ምዕራባውያን ፈርተውናል! – አንድነት ይበልጣል ሐዋሳ

የካቲት 28 / 2013 ዓ.ም
አንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ

Newsምዕራባውያን በውሸት ዜና እየተሸወዱ አይደለም

የአሜሪካና ሌሎች ምዕራባውያን መንግሥታት፣ ክፍያቸውን ከወያኔ ትርፍራፊዎች የሚያገኙ ቅጥረኞች (ሎቢስቶች) የሚያሰራጩትን የውሸት ዜና ተከትለው በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና ሲያሳድሩ እየተመለከትን ነው፡፡ ምዕራባውያኑ የሚሆኑትን እየሆኑ ያሉት በወያኔ ትርፍራፊዎችና በሎቢስቶቻቸው የውሸት ዜና ተሸውደው አይደለም፡፡ ምዕራባውያን፣ የወያኔ ዜናዎች የውሸት መሆናቸውን ያውቃሉ፤ ሆኖም ለራሳቸው ድብቅ ዓላማ ስለሚጠቅሟቸው ነው የዜናዎቹን ጭራ ይዘው እያጋነኑ የሚያናፍሱት፡፡ የተቀናጀው የፈጠራ ዜና የሽፋኑ ሥዕል ብቻ ነው፡፡ ወደ ውስጥ ገባ ብለን ዝርዝሩን ስንመረምር የምናገኘው ዕውነት ግን ሌላ ነው፡፡ የአሜሪካው ሲአይኤም ሆነ የሌሎቹ ሐገራት የስለላ ድርጅቶች፣ የወያኔን የ30 ዓመታትም ሆነ የዛሬውን የክፋትና የጥፋት ድርጊቱን እንዲሁም “የበሬ ወለደ” ዜና ፈጣሪነቱን ከእኛም በላይ ያውቁታል፡፡ በኢትዮጵያ / አዲስ አበባ በኤምባሲዎች፣ በዓለምና አሕጉር አቀፍ ድርጅቶች፣ በዓለም አቀፍ የዜና ማሠራጫዎችና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ ያሰማሯቸው ወኪሎቻቸው አንዱ ሥራቸው መረጃ ማነፍነፍ፣ መተንተንና ማቅረብ አይደለም?!! የምዕራባውያን ዋናው ችግራቸው የመረጃ እጥረት ወይም የተሳሳተ መረጃ አቅርቦት የሚመስለን ካለን በጣም ተሳስተናል ማለት ነው፡፡ በኛም በኩል ዋናው ችግራችን የዓለም አቀፍ ሕዝብ ግንኙነትና የዲፕሎማሲያችን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ድክመት ብቻ ከመሰልንም አሁንም የተሳሳትን ይመስለኛል፡፡

ምዕራባውያን የአድዋን ድል በዛሬው አውድ እንዳንደግመው ፈርተውናል!

ምዕራባውያን ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ለያዙት አድማ እና እያሳደሩ ለሚገኘው ጫና ዋናው መንስኤና ችግራቸው ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ቁመናና አዝማሚያ ፈርተዋል፡፡ ከ125 ዓመት በፊት፣ ኢትዮጵያ አድዋ ላይ፣ በነጭ ቅኝ ገዢዎች ላይ ተአምር የሚመስል ደማቅ ድል አስመዝግባለች፡፡ የአድዋ ድል በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩ አፍሪካውያን ብቻ ሣይሆን በመላው ዓላም ለሚገኙ ነጭ ያልሆኑ ሕዝቦች ትልቅ መነቃቃት፣ በራስ መተማመንና ኩራት መፍጠሩ ብቻ ሣይሆን ዘመን ተሻጋሪ ምሳሌም ሆኖ ቀርቷል፡፡

ምዕራባውያን፣ ይህ የኢትዮጵያ አርአያነት ዛሬ ደግሞ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛትን በመስበር አውድም እንዳይደገምና ልዩ ተጠቃሚነታቸውን እንዳያስቀርባቸው በጣም ፈርተዋል፡፡ ይህ ከሆነ የዓለም የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የባሕል፣ የሥነልቡናና ወታደራዊ የኃይል ሚዛን ምዕራባውያንን በሚጎዳና ኢትዮጵያና የተገፉ የዓለም ሕዝቦችን ሁሉ በሚጠቅም መልኩ ሊቀየር ነው ማለት ነው፡፡ ምዕራባውያን የበላይነት ልዩ ተጠቃሚነታቸውና ፈላጭ ቆራጭነታቸው እንዳይቀርባቸው ሲሉ ሐገራችን ባለችበት ስትረግጥ እንድትኖር ይፈልጋሉ፡፡ ሐገራችን ከከረመ አምባገነንነት፣ በተለይም ከጥገኛው የወያኔ አቆርቋዥነት እንድትገላገል፣ ከድህነትና ከጥገኝነት እንድትወጣ፣ በባዕዳን የምትታለብ የወተት ላም መሆኗ እንዲያበቃ አይፈልጉም፡፡ ትልቁን ሥዕል ብናይ፣ ኢትዮጵያን ለራሷ ብቻ ሣይሆን ለቀጠናችንና ለመላ አፍሪካ የኢኮኖሚ ነጻነትና ጥንካሬ ማሣያ ምሣሌ እንዳትሆን ፈርተዋታል! በአድዋ፣ በቀጥተኛ ቅኝ አገዛዝ ላይ ያስመዘገብነውን ድል፣ ከ125 ዓመታት በኋላ ዛሬ ደግሞ በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ላይ እንዳንደግመውና ሌሎችንም እንዳናነሳሳባቸው በእጅጉ ፈርተውናል! ዛሬ የተከፈተብን ዓለም አቀፍ ሤራና ሻጥር ድብቁ መንስኤና ዕውነተኛው ገፊ ምክንያት ይህ ነው፡፡

ፈተናውን መሻገር እንችላለን! ግን እንዴት?

ይህንን ፈተና በአሸናፊነት መሻገር አለብን፣ እንችላለንም! ዋናው ነገር ለዚህ ዕውነተኛ፣ ነገር ግን ድብቅ ለሆነ የሤራ መንስኤ የሚመጥን ሁለገብ ጥበብና ብልሐት ማሣየትና መጠቀም ይኖርብናል፡፡ ከአድዋም ያገኘነውን በራስ መተማመን፣ አንድነት፣ ቁርጠኝነትና ጀግንነት ዛሬም የግድ መድገም ይኖርብናል! የዲፕሎማሲ አቅማችንን በፍጥነት ማሳደግ አለብን፤ በዲፕሎማሲው ዘርፍም በተቀናጀና መላ ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን አስተባብሮ ባሳተፈ ሁኔታ መፋለም አለብን፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ምዕራባውያን በየጊዜው በሚፈጥሩልን ሻጥረኛ አጀንዳዎችም ስንጎተት መገኘትም የለብንም፡፡ በዲፕሎማሲውና በሕዝብ ግንኙነቱም መድረክ የራሳችንን ዘላቂ/ስትራቴጂያዊ አጀንዳ ቀርጸን በሚገባ አቅደን መፈጸምና ቀድመን መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡

ለውጡን ለማጎልበት ወጥሮና ተባብሮ መሥራት

የዲፕሎማሲውንም ሆነ ሌሎች ትግሎቻችንን ሁሉ የሚገዛና የሚመራ ገዢ ሥራም አለብን፡፡ ይኸውም፣ ከልዩም፣ ልዩ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ትልቁና መቋረጥ የሌለበት ሥራ ነው፤ በጅምር ላይ ያለውን የዴሞክራሲ፣ የአንድነትና የሁለገብ ዕድገት እንዲሁም ሉዓላዊነታችንን የማስከበር አጀንዳዎቻችን ፈራቸውን እንዳይስቱና እንዲያውም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ወጥሮና ተባብሮ መሥራት ነው፡፡ የምዕራባውያንም ፍርሐት፣ የኢትዮጵያውያንም ተስፋ ያለው በለውጡ ላይ ነው! ዓይናችንንና ልባችንን ለአፍታ ልንነቅልበት የማይገባ ዋናውና ወሣኙ ሥራችን መሆን ያለበት ለውጡ ነው! በዓለም አቀፍ ጫጫታውና በወጀቡ ውስጥ ሆነንም ቢሆን የለውጥ ሥራችንን ለአፍታም እንኳ ማቋረጥና ማዘግየት የለብንም!! ወደ ኋላ መመለስ የሚባልማ ነገር ከቶ ሊታሰብ አይገባም!! እንዴት ተደርጎ?!! ለእጅር አዙር ቅኝ አገዛዝ፣ (በይበልጥና በስፋት) በወያኔ የአገዛዝ ዘመን የገበርነው ይበቃናል፡፡

ፈጣሪ ይርዳን!

5 Comments

 1. All Ethiopians residing in the Western countries need to take a stand. They cannot be working for the Western countries and claim to be Ethiopians at the same time. There is no Ethiopian-Western, it is either Western or Ethiopian, not both. The United Nations (UN) is at loss of ability to unite the West and Ethiopia.

 2. ዋና ዋና ጥያቄዎች የዲፕሎማሲ እውቀታችን አነስተኛ ከሆንን ሰዎች፡፡
  የአሜሪካ ዉጭ ፖሊሲ በ”National Interest” የተመሰረተ ነው ከተባለ፤ እንደዚህ በጥቂት ወራት በሚቆጠር ጊዜ ውስጥ የማይክ ፖምፔዮ እና የአንቶኒ ብሊንከን አቋም እንዴት እንደዚህ በተቃራኒ አቅጣጫ ሊለያይ ቻለ? ነው ወይስ የሪፓብሊካንስ እና ዲሞክራትስ “national interest” ይለያያል? ነው ወይስ ጉዳዩ ከወያኔ በላይ ነው? ሱሳን ራይስ ይህን ያህል ተጸእኖ? [ኢሳያስ በbaድሜ ጦርነት ጊዜ “ህጻን” ስላላት ቂም á‹­á‹› ይሆን?] አሜሪካ ወያኔን ወደስልጣን እመልሳለሁ ብላ ታስብ ይሆን? በደርግ ላይ የፈጸሙትን ስህተት [ጠቅሎ ወደ ያኔው ሶቬት ካምፕ እንደገባው!] እንዳይደግሙት ብቻ ልቦና ይስጣቸው፤፡
  ተያያዝ ጉዳዮች፡
  1። ማርች 10 ይህንን ጉዳይ ለመቃወም እየቻልክ ሰልፍ ያልወጣህ ኢትዮጳያዊ ዲያስፖራ ወይ እንዳፈርክ ወይ እንዳዘንክ ትኖራለህ፤፤ “…ወስልተህ ብትቀር ማርያምን …..”
  2፤ ዘሃበሻ ድሮ እንደሚያደርገው ሰልፉን እስካሁን ማስተዋወቅ ያልፈለገበት ምክንያት ባይገባንም፤ በመቆየቱ የምጠረጥረው ይኖረናል፤፤ ምርጫው የሄኖክ ነው፤፡
  3። On the right day, Ethiopia must decorate Mike Pompeo, Tibor Nagy and Michael Renor

 3. ለከድር ሰተቴ

  “”የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ በ National Interest…………እንደዚህ በጥቂት ወራት በሚቆጠር ጊዜ……..እንዴት እንደዚህ በተቃራኒ አቅጣጫ ሊለያይ ቻለ?”

  በኢትዮጵያ በጥቂት ወራት ጊዜ ውስጥ ለቁጥር የሚያታክቱ አደገኛ አዝማሚያ ያላቸው ክስተቶች ስለተፈፀሙ እና እየተፈፀሙ ስለሚገኙ እንኳን የአሜሪካን መንግስት እና እኛ በታወረ ፍቅር የማንመራ ኢትዮጵያኖችም እንደየክስተቱ ፍትሀዊነት መዝነን ብዙ ከቀሞው አቋሞቻችን የተቃረኑ አቋምችን ወስደናል ።

  በታወረ ፍቅር የሚመሩት ግን አሁንም ልክ ክስተቶቹ ከመፈፀማቸው በፊት በነበሩበት ሀገርም ተወርራ፣ ተርባ፣ ታማ፣ ታርዳ ኩላሊትዋ እየተበላ……ወዘተ …..እንደቀድሞው ናቸው አሁንም። ከአጥፊዎችዋም ጋር አብረው ሀገር እያጠፉ ነው።

  በኢትዮጵያ በመንግስት ተነግረውን ከሰማናቸውም ሆኑ ወይም አልተከሰቱም ተብለን በአንድ የመንግስት አካል ተነግረውን ከእዛም ወድያውኑ በሌላ የመንግስት አካል ተከስተዋል ተብሎ ከተነገሩን ‘ውላቸው ያልታወቀ’ ክስተቶች (ለምሳሌ የኤርትራ ጦር በትግራይ) ወይንም በኢትዮጵያ መንግስት ካልተነገሩንም ግን ሆነዋል ብለን በቦታው ከነበሩ የአይን እማኞች ከሰማናቸው ክስተቶች የተነሳ ያለፉት ጥቂት ወራት በጣም አደጋ የበዛባቸው ክስተቶች ተፈፅመዋል እየተፈፀሙም ነው ብንል ትክክልነታችን ከጥያቄም አይገባም። ስለ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ፖሊሲ ተቀያያሪ ክስተቶች ከብዙ በጥቂቱ፡፥

  ባለፉት ጥቂት ወራት 1.) ኢትዮጵያ በሱዳን ተደፍራ የሀያ ስክዌር ኪሎ ሜትር ግዛትዋን ለማስመለስ ጦርነት ጀምራለች።
  2.) ኢትዮጵያ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፀ የጦር መሳሪያዎችን እና የጦር መኮንኖችን አጥታለች በሀገር ውስጥ በተከሰቱ ጦርነቶች።
  3.) ኢትዮጵያ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ረሀብተኛ እና የውስጥ ተፈናቃይ ስደተኞችን አፍርታለች።
  3.) ኤርትራ ላይ ሚሳይል ተኩሳለች።
  4.) ኤርትራ የNational Interestዋን ለማስጠበቅ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘምታ ውጊያ አካሂዳ ገብታ ሰፍራለች።
  5.)ኢትዮጵያ ምርጫ በመላ ሀገሪቱ ትግራይንም ጨምሮ ያለ ወቅቱ ለማካሄድ ወስና ከሀምሳ በሚበልጡ ተወዳዳሪ ፓርታዎችን መዝግባ ሌሎች ሀምሳ የሚጠጉ ፓርቲዎችን ምርጫ ለማሳተፍ ከልክላ የምርጫ ቅስቀሳ election campaigns ጀምራለች። ብዙ ተወዳዳሪዎች ፖለቲከኞችም እስር ላይ ናቸው እየታሰሩም ነው።
  6.) ኢትዮጵያን ለመገንባት ከባድ ነው ለማፍረስ ቀላል ነው ሲሉ የሰነበቱ ጁንታዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት እስካሁን ድረስ ላለፉት ጥቂት ወራት ቢታደኑም በቁጥጥር ስር አለመሆናቸው፡ የወልቃይትን እና የራያንም ጉዳይን እስከአሁን እንጥልጥል ላይ መጣላቸው።

  የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ በNational Interest የተመሠረተ ነው ሲባል አሜሪካም ሆነች ሌሎች ሀገራትም ከገዛ ሀገራቸው National Interest አኳያ ፖሊሲዮችን ይነድፋሉ የሚል እሳቤ ተይዞ ነው ይህ ሆኖም ሌሎች ሀገራትን የሚጎዳ ፖሊሲም እንዳይሆን አበክረው ጥንቃቄ ይወስዳሉ።

 4. Ato Andinet:

  Please stop the propaganda. I love my country but never dare say that Westerners are scared of Ethiopia as it is untrue. In reality, I believe less than 10% of citizens in Western countries know that a country by the name Ethiopia exists. The ones who know Ethiopia also associate the country to eternal war, famine, begging and poverty.
  Despite this fact, I still love my poor Ethiopia as this is the only country I have.

  Please: Let us be realistic and work hard to be respected by others, not spreading lies and propaganda.

 5. እንኳን ምዕራባውያን በጦርነት የደቀቀችው የመንም አልፈራችንም። ሱዳንም አልፈራችንም።
  በየመን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያዊ ስደተኞችን አንድ ላይ አጉረው ባለፈው እሁድ እሳት ለቀውባቸው ህይወት ግቢ ህይወት ውጪ ላይ እያሉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶቻችን እነ ሬድዋን ሁሴን በየመን በቦታው ተገኝተው ስንት እንደ ሞቱ ስንት እንደተጎዱ ስንት እንደተረፉ ለመቁጠር እንኳን ጠይቀው ተከልክለዋል በየመን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.