ዐብይ አሕመድና የኦሮምያ ልዩ ኃይል – መስፍን አረጋ

abiy 1
አብይ አህመድ ከፊት ለፊት ሆኖ  ሕዝብ እያጃጃለ፣ኦነግና የኦነግ ውልድ የሆነው ኦህዴድ የወደፊቷን ኦሮሚያ የተባለች አገር ለመመሥረት ደፋ ቀና እያለ ነው

የዐበይ አሕመድ አካሄድ በገሃድ የሚያመለክተው መዳረሻው በጦቢያ ፍስራሽ ላይ የኦሮሞ አጼጌ (Oromo empire) መመሥረት ነው፡፡  ወደዚህ መዳረሻው በፍጥነት ለመድረስ ደግሞ  የኦሮሙማ፣ በኦሮሙማ፣ ለኦሮሙማ የሆነ ግዙፍ ሠራዊት ያስፈልገዋል፡፡

በስሙ የጦቢያ መከላከያ የሚባለውን ሠራዊት፣ በግብሩ ግን በራሱ ባብይ አሕመድ ጠቅላይ አዛዥነት፣ በብርሃኑ ጁላ ኢታማዦር ሹምነት፣ በቀንዓ ያደታ መከላከያ ሚኒስትርነት፣ በይልማ መርዳሳ አየር ኃይል አዛዥነት … ሙሉ በሙሉ የኦሮሙማ ሠራዊት አድርጎ፣ የኦሮሙማን አጀንዳ እንዲያስፈጽም በመላ ጦቢያ ላይ አሰማርቶታል፡፡

የኦሮሙማ መከላከያ ሠራዊት ስለተመሠረተ ደግሞ፣ የሚቀረው በመላው ጦቢያ ላይ የሚሠማራ፣ የኦሮሙማን ሕግ የሚያስከብር የኦሮሙማ የፖሊስ ሠራዊት ነው፡፡  ለዚህ የታጨው ደግሞ የኦሮምያ ልዩ ኃይል ነው፡፡

የትግራይ (የወያኔ) ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ ፈራርሷል፡፡  ያማራ ልዩ ኃይል ደግሞ ከኤርትራ ሠራዊት ጋር እኩል ተኮንኖ በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጠረጠር ለማድረግ፣ ዐብይ አህመድ ባሜሪቃ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባንቶኒ ብሊንከን (Antony Blinken) አማካኝነት “ከትግራይ” ባፋጣኝ ለቆ ይውጣ የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡  ከዚህ መግለጫ በኋላ የሚከተለው ደግሞ ያማራ ልዩ ኃይልን በዘር ማጥፋት ወንጀል አስከስሶ፣ “ዘር አጥፊወችን እያደኑ የሚያጠፉት የሰው ዘር ጠበቃወቹ” አሜሪቃ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ ተረባርበው ድምጥማጡን እንዲያጠፉት ማድረግ ብቻና ብቻ ነው፡፡

የኦሮምያ ልዩ ኃይል በተከታታይ ዞሮች እየሰለጠነ መጠናከሩን ይቀጥልና፣ ልክ እንደ ትግራይ ልዩ ኃይል ያማራ ልዩ ኃይል ድምጥማጡ ሲጠፋ፣ ስሙን ወዲያውኑ ቀይሮ በመላ አገሪቱ ላይ የኦሮሙማን ሕግ የሚያስከብር፣ ምናልባትም ነፍጠኛን በቁማር “በሰበረው” በቁማርተኛው በሽመልስ አብዲሳ ጠቅላይ አዛዥነት የሚመራ የኦሮሙማ ፖሊስ ሠራዊት ይሆናል፡፡

የኦሮሙማ ፖሊስ የኦሮሙማን ሕግ ለማስከበር በመላ ጦቢያ ላይ ሲሰማራ፣ ጦቢያ “ከኦሮምያ ትወጣለች” (Ethiopia out of Oromia)፣ የኦሮሞ አጼጌ (Oromo Empire) ደግሞ በይፋ ይታወጃል፡፡

ዐብይ አሕመድ ደግሞ በቅሎ መቀመጥን ካበሾች ተምሮ ጃናሞራን ከፈጃት “ምስሌ” ከሚባለው አምስተኛው ሉባ፣ እንዲሁም ላኮምልዛን (ወሎን)፣ ሸዋን፣ ጎዣምን፣ ደምቢያን … በመጨፍጨፍ “ድኾች ሁሉ የሚበለጽጉባቸውን ምድሮች” ምድረበዳ ካደረጉት፣ በተጨማሪ ደግሞ “ባሕር የሚለብሱትን ሲዳማዎች ባሕር ከጨመሯቸው”  ሐርሙፋ ከሚባሉት ከሜልባ ልጆች ቀጥሎ፣ ድፍን ጦቢያን ኦሮሞ ያደረገ ሰባተኛውና የመጨረሻው ሉባ ይሆናል፡፡

ባለመታደል ያገራችን የጦቢያ ጠላቶች ከጊዜ ወደጊዜ የሚሄዱት እየከፉና እየከፉ ነው፡፡  ደርግ ሲሄድ ወያኔ መጣ፡፡  ወያኔ ሲሸሽ ኦሮሙማ ተተካ፡፡  በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን ዐብይ አህመድን የመሰለ ሳይታጠቅ የሚገድል ጠላት አገራችን ጦቢያ በታሪኳ መቸም አይታ አታውቅም፣ ወደፊትም መቸም የምታይ አይመስለኝም፣ ለዚያውም ደግሞ ዐብይ አህመድ ገድሎ፣ መቸም ስሟ እንዳይነሳ ሶፍ ኡመር ዋሻ ውስጥ ለሃቹ (ለዘላለሙ) ሳይቀብራት በፊት እጆቿን የምትዘረጋለት እግዚአብሔር  በማያልቅበት ታምሩ ካተረፋት፡፡

 

አማራና ትግሬ በጥቅል ሐበሻ
ርስበርስ ተዳምተህ በምክኒያት ተልካሻ
ስትዳከምለት በስተመጨረሻ፣
ሥጋህን በጫጭቆ የኦነጉ ውሻ
ለሃች ይቀብርሃል እሶፍ ኡመር ዋሻ፡

Mesfin Arega
[email protected]

2 Comments

  1. ወንድሜ መስፍን እኔ ጭራሽ በሃሳብህ አልስማማም። ለዚህም ጉዳይ ሶስት ነገሮች አሉኝ። በመጀመሪያ ጠ/ሚሩ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ይሰራሉ ብየ አላምንም። አዎን የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች ያው በሻቢያና በወያኔ እንዳየነው ሃተፍ ተፍ ማለታቸውን እናያለን። በሁለተኛ ደረጃ እልፍ የጦር መሳሪያ ብታሰልፍ ጉዳዪ አይሳካም። ለምን ያልክ እንደሆነ እኛ ስንቧቀስ እሳት የሚያቀብሉን ሃይሎች ቁጥራቸው ብዙ ነውና። ወያኔና ሻቢያ በጋራ ነበር ደርግን የወጉት። ወጉት ሲባል በጦር ሜዳ ብቻ ሳይሆን ከቤተመንግስት እስከ መስክ በየስርቻው የራሳቸውን ሰዎችን አሰልፈው በመግደል፤ በማሰር፤ ሚስጥር በማቀበል። አልፎ ተርፎም በእድርና በሌሎችም ጉዳዮች ገንዘብ ሁሉ በማዋጣት ይደጋገፉ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ። ተመልሰው ግን ተፋልመዋል። እየተፋለሙም ነው። በጦር ብዛትዓላማ ግቡን አይመታም። እንዲያም ሆኖ ወያኔና ሻቢያ ህዝባቸው በረሃብና በመከራ ወድቆ ራሳቸውን አበለጠጉ እንጂ ነጻ ሆኛለሁ ብሎ ሰው በሃገሩ እፎይ ብሎ አልተቀመጠም። ዛሬም ስደት ትላንትም ስደት እልፍ የለሽ ፓለቲካ ነው። ሶስተኛው ነጥብ የሽዋው ኦሮሞ ከሃረሩ ወይም ከወለጋው ብሎም በሌሎች አካባቢዎች ካሉት ጋር የቋንቋ ጥምረት እንጂ የኦነግ ባንዲራ አፍቃሪ አይደለም። ስለሆነም ኦሮሞ ያጠቃሃል ገለ መሌ ማለቱ ነሲባዊ እይታ እንጂ እውነትነት የለውም። ይህን ስል የደረሰውን በደል በመዘንጋት አይደለም። በወያኔ/በግብጽ/በሱዳን የተቀናበረው አማራን የማስጨረስ፤ ቤ/ክርስቲያን የማቃጠል፤ ጊዜው የእኛ ነው ኑ እንብላ መባሉን ዘንግቼው አይደለም። ይህ በዘር ፓለቲካ ከሰከረ ጭንቅላት የሚጠበቅ ነው። የዘር ፓለቲካ ፍጻሜውም እንደ ውሻ ተነካክሶ ማለቅ ነው። የቆመው በሞተው ላይ ሲጨፍር፤ ስልጣን ላይ ያለው ሌላውን ሲያጥላላና ሲያቅራራ ታሪካችን እልፍ ጊዜ ተደጋግሟል። የአሁኑን ካለፈው የከፋ የሚያረገው የክልል ፓለቲካውና ወያኔና ሻቢያ የዘሩት የውሸት ትንግርት ፈንጂ አማራ ጠላታችሁ ነው መባሉ ነው። የአረናው ጡሩንበኛ ከአማራ ህዝብ በስተቀር ሌላውን ሁሉ አመሰግናለሁ ያለው በዚሁ በጠባብ ጭንቅላቱ ነው። አማራ ሆነው ለትግራይ ህዝብ የሚያዝኑና የሚያነቡ እንዳሉ ማን በነገረው? ግን የወያኔ ግርፎች ሁሌም ጥላቸው ከአማራ ህዝብ ጋር ነው። ጥቂት ቆይተው አማራ ቅኝ ግዛት ይዞን ነበር ማለታቸው አይቀሬ ነው። ለመኖር የፓለቲካ መቆራቆስ የአፍሪቃን አህጉር ቀፍድዶ የያዘ በሽታ ነው።
    ባጭሩ ጥቁሩ ህዝብ የራሱን ሃገር እሳት እየለኮሰና እያስለኮሰ ወደ ሌላው ዓለም መኮብለሉ ኑሮውን ሙሉ አያረገውም። በምንም ሂሳብ ቢሆን አሁን ባለው የሰዎች ህጋዊና ህጋዊ ያልሆነ ዝውውር የተነሳ ሃገራት ቆራጥ እርምጃ እንደሚወስድ ህዝቡም እንደሚነሳ ጥርጥር የለኝም። በቅርቡ ሃገር ቤት ሂጄ መንገድ ላይ ሰዎችን አቆሙናን አንድን ቤተሰብ ስሚ እስቲ እሟሃይ ‘ልጆቹ ወጡልሽ” ሲሉ ሰምቼ እህቴን የት ነው የሚወጡት ብላት ውጭ ሃገር ነዋ ስትለኝ ግርም አለኝ። ወጡልሽ? አይ ሃገር። የሚያስገርም ነው። ወጥቶ እንዴት እንደሚኖር ማን በነገራቸው? ግን ሰሚ የለም። ስለሆነም አብይና የኦሮሞ ልዪ ሃይል ምንም የሚያረጉት ነገር አይኖርም። መረጃ አልባ የአንድ ሃገር መሪና የክልል ሃይሎችን መኮነንም ትክክል አይመስለኝም። የሃገሪቱ ችግር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይደለም። ስለሆነም ነገሮችን ለማርገብ መስራቱ ይበጃል እንጂ ቆንጭራ ማቀበሉ አይጠቅምም። በቃኝ!

  2. መስፍን አረጋ ትክክል ነው ፡፡ኦሮሙማ የጀርመን ስሪት ነው አሮሚያ በጅርመኑ ተጓዥ አገር አሳሽ ዮዋን ክራምፍ “Travels, Researches and Missionary Labours During an Eighteen Years’ Residence in Eastern Africa” በ1861ዓም የተሰየመ ስምው ይህ ስሪት በጠላቶቻችን አማካይነተ የተሰጠና የዛሬ ሙታን የኦሮሙማ አቀንቃኞች ከዚህ ቀቢጸ ተስፋ ተነስተው ኢትዮ|ያን ሊውጧት ኢትዮጵ\ው\ንን አወናብደው ወይም አሳምነው ኦነግ አማካይነተ አስጨፍጭፈው አሻፈረኝ ያላቸውን በነፍሰገዳዩ አየበተኑን ይገኛሉ፡፡
    ለዚህም ሰባተኛው ንጉስ አቢይ አህመድ ህዝብ እየደናገረ ቀንቀን ኢትዮጵያ እያለ ከመጋረጃ ጀርባ ከኦነግ እየመከረ አጀንዳውን በማስጸም ላይ ይገኛል ሪፐፐብሊካቸውን ለመመስረት አብዘኛው ተግባራት አከናውነዋል

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.