በኒዮርክና አካባቢው ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ

ህወሀት (TPLF) ስሜን እዝ በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ባደረሰው ድንገተኛና አሰቃቂ ጭፍጨፋ ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት ወንጀለኞችን ወደህግ ለማቅረብ ሲል ትግራይ ውስጥ የህግ ማስከበር ዘመቻ አካሂዶ ዘመቻውን በ 17 ቀን ውስጥ በድል አጠናቆ የትግራይ ክልል ጊዜአዊ አስተዳደር አቋቁሞ ህዝቡ ወደሰላሚው ኑሮው እንዲመለስ በማድረግ ከፍተኛ የማቋቋምና የመልሶ ግንባታ ስራ እየሰራ ባለበት ወቅት አንዳንድ ታላላቅ መንግስታትና አለም አቀፍ የዜና አውታሮች የተሳሳተና የተዛባ መረጃ እያቀረቡና ኢትዮጵያን እንደጥፋተኛ እያቀረቡ ይታያሉ:: በዚህ የተሳሳተ መረጃ ተነስተውም የኢትዮጵያን ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ቀርቦ በኢትዮጵያ ላይ አቋም እንዲያዝ ለነገ ሀሙስ(Thursday) March 11th, 2021 ለሁለተኛ ጊዜ ስብሰባ ያደርጋሉ:

ይህን የተሳሳተና የተዛባ አቋም የያዙትን ሀገራትና ሚዲያወች ለመቃወም በኒዮርክና አካባቢው የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከ WD እና አካባቢው ከሚመጡ ወገኖቻችን ጋር በመሆን ነገ ሀሙስ(Thursday) ከ ጠዋቱ 9 AM ጀምሮ በ 1st Avenue እና በ2nd avenue መካከል ከ 43rd street እስከ 47th street ባሉት መንገዶች ላይ ተገናኝተን ተቃውሟችንን የምናሰማ ሲሆን በመቀጠልም የ New York Times እና CNN ወደሚገኙበት ህንጻ በመሄድ ተመሳሳይ ተቃውሞ የምናሰማ ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ በዚሁ ሰአትና ቦታ በመገኘት እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ እንበላቸው::

ወንድማገኝ አዲሱ መርሻ
ከኒዮርክና አካባቢው የሰልፉ አስተባባሪ አባል

Image 1

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.