በሬ ከአራጁ ይውላል! ጆኖሳይዱ በውጭ ገለልተኛ ተቌም (ICC) ይጣራል! – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

e723ዶክተር አብይ በብልጽግና ስም፣ በዴሞክራሲና ምርጫ ስም፣ ለህዝብ ያሻገረው የማያባራ ጦርነትና ጆኖሳይድ ነው!

‹‹በየአቅጣጫው አማራን የማጥፋት ሰራ እየተሰራ ነው››አቶ ምስጋናው በለጠ የህግ ባለሙያ  በሰጡት ቃለመጠይቅ (https://www.youtub.com/watch?v=Zv2HzRiOGQA)ማስረጃ በማቅረብ ‹‹ብልጽግና ሸኔ›› መሆኑን አጋልጠዋል ይስሙት፡፡

በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል፣ በትግራይ ማይካድራ፣ በደቡብ በጉራፈርዳ የአማራን ንጹሃን ዜጎች የዘር ማፅዳት ፕሮግራም እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ከነማስረጃው ገልጸዋል፡፡ የዘር ማፅዳቱን ዘመቻ ብልጽግና ፓርቲ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ የፌዴራል መንግሥትና የክልል መንግስቶች፣ አሜሪካ መንግሥት፣ የእንግሊዝ መንግሥት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ቢቢሲ፣ ሲኤን ኤን፣ አልጀዚራ፣  ኢቲቪ፣ ዋልታ፣ ፋና፣ የአማራ ሚዲያና የክልል ሚዲያዎች  ወዘተ አልዘገቡትም!!!  በአማራ የዘር ማፅዳት የተፈናቀለው ህዝብ ከአራት መቶ ሽህ በላይ ሲሆን ወደ አማራ ክልል የሸሹ ተፈናቃች ቁጥር መቶሰባ ስድስት ሽህ ደርሶል፡፡  ‹ብልፅግና ሸኔ› ኦነግ ሸኔና ኦነግ በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (International Criminal Court) መቅረባቸው አይቀርም!!! እንደ ህወሓት የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ደኢህዴን ወንጀለኞች ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ ኦነግ ሸኔ ‹‹የሰው አንገት ከመቁረጥህ በፊት አስብ፣ ምክንያቱም መልሰህ አትተክለውምና!!!››

ብልፅግና ሸኔ!!! ብልጽግና አባ ቶርቤ! እጩ ተመራጮችን መግደል ጀምሮል፣‹ በሬ ከአራጁ ይውላል!› በስድስተኛው ዙር ምርጫ ቢሸነፉ ያዘጋጁልን ድግስ በተለይ ለአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ናዝሬት፣ ሻሸመኔ፣ ጅማ፣ አሰላ፣ ወዘተ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የህዝቡን ደህንነትና የጸጥታ ሁኔታ የፌዴራልና የክልል መንግስቶች እንዲሁም  ምርጫ ቦርድ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡  በውጭ የሚኖሩ አንድ ሽሀ አንድ የአማራ ዲያስፖራ ዜጎች ድርጅቶች ህብረት በማጣት አንድ ሳይሆኑ ለአማራ ህዝብ ሳይደርሱለት መቅረታቸው ያሳዝናል፡፡   አባ ቶርቤ!!! …ማነህ ባለሳምንት!!!

 • የኦሮሞ ጦር (ልዩ ሀይልከእንጦጦ ተራራ ጀርባ የሰፈረው ለምን አላማ ይሆን???/መርእድ እስጢፋኖስ/ |01/02/2021 | /EthioReference/ ከ2011ዓ.ም መገባደጃ ጀምሮ አዲስአበባ ከተማ ዙሪያዋን ከብቦ የሰፈረው የኦሮሞ ጦር ይበልጥ ወደ መዲናዋ መቅረቡ ነዋሪዎችን እያሳሰበ ነው።  የኦሮሚያ ክልል ከ30-35ሽህ ልዩ ሀይል በ34 በሆነ ዙር እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባርም በሽዎች የሚቆጠር አዲስ ወታደሮች ማስመረቃቸውን ከሰሞኑ አስተውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጭ ሃገራት ኤምባሲዎች ለዘጎቻቸው ጥብቅ የሆነ የደህንነት መልዕክት ማስተላለፍ መጀመራቸው ተሰምቷል። በተለይ የአሜሪካ የእንግሊዝ የእስራኤል ኢምባሲዎች “አዲስ አበባ ዙሪያ የሰፈረ ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ጦር አለ። ጦሩ በማን እንደሚመራም አይታወቅም። እናም እንጦጦን ጨምሮ ማንኛውም የውጭ ሃገር ዜጋ ለጊዜው ከአዲስ አበባ ውጪ እንዳይንቀሳቀስ። በእንጦጦ ጫካም ለጊዜው የእግር ጉዞ እንዳያደርግ” የሚል መልእክት ለዜጎቻቸው በኢሜይል ማስተላለፋቸው ነው የተሰማው።
 • መተሃራ የስር ፋብሪካ የኦነግ ሸኔ የጦር ካንፕ ሆኖል
 • አርባ ምንጭ ነጭ ሣር ፓርክ የኦነግ ሸኔ የጦር ካንፕ ሆኖል

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በሰጠው የአቋም መግለጫ መሠረት ‹‹ከሁሉ አስቀድመን፣ በአገራችን ምዕራብ ኦሮምያ ክልል፣ ወለጋ ውስጥ፣  በሆሮጉድሩ ወረዳ  ውስጥ ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጸመ ጥቃት ከ60 በላይ ንጹሃን  ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና በኦነግ ሸኔ አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ባልደራስ ይገልጻል፤ የሟቾችን ነፍስ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን፡፡ ለውድ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው  መጽናናትን  እንመኛለን፡፡ ፓርቲያች ዘሰቀን በአማራ እና በሌሎች ንጹሃን ዜጎች ላይ ሆነ ተብሎ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ኦነግን ከኤርትራ በረሃ ወደ አገር ቤት ከነትጥቁ እንዲገባ ያደረገው፣ በኦሮምያ ክልል  ጸጥታ መዋቅር ውስጥ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ እንዲካተት ያደረገው እና በመንግሥታዊ ስልጣኑ ሽፋን በመስጠት ለዚህ አሸባሪነት ደረጃ የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳድር ከማንም በላይ ተጠያቂ እንደሆነ ፓርቲችን ባልደራስ በጽኑ ያምናል፡፡ ይሄንን አረመኔያዊ ወንጀል የፈጸሙ እና እንዲፈጸም ያደረጉ ሁሉ በፈጣሪም ሆነ በምድሩ ሕግ የሚጠየቁበት ጊዜ እሩቅ አይደለም ። ፓርቲያችንም ለዚህ እውን መሆን በትጋት እንደሚሰራ መግለጽ ይወዳል፡፡ በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ሳያቋርጥ ለባለፉት 3 ዓመታት የቀጠለው የዜጎች ሞት እና መፈናቀል ክልሉን እየመራ ያለው ኦህዴድ/ብልጽግና፣ በተረኝነት አገርን ከመዝረፍ ውጪ  መምራት እንደማይችለ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ሃቅ ነው፡፡ ይህ ኃይል  ተጨማሪ ዓመታትን በስልጣን ላይ ሲቆይ አገራችን ኢትዮጵያ  ወደማትወጣበት ውስጣዊ እና አከባቢያዊ ገደል ውስጥ ይዞ የሚገባ ስለሆነ በቃ ሊባል የሚገባበት ምእራፍ ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን መሰል በዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ንብረት ማውደም እና ዘራፍ ከምንም በላይ መንግስታዊ ሽፋን የተሰጠው እንዲህ አይነቱ ዕኩይ ተግባር ባለበት ሁኔታ፤ የዘንድሮ ምርጫ ሰላማዊ ለማድረግ መንግስት ጸጥታ የማስጠበቅ እና የዜጎችን ደህንነት፣ የፖለቲካ ኃይሎች በሰላማዊ እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚኖራቸው  እንቅስቃሴ አደጋ ውስጥ የሚከት መሆኑ ፓርቲያችን ይገነዘባል። በተጨማሪ መንግስት እንዲህ አይነቱ ደተኝነት የሚያሳየው በሥልጣን ለመቀጠል ካለው የሥልጣን ጥምኝነት ብሎ ፓርቲያችን ያምናል፡፡›› በማለት ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የአቋም መግለጫ ሲያወጣ፣ሌሎች  ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ኢዜማ፣ እናት ወዘተ ፓርቲዎች ዝምታ እንዲሁም ብሄራዊ ክልላዊ  መንግሥታት (የሱማሌ፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ አፋር፣ ደቡብ፣ ሲዳማ፣) የኦነግ ሸኔን፣ የብልፅግና ሸኔ የዘር ማጽዳት ዘመቻ መቃወምና ማጋለጥ ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታችሁን መወጣት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁ መሆኑን ዘንግታችሁታል፡፡ አንድ ቀን ያስጠይቃል!!!

‹‹በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጉር ወረዳ ዳቢስ በሚባል ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውን የዞኑ አስተዳዳሪና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ።  “በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ብሔር አባላት ላይ መሆኑን” የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ደቻሳ ይህንኑ አረጋግጠዋል።…”ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ብለዋል።… በአካባቢው ሸኔ የሚባል ኃይል አባ ቶርቤ ከሚባል ቡድን ጋር ተቀናጅቶ በሰላማዊ ዜጎች፣ በመንግሥት ባለስልጣናት እና በፀጥታ አካላት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽሙ እንደነበር አስታውሰዋል። የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ያሏቸው ቡድኖች ከርቀት በልዩ ኃይሉ ላይ ጥቃት በመፈፀማቸው “ወደ እኛ ሳይደርሱ ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ ተመልሷል” ብለዋል።

‹‹በሬሳ ክምር መሀል በህይወት የተገኘው አሳዛኙ ህፃን!! እናትና አባት እንዲሁም ዘመዶቹን በሙሉ ገድለውበታል፡፡ በምን አግባብ እንደተረፈ እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ ህጻኑ አስከሬን ልናነሳ ወደ ሟች ወገኖቻችን ባመራንበት ወቅት በደም የታጠበች እናቱ ጋ ሂዶ ጡት ይጠባል፡፡ ከስልሳ ሰወች አንድ ህጻኑ ተርፏል።  አባትና እናት እህትና ወንድሙ አንድ ላይ ታርደው ተጥለዋል። ህጻኑ ስለመሞታቸው እንኳን አያውቅም ነበር፡፡ እህትና ወንድሞቹ ተኝተዋል ብሎ በማሰብ እየሄደም ሊቀስቀስና አብሯቸው ሊጫወት ይሞክራል። ነገር ግን ሁሉም ትተውት ሂደዋል። በዚህች መራራ ዓለም አራት እህትና ወንድም ሁለት እናትና አባቱን አጥቶ ከ60 አስከሬን አንድ ብቻውን እሱ ተርፎ ተገኝቷል።  ህጻኑ እንኳን ማንነቱን ሊያውቅ ይቅርና ቤተሰቡ ማንቀላፋታቸውን እንጂ መገደላቸውን አያውቅም ነበር፡፡ ከእሱ ጋር በእድሜ ሚመሳሰሉትም አብረው ተገድለዋል። ይህ ህጻን እንዴት እንደተረፈ ቤተሰቦቹ ሲጨፈጨፉ የት እንደነበር አምላክ ይወቀው፡፡ ጨካኝና ሰው በላ አረመኔወች አቅፈን እናጫውትህ ቢሉት እንኳን እጁን ዘርግቶ እቀፉኝ የሚል ነው። ነገር ግን ከአማራው አብራክ ወጥቷልና የምህረት ዓይናቸው ታውሯል፡፡ ጀግንነታቸውም ያልታጠቀን ገበሬ ሴትና ህጻናትን በሰቅጣጭ ግድያ መግደል ነው። የእነሱ ጀግንነት ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ የኦሮሞ ክልል ባለስልጣናት በዚህ ሁኔታ ይደሰቱ ይሆናል ነገር ግን በቀልም ይሁን ምህረት ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል!!    ይህንን ህጻንና መሰል ወገኖቻችንን ለመታደግ በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ያለነው አንድም ከቦታው ርቀት ሁለተኛም የኦሮሙማው መንግስት ክልሉን በ30+ ዙር የሰለጠነውን ጦሩን ድንበር ላይ በዝግ አሳጥሮ ነው፡፡ አማራው አጸፋ ሚሰጥ ከሆነ ኦነግ ወደ ጫካው ገብቶ በምትኩ የኦሮሞ ልዩ ሀይል መሳሪያ ገፈፋ በሚል ህዝባችንን በህጋዊ ሽፋን መልኩ ይጨፈጭፋል። በዘመነ ወያኔ አክሱም ወይም ሽሬ ላይ የአማራ ህዝብ ቢጨፈጨፍ እዚያው ድረስ ገብቶ መታደግ እንደማይቻል ሁሉ በመተከልና ወለጋም እንዲሁ በንቀት ታይቶ ከክልል ክልል የመሻገሩን ሁኔታ  እንኳንስ የኦሮሞ ልዩ ሀይል ~ህይወቱን (ተቋሙን) የታደግነው የሀገር መከላከያ ለኦነግ አንቀላፍቶ እያሳለፈ ህዝባችንንም እያስጨፈጨፈ አማራው ተደራጅቶ ራሱን ሲከላከል ፈጥኖ የደረሰ በማስመሰል ውጊያውን ከአማራው ገበሬ ጋር የሚያደርግ ስብስብ ነው። ስለዚህ መንግስታዊነትን እንደ ሽፋን እየተጠቀሙ ያሉ ኦነጋዊ አመራሮች ሚከሽፉት የቆሙበትን ስርዓት ስንንጠውና ስናፈርሰው መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል።››

‹‹ሸረሪቷን ጨርሰን የሸረሪት ድሯን እየጠረግን ነው ከተባለ ወዲህ ወለጋ የማይቋረጥ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እየተደረገ መሆኑን እየሰማን ነው!!!…. ታጥቆ የገባውን የኦነግ ጦር ማስወገድ ያልፈቀደው የሽመልስ አብዲሳ አስተዳደር እና የፌደራል መንግስት ፡ አማራ አርሶአደሮችን ትጥቅ ፍቱ በማለት የክልሉ ፖሊስ ሳይቀር እንዲወጋቸው እያደረጉ ነው። ገዳይ ታጣቂ የተሠማራባቸው አርሶአደሮች ደግሞ ትጥቅ ከምንፈታ ሞትን እንመርጣለን ብለዋል። በወለጋ ከተሠማራው ጠላት ሊታደጋቸው ያልቻለ ክልል ትጥቅ ፍቱ ማለት እንግደላችሁ ማለት እንጂ ሌላ ገፅታ የለውም።

[ስልጣን ላይ ያለው ከነ ሌንጮ ለታ አመራር የቀጠለ የአማራ ዘር ማፅዳት እየመራ ያለ አዲስ ትውልድ ነው። አማራን የመስበር ሕልማቸው አካል ነውና ያን ለማረጋገጥ እያስፈፀሙት ያለ ነው።]

ዛሬም ወያኔን ሰበብ አድርገው ለመቅረብ እንደማያፍሩ ቢታወቅም ኦነግ-ሸኔ በኦሮሞ ብልፅግና የሚቀለብ የኃይል ሚዛን አስጠባቂ ጦር መሆኑን መገመት ስህተት አይደለም።  እያንዳንዱን ስሌትና ሁኔታ አጢነው። አማራ የቸገረው ሀሞት ያለው፣ አማራ ሆኖ መቆም የሚችል አመራር ነው።  በማጎብደድ ጀርባው የጎበጠ አንደበቱ የታሠረ  የጠላት አሽከር ሲወክልህ መቆጣትም ማዘንም የማይችል ፡ የማትችል ያደርግሃል።  መናቅን ያለማምድሃል። ዘርህ ተመርጦ መገደልህን ያመቻምቸዋል።   “ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ”! የዚህ አመራር አስተሳሰብ ወራሹ ልሒቅም ከአገርቤት እስከ ውጭ አገር ዝም ብሏል። የወያኔ ደጋፊ ልሒቅ ግን የአውሮፓ ሕብረትና UN ደጆችን እያጨናነቀ ይገኛል። አማራ እየተጨፈጨፈ ዝም ብሏል። ዝም በል የሚልህ ይበዛል፡፡ የጠላቶች የፍርድ ቀን ሩቅ አይደለም!››

ተጠያቂው ማን ነው? ኦሮሚያ፣ መተከል እና ትግራይ…!!!

ኦሮሚያ እና መተከል፤ በተደጋጋሚ በኦሮሚያ ክልል፣ በወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ክልል፣ መተከል ዞን በንጹሀን ዜጎች ላይ ለሚፈጸመው ተከታታይ ጥቃት ኦነግ ሽኔ እና ሌሎች ታጣቂ ጏይሎች ብቻ ሳይሆኑ ጥቃቱን ባለማስቆም የክልሎቹ መንግስታት እና የፌደራል መንግስቱም እኩል ተጠያቂዎች ናቸው።

ትግራይ፤ በተመሳሳይ ሁኔታም ትግራይ ውስጥ በንጹሐን ዜጎች ላይ ለደረሰው እና እየደረሰ ላለው አሰቃቂ ጉዳት፤ በሰሜን ዕዝ እና በማይካድራ የደረሱትን እጅግ አሰቃቂ ጥቃቶች ጨምሮ በእኔ እምነት ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው በቅደም ተከተል፤

 • 1ኛ/ በዋነኝነት ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ ለደረሰው ጠቅላላ ጉዳት፣
 • 2ኛ/ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጠናቋል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው ሰቆቃ፣
 • 3ኛ/ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ ማን ይጠይቃቸዋል፣ የት እና መቼ የሚሉት ጥያቄዎች እንዳሉ ሆነው እነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ ናቸው ብዮ አምናለሁ

ምንጭ፡

(1) መንግስታዊ ሽፋን የተሰጠው የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የምርጫ ቦርድ አሻጥር አስመልክቶ ከባልደራስ የተሰጠ የአቋም መግለጫ ! EthioReference Posted by admin | 11/03/2021 | 

(2) ቅዳሜ ዕለት በሆሮ ጉድሩ በታጣቂዎች ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ10 መጋቢት 2021

(3) በሬሳ ክምር መሀል በህይወት የተገኘው አሳዛኙ ህፃን!! (ስንታየሀ ታከለ) EthioReference 11/03/2021 | 

(4) ለ30 ዓመታት በአማራ ደም የራሰው የወለጋ ምድር! አንሙት አብርሃም EthioReference | 10/03/2021 | 

(5) ተጠያቂው ማን ነው? ኦሮሚያ፣ መተከል እና ትግራይ! ያሬድ ሀይለማርያም EthioReference | 10/03/2021 | 

3 Comments

 1. ውሻ በበላበት ይጮሃል ይላሉ አበው። አየርላንድ ተመድ እና የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ግንባር ቀደሙን እንቅስቃሴ ማድረጓ ከወያኔ ጋር በነበራት የቀደመ ጋብቻ ነው። ወያኔም የሃገር አለቃ ከሆነ በህዋላ እንደ ልባቸው ከወያኔ ጋር አብረው የዘረፉና ያዘረፉ እንዳሉ የታወቀ ነው። ወያኔ በረሃ እያለ በሱዳን/በትግራይ ከአየርላንድ የተላኩ የህክምናና የጦር አሰልጣኞች እንደነበሩ የአይን እማኝ ምስክሮች ዛሬም ይናገራሉ። ሰርቆ የሚያበላው ወያኔ እነዚህንም ነጮች ልባቸውን በሴት ፍቅርና በንዋይ ሰንጎ በመያዝ መገልገያው እንዳደረጋቸው መረጃው ክምር ነው። ስለሆነም የአየርላንድ ኡኡታ ከዚህ የመነጨ ነው። በየሥፍራው በዘሩ እየተለየ ለሚጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ ግን አንድም ሃገር ያኔም ወያኔ ሲጨፈጭፍ አሁንም የኦሮሞ አክራሪዎችና ሌሎች ሃይሎች በገንዘብ እየተነድ በቤ/ክርስቲያን ውስጥ ሳይቀር ሲያርድ፤ ቤት ቆልፈው በእሳት ሲያጋዪ፤ ነፍሰ ጡር ሴት ሆድ ሲቀድ፤ እልፎች ከቀያቸው ተበትነው ለረሃብና ለበሽታ ሲጋለጡ ለምን ብሎ የጠየቀ የለም። በመሰረቱ የወያኔና የሻቢያ ፓለቲካ የአማራን ህዝብ እንደ ቅኝ ገዢ በመሳል ለአለም ሁሉ የውሸት የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ በመንዛታቸው መንግሥታት ሁሉም ባይሆኑ ሃሳቡን እንዳለ ተግተውታል። የዘር ማጥፋት በትግራይ ሆነ የሚሉን እነዚህ ወስላታ ሃገራት 2 ሚሊዪን አማሮች የት እንደ ደረሱ አላውቅም ሲባል ዝም ብለው የሰሙ ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰቃየው የድር አራዊቱ፤ ለማዳ እንስሳው፤ የቆሙ ዛፎችና እጻዋቶች ጭምር ነው። የኦሮሞ/የኦነግ ጦር ወዘተ ሁሉ እሳት የሚበላው ጭድ ነው። በቅርቡ አንድ የአማራ ዲስኩረኛ ሲናገር “ወያኔ ጦርነት እንደሚጀምር አስቀድመን አውቀን ስለነበር ተዘጋጅተናል” በማለት ሲያሽካካ አይ ሰው ምን አለ ዝም ቢል በማለት አልፌዋለሁ። ታዲያ ወያኔ ጦርነት እንደሚጀምር ከደረሱበት ለምን የሰሜን ጦር እስኪመታ ተጠበቀ? አሁንስ መቼ ጦርነቱ አለቀ? እድሜ ለቻይና ማይክሮፎን መደንፋት ነው። ግን ይህ ለህዝባችን ምን ጥቅም አለው? ማን ሙቶ ማን ይኖራል? ማብቂያውስ መቼ ነው? ግራ ያጋባል? ሰው በልዪነቱ ተከባብሮ ዘርና ቋንቋውን ወይም አፓርታይዳዊውን የክልል ፓለቲካ የሙጥኝ ሳይል የሚኖርበት ዘመን መቼ ነው?
  አዎን በትግራይ ውስጥ ወያኔ በጫረው እሳት በደል አልተሰራም ማለት ይቸግራል። አቦይ ስብሃትን ከገደል ከማውጣት ይልቅ በዚያው እንዲያሸልቡ ቢደረግ እንዴት ማለፊያ ነበር። ግን ምድሪቱ ሊሞት የሚገባው የማይሞትባት፤ ሊሞት የማይገባው የሚሞትባት ናት። ዛሬ በትግራይ ምድር ያለው ዋይታ ጠላ ሽጣ ያሳደገችው ልጆቿ ሞተውባት ነው። ወያኔ ግፈኛ ነው። የሰው ደም ለወያኔ ምንም አይመስለውም። ታሪካቸውን መርምሮ ማየት ለዚህ ሃሳብ ድጋፍ ይሰጣል። ሃውዜንን ያስደበደቡ እብዶች፤ አሁን በትግራይ በደል ተሰራ ለማለት ሰው ሰብስበው ቢረሽኑ እኔ አልደነቅም። ግን ውጊያውን የከፈተው ማን ነው? ወያኔ አይደለምን? እብሪት፤ እብደት፤ እኛ ብቻ ማለት እንዲህ እንደ ሮም አወዳደቅ ፍርክስክስ አደረጋቸው። ደግመው ሊሰሩ ቢሞክሩም እንደ ድሮው አይሆንም። ቀን በሄደ ቁጥር የውሸት ታሪካቸው ይዘነጋል። እነርሱም ተፈጥሮ በወረፋ አፈር ናቸውና አፈር ይሆናሉ። እስከዚያው ግን ልክ እንደ ለመድት ሲያማቱና ሲያጋድሉ ሲገድሉና በትግራይ ልጆች ህይወት ቁማር ሲጫወቱ ጀንበር ጠልቃ ትወጣለች። ትግራይ ውስጥ ተፈጸመ የተባለው ወንጀል ማጣራት አስፈላጊ ነው። የሰሜን እዝም ፈጸመው የኤርትራ ወታደር መታወቁ አስፈላጊ ነው። እንደ እኔ እይታ ግን የምርመራው መዝገብ መስቀለኛ አላማው ወያኔ ቢሆን የተሻለ ነው ባይ ነኝ። ግን እናስብ ወንጀል የሚፈጸመው ትግራይ ውስጥ ብቻ አይደለም። የሌሎች እንባና ዋይታስ ማን ይይላቸው? ግራም ነፈሰ ቀኝ ለወያኔ ባደሩ ጋዜጠኞችና የፓለቲካ ደላላዎች የሚነዛውን ወሬ እንዳለ ስልቅጦ ራሴን ከማለት መመርመር አስፈላጊ ነው። ዛሬ በኢንተርኔት ብዙ ጉድ ይሰራል። 95% የኢንተርኔት ትራፊክ የሚጨናነቀው ጥብ በሆነ ሃሳብና ተንቀሳቃሽ ምስል ነው። አለማችን ወደ ማትመለስበት ማጥ እየገባች ነው። እኮ በል ቆይና እይ! ምርመራውም ይሁን! በቃኝ!

 2. The Balderas terrorists had shown their faces in public during the Adwa Victory celebration in Addis Ababa. They are all being searched for allover Addis Ababa. These Balderas terrorists can not escape out of Addis Ababa in any direction. The public in Addis Ababa should assist by turning these Balderas terrorists over to the authorities inorder to end this operation soon.

 3. በኤርትራ ህግ መሠረት የኤርትራ ወታደር አስገድዶ ከደፈረ በሞት ፍርድ ይቀጣል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.