የዲሲ/ካናዳ ሰልፎች ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለፒፒ የፖለቲካ ትርፍ የሰጡ ሰልፍች ናቸው – ግርማ ካሳ

159365892 2953213261580041 3943039510582496369 oበዲሲና በካናዳ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ ሕወሃትን በመቃወም የተደረገ ሰልፍ የሚደገፍ ሰልፍ ነው፡፡ የህወሃት ሰዎች የአገራችንን ገጽታ በአለም አቀፍ መድረክ እያቆሸሹት በመሆኑ በዚህ መልኩ ትልቅ ተነሳሽነት ኖሮ ሰልፍ መደረጉ ጥሩ ነው፡፡
ሆኖም ግን እጅግ በጣም በሰልፎቹ አዝኛለሁ፡፡የሰልፉ አዘጋጆች ሰልፎቹን ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግነት ሃይጃክ አድርገዉታል። ብዙዎቹ በሰልፉ የተገኙት ለኢትዮጵያ ብለው ነው። ነገር ግን ሰልፉ ለኢትዮጵያ የተደረገ ሰልፍ ነበር ግን ማለት አይቻልም።
በሰልፎቹ የማይካድራ ጄኖሳይድ ሲወገዝ ነበር። ጥሩ ነው፡፡ ተገቢ ነው፡፡ የመተከልና የወለጋ ፣ የአርሲ፣ ባሌ ጄኖሳይዶች ግን አልተነሱም። በትግራይም ማንም ይግደላቸው ማንም፣ ዜጎች ተጨፍጭፈዋል፥ ሴቶች ተደፍረዋል፡፡ ለነርሱም መጮህ ይገባ ነበር፡፡ ያ አልሆነም፡፡ ምክንያቱም የሰልፉ አዘጋጆች ፣ ግንቦት ሰባቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች አብይ አህመድን ያስቀይማል ብለው ስላሰቡ ነው።
ስለዚህ ሰልፉ ኢትዮጵያ የተጠቀመችበት ሳይሆን የዶር አብይ አህመድ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና የፕሮፖጋንዳ ትርፍ ያገኘበት ነው።
ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጽ ነበር። አሁን ግን የተለየ ነገር ነው እየሆነ ያለው። እስቲ አስቡት፣ የዲሲውንና ካናዳውን ሰልፎች በመገናኛ ሜዲያ በኢቢሲ ቻግኒ ስደተኞች ካምፕ ያሉ ቢሰሙት፣ በወለጋ ሆሮጉድሩ ያሉ የጥቃት ሰለባ የሆኑ ማህበረሰባት ቢሰሙት ፣ በትግራይ የተደፈሩ እህቶችና ቤተሰቦቻቸው ቢሰሙት ምንድን ነው የሚሰማቸው ? እኛ በነዚህ ወገኖች ቦታ ብንሆንም ምንድን ነው የሚሰማን ?????
ኢቢሲና የመንግስት ሜዲያዎች በወለጋ ላለፉት 3 ቀናት ብቻ የተፈጸሙ ሰቆቃዎችን፣ ዜጎች በማንነታቸው አማራ ተብለው ሲታረዱ፣ ሕጻናት ወንዝ ውስጥ ሲወረወሩ …ያለውን ሁኔታ ለሕዝብ ማቅረብ ነበረባቸው፡፡ አላደረጉትም። ግን የዲሲዉን ሰልፍ ፣ ልክ ዶር አብይን በመደገፍ በኦሮሞ ክልል ሲደረግ የነበረ አይነት ሰልፍ ሰሞን እንዳደረጉት፣ በቀዳሚነት ነው በስፋት የዘገቡት።
በጣም የገረመኝ ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን ነው። የአማራ ብልጽግና መሪ ነው። የአማራው ማህበረሰብ ሲታረድ፣ ሲጨፈጨፍ ትኩረቱን እርሱ ላይ አድርጎ መረባረብ ሲገባው፣ ለሞቱትና ለታረዱት ሐዘኑን መግልጽ ሲገባው፣ ዲሲ የተደረገውን ሰልፍ እያነሳ “ኮራንባችሁ” ብሎ መጻፉ።
የአቶ ደመቀን አስተያየትና ሌሎች የብልጽግና አመራሮች የሚሉትን ስናይ፣ የዲሲውና የካናዳው ሰልፎች ሕዝብን እንዲያልቅ ሁኔታዎች ያመቻቸው የብልጽግና ፓርቲ መሪዎች እንዲኮሩና እንዲደሰቱ ያደረገ ሰልፍ ነው፡፡
በሌሎች ከተማዎች የሚደረጉ ሰልፎች ከዛሬ ሰልፎች ትልቅ ትምህርት በመውሰድ ሰልፎቹን በርግጥም ለኢትዮጵያ የሚደረግ ሰልፍ ያደርጉት ዘንድ እጠይቃከሁ። ለሕሊናችን፣ ለእውነት፣ ለፍትህ እንደር። የጥቁት አምባገነኖች መጠቀሚያ አንሁን !!!
159320037 10224615804733314 8415138427074828297 n 159335788 10224615904375805 864783627833840157 n

7 Comments

 1. አይ ግርማ ካሳ፤ ሰው አንድ ቀን እንኳ ተሳስቶ ትክክል አያስብም? መጀመሪያ ህገር ሲኖር አይደል እንዴ? ለመሆኑ አንተ ራስህ ሰልፍ ወጥተህ ነበር? ወይስ በፌስ ቡክ ነው የተከታተልከው? ግልጽ አላደረክም፤፤ There is no “ifs and buts” to join this demo. ሰልፉን እየቻልክ አስበህበት ቀርተህ ከሆነ እውነት እልሃለሁ እንዳፈርክ ትኖራለህ፡፤ ችግሩ ከብልጽግና፤ ከአቢይ እና ደመቀ በላይ ነው ነሚቾ!
  በተረፈ እንግዲህ ካልተመችሀ በቃ አንተ ደግሞ ሌላ የአንተ መፈክሮች የሚሰሙበት ሰልፍ አዘጋጅ፤፤ የፈልከውን ደግፍ (ጁንታውን ጨምሮ) የፈልከውን አውግዝ (ብልጽግናን ጨምሮ)፤፤ ምርጫው ያንተ ነው፤፤ ዲሞክራሲን ተለማመድ፤ የማይፈልጉትን ማየት እና መስማት መቻልን ይጨምራል፤፤ ሌሎች እንደኔ ካላሰቡ ብለህ መንጨርጨሩ የሚጎዳው ራስህን ነው፡፡ ካላስ!

 2. I am sorry to say this but this is the truth, at least in my surroundings.
  As long as we diasporas somehow come up with things to say so we don’t have to work double shifts to send back home remittance we feel like we are ok. Many diasporas showed up at this protest to somehow prove to the west that the Abiy administration’s actions are not worthy of sanctions, just because we don’t want sanctions.
  It was all in a day’s work, we tried.
  We diasporas don’t want sanctions because we don’t want or cannot or are not willing to be asked for too much, it just scares us already because we only can do so much when it comes to sending financial remittance.
  The Amara genocide is for now not mentioned by those in my surroundings because most of us maybe including me might be in denial as usual, we feel we can make everything ok by not inturupting the money flow to Ethiopia. I find many proud violent diasporas who spent decades in the diaspora saying “I sent this much , I sent this much” and they were expecting not to be asked for nomore by now, because that’s what TPLF promised them when TPLFites in the diaspora encouraged them to start sending.

  Think about those in the diaspora who told everyone the nature of TPLF before GERD’s construction started-If GERD was not financed by diasporas since the start TPLF would not have lasted in power this long.

  But diasporas prolonged TPLF by financing GERD, we diasporas worshipping TPLF regardless what TPLF does as long TPLF was for constructing a dam was and is a shame.

  Meaning diasporas were willing to give money and willing to give deaf ear to TPLF’s nature (a genocidal maniac ) just because we like dam electricity. We didn’t even wait until the genocidal maniac TPLF leave out of office to finance GERD. So if you expect we diasporas were out there today worried about genocide going on back home , we don’t want to hear it. We knew.

 3. ይህ የሚያኮራ ሰልፍ እስከዛሬ ያልታየ ነው:: ለምን ጥላሸት ለመቀባት ሞከርክ? ይህ የፖለቲካ ሰልፍ ሳይሆን ሀገርንና ክብርን የመጠበቅ አለም አቀፍ ንቅናቄ ነው:: ወደድም ጠላኸውም በዚህ ፈታኝ ወቅት ለኢትዮጵያ አንድነት ከመሰባሰብና ከመደራጀት ውጪ አማራጭ የለም:: ያንተ ቢጤ የፖለቲካ ደላላዎች ማራገቡን እስቲ ለጊዜው ተዉት::

 4. አይ ግርማ ከሣ መቸ ይሆን ትንሹንም ትልቁንም ከመውቀስና ከማቆሸሽ ራስህን ማፅዳት የምትችለው? እንዲያው ይህ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወቀስበት ምኑ ነው? ከላይ እንደተጠቀሱት ሃሳቦች የሀገርን ሉዓላዊነት ለዐለሙ ህብረተሰብ እውነታውን ለማሳወቅ፤ ወያኔ በወገን እና በሀገር ላይ የፈፀመውን መጥፎ ተግባር ለመግለፅ፤ዓለምም በሀሰት ጎዳና እንዳይጓዝ እና ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጥ፤ ስልፍ የወጣውም ህገራችን በገጠማት ችግር የልብ ብሶቱን እና ምሬቱን ለመግለጥፅ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ ለመንቀፍና ለመደገፍ ወይም አደባባይ ወጥቶ ለመታየት አይደለም፡፡እንዲያው ማጀት ( ጓዳ ) ያለው ሁሉ ለሰላማዊ ሰልፉ ይፃፍ ነው የምትለውን? ወይንስ ደብረ ፅዮን እና ጌታቸው ረዳ በሰልፉ በአታሞ ካልተወደሱ ነው? በእኔ እምነት የጆ ባይደን አስተዳደር ስልጣን በያዘ 2 ወር ባልሞላው ጊዜ ውስጥ የቆየ ቂም ይመስላል በማያገባው በስው ሀገር ጣልቃ በመግባት እከሌ ይውጣ የሚል ትዕዛዝ በመስጠቱ እንዲሁም በኣለም መንግስታት የ30 ቀኑን ስልጣን ተገን በማድረግ ጎልቶት የነበረውን ጉልቻ ( ወያኔን) መልሶ ለመጎለት ያሰበውን አላማ ለማጋለጥ ነው፡፡ በመሆኑም አያ ግርማ ከሣ ከመጻፍህ በፊት አጀንዳውን ተረዳው፡፡የወያኔ አፈቀላጤ ከሆንክም በግልጽ አሳውቅ ካልሆንክም የጀርባ የፖለቲካ አራጋቢ አትሁን፡፡

 5. አቶ ግርማ ካሳ ብዙ ጊዜ ሚዛናዊ ዳኝነት ያለው፣ የወገን ኅሊና የሆነ ድምጽ በድፍረት ስለሚያሰሙ ይደነቃሉ።
  ሰልፉን የውጭ መንግሥታት ሕወሃት ላይ ነፍስ ለመዝራት የሚያደርጉትን ርብርብ ለመቃወም በመደረጉ እደግፋለሁ። በሀገራቸው ጉዳይ ጊዜያቸውን ሰውተው ድምጽ የሚያሰሙ ሰዎች ምስጉን ናቸው።
  ገለልተኛ አጣሪ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ግን የሚደገፍ ነው። ብልጽግና እና ሕወሃት በመላው ሀገር ኢትዮጵያውያንን እየጨፈጨፉ መቼም ራሳቸው የሚሰጡት መረጃ ሊታመን አይችልም። ግፋቸውንም ሊያቆሙ አልቻሉም። የሚያሳዝነው ከትግራይ ጦርነት በፊትና በኋላም እጅግ ዘግናኝና መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ሲካሄድ የከረመ ሲሆን የዚህ ዝርዝር መረጃ ያላቸው ምእራባውያን ቁብም ሳይሰጣቸው እነሱ በቀጠናው ጣልቃ ገብተው የመሳሪያ ንግዳቸውን ለማጧጧፍ እድል በሚያገኙበት በዚህ ሽንቁር ላይ የመረባረባቸው ነገር ነው። ይህንን በመርጦ አልቃሽነት ፈትፋችነት መቃወሙ ተገቢ ነው።
  እድሉን አግኝተው ሰልፍ የሚወጡ ሰዎች ከመስከረም እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ የዘለቀውን ዘር ተኮር የአማራ የአገው፣ የኮንሶ ኢትዮጵያውያን በደቡብ፣ በወለጋና ቤንሻንጉል የተካሄዱ ጭፍጨፋዎች ቢያንጸባርቁ ተገቢ ነበር። ዓላማው ከሀገር ጎን እንጂ ከመንግሥት ጎን ለመቆም ሊሆን አይችልምና።
  መቼም የትግራይን ሁኔታ በተመለከተ ከግራም ከቀኝም ተአማኒ መረጃ ስላልተገኘ ለቅሷችንን ለሌላ ጊዜ እናቆየው ቢባል (ሕወሃትም የሐውዜናዊ ድራማዎች ባለቤት ራሱ ገድሎና አስገድሎ፣ ራሱ አልቃሽ፣ አስለቃሽ፣ አላቃሽ እና ሬሳ ሳጥን ሻጭ መሆኑ ስለሚታወቅ) ሌላውን በመንግስታዊ ተሳትፎ እየተካሄደ ያለ ሰቆቃ እንዳልሰሙ ለመሆን አይቻልም። ሌላ ይቅርና በዚሁ ሰልፉ በተደረገበት ዋዜማ የየካቲት ወር መጨረሻ ሳምንት ያልተቋረጠ የዘር ጭፍጨፋ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሲካሄድ ነበር።
  ዛሬ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነው የኦህዴድ /ብልጽግና ድርጅት በሀገር ላይ እየፈጸመው ስላለው በደል አንድም ቃል አለመተንፈስ በተጨፍጫፊዎችና በተሳዳጆች ወገኖች ደምና ሕይወት እንደመሳለቅ ነው። ከአንድ ሰላማዊ የገበሬ ቤተሰብ ስድስትና ሰባት ሰው ከመፍጀት የተለየ ትርጉም አለው እንዴ ይህ የዘር ጭፍጨፋ የሚባለው ነገር?
  እግዚአብሔር የትኛውን አለንጋ መዞ እንደሚቀጣ አይታወቅም። ቅጣት ግን አይቀርም። ንጹሐንን በጅምላ እያረዱ ቀብሮ፣ አፈናቅሎ እንደ ቃየል መቅበዝበዝ እንጂ ሰላም አይኖርም። እኛ ባንጮህ ደማቸው ይጮኻል። ሥልጣን ላይ ያሉም የተወገዱም የእጃቸውን ያገኛሉ።

  አዲሱ ጅብ እግሬን/ እወገቤ አድርሶት
  ስላሮጌው ጅብ ነው/ ዛሬም የኔ ብሶት

  መንግሥት እውነትን ይዞ በሕወሃት መር የባእዳን ፕሮፓጋንዳ ተሸንፎ ከሆነ የተሸነፈበት ዋና ምክንያት ገዢው ፓርቲ ራሱ በአሳፋሪ የሥልጣን እና የህገር ስልቀጣ ስግብግብነት ተሰማርቶና በሌሎች ከፋፋይና ከንቱ ሥራዎች ተጠምዶ የሀገር አንድነትን ሲያናጋ በመክረሙ ነው።

  ዋናው ጉዳይ
  ምእራባውያን በኢትዮጵያ ለሚፈሰው ደም ተጨንቀው ሳይሆን የየመኑ ፕሮጄክት ወደ ፍጻሜው ስለተቃረበ አዲስ የጦርነት አድማስ፣ የመሳሪያና የወሬ ንግድ ገበያ በትጋት በማፈላለግ ላይ መሆናቸው ግልጽ ነው። ገና ቢሮውን ከተረከቡ ወር ያልሞላቸው ሚስተር ብሊንኪንግ ኢትዮጵያን ልዩ ሥራቸው ማድረጋቸውን እና በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ጸጥታው ምክርቤት መሮጣቸውን አስትውለህ ወገኔ ለብርቱ የአርስ በእርስ ጦርነት፣ ቀጠናዊ ቀውስና መጠነ ሰፊ የባእዳን ጣልቃ ገብነት አእምሮህን አዘጋጅ። ሕወሃትን ያስወገዷት እነሱው ናቸው። አሁን ወደዋት ሳይሆን ቀጠናውን የሚያምሱበት እጀታ በመፈለግ ነው ሙሉ ለሙሉ ተቆርጣ እንዳትጠፋ በመሟሟት ላይ የሚገኙት። የዲሞክራቶች መንግሥት ደግሞ በዚህ ረገድ አንጸባራቂ ገድል ያለው ነው። ካርተር ያስጠቃትን ኢትዮጵያ፣ ክሊንተን ያፈረሳቸውን ሶማልያና ዮጎዝላቪያ፣ ሚስቱ ክሊንተን ያፈረሰቻትን ሊቢያን ማስታወስ ይገባል። ይቅርታ ያለንበት አደጋ ነጭ ነጩን መነጋገር ግድ ስለሚለን ነው።
  በበኩሌ የሚያስመሰግን እና እጅግ ጠቃሚ እንዲሁም ገንቢ ሂስ ነው እላለሁ የአቶ ግርማን አስተያየት።

 6. እስክንድርን ያላስታወሰ፤የአማራን እልቂትና ሰቆቃ የረሳ ሰልፍ በሙጃዎች የተሞላ ነዉ ግርማ ካሳ እንደ ሁልጊዜዉ ለህሊናህ የቆምክ ነህ በብሺሺቅ ፖለቲካ የሰሩ የመሰላቸዉን እርሳቸዉ የምናስብ ሰዎች እናስብላቸዋለን እነሱ ይኑሩ ሀላፊነት መሸከም ግዴታ የለባቸዉም የመጣዉ ይጋልባቸዋል።

 7. አቶ ግርማ ካሳ፤ “የጨዉ ክምር ሲናድ፤ ሞኝ ይስቃል፣ ብልህ ያለቅሳል።” የታባለዉን የአበው ብሂል አስታወሱኝ።
  “በዲሲና በካናዳ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ ሕወሃትን በመቃወም የተደረገ ሰልፍ የሚደገፍ ሰልፍ ነው፡፡ የህወሃት ሰዎች የአገራችንን ገጽታ በአለም አቀፍ መድረክ እያቆሸሹት በመሆኑ በዚህ መልኩ ትልቅ ተነሳሽነት ኖሮ ሰልፍ መደረጉ ጥሩ ነው፡፡ ሆኖም ግን እጅግ በጣም በሰልፎቹ አዝኛለሁ፡፡የሰልፉ አዘጋጆች ሰልፎቹን ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግነት ሃይጃክ አድርገዉታል። ብዙዎቹ በሰልፉ የተገኙት ለኢትዮጵያ ብለው ነው። ነገር ግን ሰልፉ ለኢትዮጵያ የተደረገ ሰልፍ ነበር ግን ማለት አይቻልም።….”

  በዚህ አስተያየትዎ፤ በሃገረ አሜሪካና በካናዳ የሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች፤ በእናት ሃገራችን በኢትዮጵያና በህዝብዋ ላይ ያንዣበበዉን አስከፊ የጥፋት ሴራ በመገንዘብ፤ ፈጥነዉ የሰጡት ምላሽ እንዳልተዋጠልዎት በድፍረት መናገርዎ መልካም ነዉ። ይህንንም በማድረግዎ፤ የሳቱትን የዕውነት መስመር ቆም ብለው ለመቃኘት አጋጣሚዉን ያገኛሉ። ነገርግን በሰልፎቹ በጣም ያዘኑበት ምክንያት፤ በምንም መስፈርት ቢለካ፤ ሚዛን የማይደፋ ተራ ስንኩል ሰበብ ከመሆን አይዘልም። በእርግጥ በሰልፉ በጣም የሚያዝን፣ የሚበሳጭና የሚቀሰፍ ከወያኔ፣ ከአሮጌ ጅቦቹና ከግብረአበሮቻቸዉ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም።
  አቶ ግርማ፤ ዲያስፖራው የተገላገለውን ግንቦት7 የሚባለውን የባንዳ መንጋ፤ አዋራውን አራግፈው ባልዋለበት ስሙን ለማወደስ የመረጡት ስልትም ሩቅ አያስኬድም።

  አቶ ግርማ ካሳ በዚህ ፈታኝ ወቅት፤ መያዝ ያለብዎትን አቅዋም ጠንቅቀው ይረዳሉ። ይህም ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ወይም ከወያኔና ግብረአበሮቹ አንዱን መምረጥ ነው። እንደ እርስዎ ላለ መሃል ሰፋሪነቱ አይመጥንም። ወያኔ በገንዘብ ሎቢስቶችን ቀጥሮ ጉዳዩን ለማስፈጸም የሚተጋ ብቻ ሳይሆን፣ በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅትና በሙያ ተቅዋማት፣ ቀድሞ የሰገሰጋቸውን ታማኝ አባላትና አጋሮቹን በማንቀሳቀስ ከወደቀበት አፈር ልሶ ለመነሳት የሚያደርገዉን ጥረት በቸልታ የሚታለፍና ጊዜ የሚሰጠው አይደለም። በግልጽ የምናውቀው ቴድሮስ አድሃኖም እንዲሁም የአሜሪካው ፕሬዚደንት የጆይ ባይደን አማካሪ (የሰየ አብረሃ የቅርብ ዘመድ) ዘር ከልግዋም ስብዋቸው የሚጎነጉኑት ሴራ የአደባብይ ሚስጥር መሁኑን የሚሳነው የለም።
  በቅን መንፈስና ልቦና፣ በፍጹም ኢትዮጵያዊ ስሜትና የወገን ፍቅር ተነሳስቶ፤ ለዕውነትና ለአንድነት ድምጽ የሆኑ በአስርት ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ድንቅ ተግባር በዘፈቀድ ማጣጣል በፍጹም እይገባም።

  ኢትዮጵያ ትቅደም

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.