።
.
ጁንታው አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ግን ዛሬም በውጭ ከሚገኘው ድምፂ ወያኔ ጋር ሆኖ በኢትዮጲያ ህዝብ ላይ ሞት ይደግሳል፣ በህክምና ምክንያት ለኢትዮጲያ ሞት ለሚደግስ ካሃዲ ጋንዲ ሆስፒታል መታከም በቂው ነው!!! ክህደቱ እውን ለአማራ ህዝብ ቢቆሮቆር ኖሮ እንደ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፣ ለአማራ ህዝብ ሲል በአገሩ መስዋእትነት ሊከፍል ይገባው ነበር!!! ክህደቱ ለትግራይ ህዝብ ቢቆሮቆር ኖሮ እንደ ሓየሎም አርአያ በአገሩ መስዋእትነት ሊከፍል ይገባው ነበር! ዳሩ ግን ክህደቱ ለጁንታው ስለሚቆረቆር በዲሲ ጎዶናዎች መስዋእትነት ለመክፈል ወስነዋል፣ ይህ ደግሞ አይሆንም!!! ከሆነ ተጠያቂው የደህንነት ቢሮ ነው!!!
.
ነገም ክህደቱ እንደ ጁንታው ብርሃነ ገብረክርስቶስ ለህክምና ከተፈቀደለት፣ ከጆን ኤፍ ኬነዲ(NYC) ኤርፖርት በቀጥታ TMH ሄዶ ኢትዮጲያ መፍረስ አለባት እስከሚልህ ድረስ የምትጠብቅ ኢትዮጲያዊ ካለህ የጁንታው እና ተላላኪዎቹ ፖለቲካ አልገባህም ማለት ነው።
ናትናኤል አስመላሽ
ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ከመተከል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ዳግም ከባህር ዳር ሊፈናቀሉ መሆኑን ተቃወሙ፣ዶ/ር አብይ የጠ/ሚኒስትር ስልጣን ገደብ ይኑረው ማለታቸው በኢህአዲግ ጎራ መደናገጥ ፈጠረ፣የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ያቀረበበት የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በአዲሱ መከላከያ ሚኒስትር ተጨማሪ አስር ዓመት ተፈቀደለት፣ሀይለማርያም ደሳለኝ የደ/ሱዳን መሪዎች ስልጣን ይልቀቁ ማለታቸው ለመስቀለኛጥያቄ ዳረጋቸው፣የሶማሌ ሕዝብ ተቃውሞ፣ኢትዮጵያዊው የሁበር አሽከርካሪ መቀጣት ሌሎችም ዜናዎችም አሉን

4 Comments

  1. ልደቱ ከጀርባው ደጋፊ የሌለው የማይጎዳ ባንዳ ነው ከስሜት በስተቀር መረጃ የለንም ይህንን ስልም ጤነኛ ነው ብዬ ለማለት ይቸግረኛል ሳሙና ነው ከብርሀኑ ነጋ አንዳርጋቸው ጽጌም አይብስም ጥፋቱ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን የሚገባው አብይ ካላጣው ሰው እንዴት አርከበን ወሳኝ ቁልፍ ቦታ ላይ አስቀመጠው? ህዝቡስ ነገር ሳያገናዝብ እንዴት የጥላቻውን ሰይፍ ልደቱና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ አሳረፈ? ከትግሬዎች ክፋቱን ሳይሆን ህብረትን እንማር።

  2. Recently Lobbyist Lidetu Ayalew is labeled ‘A ONE MAN ARMY’ by the Ethiopian government cadres, he is currently feared more than he was ever feared, by the Ethiopian government’s security apparatus.

  3. በመሰረቱ ሰው መታከም አይገባውም ብሎ ማሰብ ምንም ይሁን ምን በመንም መመዘኛ ትክክል አይደልም እንኳን በህግ አትፈለግም ተብሎ የተለቀቀ ግለሰብ አይደለም በህግ ቁጥጥር ስር ያሉ ግለሰቦችም ጭምር ህክምና ሊከለከሉ አይገባም፡፡ እንዲህ አይነት አስተሳስብ በተለይ የፖለቲካ ፓርቲወች የሚያራምዱት ከሆነ እግዚኦ ማሃረነ ሰውረን ነው የሚያስብለው። እንዲህ አይነት ፖለቲክኞችን ወደስልጣን አታምጣ ብሎ አምላክን መለምን ነው፡ ማንም ሰው ወደድነውም ጠላነው በህግ የማይፈለግ ከሆነ ህክምና ይክልክል ብሎ ማሰብ የሃሳብ ማንነትን የሚይሳይ ወይም አሁን አቶ ልደቱ እንዳስታወቁት የተከለክሉት ይህን መሰል አስተሳሰብ ባላቸው ልባቸው በበቅል የተሞላ ፖለቲክኞች መሆኑ ወዴት እየሀድን እንደሆነ ማሰብ በጣም ያማል እረ ልብ ነግዛ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ሃገር በእንዲህ ያለ አስተሳሰብ አይገነባም የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈለጋል

  4. I think it is good to let Kihedetu have a medical leave once he left the country and open his stinking Banda mouth he will not return back to Ethiopia. As one activist reported he has no job for the last thirty years and yet he owns a hotel as an investor. How come? His medical travel will forfeit his ownership, and let him taste the real life in foreign land and learn how to earn money with real work not with political prostitution.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.