ብልጽግና ፓርቲ ዶክተር አቢይ አህመድን በጅማ ዞን አጋሮ ከተማ ለምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪ አድርጎ ማቅረቡን አስታወቀ

160225847 10219861771836502 8154847554857754059 n
ፓርቲው ይህን ያስታወቀው በዛሬው ዕለት በአጋሮ ከተማ ማኒፌስቶውንና የምርጫ ምልክቱን ለአባላቱና ደጋፊዎቹ ባስተዋወቀበት ወቅት ነው፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የአጋሮ ከተማ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ነዚፍ መሀመድአሚን በትውውቅ መድረኩ ባደረጉት ንግግር “ፓርቲው አስከፊውን ሥርዓት ያስወገደና ለአገራችን ትልቅ የለውጥ ብርሀን መፈንጠቅ የቻለ ነው” ብለዋል፡፡
ፓርቲው ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሀዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን አንደሚወጣ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.